TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጨፌ ኦሮሚያ🔝

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ የ6 ወራት የስራ አፈጻጸምን ለጨፌ ኦሮሚያ ያቀረቡ ሲሆን፣ በሪፖርታቸው የመሬት ወረራና ሕግ ወጥ ግንባታን ለመከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ህዝቡ #የሕግ_የበላይነትን የማስከበር ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ባለፉት 6 ወራት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን አቶ ለማ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ መንግስት #ሰላም_እንዲኖር እየሰራ ቢሆንም በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች የጸጥታ ችግሮች መከሰታቸውን የገለጹት አቶ ለማ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ችግሩ እንዲከሰት ያደረጉ አካላትን ወደ ሕግ የማቅረብ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡

በተለይ በጉጂና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተከሰቱትን #የጸጥታ_ችግሮች በትዕግስትና በሳል አመራር በመስጠት ሁኔታው ወደ #ሰላም እንዲመጣ መደረጉን አቶ ለማ በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡ ህዝቡ ከመጣው ለውጥ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ ስራዎች መሰራታቸውንም አቶ ለማ ገልጸዋል፡፡ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በተሰራው ስራ የተለያዩ ፓርቲዎች ወደ አገር ገብተው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡

#OBNLive

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትራፊክ አደጋ...

#አርባምንጭ

በአርባምንጭ ከተማ #በዛሬው_ዕለት በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ የሰው ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

Via Gamo Zone Administration public Relation office

•ወገኖቼ መነጋገር አለብን! እንደወጣን እየቀረን ነው! በየቦታው በየከተማው በትራፊክ አደጋ ብዙ ዜጎቻችን እያለቁ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል‼️

በአርባምንጭ ከተማ ዛሬ ጠዋት ላይ በደረሰ #የመኪና_አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር #አባሃጅ_ጉጆ እንደገለጹት የካቲት 19/2011 ዓ.ም ጠዋት 2 ሰዓት ላይ በአርባምንጭ ከተማ ወዜ ቀበሌ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 53362 ኢት የሆነ ሲኖ ትራክ መኪና እና ኮድ 4-15376 ኢት የሆነ ፒካፕ መኪና ከፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከረክሩ በተፈጠረ አደጋ እስከ አሁን የ5 ሠዎች ሕይወት አልፏል፡፡

በቦታው ከነበሩ አይን እማኞች በተገኘ መረጃ አደጋው የተፈጠረው በፍጥነት ሲያሽከረክር የነበረው የሲኖ ትራክ አሽከርካሪ ባለ 3 እግር ባጃጅን ለማትረፍ የቀኝ መስመሩን ትቶ ወደ ግራ በመታጠፍ ፒካፕ መኪናን በመግጨት ከመስመር ያስወጣው ሲሆን በእግረኛ መንገድ ስትጓዝ የነበረች የ13 ዓመት ሕጻንን ጨምሮ በፒካፕ መኪናው ውስጥ የነበሩ 3 ተሳፋሪዎች ሕወታቸው አልፏል፡፡

ይሕ በእንዲህ እንዳለ የሲኖ ትራክ አሽከሪው #በፀፀት ራሱን ከመብራት ታዎር ላይ በመጣል ሕይወቱ ማለፉን ም/ኢንስፐክተር አባሃጅ ገልጸው በአደጋው ሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

አሽከርካሪዎች ከተፈቀደ ፍጥነት ወሰን በላይ ባለማሽከርከር በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ የሚደርሰውን አደጋ #መቀነስ እንደሚጠበቅባቸው የከተማው ፖሊስ አዛዥ ም/ኢ/ር አባሃጅ ጉጆ አሳስበዋል፡፡

Via Gamo Zone Administration public Relation office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በ46ኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የሚኒስትሮች ካውንስል ስብሰባ ለመሳተፍ ማምሻውን ጅቡቲ ገብተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሶስት ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ቁጥር 02901 ድሬ ያሪስ ፣ የሰሌዳ ቁጥር 02285 ድሬ ያሪስ እና የሰሌዳ ቁጥር 04658 ሱማ ሚኒባስ የሚል ሀሰተኛ ታርጋ በመለጠፍ የካቲት 18 ቀን 2011 ዓ ም ወደ አገር ዉስጥ ሊገቡ ሲሉ በቶጎ ጫሌ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምሴተ ጥበብ የስነ ፅሁፍ ምሽት
#update የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጄዳ ከሚገኘው የኢፌዲሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት፣ ከሚመለከተው የሳኡዲ አረቢያ መንግስት እና ከዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) ጋር በመተባበር በሳኡዲ አረቢያ ጂዛን አካባቢ ያለመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩ የነበሩ 600 ዜጎች በዛሬው ዕለት በሰላም ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ለተማሩና ሐሳብ ላላቸው ዜጎች #የብድር ሥርዓት ሊዘረጋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ተናገሩ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር #ዐብይ_አህመድ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ባለፉት ጊዜያት ትልልቅ ሐሳብ ላላቸው ሳይሆን ትልልቅ ሀብት ላላቸው ብቻ ከፍተኛ የብድር አገልግሎት ስትሰጥ ቆይታለች፤ በዚህም የሚፈለገው ለውጥ ሳይመዘገብ ቀርቷል፡፡

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢቦላ‼️

በዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ኢቦላን ለመላከል እየተከናወነ ያለውን ስራ ለጋሾች እንዲደገፉ የአለም ጤና ድርጅት ጠየቀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር #ቴድሮስ_አድሀኖም የገንዘብ እጥረት ቁልፍ ውጤቶችን እንዳይሸረሸራቸው ስጋት መኖሩን ተናግረዋል፡፡

ከስፍራ ወደ ስፍራ የሚንቀሳቀስ ማህበረሰብ ባለበት አካባቢ ያለው የጤና ስርአት ክፍተት እና የፀጥታ ሁኔታ ሌሎች ፈተናዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በሀገሪቱ በኢቦላ የተጠቁትን ቡቴምቦና እና ካትዋን ለመመልከት እንዲሁም ከአዲሱ ኘሬዚዳንት ፊሊክስ ተሲኬዳ ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸውን ዶክተር ቴድሮስ አስታውቀዋል፡፡

በሀገሪቱ የሚከናወነውን የመከላከል ስራ ለማጠናከር የሚያግዝ የግብአት ድጋፍ መላኩንም አስታውቀዋል፡፡

በኮንጎ የተከሰተውን ኢቦላን ለመከላከል የአለም ጤና ድርጅት ከጠየቀው የ1መቶ 48 ሚሊዮን ዶላር አለም አቀፍ ድጋፍ እስካሁን ያገኘው ከ1ዐ ሚሊዮን ዶላር የዘለለ አይደለም፡፡

በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የደረሰውን ትግል ውጤታማ ለማድረግ የለጋሾች ድጋፍ ለአለም ጤናማነት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩበት እንደሆነ ዶክተር ቴድሮስ አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠው ሙሉ መግለጫ፦

"በ10ኛው የደኢህዴን ድርጅታዊ ጉባኤ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አቅጣጫ ከተቀመጠላቸው ጉዳዮች አንዱ #አዳዲስ_ክልል ሆኖ #የመደራጀት ጥያቄ ነው፡፡ ስለሆነም ይህ ጥያቄ በክልላችን አሁን ያለበት ደረጃና በጉባኤው በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እየተፈፀመ ስለመሆኑ በዝርዝር ተገምግሟል፡፡ ዘላቂ መፍትሄውን በተመለከተ፤ በሰከነ እና ሃላፊነት በተሞላ መንገድ ማየት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ማእከላዊ ኮሚቴው ትኩረት ሰጥቶ ተወያይቶበታል፡፡ በመሆኑም በክልላችን እየተነሱ ያሉ ክልል ሆኖ የመደራጀት ጥያቄዎች የህዝቦችን ትስስርና አንድነት በሚያጠናክር፣ የድርጅት ቀጣይነትና የሁሉንም ህዝቦች ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ አኳኋን በደኢህዴን መሪነት እንዲፈፀም ልዩ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን፡፡"

https://telegra.ph/ከደኢህዴን-ማዕከላዊ-ኮሚቴ-የተሰጠው-ሙሉ-መግለጫ-02-26
"ህዝቡ አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ ለማድረግ እየተፈፀሙ ያሉ ሴራዎችን መታገል አለበት"– የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት
.
.
የተለያዩ የአገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮችን ሌላ መልክ በመስጠት አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳና እርስ በእርሱ እንዲጋጭ ለማድረግ እየተፈፀሙ ያሉ ሴራዎችን መላው ህዝብ እንዲታገል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ #ለማ_መገርሳ ጥሪ አቀረቡ።

የክልሉ ፕሬዚዳንት ጥሪውን ያቀረቡት በአዳማ ከተማ ዛሬ በተጀመረው 9ኛው የጨፌው ጉባኤ ላይ ከጨፌው አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው።

አባላቱ በክልሉ ሰላም፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር፣ ህገ-ወጥነትን በመከላከል፣ ክልሉ በአዲስ አበባ ላይ ካለው ጥቅም ጋር የተያያዘ እና ሌሎች በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥያቄ አንስተዋል።

የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ በዚሁ ወቅት ህዝቡ ጠረፍ አካባቢ ይፈፀም የነበረውን የፖለቲካ #ሴራ ወደመሃል አገር ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት ሊገታ ይገባል ብለዋል።

ህገ-ወጥነትን ለመከላከል የሚወሰደውን እርምጃ እንደአብነት ያነሱት አቶ ለማ የህዝቡን ጥቅም ማእከል አድርጎ የሚሰራ አመራር እና ህዝቡ ሌሎች በሚቀርፁለት አጀንዳ መመራት እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

እንዲያም ሆኖ “ህገ-ወጥ ቤቶች ሲገነቡ ቁጭ ብሎ የሚመለከት አመራር እያለ ቤት እንዲፈርስ መደረጉ በራሱ #ጥፋት ነው” ሲሉም ገልፀዋል።

የቀበሌና የጎጥ አመራር እንዲሁም የከተሞቹ ካቢኔዎች ቤቶቹ ሲገነቡ ያለእነርሱ እውቅና መገንባታቸው፤ ከዚህም አልፎ ግንባታዎቹን በእጅ አዙር ህጋዊ ሲያስደርጉ በመቆየታቸው ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ኦሮሞ እና ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላቸውን ጥቅም አስመልክቶ በተነሳው ጥያቄ ላይ ማብራሪያ ሲሰጡም ለውጡን ለመቀልበስ በዳራ አገር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ቡድኖች አሁን በአዲስ አበባ ጉዳይ አንዱን በሌላው በማስነሳት እርስ በእርስ ለማበላላት የሚፈፅሙት ተግባር ስለሆነ ህዝቡ ጉዳዩን በጥንቃቄ ማየት እንዳለበት አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ጉዳይ በታሪክና በህገ-መንግስቱ መሰረት በምክክርና ህግን በተከተለ ሁኔታ ብቻ የሚፈታ እንደሚሆነም ነው አቶ ለማ ያብራሩት።

የልማት ፕሮጀክቶች መጓተት ዋነኛው ምከንያቶች የፋይናንሰ ችግር፣ የተቋራጮች አቅም ማነስ እንደሆነም አነሰተዋል።

የእነዚህ ሁለት ችግሮች ውጤት ተደማምሮ በልማት ፕሮጀክቶቹ ላይ ጫና ማሳደሩን የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ ተናግረዋል።

ከዚሀም በተጨማሪ የክልሉ መንግስት በሰላም ማስከበርና በተፈናቃዮች ጉዳይ ላይ መጠመዱ የልማት ፕሮጀክቶቹ ቁጥጥር እንዲላላ ማድረጉንም አንስተዋል።

በሰላም ማስፈን ተግባር ላይ የክልሉ መንግስት ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ሰላም ለማውረድ በትእግስት ያከናወነውን ተግባር እንደ ድል መቁጠር ይገባል ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።

አስከ ነገ የሚቆየው ጉባኤው በአስፈጻሚ አካላት የተከናወኑ ስራዎችን ይገመገማሉ፣ አዋጆችን ይጸድቃል፤ ልዩ ልዩ ሹመቶችን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ህዝቡ አንዱ በሌላው ላይ #እንዲነሳ ለማድረግ እየተፈፀሙ ያሉ #ሴራዎችን መታገል አለበት" – የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት #ለማ_መገርሳ

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ናይጄሪያ...

ትናንት የናይጄሪያ ነፃው ብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ #ቡሃሪ ቢያንስ በስድስት ክፍላተ ሃገር ዋናው ተፎካካሪያቸው #አቲኩ አቡበከር ደግሞ በፌዴራል ካፒታል ክፍለ ግዛት እንዳሸነፉ ገልፅዋል።

የአቲኩ አቡበከር ህዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኡቼ ሴኮንደስ በበኩላቸው ፓርቲያቸው በናሳራዋ ክፍለ ሃገር እና በዋና ከተማዋ የድምፅ ቆጠራ መዛባት እንዳለ ደርሶበታል ብለዋል።

አቡጃ ላይ በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲናገሩ የቡሃሪ መንግሥት ከምርጫው ኮሚሽን ጋር ተመሳጥሮ በሀገሪቱ ዙሪያ በሚገኙ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ ቆጠራ እንዲዛባ እያደረገ ነው ሲሉ ወንጅለዋል። እኛ ደግሞ ትክክለኛውን የድምፅ ውጤት ከየምርጫ ጣቢያው ይዘናል ሲሉም አክለዋል። በናይጄሪያ በሰላሳ ስድስቱም ክፍላተ ሃገር እና በፌዴራል መዲና ክፍለ ግዛት በጠቅላላ ምርጫው የተካሄደ ሲሆን በእያንዳንድ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በተዛባባቸው አካባቢዎች እንዲዘገይ ተደርጓል።

ከሰባ የሚበልጡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ያቀፈው “ዘ ሲቹዌሽን ሩም” የተሰኘው ቡድን እንዳስታወቀው ከምርጫው በተያያዙ ሁከቶች ቢያንስ ሰላሳ ዘጠኝ ሰው ተገድሏል።

የምርጫ ኮሚሽኑ “በአንዳንድ አካባቢዎች ድምፅ አሰጣጡ እንዲዘገይ ቢደረግም በምርጫው አፈጻጸም በአጠቃላዩ ረክተናል ማለታቸውን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘግቧል።

በናይጄሪያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ስቱዋርት ሲሚንግተን ትናንት ሰኞ ባወጡት መግለጫ ህዝቡ ብሄራዊ የምርጫ ኮሚሽኑ የድምፅ ውጤቶችን አጠናቅሮ ይፋ እስከሚያደርግ በትዕግስት እንዲጠብቅና ከሁከት እንዲቆጠብ ጥሪ አቅርበዋል።

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ...

"ፀግሽ እባክህ #ሚዛን_ቴፒ_ዩኒቨርሲቲ የቴፒ ግቢ የክረምት ተማሪዎች የርቀት ኮርስ ሞጁልና አሳይንመንት አልተሰጠንም፤ የሚንማር መሆኑ ራሱ ያጠራጥራል፤ የሚመለከተው አካል የክልልም ሆነ የፌደራል መንግስት ትኩረት ሰጥቶ መፍትሔ ቢፈልግ መልካም ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia