TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ROBE

"ከነሱ እንዳትገዙ... ቤት አታከራዩ... ያከራያችሁም አስወጧቸው ተብሎ በትክክልም የተከራየው እቃውን እያጋዘ ወደሌላ አካባቢ እየሄደ ነው። አሁን እራሱ አብዛኛው ሰው በራሱ ሀገር ስደተኛ ሆኖ ነው ያለው።" (ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የሮቤ ከተማ ነዋሪ)
.
.
"በወቅቱ ሶስት ሰዎች በአንድ ቦታ ሲቀበሩ፤ በርካታ ሰዎች በአንድ ቦታ ሲሞቱ በተፈጠረ ስሜታዊነት የተባለው ነገር ተደርጎ ካልሆነ በቀር እንደሀገርም ሆነ እንደ ብሄር የተፈጠረ ነገር የለም። ተሰጠ የተባለው ትዕዛዝ ተግባራዊ አይሆንም። ህዝቡ ተስማምቶበታል። በዚህች ሀገር ቻይና መጥቶ ከእኛ ጋር እየሰራ ባለበት ሁኔታ፣ ከአውሮፓውያን ጋር አብረን እየሰራን ባለንበት ሁኔታ የሀገራችን ብሄሮችና ብሄረሰቦች በእኩልነት አብሮ ሊኖርና በጋራ ለመጠቀም ሁሉም መብት አለው።" ሃጂ ቃሲም ኡስማን (የሮቤ ከተማ ነዋሪና የሀገር ሽማግሌ)
.
.
"በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እየተለቀቁ ያሉ መረጃዎች የባሌንም ሆነ የሮቤን ከተማ የሚወክሉ አይደሉም። የሆነ ቡድን ተሰባስቦ ተዕዛዝ ሊያወጣ ይችላል። የትኛውም ብሄር ቢሆን በከተማችን እስካሁን ምንም ችግር ደርሶበት አያውቅም። መልካም የሚባል የአብሮነት ህይወት ነበረው። ነገር ግን አሁን የተፈጠረው ችግር ከብሄር የሚያያዝና ቤት መከራየትን አብሮነትን የሚከለክል አይደለም።...ከአክቲቪስት ጃዋር መሃመድ ጋር በተያያዘ ተደርጎ በነባረው ሰልፍ ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ ሰው በስሜት የተለያዩ ነገሮችን ሊያስተላልፍ ይችላል። የሮቤን ከተማ ነዋሪ ለማፈናቀል ነው እየተባለ በማህበራዊ መገናኛዎች የሚተላለፉ መረጃዎችን መቀበል ተገቢ አይደለም።" አቶ ግድም ኡመር (የሮቤ ከተማ ከንቲባ)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia @tsegabwolde