TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኢትዮጵያ የካሜሩን አምባሳደርና በአፍሪካ ኅብረት የካሜሩን አምባሳደር እንዲሁም ልዩ መልዕክተኛ ጃኮስ አልፍሬድ ሰኞ፣ ነሐሴ 6/2011 ማለዳ ላይ ሞተው መገኘታቸውን የአፍሪካ ኅብረት ዋና ፀሐፊ #ሙሳ_ፋኪ_መሐመት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል። በአፍሪካ ኅብረት ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሞተው የተገኙት አምባሳደሩ፥ የህልፈታቸው ምክንያት በውል አልታወቀም። የአፍሪካ ኅብረትም #ለወዳጆቻቸው እና ለመላው #የካሜሩን ሕዝብ መፅናናትን ተመኝቷል።

Via #አዲስማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“በጸጥታ ኀይሎች ሕይወቱ ስላለፈው ሙሉጌታ ፖሊስ #መረጃ አልሰጠንም” ቤተሰቦች

•ፖሊስ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል

ሰኔ 18/2011 ጠዋት 4 ሰዓት አካበቢ በተለምዶ ሳሪስ አዲስ ሰፈር ድልድይ አካበቢ በሚባለው ልዩ ቦታ በፀጥታ ኀይሎች ሕይወታቸው አልፏል የተባሉትን የሙሉጌታ ደጀኔን ግድያ በተመለከተ መረጃ እያገኙ እንዳልሆነ ቤተሰቦቻቸው ቅሬታ አቀረቡ።

በዕለቱ ኹለት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት አድርሰው በመመለስ ላይ ሳሉ ሲቪል የለበሱ የጸጥታ ኀይሎች በመኪና እንደተከተሏቸውና እሳቸውም ለመሸሽ መሞከራቸውን የሟች ታናሽ ወንድም ዮናስ ደጀኔ ተናግረዋል።

በዕለቱ ሟች ሙሉጌታ እኚህ ማንነታቸውን ያላወቋቸው ኹለት ሰዎች በመኪና ሲከታተሏቸው እንደነበር እና መንገዱ በመዘጋቱም በእግራቸው ወርደው ሊሸሹአቸው ሞክረው እንደነበር ዮናስ ተናግረዋል። “ኮሮላ መኪናውን አቁሞ ነበር። እነሱም ለኹለት ይዘውታል፤ አጥፍቶ ከሆነ እንኳን ለሕግ ማቅረብ ነው እንጂ እርሱን መግደላቸው አሳዛኝ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። “የፖሊስ ልብስ የለበሱትን ግለሰቦች እናንተ ውሰዱኝ እነሱን አላውቃቸውም በማለት ደጋግሞ ሲጠይቅ እንደነበር በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ነግረውኛል።”

#አዲስማለዳ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-14-2
ከ50 በመቶ በላይ ወጣቶች የጫት ሱስ ተጠቂ ሆነዋል ተባለ!

የሴቶች ሕፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ባሳፍነው ሳምንት ይፋ ባደረገው ጥናት በኢትዮጵያ ካሉ አዋቂዎች እና ወጣቶች መካከል 51 በመቶ የሚሆኑት ጫት ቃሚዎች መሆናቸውን እና ከዚህም ውስጥ የወንድ ጫት ቃሚዎች ቁጥር ከፍተኛው እንደሆነ ጥናቱ አመላክቷል።

ከከተሞች ይልቅ #በገጠራማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ጫት መቃም እንደበለጠ የገለጸው ጥናቱ፤ በተለይም በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሶማሌ እና በአማራ ክልሎች ከሌላው የአገሪቱ አካባቢዎች በበለጠ በገጠራማ ክፍሎቻቸው የጫት ቃሚዎች ቁጥር እንደሚበዛም አመላክቷል። ጥናቱ በማከልም ከተለዩት የጫት ቃሚዎች በአማካኝ በ17 ዓመት ዕድሜያቸው ጫት መቃም እንደሚጀምሩ ገልጿል።

በጫት ምርት፣ ንግድ እንዲሁም ማኅበራዊ ውጤቶች ላይ በርካታ ምርምሮችን እንዲሁም መጽሐፍትን ያዘጋጁት ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳ፤ ጥናቱ በተለይም የጫት ቃሚዎች ቁጥር በገጠራማ አካባቢዎች ቁጥሩ ከፍ ያለ ነው የሚለውን እንደማይስማሙበት ገልጸው በተለያዩ ዓመታት በሠሯቸው ጥናቶች ከተሜው የበለጠ ጫትን እንደሚቅም ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።

#አዲስማለዳ

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-19
የደቡብ ክልል የ2012 በጀት አለመጽደቅ ውዝግብ አስነሳ!

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ላለፉት ስምንት ወራት መሰብሰብ ባለመቻሉ የክልሉን በጀት ያላፀደቀ ሲሆን የ2011 በጀት ላይ በመመስረት የአንድ ወር በጀት ብቻ ታስቦ መለቀቁ የዋጋ ግሽበትን ያላማከለ እና የዞን አመራሮችን ጫና ውስጥ የከከተ ነው ተባለ።

‹‹የተለቀቀው አንድ አስራ ሁለተኛ በጀት ያለፈው አመት ቀመር ላይ በመመስረቱ መደበኛ ስራዎችን ለማከናወንም ሆነ ለአስቸኳይ ወጪዎች በቂ አይሆንም፡፡ በተጨማሪም ገንዘቡ የግብር ከፋዩ ገንዘብ እንደመሆኑ ይህንን መከልከል አግባብነት የለውም›› ሲሉ የወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ወብን) የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ተከተል ላቤና ገለፀዋል።

የክልሉ ፕሬስ ሴክሪታሪያት ኀላፊ ፍቅሬ አማን በበኩላቸው የመንግስት ሰራተኞችን ደመወዝ ለመክፈል፣ መደበኛ ስራዎችን ለማስኬድ እንዲሁም #አስቸኳይ ስራዎችን ለማከናወን ጊዜያዊ በጀቱ በቂ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አክለውም ክልሉ የገቢ ግብር ማሰባሰብ ስራውን በማካሄድ ላይ መሆኑን ገልጸው የገንዘብ እጥረት አይኖርም ብለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በየትኛውም አይነት ሁኔታ ተሰብስቦ መደበኛ ስራውን መስራት በአዋጅ የተሰጠው ተግባሩ ነው ያሉት የወብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ይህንን ስራውን በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ማከናወን አለመቻሉም አግባብ አይደለም ሲሉ ይተቻሉ፡፡

#አዲስማለዳ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-19-2
ጣና ሐይቅን የወረረው የእምቦጭ አረም ስጋት ሆኖ ቀጥሏል!

ጣና ሐይቅን የወረረው የእምቦጭ አረምን ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ ባይቻልም እንኳን፣ መስፋፋቱ እንዲገታ ለማድረግ የሚረዱ እንቅስቃሴዎች ባሉበት መቆማቸውን የአማራ ክልል የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ባለስልጣን ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስታውቋል፡፡

አረሙን በጢንዚዛ ለማጥፋት የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ያደረገው ጥናት ተጠናቆ፣ ምርምሩ ተሠርቶና ጥንዚዛዎቹ የት ቦታ ይለቀቁ የሚለው ሁሉ የተለየ ቢሆንም፤ ገና ተግባራዊ እንዳልሆነ ምርምሩን በበላይነት የሚመሩት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህሩ ጌታቸው በነበሩ (ዶ/ር) ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስረድተዋል፡፡

እንደ ጌታቸው ገለጻም፣ የተደረገው ጥናት ተግባራዊ እንዳይሆን ካደረጉት ችግሮች መካከል፣ በጥናት መፍትሔ ይሆናል ለተባለው የጢንዚዛ ማራቢያ ማዕከል መገንባት ያለመቻሉ ነው። ግንባታውን ታሳቢ ያደረገ ጨረታ የወጣ ቢሆንም፣ በጨረታው የቀረበው ዋጋ ከተገቢው በላይ ከፍተኛ መሆኑ የእንቦጭ አረምን ለመግታት የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደገታው ነው አያይዘው ያነሱት። ‹‹እንቦጭን በቀላሉ ለማጥፋት እንዳይቻልና ስጋት ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎታል›› ብለዋል።

#አዲስማለዳ_ጋዜጣ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-29-2
በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ የ10 ሰው እና የ10 ዝሆኖች ህይወት አለፈ!

በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ በህገ-ወጥ እርሻና ሰፈራ መስፋፋት እንዲሁም ህገ ወጥ አደን ሳቢያ የተቆጡ ዝሆኖች በ2011 14 ሰዎችን ያጠቁ ሲሆን ስድስቱ ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል። ሌሎች አራት ሰዎችም በተለያየ ጊዜ በደረሰባቸው ጥቃት ህይወታቸው ሲያልፍ በተመሳሳይም አራት ግለሰቦች ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል።

አስር ዝሆኖች በአንድ ዓመት ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሦስቱ ግልገሎች መሆናቸውን የመጠለያው ኃላፊ አደም ሞሐመድ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገልጸዋል። ሰባቱ አዋቂ ዝሆኖችም በህገወጥ አደን ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ ግልገሎቹ በአካባቢው በሰፈሩት ሰዎች በመረበሻቸውና ለጭንቀት በመዳረጋቸው መሞታቸውን ገልጸዋል።

Via #አዲስማለዳ_ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በጅዳ አውሮፕላን ማረፊያ ችግር ገጠመው!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 767 በሳኡዲ ዐረቢያ ጅዳ ንጉስ አብዱላዚዝ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለመነሳት በማኮብኮብ ላይ ሳለ ከዐስሩ ጎማዎቹ ውስጥ ስምንቱ በመፈንዳታቸው ሳይነሳ ቀርቷል። የገጠመውን ችግር ተከትሎም የማኮብኮቢያ ሜዳው ዝግ እንዲሆን ተደርጎ ነበር።

ትናንት መስከረም 1/2012 በጅዳ ችግር የገጠመው ኢትዮጵያ አውሮፕላን ከማኮብኮቢያው ሜዳ ጥገና ወደ ሚያገኝበት ስፍራ እስኪወሰድ ድረስ ማኮብኮቢያው ሜዳ ለስምንት ሰዓታት ተዘግቶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። አውሮፕላኑ በሰዓቱ ከጅዳ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነበር።

Via #አዲስማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በቀጣይ ወር የ2021 ዲቪ ሎተሪ እንደሚጀመር የአሜሪካን ኤምባሲ አስታዉቋል። ኤምባሲዉ ሐሙስ መስከረም 15/2012 ስለፕሮግራሙ መስፈርቶች እና የአመዘጋገብ ሂደቱን በተመለከተ መግለጫ ይሰጣል።

Via #አዲስማለዳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ያስተምሩ የነበሩ መምህራን ችግር ላይ መሆናቸውን ገለጸዋል።

በጸጥታ ችግር ምክንያት ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው አዲስ አበባ የሚገኙ የመቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ከ2 እስከ 3 ወር ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ይገልፃሉ።

በአራቱ ዩኒቨርሲቲዎች ያስተምሩ የነበሩት መምህራን፤ የደሞዝ ክፍያው የተዛባው ከጥቅምት 2013 ጀምሮ ቢሆንም በመሀል በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ተወካዮች በኩል ክፍያ ተፈጽሞላቸው እንደነበር ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ከግንቦት ወር ጀምሮ የ3 ወር ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው እና በባንክ ያላቸውን ገንዘብ እንዳይጠቀሙ የባንክ አካውንታቸው መታገዱን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ይገልጻሉ።

በመቶዎች የሚቆጠሩት መምህራኑ፤ የሚሰሩባቸው ዩኒቨርሲቲዎች በሚገኙበት አካባቢ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ዝውውር ቢጠይቁም ጥያቄያቸው ተቀባይነት አለማግኘቱን ተናግረዋል።

የተለያዩ መምህራን ተደራጅተው ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት የደሞዝ ጥያቄ በደብዳቤ ያቀረቡ ሲሆን ሚኒስቴሩም ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ ባንክ እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር እየሠራ እንደሚገኝ ገልጾላቸው ነበር።

ይሁን እንጂ እስካሁን ደሞዛቸው እንዳልተከፈላቸውና የአብዛኞቹ መምህራን የባንክ አካውንት አለመለቀቁን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገልፀዋል። #አዲስማለዳ

@tikvahuniversity