TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሀዘን መግለጫ ከኢትዮ ቴሌኮም!

ኢትዮ ቴሌኮም በምዕራብ ሪጂን የኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ታደሰ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጿል። አትዮ ቴሌኮም ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹ፣ ለዘመዶቹ እንዲሁም ለስራ ባለልደረቦቹ መፅናናትን ተመኝቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሮፌሰር ፍቅሬ እንቁስላሴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

የሀዘን መግለጫ፦

የኢትዮጵያ ህክማና ማህበር አንጋፋ አባል እና የሜዲካል ጆርናል የቦርድ አባል እንዲሁም ምክትል ሰብሳቢ በመሆን ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት ፕሮፌሰር ፍቅሬ እንቁስላሴ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም በዛሬው ዕለት ጥቅምት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በፕሮፌሰር ፍቅሬ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለስራ ባለደረቦቻቸው በማህበሩ ስም መፅናናትን እየተመኘን የስርዓተ ቀብር መርሀ ግብሩ በቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ በነገው ዕለት ጥቅምት 18 ቀን 2012 ዓ/ም የሚከናወን መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጰያ ህክምና ማህበር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIGRAY | የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በክልሉ የአንበጣ መንጋ የተከሰተባቸውን አካባቢዎች ተመልክተዋል። ዶክተር ደብረፂዮን በመስክ ጉብኝታቸው በደቡብ ምስራቅ ዞን እንደርታ ወረዳ በመገኘት የአንበጣ መንጋው እያደረሰ ያለውን ጉዳት ተመልክተዋል። በጉብኝታቸው ወቅትም ህዝቡ የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል እያደረገ ላለው ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቢሮ ሕርሻን ልምዓት ገጠርን ክልል ትግራይ ኣብ ከባቢኹም ምልክት ናይ ኣምበጣ እንተሪእኹም ሓብሬታ በዘን ዝስዕባ ቁፅሪ ስልክታት ክትሕብሩሉ ፃዊዒት የቕርብ ኣሎ።

Assefa +251 98 352 5569
Birhane +251 91 477 4386
Michiele +251914724744

#PLEASE_SHARE!

Via Shewit Wudaassie
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AMHARA

የአማራ ክልል የግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሰሎሞን አሰፋ (ዶክተር) ባለፈው ሰኔ ወር ከሳዑዲ ዐረብያ ወደ ኢትዮጵያ የገባ አንበጣ መንጋ በሶማሌ እና አፋር ክልሎች ላይ ተባዝቶ ወደ አማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ሰብል አብቃይ አካባቢዎች መዛመቱን አስታውቀዋል፡፡ በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦና ሀብሩ ወረዳዎች፣ በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦና እና አርጎባ ወረዳዎች፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ባቲ፣ ደዌ ሀረዋ እና አርጡማ ፉርሲ ወረዳዎች ላይ አልፎ አልፎ ቢከሰትም በሰብል ላይ ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩን ምክትል ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

https://telegra.ph/eth-10-28-2

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በካናዳ ሀገር የቅርብ ጓደኛውን በመግደል የተጠረጠረው የ26 ዓመቱ ግለሰብ በአየር ትራንስፖርት ወደ #ኢትዮጵያ ማምለጡን የካናዳ ሃሚልተን ፖሊሰ አስታወቀ። በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ኢብራሂም ኢሳክ ሁሴን የተባለው ግለሰብ፣ ከቶርንቶ ወደ ኢትዮጵያ ማምለጡን ተረጋግጧል ያለው ፖሊስ፣ የ29 ዓመቱን ኦብሳ ጁነዲ የተባለውን የቅርብ ጓደኛውን በመግደል መጠርጠሩ ታውቋል።

ሟች በጭንቅላቱ ላይ #በተተኮሰ_ጥይት የሞተ ሲሆን ወዲያውኑ ሕይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ ከግድያው 20 ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል አለመግባባቶች እንደነበሩ ማስረጃዎች አሉኝ ያለ ሲሆን ይህንንም በአካባቢው ከነበሩ የዓይን እማኞች ማረጋገጡን ገልጿል።

የአለመግባባቱ ምንጭ ምን እንደሆነ ባይረጋገጥም ፓሊስ ባደረገው ፍተሻ በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት አደንዛዥ ዕፅ መገኘቱን ይፋ አድርጓል። በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው #ካናዳዊው ግለሰብ የተወለደው ኬንያ ውስጥ ቢሆንም ለምን ወደ ኢትዮጵያ ሊያመልጥ እንደቻለ አልታወቀም። ተጠርጣሪው ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት መሆኑንም ፖሊሰ ገልጿል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሳዛኝ ዜና! በኢትዮ ቴሌኮም የምዕራብ ሪጅን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ገመቺስ ታደሰ ጉቴ ትላንት ማምሻውን በነቀምቴ መኖሪያ ቤታቸው ደጃፍ በጥይት ተመተው መገደላቸው ተሰምቷል። ድርጊቱ በማን እና ለምን እንደተፈፀመ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ነገር ግን አቶ ግመቺስን ከቤት ያስጠራው ጓደኛ ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ተይዟል ተብሏል። የአቶ ገመቺስ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ ጥቅምት 17/2012 ዓ/ም…
#UPDATE

ነቀምት ላይ የተገደሉት የኢትዮ-ቴሌኮም(ethio telecom) የምዕራብ ሪጅን ኦፕሬሽንስ ዳይሬክተር ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጨረር አክሊሉ እንዳረጋገጡት፤ የምዕራብ ሪጅን ኦፕሬሽንስ ዳይሬክተር የነበሩት ገመቺስ ታደሰ እስካሁን ባለተገለፀ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ስርዓተ ቀብራቸውም ጥቅምት 17 ከቀኑ 8፡00 በነቀምቴ ከተማ መፈፀሙን ገልጸዋል፡፡ ባለሥልጣኑ የሞቱበትን ምክንያት እስካሁን ከፖሊስ እንዳልተገለጸላቸው ኃላፊዋ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ #AahaduTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለታዳጊ ሴቶች የማሕጸን ካንሰር መከላከያ ክትባት ዛሬ መሰጠት ጀመረ፡፡ በክልሉ ጤና ቢሮ የክትባት ኦፊሰር አቶ ሻውል ተሰማ  እንደገለጹት በነጻ የማጸን በር ካንሰር በሽታ መከላከያ ክትባቱ የሚሰጠው እድሜያቸው 14 ዓመት ብቻ ለሆኑ ታዳጊ ሴቶች ነው፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የአንበጣ መንጋ በተከሰተባቸው አካባቢዎች #በአውሮፕላን የታገዘ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ የመከላከል ስራ መጀመሩን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለኔ የሚገባኝ የአፍሪቃውያን ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ መዳኛ ይሄ ነው - ኡቡንቱ!

ስለሰው መጥፎውን አስሬ በመውቀስ እና አግዝፎ በመኮነን የሚቀየር ነገር የለም - ጥፋቱን ከማባባስ ውጪ። በህብረት እና በመልካምነት ክፉውን ስራ በደግ ማጣፋት ለግለሰቡም ለማህበረሰቡም ዳግም ከክፉው ለመራቅ ይጠቅማል። ያው እንደ law of attraction መሆኑ ነው!

በወቀሳ ብዛት የትኩረት አቅጣጫዎች ሁሉ አሉታዊ ይሆኑና ገደብ የለሽ አሉታዊ ነገሮችን እንደ ማግኔት እየተሳሳቡ ዙሪያችንን እንዲከቡት እድል ይሰጣል። በአንፃሩ አጉልተን የምናነሳቸው አወንታዊ ነገሮች መሰል መልካም ነገሮችን የመሳብ ጉልበታቸው ከፍተኛ ነው። ይህ የተፈጥሮ ህግ ነው።

የጥንነት አፍሪቃውያን ይህ የተፈጥሮ ህግ የገባቸው እንደነበሩ በደቡብ አፍሪቃ ቅሪታቸው የቀረ የጎሳ እሴቶች ምስክር ናቸው። ይህ እሴት UBUNTU ይሉታል - የህይወት መርሃችን ብናደርገው እኛም ተለውጠን ዙሪያችንን ለመለወጥ ትልቅ ጉልበት ይሰጠናል።

ሰው ሁሉ መልካም ነው!

Via Yonatan TR

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ባለፈው ሳምንት ረቡዕና ሀሙስ በተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሱ ተቃውሞዎችን ተከትሎ የተቀሰቀሱ ግጭቶች የብሔርና የሃይማኖት መልክ ይዘው ለቀናት ከቀጠሉና ከ67 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፉ በኋላ በድርጊቱ ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጠሪዎች እየተያዙ ይገኛሉ።

(BBC)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀረር

ጥቅምት 17/2012 ዓ/ም

ባለፈው ሳምንት በሐረር ከተማ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ዛሬም በከተማዋ የነበረው እንቅስቃሴ መቀዝቀዙን ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ክፍል ያናገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው የዋሉ ሲሆን ወደ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ተገልጋዮች ስለማይታዩ ጭር እንዳሉና አንዳንድ ሱቆችም ዝግ ሆነው ውለዋል።

በከተማዋ ያሉ መንገዶች እምብዛም ተሽከርካሪዎች ስለማይታዩባቸው ጭር ማለታቸውን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ የጸጥታ አካላትም በከተማዋ እየተዘዋወሩ ጥበቃ እያደረጉ እንደሆነም ተገልጿል።

በተጨማሪም ቀደም ካሉት ቀናት በተለየ የጸጥታ አካላት ስለትም ሆነ ዱላ ይዞ መንቀሳቀስን ከልክለዋል። እነዚህን ቁሶች ይዘው ከሚገኙ ሰዎች ላይ እንደሚቀሙ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሰልፍም ሆነ ግጭት እስካሁኗ ሰዓት ድረስ አለመከሰቱን ለማወቅ ተችሏል።

(BBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሞጆ

ጥቅምት 17/2012 ዓ/ም


ዛሬ ጠዋት በሞጆ ከተማ በተከሰተ ሁከት ሁለት ሰዎች በጥይት ተመተዋል። በከተማዋ ዛሬ ጠዋት 'የታሰሩ ሰዎች ከእስር ይለቀቁ' በማለት ሰልፍ የወጡ ሰዎች ከመንግሥት ጸጥታ አስከባሪዎች ጋር ተጋጭተው በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማው ከንቲባ ወ/ሮ መሰረት አሰፋ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቅዳሜ ሌሊት ላይም በከተማዋ በምሽት ሰልፍ ተካሂዶ እንደነበር ከንቲባዋ ተናግረዋል። "ቅዳሜ ሌሊት 'ቤተክርስቲያን ተቃጥለ' የሚል ወሬ ተናፍሶ ሌሊቱን ሁከት ተፈጥሮ ነበር። በንብረት ላይ ጉዳት ደርሶ ነበር" ብለዋል።

ከንቲባዋ ጨምረው እንደተናገሩት ቅዳሜ ሌሊት ቤተ-ክርስቲያን ተቃጥሏል እየተባለ የተናፈሰው ወሬ ሃሰት መሆኑን እና ይህ የተደረገው "በከተማው ሆን ተብሎ ረብሻ ለመፍጠር" ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ መልኩ ዛሬም 'የታሰሩ ሰዎች ከእስር ይለቀቁ' በማለት አደባባይ እንደወጡ እና ከጸጥታ አካላት ጋር እንደተጋጩ እንዲሁም በተከፈተው ተኩስ ሁለት ሰዎች መጎዳታቸውን አስረድተዋል። እስካሁን የብሔር ግጭት ለመቀስቀስ የሞከሩ 9 ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የተናገሩት ከንቲባዋ፤ ዛሬ ተከስቶ የነበረው ሁከት በቁጥጥር ሥር ውሎ በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ጨምረው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ BBC አማርኛው አገልግሎት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዳማ #ሰበታ

ጥቅምት 17/2012 ዓ/ም

አዳማ ከተማ ከባለፈው ሳምንት በተሻለ መልኩ አንጻራዊ ሰላም እንደሚታይባት በከተማይቱ የሚገኝ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ዘግቧል። የአዳማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ራውዳ ሁሴን በከተማዋ ዛሬ ጠዋት የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ ጥሪዎች ሲደረጉ መቆየታቸውን ጠቅሰው የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ይህን ለማስቆም ጥረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በነዋሪዎች ዘንድ ከሚስተዋለው የደህንነት ስጋት ውጪ ከተማዋ ከሞላ ጎደል ወደ ቀድሞ የንግድ እንቅስቃሴ እየተመለሰች መሆኑን በስፍራው የሚገኝ የቢቢሲ ጋዜጠኛ ዘግቧል። ሰበታ ከተማ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች መሆኑን የከተማው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ታዬ ዋቅኬኔ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የንግድ ተቋሞቻቸውን ዘግተው ከነበሩት እና ከአጠቃላይ ነዋሪው ጋር ውይይት ማድረጉ እንደቀጠለ ተናግረው፤ መልካም የሚባል ለውጦች እየተመለከቱ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

(BBC)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BaleRobe #BaleGoba

በማሕበራዊ ሚዲያዎች ዛሬ ጠዋት በባሌ ዞን በሚገኙ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋል ሲባል የነበር ቢሆንም በከተሞቹ ዛሬ ምንም አይነት የተቃውሞ ሰልፎች አለመካሄዳቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በተመሳሳይ መልኩ በነዋሪዎች ዘንድ ካለው የደህንነት ስጋት ውጪ በከተሞቹ አንጻራዊ ሰላም መኖሩን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልል መንግስት...

ባለፈው ሳምንት ከተደረጉ ሰልፎች ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱ እና ሕዝቡም ወደ የዕለት ተዕለት ሕይወቱ  መመለሱን የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል። ግጭት ተፈጠሮባቸው በነበሩ አካባቢዎች በደህንነት ስጋት አካባቢዎቹን ለቀው የሸሹ ሰዎች ወደየመኖሪያ አካባቢያቸው  መመለሳቸውም ተገልጿል።

https://telegra.ph/ETH-10-28-3

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ነቀምቴ

"...ጥቃት ያደረሰባቸው ሰው ማንነት ገና አልታወቀም። የፀጥታ ሰዎች ግን ክትትል እያደረጉ ነው። ከሰሞኑ ጉዳይ ጋር አይገናኝም!" አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ
.
.
ኢትዮ-ቴሌኮም የምዕራብ ሪጅን ሥራ አስኪያጅ አቶ ገመቺስ ታደሰ ትናንት ምሽት በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸውን የነቀምት ከተማ ኮምንኬሽን ጽህፈት ቤት ዛሬ አስታውቋል። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ቦኮንጃ ለጀርመን ራድዮ ጣቢያ እንደተናገሩት አቶ ገመቺስ የተገደሉት ተተኩሶባቸው ነው፤ ጥቃቱን ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ማንነት ለመለየትም የፀጥታ አካላት ክትትል እያደረጉ ነው። ግድያው ሰሞኑን በኦሮምያ ከተፈጠረው አመረጋጋት ጋር የተያያዘ ስለ መሆን አለመሆኑ የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ ግድያው ከሰሞኑ ተቃውሞ ጋር የተያያዘ አይደለም ብለዋል።

«ትናንት ማታ የተመቱት ግለሰብ በመሣሪያ ነው የተመቱት። በመኖሪያ ቤታቸው ነው ጥቃቱ የደረሰበት። ጥቃት ያደረሰባቸው ሰው ማንነት ገና አልታወቀም። የፀጥታ ሰዎች ግን ክትትል እያደረጉ ነው። ከሰሞኑ ጉዳይ ጋር አይገናኝም። ከዚሁ ጋር በተገናኘ የተለየ ሰልፍ የወጣ የለም። የተለየ ያሳየው ተቃውሞም የለም።» የነቀምት ከተማን ጨምሮ የወለጋ አራቱም ዞኖች ላለፉት አራት ወራት በወታደራዊ እዝ (ኮማንድ ፖስት) ስር ናቸው።

Via DW(የጀርመን ድምፅ ራድዮ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀረር❤️በአካባቢያቸው ሰላምና አንድነትን ለማጠናከር በቅንጅት እንደሚሰሩ በሐረሪ ክልል የኃይማኖት አባቶች ተናግረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጫማ አዳሹ ወጣት የ1,500,000 ብር እድለኛ ሆነ!

ጫማ በማደስ ራሱንና 3 ቤተሰቦቹን የሚያስተዳድረው ወጣት የእንቁጣጣሽ ሎተሪ 4ኛ ዕጣ አሸነፈ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ክ/ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት ብሩክ ገላው በእንቁጣጣሽ ሎተሪ 4ኛ ዕጣ 1,500,000 ብር እድለኛ ሆኖ የሽልማት ቼኩን ተረከበ፡፡

ዕድለኛው መርካቶ ውስጥ አንድ የግል ጫማ ቤት ውስጥ ጫማ በማደስ የሚሰራ ሲሆን ባለትዳርና የሁለት ልጅ አባት ነው፡፡ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበረን ቆይታ “በርካታ ጊዜ ሎተሪ እየቆረጥሁ እድሌን እሞክር ነበር፤ ይህን የሰጠኝ የልጆቼ አምላክ ነው ለእነሱም የሚሆን መጠለያ እገዛበታለሁ” በማለት ተናግሯል፡፡

ምንጭ፦ ብሄራዊ ሎተሪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#ሮቤ

በተቃውሞ ስትናጥ በሰነበተችው በባሌ ሮቤ ከተማ የተሰበሰቡ ሰዎች ከሌሎች ብሔር አባላት መገበያየት፣ ቤት መሸጥና እና ማከራየትን የሚያግድ ትዕዛዝ ካስተላለፉ በኋላ ከተማዋ አሁንም ሥጋት ላይ ነች። የከተማዋ ከንቲባ እና አንድ ሐይማኖታዊ መሪ ግን ተላለፈ የተባለው ትዕዛዝ የባሌን ሕዝብም ሆነ የሮቤን ከተማ አይወክልም ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia