TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አርባ_ምንጭ

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አርባምንጭ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። #PMO #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አርባ_ምንጭ

ዛሬ ሐምሌ 22፣ 2011 ዓ.ም 200 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ኃገር አቀፍ ፕሮግራም ተጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም በአርባ ምንጭ ተገኝተው ችግኞችን ተክለዋል። ይህ አረንጓዴ አሻራን እንተው የሚል ዓላማን ያነገበው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ማህበራዊ ምርታማነትን ለመጨመር፤ ተጋላጭነት ለመቋቋም ያለመ ነው።

Via #bbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ "መልካም ወጣት" ለችግኝ ተከላ ወደ ታቦር ተራራ እየተጓዙ ናቸው።
Channel photo updated
#መቐለ

"ዘመቻ መለስ ለአረንጓዴ ልማት" በሚል መሪ ቃል ከ80 ሚልዮን ችግኝ በላይ በዚህ የክረምት ወቅት ለመትከል የታቀደ ሲሆን እስከ ትናንት ድረስ 30ሚልየን ችግኞች ተተክለዋል። በዛሬው እለት በትግራይ #መቐለ ከተማ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ አመራሮች፣ የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ አባላት ፣የክሉሉ የፀጥታ ሀይል አባላት፣ ከተለያዩ የክልል ቢሮዎች የተውጣጡ የመንግስት ሰራተኞች እና ነዋሪዎች በተገኙበት ችግኝ ተከላ ተካሂዷል። ዛሬ ሀምሌ 22 /2011 በክልል ደረጃ 9 ሚልየን ችግኞች እንደሚተከሉ ታውቋል።

Via Tigray Express
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ - ዘፀአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተ ክርስቲያን

ፎቶ፦ ኤልያስ ዱካሞ/TIKVAH-ETH/
የራይድ አሽከርካሪዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር #Ride
#አረንጓዴአሻራ

የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ በከተማዋ ሁሉም ክፍሎች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ ከኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ጋር በመሆን የሺ ደበሌ አከባቢ ችግኝ ተክለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አንዋር_መስጂድ

"በትላንትናው እለት በአንዋር መስጂድ ሀጂ ዶክተር ተቀዳሚ ሙፍትሂ ባሉበት የአንዋር መስጂድ ኢማም ሸህ ጠሀ ባሉበት የችግኝ የከላ ተፈፅሙዋል!" ሱሌማን/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ASTU የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች እና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። #አዳማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮኮሳ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል። #ኦሮሚያ #ኢትዮጵያ
#ደሴ "ወገኔ በጎ አድራጎት" አባላት አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፍኖተ_ሰላም የምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሠላም ከተማ ነዋሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና የፀጥታ ኃይል አባላት በጋራ በመሆን ችግኝ እየተከሉ ነው። በፍኖተ ሠላም ከተማ ዛሬ ብቻ 45 ሺህ ችግኞች እንደሚተከሉ ይጠበቃል፡፡
#ቢሾፍቱ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሣ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን አስጀምረዋል፡፡ በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም በርካታ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎችም ይህን መርሃ ግብር በማስኬድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁለት መቶ ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር የመትከል ፕሮግራም በመላው ሀገሪቱ እየተካሄደ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia