TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
⬆️ይህ የወላጆች፣ ተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲ ውል የሚመለከተው መረጃ በ @tikvahethmagazine /TIKVAH-ETH/ የቀረበው ከ20 ቀን በፊት ነው። በወቅቱ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ውሉን አሟልተው የማይመጡ ተማሪዎችን እንደማይመዘግብ ገልፆ ነበር። ደብረ ማርቆስም በተመሳሳይ ከጥቂት ቀናቶች በፊት ነበር ይህን ያለው። ነገር ግን ይህን ጉዳይ ለመላው የሀገሪቱ ተማሪዎች ሊያብራራ የመጣ አካል አልነበረም። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለሚዲያዎች አልተናገረም። በዚህ ተማሪዎች ወደተቋማቸው እየገቡ ባሉበት ወቅት ይህ መባሉ ብዙዎችን እያደናገረ ይገኛል። ቀደም ብሎ ሰፊ ሽፋን ሊሰጠው ሲገባ ይህ አልተደረገም። አሁንም ተማሪዎች ውሉን ለመፈራረም ሲሄዱ ብዙ ቦታ አናውቅም የሚል ምላሽ እየተሰጣቸው ይገኛል። ከላይ እስከታች በተናበበ መልኩ ስራዎች ሊሰሩ ይገባ ነበር።

@tsegabwode @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሙሃመድ አብዱላሂ የኮንኮርዲያ ዓመታዊ የአመራር ሽልማት አሸናፊ ሆነው ተመረጡ። መሪዎቹ ሽልማቱን አሸናፊ የሆኑት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ባሉ አገሮች መካከል ለተፈጠረው ሰላም እና የኢኮኖሚ ትስስር ላበረከቱት አስተዋጽዖ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንድ ሰው «በተባራሪ ጥይት» መገደሉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል!

በድሬዳዋ ከተማ #በተቀሰቀሰው ግጭት አንድ ሰው «በተባራሪ ጥይት» መገደሉን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ። በግጭቱ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን እና በውል ያልታወቀ ንብረት መዘረፉን የአስተዳደሩ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ተወካይ ኃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። 

በድሬዳዋ ደቻቱና አምስተኛ ከተባሉ አካባቢዎች ተነስቶ ወደ ሌሎች እየተስፋፋ በመጣው ግጭት ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ሲወድም የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉን የአስተዳደሩ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ከሃምሳ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ገልጿል። 

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-24-8

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዘላቂ ሰላምን ፍለጋ በኢትዮጵያ⬆️

የሀገሪቱ የሰላም እጦት ኢኮኖሚውን እንደጎዳው ተገለፀ። ለሁለት ቀናት በመቐለ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የምሁራንና የፖለቲካ አመራሮች የውይይት መድረክ ዛሬ ተጠናቋል። በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የዴሞክራሲ፣ የልማትና የህዝቦች ተጠቃሚነት ጥያቄዎች መመለስ እንደሚገባ በውይይት መድረኩ ላይ ተጠቁሟል፡፡

Via DW አማርኛ/ድምፂ ወያነ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግብፅ

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል–ሲሲ ኢትዮጵያ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ ለመገንባት ስትነሳ አመርቂ ጥናት #አልሰራችም ሲሉ ከሰዋል። በግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር ፈቅ ሳይል መቀጠሉ በቀጠናው መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ሲሉ #አስጠንቅቀዋል

የግብፁ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በተባበሩት መንግስታት መደበኛ ጉባኤ ያላይ ያደረጉትን ንግግር ከዚህ በታች በምታገኙት የዩትዩብ ሊንክ ገብታችሁ ማድመጥ ትችላላችሁ፦ "President Abdel Fattah el-Sisi Speech at 74th UN General Assembly" https://youtu.be/ibx4s7ZAs78

ከ12ኛው ደቂቃ ጀምሮ...

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የቶጎ ጫሌ መቅርጫ ጣቢያ 7 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 5 ኪሎ ግራም ወርቅና የተለያዩ ሀገራት ገኝዘቦችን ያዘ። መስከረም 13 ከለሊቱ 9 ሰአት አካባቢ አንድ ወደውጭ የሚላክ ጫት የጫነ አይሱዙ መኪና ላይ የቶጎጫሌ ፈታሾች ባደረጉት ጥረትና ጠንካራ ፍተሻ ነው ጥፍጥፍ ወርቁ፣ 175 ሺህ 584 የሳውዲ ሪያል እንዲሁም 7 ሺህ 155 ድርሃም በቁጥጥር ስር የዋለው።

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የቶጎ ጫሌ መቅረጫ ጣቢያ ፈታሾች ቀን ከሌሊት ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ኮንትሮባንድን ለመከላከል እያደረጉት ላለዉ ጠንካራ ስራ የገቢዎች ሚኒስቴር አድናቆቱን ገልጿል። የተያዘው ወርቅና ገንዘብ ለብሄራዊ ባንክ ገቢ እንደሚሆንም ተመልክቷል።

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከኩዌቱ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሼህ ሳባህ ካሊድ አል ሃማድ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 74ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን ተገናኝተው በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"President Abdel Fattah el-Sisi Speech at 74th UN General Assembly"
"President Abdel Fattah el-Sisi Speech at 74th UN General Assembly"
የግብፁ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ስለ ህዳሴ ግድቡ የተናገሩትን ትላንት ማስቀመጥልናችሁ ሊንክ ማየት ላልቻላችሁ በቀላሉ ከዚህ ከቴሌግራም ሳትወጡ ከላይ ባለው የድምፅ ፋይል ማድመጥ ትችላላችሁ።

JOHEN/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ከአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ!
"ምርመራው ዘግይቷል የሚባለው ነገር ትክክል አይደለም..." የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው

ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈፀሙትን ጥቃቶች የተመለከተው ምርመራ እንደቀጠለ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል እንደሻው ጣሰው ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል፡፡ ምርመራው ዘግይቷል የሚባለው ነገርም ትክክል አይደለም ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፡፡ የተወሰ ጊዜም እንደሚወስድ ይታወቅ እንደነበርም አብራርተዋል፡

ፖሊስ በጅምር ላይ የነበረውን ምርመራ አስመልክቶ መግለጫ መስጠቱን ያስታወሱት ኮሚሺነሩ፣ ሲጠናቀቅም ለሚመለከተው አካልና ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ኮሚሺነሩ አክለው እንዳሉትም ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ ከታሰሩ ተጠርጣሪዎች አብዛኛዎቹ ተለቀዋል፡፡ አሁን በቁጥጥር ሥር የሚገኙት ቁጥርም ከመቶ እንደማይበልጥ አስረድተዋል፡፡ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚሁ ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር፣ በመንግሥት ከሚገልፀው የበለጠ መሆኑን እንደሚናገሩ ይታወቃል፡፡

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን!

በ2011ዓ.ም ሁሉንም አይነት አደገኛ እጾችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና ከወንጀል ድርጊቱ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ የሆኑ 80 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፌዴራል ፖሊስ ገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ ለመልሶ ማልማት በተከለሉና በሻሸመኔ አካባቢ የተተከሉ እፆችን እንዲወገድ ማድረጉንም ጠቁሟል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-25

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢሕአዴግ የስያሜና የርዕዮተ ዓለም ለውጥ ለማድረግ ገና ውሳኔ አላሳለፍኩም አለ!

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በውኅደት አዲስ ፓርቲ እየመሰረተ ነው ፤ ስያሜውም ታውቋል መባሉን ተከትሎ አሐዱ ቴሌቪዥን የጠየቃቸው የግንባሩ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅት ዘርፍ ኃላፊው ፍቃዱ ተሰማ፤ የስያሜና የርዕዮተ አለም ለውጥን በተመለከተ የተደረሰበት ምንም ውሳኔ የለም ብለዋል፡፡

ሆኖም በውህደቱና ወጥ ፓርቲ ሆኖ ለመምጣት የተካሄደው ጥናት ላይ ውይይቶች እየተደረጉ ናቸው ያሉት ፈቃዱ፤ ውይይቶቹ ሲጠናቀቁም የግንባሩ እህት እና አጋራ ድርጅቶች አንድ በሚሆኑበት ዙሪያ ውሳኔ እንደሚተላለፍ ገልፀዋል፡፡ እስካሁን ግን በኢህአዴግ ውህደትና የስያሜ ለውጥ ላይ “ያለቀ ነገር የለም” ሲሉም አስረግጠዋል፡፡

ግንባሩ በጊዜው ይካሄዳል ባለው ምርጫ ላይ በአዲስ አደረጃት እንደሚመጣ ሊቀመንብሩ አብይ አህመድ በተደጋጋሚ ቢናገሩም በብሄራዊ ድርጅቶቹ መካካል እስካሁን መግባባት ላይ አለመደረሱን የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ፡፡

ምንጭ፦አሐዱ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በትብብር ስለሚሠጡ ስልጠናዎች ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተሠጠ ጥብቅ ማሳሰቢያ፦

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ እየታየ ያለዉን የከፍተኛ ትምህርት መስፋፋት ጥራትን በማያጓድል መልኩ እንዲከናወን ለማስቻል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በመንግስት ዩኒቨርስቲዎችና በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲሁም ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት ፍቃድ ከሌላቸዉ ሌሎች ድርጅቶች ጋር በመደበኛ፣ በርቀት፣ በማታ፣ ቅዳሜና እሁድ እና በኦንላይን የትምህርት አሰጣጥ ዘዴዎች ከተገቢዉ የመንግስት አካል የዕውቅና ፈቃድ ሳያገኙ በትብብር የሚሠጡ ትምህርትና ስልጠናዎች እንዲቋረጡ ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በሚኒስቴር መስሪያቤታችን መመሪያ መሠጠቱ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

1. ተቋማት በተጠቀሱት የትምህርትና ስልጠና አሰጣጥ ዘዴዎች ያስመረቋቸዉን እና በማስተማር ላይ ያሉትን ተማሪዎች ዝርዝር እስከ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ እድታሳዉቁ፣

2. በተጠቀሱት የትምህርትና ስልጠና አሰጣጥ ዘዴዎች ትምህርታቸዉን እየተከታተሉ ያሉ ተማሪዎች ካሉ ትምህርታቸዉን ለማስቀጠል ለማመቻቸት እንዲረዳ የትምህርትና ተያያዥ መረጃዎቻቸዉን እስከ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ለኤጀንሲዉ እንድታሳዉቁ

3. በዚህ ረገድ ከመንግስት ዕዉቅና ዉጪ የሚከናወኑ ተግባራትን ለሚኒስቴር መስሪያቤታችንና ለከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ጥቆማ በማድረስ ዜጎች ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
መስከረም 2012 ዓ.ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኢትያጵያ የጦማሪያን ማህበር ቢቋቋም ጠቀሜታው ምን ይሆን?

#በዩኔስኮ አዘጋጅነት የአንድ ቀን #የጦማሪያን ፎረም ትላንት ተካሂዷል፡፡ ፎረሙ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከኡጋንዳና ከኬኒያ የመጡ እንግዶች ያላቸውን ልምድም ያካፈሉበት መድረክ ሆኖ አልፏል፡፡ በተለይ በኬኒያ ያለው የጦማሪያን ማህበር በኢትዮጵያ ማህበሩ ቢቋቋም ከተጠያቂነት፣ መብትን ከማስከበር፣ ሀገራዊ ጉዳዮችን እንደ ዓላማ ይዞ ከመንቀሳቀስና በኬኒያ ካጋጠማቸው የመንግስት ጫና ጋር በማጣቀስ ለተሳታፊዎች ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-25-2
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዘመናዊ ህንፃ ለመገንባት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሰደው መሬት ላይ ግንባታ ለማካሄድ እየተዘጋጀ ባለበት ሁኔታ መሬቱን መነጠቁን ገለጸ። በጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቦጃ ታደሰ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ፍርድ ቤቱ በ2009 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘመናዊ የህንፃ ግንባታ ለማካሄድ ጥያቄ አቅርቦ ከአንድ ዓመት በኋላ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ስም በመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም ከሒልተን ሆቴልና ከካዛንቺስ ጫፍ ከቤተመንግስቱ ፊትለፊት አንድ ሄክታር መሬት ካርታ በመረከብ ግንባታውን ለማካሄድ የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-25-3
#update በቀጣይ ወር የ2021 ዲቪ ሎተሪ እንደሚጀመር የአሜሪካን ኤምባሲ አስታዉቋል። ኤምባሲዉ ሐሙስ መስከረም 15/2012 ስለፕሮግራሙ መስፈርቶች እና የአመዘጋገብ ሂደቱን በተመለከተ መግለጫ ይሰጣል።

Via #አዲስማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች የማይስ አሸናፊዎች (MICE Champion Award) ሽልማት ተበረከተላቸው። ምክትል ከንቲባው በናይጄሪያ ሌጎስ በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ ዲያስፖራ ቱሪዝም ኮንፍረንስ ላይ ሽልማቱ የተበረከተላቸው፡፡
@tsrgabwolde @tikvahethiopia
ትራምፕን ከስልጣናቸው ለማስወገድ በአሜሪካ ምክር ቤት ድምጽ እንዲሰጥባቸው ሊደረግ ነው!

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከስልጣናቸው እንዲወገዱ የአገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት/ኮንግረስ/ ድምጽ እንዲሰጥባቸው የዲሞክራቲክ ፓርቲ ከወዲሁ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ምክር ቤቱ ድምጹን የሚሰጠው በአውሮፓዊያኑ 2016 በተደረገው የፕሬዝዳንት ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ የወቅቱን ተቀናቃኛቸውን ለማሸነፍ በሚል በዮክሬን ላይ ተገቢ ያልሆነ ጫና አድርገዋል የሚል ክስ ስለቀረበባቸው መሆኑን ተነግሯል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን ካሸነፉ በሃላ የፖለቲካ ተፎካካሪያቸውን ጆን ባይደንና ልጃቸውን ዩክሬን በሙስና እንድትከሳቸው፣ አለበለዚያ ግን አሜሪካ የምትሰጠውን ወታደራዊ ድጋፍ እንደምታቆም ጫና አድርገዋል በሚል ነው ዴሞክራቶች ክሱን ያቀረቡት፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጉዳዮ ትክክል እንዳልሆነና የፈጠራ ወሬ እንደሆነ አድርገው ክሱን አጣጥለውታል ተብሏል፡፡ በአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫውን ድምጽ የያዙት ዲሞክራቶች በመሆናቸው ክሱን ገፍተው ከሄዱበት ፕሬዝዳንቱን ከስልጣናቸው ለማንሳት የሚሰጠው ድምጽ በአመዛኙ ይሁንታ ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይሁን እንጂ በአገሪቱ ሴኔት #አብላጫ ወንበር የያዙት ፕሬዝዳንቱን የሚደግፉት የሪፐብሊካን ፓርቲ በመሆናቸው የዴሞክራቶች ውሳኔ በሴኔቱ ውድቅ የመደረግ እድሉ ሰፊ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ/ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢዜማ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ነሃሴ 27 ቀን 2011 ዓም "ኢሳት በዚህ ሳምንት" በሚባለው ፕሮግራም ላይ ቀርበው በሰጡት ቃለምልልስ የምርጫ ቦርድን እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅም ሆነ የምርጫ እና የፖለቲካ ፖርቲዎችን ህግ በማርቀቅ ሂደት ሂደት በፓርቲየቸው የተወከሉ የህግ ባለሞያዎች በህግ ማርቀቅ ሂደቱ በንቃት ተሳትፈዋል ሲሉ የተናገሩት እውነታውን አዛብቶ የሚያቀርብ ገለፃ ሆኖ እንዳገኘው ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። ቦርዱ የኢዜማ ፓርቲ መሪ እውነታ አዛብቶ የሚያቀርብ ንግግር ተናግረዋል በዚህም ላይ ማስተካከያ ሰጥቻለሁ ወደፊትም በተመሳሳይ ክትትል በማድረግ የተዛቡ መረጃዎችን እርምት እሰጣለሁ ብሏል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ምርጫ ቦርድ የሰጠው ማስተካከያ👇
https://telegra.ph/ETH-09-25-4

የኢዜማ ፓርቲ መሪ ንግግር ከስር በሚገኘው ሊንክ ከ4ተኛ ደቂቃ ጀምሮ ይገኛል፦ https://www.youtube.com/watch?v=d5nK4wIQwBg&feature=youtu.be

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEW

📝ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የውል ቅፅ ሞልታቹ ኑ፤ ውሉን ሞልታችሁ ባትመጡ ቀርታችሁ እንግልት እና መጉላት እንዳይደርስባቹ ብሏል።

📝የኢትዮጵያ ቴክስታይል ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ይፋ ተደርጓል።

📝በፍኖተ ሰላም የሚገኙ ተማሪዎች ውል እንዲሞሉ ጥሪ ቀርቧል።

📝የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ይፋ ተደርጓል።

📝ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ይፋ ተደርጓል።

📝የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች መግቢያ ቀን ይፋ ተደርጓል።

📝የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ይፋ ተደርጓል።

📝የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ይፋ ተደርጓል።

📝የጅማ ከተማ ወላጆች እና ተማሪዎች ውል እድትገቡ።

📝አርባምንጭ የምትገኙ ውል እድትገቡ።

@tikvahethmagazine

ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎችን በTIKVAH-MAGAZINE ማግኘት ትችሎችሁ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ