TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አካል ከሚሆኑት 16 የኃይል ማመንጫ ጀኔሬተሮች መካከል አምስቱ ጀኔሬተሮች፣ የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ የሚፈለገው ውኃ ከተሞላ በኋላ እንዲገጠሙ ተወሰነ፡፡

ከፍተኛ ሀብት የሚወጣባቸው እነዚህ ውስን ጀኔሬተሮች ግድቡ ሙሉ በሙሉ በውኃ ሳይሞላ ኃይል ማመንጨት እንደማይችሉ እየታወቀ እንዲደረደሩ ማድረግ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የሌለው፣ ይልቁንም ለእነዚህ ጀኔሬተሮች የሚወጣውን ሀብት ለሌላ ፍላጎት በማዋል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማስገኘት የውሳኔው ምክንያትነት እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሆሮ (ኢንጂነር) አገኘሁት ባለው መረጃ እንዳመለከተው፣ የኃይል ማመንጫ ግድቡ ቀሪ ግንባታ በሦስት ምዕራፎች ተከፍሎ እንዲከናወን የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ያቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ መንግሥት ተቀብሎ እንዳፀደቀውና ግንባታውም በዚሁ በተከለሰ የግንባታ መርሐ ግብር መሠረት መከናወን ተጀምሯል፡፡

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-01

Via #Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ🛬እስራኤል ገቡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እስራኤል ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬም በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሆ ፅህፈት ቤት የክብር አቀባበል ይደረግላቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በእስራኤል የሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይህ ይፋዊ ስራ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማሻሻል እና ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋርም የውጭ ጉዳይ ሚኒስሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችም በመጎብት ላይ ይገኛሉ። በዚህ ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሆ፣ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሬቬን ሪቭሊን ጋር ይወያያሉ ተብሏል፡፡

እንዲሁም በናዚ የተጨፈጨፉ አይሁዳዊያን ማስታወሻ ሀውልትን እና የሀገሪቱን የሳይበር ዳይሬክቶሬት እንደሚጎበኙ ነው የሚጠበቀው፡፡ ኢትዮጵያ እና እስራኤል በግብርና፣ በውሃና መስኖ፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ዘርፎች ላይ በትብብር ይሰራሉ፡፡ በፀጥታ፣ ግብርና እና በቴክኖሎጂ በተለይ በሳይበር ዘርፍ ያለውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ይደረጋል ነው የተባለው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በእስራኤል የሚያደርጉት ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ለማጠናከር ሀገራቱ ያላቸውን ፍላጎት ማሳያ መሆኑንም በኢትዮጵያ የእስራኤል ኢምባሲ አስታውቋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሰሞኑን መነጋገሪያ የሆነው የፍየሎች እስር!

ከሰሞኑ ባለቤትነታቸው #የአረና ትግራይ ፓርቲ አባል ናቸው የተባሉ አስራ ስድስት ፍየሎች የመታሰራቸው ዜና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል። የአረና ፓርቲ ሊቀመንብር አቶ አብርሃ ደስታ በላፈው ረቡዕ የፓርቲው አባል ንብረት የሆኑ 16 ፍየሎች በትግራይ ክልል ቆላ ተምቤን ወረዳ ንኡስ ወረዳ ወርቅ አንባ ቀይሕ ተኽሊ ቀበሌ ውስጥ መታሰራቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የፍየሎቹ ባለቤት የሆኑት አቶ ዜናዊ አስመላሽ 16 ፍየሎቻቸው ታስረውባቸው እንደነበረ ተናግረው፤ ታስረው ከነበሩት ፍየሎች ሶስቱ አምልጠው ወደ ቤት መመለሳቸውን #ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ይህን ጉዳይ ሌሎች የውጭ ሀገር ሚዲያዎችም ሲቀባበሉት ታይቷል👇
#Congratulations

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ የሕክምና ባለሙያዎችን በስካይ ላይት ሆቴል እያስመረቀ ነው፡፡ ኮሌጁ በቅድመ- እና ድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን የሕክምና ባለሙያዎችን ነው በማስመረቅ ላይ ያለው፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴና የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላበረከቱም የክብር ዶክትሬቶች ይሰጣሉም ተብሏል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተሻሻለዉ የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ጸድቆ ስራ ላይ ዋለ!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎችን ከመቀበልና ከማስመረቅ ባለፈ፤ ከጥራትና ብቃት እንዲሁም ሀገሪቱ ቅድሚያ በምትሰጠው ዘርፍ በቂና ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት በኩል ውስንነቶች ያሉ በመሆኑ፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህግና ስርዓትን ተከትለው ተልዕኳቸውን በስኬት በመወጣት መንግስትና ህዝብ የሚጠብቅባቸውን ውጤት ማስገኘት እንዳይችሉ ዘርፉን የሚመራው ህግ የነበረው የይዘት ክፍተትና ይህም ያስከተለው የአፈጻጸም ጉድለት አንዱ የዘርፉ ችግር ሆኖ በመገኘቱ፤ የከፍተኛ ትምህርት ስርዓትና ተቋማት የትምህርት አግባብነትና ጥራትን ያረጋገጡ እንዲሆኑ፤

ተቋማት የትምህርትና ስልጠና፣ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት መስጫ ማዕከል እንዲሆኑ፤ ሀገሪቱ ቅድሚያ ለምትሰጣቸው ዘርፎችና ችግሮች ቅድሚያ የሚሰጡ እና ተቋማዊ አስተዳደሩ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ፍትሐዊነት የሰፈነበት ማድረግ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ከሀገራችን የዕድገትና ተቋማቱ ሊኖራቸው ከሚገባ ቁመና ጋር የተጣጣመ ለማድረግና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል፤ በዕውቀት፣ በክህሎት እና በስነ-ምግባር የዳበሩ ብቁ ዜጎች ማፍራት፤

በህግና ስርዓትን ማዕቀፍ ውስጥ ተጠያቂነትንና ኃላፊነትን ባረጋገጠ መልኩ ተቋማዊ እና አካዳሚክ ነጻነታቸው ተጠብቆ፤ ተልዕኳቸውን መወጣት እንዲችሉ ለማድረግ ነባሩን ህግ በማሻሻል አዲስ ህግ ማውጣት በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፊዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 55(1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

https://moshe.gov.et/visitor/documents/8
https://drive.google.com/file/d/1kwTHQUyk4CnRNtcySgsDGceytiCS6x2h/view?usp=embed_facebook
#ISRAEL📸በእስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በናዚ የተጨፈጨፉ አይሁዳውያን ማስታወሻ ማዕከልን ያድ ቫሼምን ጎበኙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለዑካቸው በማእከሉ የሚገኙትን የመታሰቢያ ሙዚየም፣ የህፃናት መታሰቢያን እና አዳራሽ ጎብኝተዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማእከሉ የክብር መፅሃፍ ላይ መልእክታቸውን አስፍረዋል።

ምንጭ፡-ኤፍ ቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations ናሽናል ኮሌጅ በዲግሪና ቲኢቪቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በኦሮሚያ ባህል ማዕከል እያስመረቀ ይገኛል።

ፎቶ📸እዩኤል/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ ከተማ ወደ ቀድሞ ሰላሟ እየተመለሰች መሆኑ ተገለጸ!

ሀዋሳ ከተማን ወደ ቀድሞ ሰላሟ እየተመለሰች በመሆኑ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች መጥተው በከተማዋ ቆይታ እንዲያደርጉ የተለያዩ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ጥሪ አቀረቡ። ከሀገሪቱ የተውጣጡ የሚዲያ አካላት ከተማዋን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ በሀዋሳ ከተማ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ የፌደራልና የክልል ባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤቶች በጋራ በመሆን ወቅታዊ ሁኔታውን በሀገር አቀፍ ያሉ የሚዲያ ተቋማት መጥተው በከተማዋ ያለውን ሰላማዊ ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡

ስለ ሀዋሳ ከተማ ሰላምና የሆቴሎች አገልግሎት አሰጣጥ አስተያየታቸውን ከሰጡ ጎብኝዎች መካከል ከአዲስ አበባ የመጡት አቶ ሚሊዮን ታፈሰ እና ከየመን የመጡት ወይዘሮ ብልቂሳ አብደላ ሀዋሳ ከተማ ከወር በፊት ሰላም እንዳልነበር መስማታቸውንና በአሁኑ ጊዜ ከተማዋ ሰላሟ መመለሱን፤ የሆቴሎች አገልግሎትም ጥሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

#SRTA

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-01-2
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለዶ/ር አብይ አህመድ አቀባበል አድርገዋል። ጋዜጣዊ መገለጫም ሰጥተዋል። ይህም በቀጥታ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ፌስቡክ ገፅ #በቀጥታ ሲሰራጭ ነበር" The Prime Minister of Israel"

WATCH LIVE! Prime Minister Benjamin Netanyahu welcomes Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed, at the Prime Minister's Office in Jerusalem🇮🇱https://www.facebook.com/IsraeliPM/
"ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ዜጎች ከቂም፣ በቀልና ጥላቻ በመራቅ በጎ በጎውን መስራት አለባቸው" – አቶ መስጠፌ መሃመድ

በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ዜጎች ከቂም፣ በቀልና ጥላቻ በመራቅ በጎ በጎውን መስራት እንዳለባቸው የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ መስጠፌ መሃመድ ገለፁ። ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ይህን ያሉት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተጀመረው የሰላምና የፍቅር ፌስቲቫል መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ነው። ፌስቲቫሉ በጅግጅጋ ስታዲየም በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድር፣ በሙዚቃ ድግሶችና ማርሽ ባንድ ተጀምሯል።

https://telegra.ph/ETG-09-01

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ኮማንድ ፖስቱ ቢኖርም ባይኖርም ከተማዋ በአስተማማኝ ሰላም ውስጥ ትገኛለች፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ዛሬ ይውጣ ቢባል ይወጣል,››የከተማው ኮማንድ ፖስት ኃላፊ ኮሎኔል ተክለ ብርሃን ገብረ መድን #HAWASSA

#ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሸንዳ

በአዲስ አበባ ደረጃ የአሸንዳ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም በሚሊኒየም አዳራሽ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በበዓሉ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማን ጨምሮ የኢፌዲሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር ፣ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ወ/ሮ ያለም ፀጋዬን ጨምሮ በአዲስ አበባ የሚኖሩ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

እንኳዕ ንበዓል ኣሸንዳ ኣብፀሐኩም!
Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
💫የአንድ እሽግ ለአንድ ልጅ የሙዚቃ ድግስ በጌትፋም ሆቴል እየተካሄደ ነው። የዝግጅቱ መግቢያ፦ 12 ደብተር - 2 እስክርቢቶ - 2 እርሳስ - 2 መቅረጫ እና 2 ላጲስ - #onepackforonechild

Via #Sol/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
💫ሰባተኛው አመታዊው "የበጎ ሰው" የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም በፋና ቲቪ በቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል።

🏷ፕሮግራሙ እንደተጠናቀቀ ዝርዝር መረጃ እናቀርባለን!
@tsegabwode @tikvahethiopia
#አሸንዳ #ADDISABEBA በአዲስ አበባ ደረጃ የአሸንዳ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም #በሚሊኒየም_አዳራሽ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በአዲስ ቴሌቪዥንና DW TV መከታተል ትችላላችሁ!

እንኳዕ ንበዓል ኣሸንዳ ኣብፀሐኩም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ 365 የሕክምና ባለሙያዎችን አስመርቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድን በበጎ ስራ!

በወሊሶ ከተማ በዛሬው እለት በትምህርት ቁሳቁሶች ዕጥረት ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል ላልቻሉ ለ370 ህፃናት ድጋፍ ተደረገ። ድጋፉንም ያደረጉት የወሊሶ ለወሊሶ የመረዳዳት እድር አባላት ናቸው ይህንን ቁሳቁስ ከተለያዩ የከተማዋ ተወላጆችና ወዳጆች የተሰበሰበ መሆኑን ከአባላቱ አመራር አካላት ለማወቅ ተችሏል።

Via ዋሌ ታሪኩ ከወሊሶ.
@tsegabwolde @tikvahethiopia