የሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ የስንብት ፕሮግራም በአሁኑ ሰዓት ላይ ቤተሰቦቹ፣ የሞያ አጋሮቹ እንዲሁም ወዳጆቹ በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር እየተካሄደ ይገኛል። የቀብር ሥነ ስርአቱም ከቀኑ በ9 ሰአት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአጣዬ 8 ሰዎች ተገደሉ!
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና አካባቢዉ ከትናንት በስቲያ በተቀሰቀሰዉ ግጭት የ5 ሰላማዊ ዜጎች እና ሕይወት ማለፉ ተገለፀ። በግጭቱ ከመንግሥት ወገን 3 የፀጥታ ኃይላት መሞታቸውንና 5 መቁሰላቸውም ተገልጧል።
የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸዉ በቀለ እንደገለፁት በአካባቢዉ ግጭቱ የተቀሰቀሰዉ ከ3 ቀን በፊት አንድ የታጠቀ ግለሰብ የክልሉ ልዩ ኃይል በሚገኝበት የጥበቃ ማማ ላይ በከፈተዉ ተኩስ ነዉ።
ግለሰቡ ጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በማይቻልበትና በኮማንድ ፖስት ስር ባለ አካባቢ 3 የእጅ ቦንቦች፤ ክላሽንኮቭ እና በርካታ ጥይቶችን ይዞ በመገኘቱ በተኩስ ልዉዉጥ እንደተገደለ አቶ ጌታቸዉ ዐስታዉቀዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-07-3
Via #DW

ፎቶ📸በብሄራዊ ቴአትር የተካሄደው የሙዚቀኛ ኤሊያስ መልካ የስንብት መርሃ-ግብር። በመርሃ ግብሩ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳሁን ፣ ረ/ፕሮፌሰር ነብዩ ባዩን ጨምሮ ቤተሰቦቹ ፣ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎቹ ተገኝተው ነበር፡፡
PHOTO: Mayor Office AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
PHOTO: Mayor Office AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ መንግስት በ2012 በጀት ዓመት ትኩረት ሰጥቶ ስለሚሰራቸው ጉዳዮች በንግግራቸው ካነሷቸው አንኳር ነጥቦች መሃል፡-
• በ2012 የለውጡን ጉዞ የተሻለ ቁመና ላይ እንዲገኝ በትኩረት ይሰራል
• በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን ከፍታ እንዲረጋገጥ መሰረት ይጣላል
• በኢኮኖሚ፣ በድፕሎማሲ እና መሰል ተግባራት የተገኙ ስኬቶችን ለቀጣይ አገራዊ ስንቅ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
• እኩልነት፣ ፍትሃዊነት፣ መከባበር እና አንድነትን ሊያመጡ የሚያስችሉ፣ ከጉድለታችን እየተማርን፣ እያረምን እና እየገነባን ያጋጥሙንን ውዝፍ እዳዎች ለማስወገድ እንጥራለን።
• ለቀጣዩ ትውልድ ከእኛ የተሻለ ስራ ሰርተን ለማስረከብ እንጥራለን።
• ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎቻችን በመደመር እሴቶች ተዋጅተው የሚፈፀሙ ይሆናል።
• ውስጣዊ አለመረጋጋት እና ግጭቶች ተፈናቃዮችን ሜዳ ከቀያቸው እንዲሰደዱ በማድረግ ለአገሪቱ ፈታኝ የነበረ ቢሆንም ችግሩን በአገራዊ አቅም ለመቋቋም ተችሏል።
• በቀጣይ ችግሮች ሳይከሰቱ መቆጣጠር የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል።
• የፀጥታውን ዘርፍ ለማጠናከር የተደራጀ የፌደራል ፖሊስ እና የክልል ኃይሎች እንዲሁም የመከላከያ ኃይል የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ትግበራ በአዲስ መልክ ተጠናክሮ እውን ይሆናል።
• አገራዊ የሰላም ግንባታውን በህዝብ ተሳትፎ ለማረጋጥ የሚያስችል ስራ ይሰራል።
• አንዳችን ለአንዳችን የሰላም ምንጭ እንጂ የቁርሾ መነሻ እንዳንሆን በጋራ አብሮነት ልንሰራ ይገባል።
• ይህን ታላቅ ህዝብ እዚህም እዚያም የሚወረወሩ አሉቧልታዎች ሊረቱት አይገባም፣ በአርቆ አሳተዋይነት የጋራ ቤታችንን መጠበቅ ይኖርብናል።
Via #EBC

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ስለ አገራዊ የፖለቲካና ዲሞክራሲ ግንብታ ጉዳዮች የተናገሩት ፡-
• በመግባባትና በመመካር ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስትርዓት ለመገንባት መንግስት የሚጠበቅበትን ያደርጋል፡፡
• የትብብርና የአንድነት ፖለቲካ እንዲሰፍን ይሰራል፡፡
• የዘንድሮው ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ እንዲሁም ተቀባይነት ያለው ፣ ምልዓተ ህዝቡን ያሳተፈና ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ የታዩ ህፀፆችን ያረመ ምርጫ ለማካሄድ መንግስት ዝግጁ ነው፡፡
• ፍርድ ቤቶችን ለመሻሻል የሶስት ዓመት ማሻሻያ ስራ በመስራት የተጀመረውን የለውጥ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣የፍትህ ተደራሽነትና ቅልጥፍናን የሚያመጣ የፍትህ ስርዓት የመዘርጋቱ ሂደት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ይከናወናል፡፡
• ላለፉት 60 ዓመታት ስራ ላይ የዋሉ የወንጀልና የንግድ ህጎች ፣ የአስተዳደር ስርዓት ህግን ጨምሮ በአዲስ መልክ ፀድቀው ወደ ስራ ይገባሉ፡፡
• ሙያዊ ጋዜጠኝነት ተላብሰው ለሚሰሩ ጋዜጠኞች መንግስት ድጋፍ ያደርጋል፡፡

የሙዚቃ አቀናባሪው የኤልያስ መልካ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ። በዚህ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ከአርቲስቱ ጋር አብረው የሰሩ አንጋፋ እና ወጣት የጥበብ ባለሙያዎች፣ ቤተሰቡ፣ የሙዚቃ አፍቃሪያን እንዲሁም በያሬድ ትምህርት ቤት ያስተማሩት መምህራን እና ሌሎችም በርካታ ሰዎች ተገኝተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
75,900+ ትክክለኛው የTIKVAH-MAGAZINE ገፅ!
በስፋት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮች የሚዳሰሱበት የTIKVAH-ETH አንዱ አካል!
Join👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

በምስራቅ አፍሪካ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል!
በምስራቅ አፍሪካ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ጊዜ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውን የዓለም የፍልሰት ድርጅት ገለጸ።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለስልጣን /ኢጋድ/ ለአገር ውስጥ ተፈናቃዮች ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ በአዲስ አበባ እየመከረ ነው።
በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ተወካይ ማውረን አቺንግ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት የአገር ውስጥ ተፈናቃይ ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል።
በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጀመሪያ 41 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፤ በየዓመቱም 25 ሚሊዮን ሰዎች ይፈናቀላሉ ብለዋል።
ከዚህ ውስጥ በዚሁ የፈረንጆች ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት በምስራቅ አፍሪካ ብቻ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ጠቁመዋል።
3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ በግጭትና በአየር ንብረት ለውጥ በተለያዩ አገራት በስደተኞች ጣቢያዎች ተጠልለው እንደሚገኙ አስረድተዋል።
Via #ENA

አሳዛኝ ዜና!
በአዊ ብሔ/አስ/ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ!
ከእንጅባራ ከተማ ወጣ ብሎ #በአካይታ ቀበሌ በቀን 26/1/2012 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ስዓት አካባቢ ከእንጅባራ አምበላ ተሳፋሪ ጭኖ ይጓዝ የነበረ ኮድ 3-13645 አማ ታርጋ የሆነ አይሱዙ የህዝብ ማመላለሻ ከአዲስ አበባ ወደ እንጅባራ አቅጣጫ ከሚመጣ ሎቤድ ኮድ 3-84604 ኢት ጋር በመጋጨቱ ወዲያውኑ የ1 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሌሎቹ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በእንጅባራ አጠቃላይ ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነ የባንጃ ወረዳ የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኢ/ር አስማረ ገብረኪዳን ተናግረው እንዲሁም በንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ገልፀዋል፡፡
Via አዊ ኮሚኒኬሽን

Mekelle University | አሜሪካ ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ በምታደርገው ድጋፍ ዙሪያ በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ማይክል ራይነር ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር ተወያዩ። በዚሁ ወቅት የመቐሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ሀገሪቱ ለዩኒቨርሲቲው እያደረገች ላለችው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። በተጨማሪም በቀጣይ የትብብር መስኮች ላይ ምክክር አድርገዋል። በውይይቱ ላይ የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳም ተሳትፍዋል።
Via#FBC
ማስተካከያ!
ዛሬ የአሜሪካ AmbassadorMichealRaynor በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የነበራቸው አጭር ቆይታ ዋና አጀንዳ በኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት ሂደት ዙርያ ያሉትን ተግዳሮቶች በሚመለከት የባለሙያዎች እይታን ለመስማት ነበር። ፕሮፌሰር ክንደያ እና የፖለቲካ ምሁሩ መረሳ ፀሃየ በጉዳዩ ለአምባሳደሩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከአምባሳደሩ ጋር በተገኙት የፖለቲካ አማካሪያቸው ጥሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ስብሰባው ላይ ተገኝተው በጉዳዩ ዙርያ የትግራይ መንግስት እና ህዝብ ሃሳብ ገልፀዋል፣ ለጥያቄዎቹም መልስ ሰጥተዋል! ከዚህ ስብሰባ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ሚድያዎች እየተዘገቡ ያሉት ሌሎች ዜናዎች ስህተት መሆናቸውን እንገልፃለን!
Via Mekelle University
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via

ግጭቱ በህዝቦች መካከል የተነሳ አይደለም!
በአማራ ክልል ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ ከተማ ላይ ባልታወቁ ሰዎች ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳር አስታወቀ።
የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ተፈራ ወንድምአገኘሁ ዛሬ በሰጠት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት የተፈጠረውን አለመረጋጋት በዘላቂነት ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የሚያስችሉ ስራዎች በቅንጅት እየተከናወኑ ነው።
በክልሉ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ ቦታዎች አካባቢ የተከሰተው ግጭት በጸረ-ሰላም ኃይሎች ምክንያት እንጂ በህዝቦች መካከል የተነሳ እንዳልሆነም አስረድተዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-07-4

#AddisAbeba
በአዲስ አበባ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የ2012 ዓ.ም የትምህርት መርሃ-ግብር በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ መሰረት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
Via Addis TV

Addis Abeba Police Commission
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አዲስ ያዘጋጀሁት የፖሊስ ደንብ ልብስ ለመደበኛው ፖሊስ አይደለም ማለቱን ሪፖርተር አስነብቧል፡፡ ባለፈው ሳምንት ይፋ የሆነው ሬንጀር የደንብ ልብስ አዲስ ለተቋቋመው ቋሚና ተወርዋሪ ልዩ ሃይል የተዘጋጀ ነው፡፡ ተወርዋሪ ሃይሉ ከመደበኛው ፖሊስ አቅም በላይ በሆኑ የጸጥታ ችግሮች ጊዜ ይሠማራል፡፡ ለከተማ አስተዳደሩም የጥበቃ ክብር ዘብ ይሆናል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-07-5

🇪🇹ከዓለም 5ኛ
🇪🇹ከአፍሪካ 2ኛ
"ኢትዮጵያ በኳታር ዶሃ በተካሄደው የ17ኛው ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ሲሳተፍ ቆይቶ በሁለት ወርቅ፣ አምስት ብር እና አንድ ነሃስ በድምሩ በስምንት ሜዳሊያ ከዓለም 5ኛ ከአፍሪካ 2ኛ በመውጣት መስከረም 28/2012 ዓ/ም ከጥዋቱ 1:50 ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ይደርሳል..."

"ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች
በዚህ ዓመት ለማካሄድ የታቀደው አጠቃላይ ምርጫ ስምንት ወራት ያህል ነው የቀሩት። ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀሩ ምርጫው እንደሚካሄድ በተደጋጋሚ ቢያረጋግጡም፤ በዚህ ወቅት ግን ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ፓርቲዎች በውድድሩ እንደሚሳተፍ ወገን የሚያደርጉት የጎላ እንቅስቃሴ አይስተዋልም። ምን እየጠበቁ ይሆን?
"ምርጫውን ከማካሄድ የተሻለ አማራጭ ያለ አይመስለኝም" ፕ/ር መረራ ጉዲና
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ፕ/ር መረራ ጉዲና አገሪቱ ባልተረጋጋችበት ሁኔታ ምርጫ መካሄድ የለበትም የሚሉ ሰዎችን መረዳት ይከብደኛል ይላሉ። እንዲያውም አገሪቱ መስቀለኛ መንገድ ላይ በመሆኗ ምንም ዓይነት ይሁን ምን ምርጫ አካሂዶ ወደ ህዝብ መቅረብ እንደሚያስፈልግ ያምናሉ። አገሪቷን ዛሬ ያለችበት ሁኔታ ውስጥ የከተተው ኢህአዴግ ራሱ ሆኖ እያለ ይሄንኑ ኢህአዴግ ለምርጫ ሁኔታዎችን ያመቻች ብሎ መጠበቅ ቀልድ ነው ይላሉ።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BBC-10-07
BBC የአማርኛው አገልግሎት!

የኢህአዴግ ውህደት...
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዝዳንት #አሻድሌ_ሀሰን ኢህአዴግን ወደ ውህደት የሚያደርገውን ሂደት በተመለከተ የተናገሩት፦
• ባልወሰናቸው ውሳኔዎች፣ ባልተሳተፍንባቸው ጉዳዮች አጠቃላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ታዳጊ ክልሎች ወስደን እንድንፈጽም ይደረጋል
• አጋር ድርጅቶነና ታዳጊ ክልሎች መባላችን እነዚህን ክልሎች የሚመሩ ድርጅቶችና መንግስታቸውም ጭምር በራሳቸው ተማምነው ክልላቸውን እንዳይመሩ ሆነዋል፣
• ባለፉት 28 ዓመታት እነዚህን ክልሎች የሚመሩ መሪ ድርጅቶችም ሆኑ መንግስታቸው ጭምር በራሳቸው ተማመነው ስራ እንዳይሰሩ ሆነዋል፣
• ባለፉት 28 ዓመታት በነበረው ሂደት ታዳጊ ክልሎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ሊታጩ አይችሉም፣ በፓርቲው ውስጥ ድምጽ መስጠት አንችልም፣ ይህ ደግሞ በራሱ ስነልቦናዊ ጫና ፈጥሮብናለ፣
• አሁን ላይ ኢህአዴግ ወደ ውህድ ፓርቲ መምጣቱ ጠንካራ አገራዊ ፓርቲ በመፍጠር የአገራችንን ችግሮች ለመቅረፍ ያግዛል።
Via አዲስ ዘመን ጋዜጣ

TIKVAH-ETHIOPIA
#attention "ከሃረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ ለባቢሌ 10 ኪሜ ሲቀረው ያለው ድልድይ በመሰበሩ ከባለፈው እሮብ ዕለት ጀምሮ መንገዱን መሻገር አስቸጋሪ ሆኗል። ቅያሪ መንገድ ለማዘጋጀት ሞክረው ነበር ግን ጭቃ እየሆነ ከባድ መኪኖች በጭቃ እየተያዙ ነገሩን አስቸጋሪ አድርጎታል፤ አሽከርካሪዎችም እየተንገላቱ ነውና የሚመለከተው አካል መፍትሄ አስቸኳይ መፍትሄ ቢፈልግለት መልካም ነው።" PHOTO:…
HARAR🚧JIGJIGA
በፌደራል መንገዶች ባለስልጣን የሚተዳደረውና ከሀረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው የመኪና መንገድ ኤረር ቀበሌ አካባቢ የሚገኘው ድልድይ በመሰንጠቁ አገልግሎት መስጠት በማቋረጡ አሽከርካሪዎችና ተገልጋዮች እየተቸገሩ መሆኑን ተናገሩ።
ከድሬዳዋ ወደ ጎዴ አልሚ የእርዳታ እህል ጭኖ እየተጓዘ ሳለ በመንገዱ መበላሸት ምክንያት በአካባቢው ቆሞ ያገኘንው የከባድ መኪና አሽከርካሪ አቶ ደረጀ የማነህ እንደሚገልፀው አደጋ የደረሰበት ድልድይ በወቅቱ ባለመጠገኑ ለሰባት ቀናት የጫነው እቃ ሳናራግፍ በስፍራው ለመቆየት ተገደናል።
በአካባቢውም የተደራጀ ጥበቃ ባለሞኖሩ ንብረቱ ለስርቆት እየተዳረገ ነው፤ ተሽከርካሪም ለማለፍ ሲሉ ለትራፊክ አደጋ እየተዳረግን ነው ብለዋል፡፡
.
.
የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን የድሬዳዋ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ኢንጅነር ሱራፌል ሚካኤል እንደገለጹት ከአራት ቀናት በፊት በስፍራው የነበሩትን ተሽከርካሪዎች በሙሉ በተለዋጭ መንገድ ወደ ጅግጅጋና ሐረር ድሬዳዋ አሸጋግረናል በአሁኑ ወቅት በቦታው የሚገኙት ትላንትናና ዛሬ የገቡ ተሽከርካሪዎች ናቸው።
ችግሩን ለመቅረፍ በአጭር ጊዜ ከፀጥታ አካላት ጋር ብንሰራም የዝናቡ ሁኔናታ በተለይ ደግሞ የአሽከርካሪዎች ትግስት ማጣት ተለዋጭ መንገዱን ይበልጥ ለተጨማሪ ብልሽት እየዳረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።
ዋናውን መንገድ በመዝጋትና የኮንቦልቻ ጃርሶ፣ ጭናክሰን መንገድ እንደአማራጭ አሽከርካሪዎች እንዲጠቀሙ በማድረግ በሁለት ቀናት ውስጥ ተለዋጭ መንገዱን ለመስራት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-07-6

የአበርገሌ ወረዳ አስተዳዳሪና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ! በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአበርገሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ሁለት የድርጅት ጉዳይ የሥራ ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ እንደገለጹት የሥራ ኃላፊዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ዛሬ ረፋድ ነው፡፡ የሥራ ኃላፊዎቹ የአማራ ክልልን ሰላምና…
#ABERGELE
በትላንትናው ዕለት በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን የአበርገሌ ወረዳ አራት አመራሮች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወቃል። ባለሥልጣናቱ ትናንት ለስብሰባ ሰቆጣ ላይ በተገኙበት ነበር የታሠሩት። የእስራቸው ምክንያት ያልታወቀው ባለሥልጣናት ካልተለቀቁ በሚል የአካባቢው ኅብረተሰብ የመንግሥት ሠራተኞች ወደሥራ እንዳይገቡ እንዳገደ የወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትላንትናው ዕለት በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን የአበርገሌ ወረዳ አራት አመራሮች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወቃል። ባለሥልጣናቱ ትናንት ለስብሰባ ሰቆጣ ላይ በተገኙበት ነበር የታሠሩት። የእስራቸው ምክንያት ያልታወቀው ባለሥልጣናት ካልተለቀቁ በሚል የአካባቢው ኅብረተሰብ የመንግሥት ሠራተኞች ወደሥራ እንዳይገቡ እንዳገደ የወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HAWASSA
ሀገራዊ ለውጡን በብቃት ሊያስቀጥል የሚችል የፖሊስ አመራር ለማፍራት እየሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡ በክልሉ ለሚገኙ መካከለኛና ከፍተኛ የፖሊስ አመራር አካላት የተዘጋጀ ሥልጠና ዛሬ ተጀምሯል።

#ATAYE
ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱ ይታወቃል። መንግስት “ለግጭቱ ተጠያቂው ኦነግ ነው” ሲል ገልፆአል።
ኦነግ በበኩሉ ተከታዩን ምላሽ ሰጥቷል፦
“አጣዬ #ኦነግ ምን ሊሰራ #ይመጣል፣ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሰራዊት እንደሌለው ብዙ ጊዜ መላልሰን ተናግረናል በመሆኑም ስሞታው #ውሸት ነው” የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ
Via ዶቼ ቬለ