TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢህአዴግ ውህደት...

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዝዳንት #አሻድሌ_ሀሰን ኢህአዴግን ወደ ውህደት የሚያደርገውን ሂደት በተመለከተ የተናገሩት፦

• ባልወሰናቸው ውሳኔዎች፣ ባልተሳተፍንባቸው ጉዳዮች አጠቃላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎች ላይ ታዳጊ ክልሎች ወስደን እንድንፈጽም ይደረጋል

• አጋር ድርጅቶነና ታዳጊ ክልሎች መባላችን እነዚህን ክልሎች የሚመሩ ድርጅቶችና መንግስታቸውም ጭምር በራሳቸው ተማምነው ክልላቸውን እንዳይመሩ ሆነዋል፣

• ባለፉት 28 ዓመታት እነዚህን ክልሎች የሚመሩ መሪ ድርጅቶችም ሆኑ መንግስታቸው ጭምር በራሳቸው ተማመነው ስራ እንዳይሰሩ ሆነዋል፣

• ባለፉት 28 ዓመታት በነበረው ሂደት ታዳጊ ክልሎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ሊታጩ አይችሉም፣ በፓርቲው ውስጥ ድምጽ መስጠት አንችልም፣ ይህ ደግሞ በራሱ ስነልቦናዊ ጫና ፈጥሮብናለ፣

• አሁን ላይ ኢህአዴግ ወደ ውህድ ፓርቲ መምጣቱ ጠንካራ አገራዊ ፓርቲ በመፍጠር የአገራችንን ችግሮች ለመቅረፍ ያግዛል።

Via አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia