TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ግምታዊ ዋጋው 400 ሺህ ብር የሚያወጣ የባህርዛፍ አጠና ያለምንም ህጋዊ ሰነድ ከአገር ሊወጣ ሲል #በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። የኮንትሮባንድ ዕቃው በሰሌዳ ቁጥር 79780/00054 በሆነ ተሳቢ መኪና ተጭኖ ሊወጣ ሲል ቶጎጫሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በጉምሩክ ባለሙያዎችና በመከላከያ ሰራዊት አባላት የጋራ ጥረት ሊያዝ ችሏል፡፡ በተያያዘም በቀን 20/05/11 ከምሽቱ 3፡30 ላይ በሌላ ተጠርጣሪ 2 ግራም የሚሆን ሜርኩሪ መሰል ማዕድን በሶማሌ ክልል አድርጎ ወደ ሶማሌ ላንድ ሊያስወጣ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል፡፡

via epa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከጥር 19 እስከ 21 ለተከታታይ ሦስት ቀናት #በሀዋሳ_ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን በመምረጥ ተጠናቀቀ። በዚህም መሰረት ወጣት አስፋው ተክሌን በሠብሳቢነት እንዲሁም ወጣት አክሊሉ ታደሰን በምክትል ሰብሳቢነት መምረጡን የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvagethiopia
#update ከጭናግሰን ከተማ የማርያምን ክብረ በዐል አክብረው ይመለሱ በነበሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ #በጅግጅጋ_ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱ ታወቀ። በግጭቱ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

via ELU

•በጅግጅጋ የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት የሟች ቁጥር 2 እንደሆነ ገልፀው መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ!!

ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለተከታተሉበት የጎንደሩ ጻዲቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የኮምፒዩተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በጻድቁ ዮሐንስ አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የተገኙት ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያገለግል መተግበሪያ የተጫነባቸውን ሁለት ኮምፒተሮች አበርክተዋል።

በቀጣይም 20 ተጨማሪ ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያግዙ ኮምፒዩተሮችን ለመስጠትም ቃል የገቡት ቀዳማዊት እመቤቷ በርካታ መጻሕፍትንም ለትምህርት ቤቱ አበርክተዋል።

ባለፈው መስከረም ወር ላይ በዚሁ ትምህርት ቤት የተገኙት ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከ60 በላይ የዓይነ ስውራን መፃፊያ መሳሪያ (ብሬይል)፣የብሬይል ወረቀት፣ የዓይነ ስውራን መምሪያ ዱላ፣ ልዩ ልዩ እስክሪብቶዎች፣ ደብተሮችንና ቦርሳዎችን ማበርከታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም በጎንደር ከተማ ሎዛ ማሪያም አካባቢ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስገንባት መጀመራቸን ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስጠንቀቂያ‼️

#በድሬዳዋ_ከተማ የትራንስፖርትና የግብይት #አድማ ለማድረግ ያቀዱ ነዋሪዎች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ #የምስራቅ_ዕዝ_ጠቅላይ_መምሪያ አስጠነቀቀ።

via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቃቤ ሕግ የቀድሞ #የሜቴክ የስራ #ሀላፊዎች በነበሩት ሻለቃ #ክንደያ_ግርማይና ሌተናል ኮሎኔል #አሰፋ_ዮሐንስ ላይ ክስ መሰረተ። በዚሁ መዝገብ ስር  በዋና ወንጀል አድራጊነት ተጠርጥረው የተከሰሱት ብርጋዴል ጄነራል ጠና ቁርንዲ፣ሻለቃ ክንደያ ግርማይና ሌተናል ኮሎኔል አሰፋ ዮሐንስ ናቸው። በወንጀሉ ተባባሪነት ክስ የተመሰረተበት ቻይናዊ ሚስተር ዩሀን ዮን ደግሞ እስካሁን አልተያዘም። ተከሳሾቹ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘትና ለማስገኘት የኮርፖሬሽኑን የግዥ አፈፃፀምን ወደ ጎን በመተው ከጨረታ ውጭ ሌሎች የግዥ ዘዴዎችን በመጠቀም ግዥ በመፈፀም ነው። በዚህም ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያለአግባብ ወጪ እንዲሆን ማድረጋቸው በክሱ ላይ ተመልክቷል። ሌተናል ኮሎኔል አሰፋ ዮሐንስ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ሃላፊ፣ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁርንዲ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የማርኬቲንግ ኃላፊና ሻለቃ ክንደያ ግርማይ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የፋይናንስ ኃላፊ ነበሩ። የግራ ቀኝ ክርክሩን  ያደመጠው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች መቃወሚያቸውን ለጥር 29 ቀን 2011 ዓ.ም አንዲያቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በዚህ ሳምንት ሐሙስ በይፋ ትጥቅ ይፈታል። ድርጅቱ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ሰላምና መተማመን ዕውቅና ለመስጠትና ወደ ጠመንጃ እንደማይመለስ ለመግለፅ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት በጅጅጋ የትጥቅ መፍታት ስነስርዓት አዘጋጅቷል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በሀገሪቱ ለፈጠሩት አዲስ የፖለቲካ መስመርም ምስጋናውን አቅርቧል።

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ጃዋር መሀመድ‼️

በቅርቡ በመንግስት እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መካከል በአምቦ በተደረገው ስምምነት መሠረት እርቁን ተግባራዊ ለማድረግ የተመረጠው የቴክኒክ ኮሚቴ ሥራውን በተግባር መጀመሩን የቴክኒክ ኮሚቴው አባል አቶ #ጀዋር_መሀመድ አስታወቁ፡፡ የእርቁ ቴክኒክ ኮሚቴ አባል አቶ ጀዋር መሃመድ ዛሬ ማምሻውን ከአቶ በቀለ ገርባ ጋር በመሆን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት የጋራ መግለጫ፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ስራዎች መኖራቸውን በመጠቆም፤ በ20 ቀናት ውስጥ የኦነግ ሰራዊት ወደ ካምፕ እንደሚገባና መንግስትም ለዚህ ድጋፍ እንደሚያደርግ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምናና የኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ለሁለት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረጉ፡፡ በእርዳታ ርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ እንደተገለጸው እርዳታው ከተደረገላቸው መካከል በጎንደር ከተማ የሚገኘው የጻዲቁ ዮሃንስ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤትና በአዘዞ ከተማ የሚገኘው የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ይገኙበታል፡፡ ለሁለቱ ትምህርት ቤቶች በእርዳታ ከተሰጡት የትምህርት ቁሳቁሶች መካከል አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችሉ  አራት ኮምፒውተሮች ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም አራት የብሬል መጻፊያ ታይፕራይተሮችና 30 በብሬል የተዘጋጁ የማስተማሪያና የማጣቀሻ መጻህፍቶች በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ለትምህርት ቤቶቹ ተበርክቶላቸዋል፡፡ ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልም ለአእምሮ ታማሚዎች ህክምና አገልግሎት የሚውል የአእምሮ ነርቭ ስርአት መለኪያ መሳሪያ በእርዳታ ተሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አየር ሃይል ጥቃት ፈፀመ‼️

#የኢፌዲሪ_አየር_ሃይል በሶማሊያ ከባይደዋ በስተምስራቅ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ቡርሃይቤ በተባለ የአልሻባብ ይዞታ ላይ ጥር 16 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የኢፌዲሪ አየር ሃይል #ተዋጊ ሂሊኮፕተሮች በፈፀሙት ለ44 ደቂቃ የዘለቀ ድብደባ 35 የአልሻባብ ታጣቂዎች ተደምስሰዋል፡፡

ከዚህ ውስጥም በስፍራው የአሸባሪ ቡድኑ የኦፕሬሽን ሃላፊ የነበረው አብዱ ኡስማንና የፈንጂ ቡድን ሃላፊው አብዱሰላም በድብደባው መገደላቸው ተረጋግጧል፡፡

በዚህ የአየር ድብደባ 2 የቴክኒክ፣ አንድ የጭነት፣ አንድ ፈንጂ የጫነ በድምሩ 4 ተሽከርካሪዎች እንዲሁም 5 ካሊበር መሳሪያዎች ወድመዋል፡፡

ከዚህ በፊትም የመከላከያ ሠራዊቱ በአልሸባብ ልዩ ልዩ ይዞታዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ እንዳደረሰበት የመከላከያ ሚኒስቴር የኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ፖሊስ‼️

ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተዉን #አለመረጋጋት ተከትሎ የከተማዉ ፖሊስ ኮሚሽን 308 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደ ነዉ፡፡

በብጥብጡ እጃቸዉ #የሌለ ግለሰቦች #እንዲፈቱ የከተማዋ የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ጠይቀዋል፡፡

የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ እዝ ጠቅላይ መምሪያ እና የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ የሃይማኖት አባቶች ሽማግሌዎች ጋር በከተማዋ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አካሂዷል፡፡

ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የስራ አድማ ይደረጋል ብለዉ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸዉ #እንዲቆጠቡም የምስራቅ እዝ መምሪያ አሳስቧል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 21/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ መንግስት “የጤፍ ባለቤት ነኝ” ያለውን የሆላንድ ድርጀት በዓለም አቀፉ የግልግል ፍርድ ቤት ሊከስ ነው።
.
.
በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ ሁለት አርሶ አደሮች በኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር "ኦነግ ታጣቂዎች" መገደላቸውንና አንድ አርሶ አደር መቁሰሉን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር የሴፍቲና ሲኬዩሪቲ ዲፓርትመንት ባለሙያዎች በባቡሩ ላይ #ድንገተኛ የእሳት አደጋ ቢከሰት እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል የሚያሳይ ልምምድ አካሂደዋል።
.
.
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የቀጠለውን የሚኒስትርና ተጠሪ መስሪያ ቤቶችን የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መርተዋል።
.
.
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፓሬሽን/ሜቴክ/ይቅርታ መጠየቅና #እርቅ ማውረድ ካለበት አካል ጋር ሁሉ እንደሚያደርግ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል #አህመድ_ሀምዛ አስታውቀዋል።
.
.
በሰቆጣ ከተማ ሦስት #ፓኪስታናውያን በሕገ ወጥ የሞባይል ሽያጭ ተሰማርተው እጅ ከፈንጅ ተይዘዋል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርተፍኬት፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ፣ የልደትና ሞት ሰርተፍኬት እንዲሁም የጋብቻ እና ፍቺ ሰርተፍኬቶች በዲጂታል ሰርተፍኬት ሊቀየሩ ነው ተብሏል።
.
.
ኢ/ር #ታከለ_ኡማ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የፈረሰውን መስጂድ በመጎብኘት የአከባቢውን የሙስሊም ማህበረሰብም አነጋግረዋል፡፡
.
.
#የፌዴራል_መንግሥት አመራሮች የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማዋ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አወያይተዋል፡፡
.
.
በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና በማህበራዊ ፍትህ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያውን አረንጓዴ የፖለቲካ ፓርቲ (Green Party) ለማቋቋም ጊዜያዊ አስተባባሪ ፓርቲ መሰየሙን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል።
.
.
ከሳውዲ አረቢያ ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት በህጋዊ መንገድ ለሚሄዱ ሰራተኞች የቪዛ አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።
.
.
ግምታዊ ዋጋው 400 ሺህ ብር የሚያወጣ የባህርዛፍ አጠና ያለምንም ህጋዊ ሰነድ ከአገር ሊወጣ ሲል #በጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ከጥር 19 እስከ 21 ለተከታታይ ሦስት ቀናት #በሀዋሳ_ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 4ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበሩን በመምረጥ ተጠናቋል።
.
.
ከጭናግሰን ከተማ የማርያምን ክብረ በዐል አክብረው ይመለሱ በነበሩ ምዕመናን ላይ ወጣቶች መንገድ መዝጋታቸውን ተከትሎ #በጅግጅጋ_ከተማ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት መረጋጋቱ ታውቋል። በግጭቱ የ2 ሰው ህይወት አልፏል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለተከታተሉበት የጎንደሩ ጻዲቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የኮምፒዩተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡
.
.
#በድሬዳዋ_ከተማ የትራንስፖርትና የግብይት #አድማ ለማድረግ ያቀዱ ነዋሪዎች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ዘንድ #የምስራቅ_ዕዝ_ጠቅላይ_መምሪያ አስጠነቅቋል።
.
.
አቃቤ ሕግ የቀድሞ #የሜቴክ የስራ #ሀላፊዎች በነበሩት ሻለቃ #ክንደያ_ግርማይና ሌተናል ኮሎኔል #አሰፋ_ዮሐንስ ላይ ክስ መስርቷል።
.
.
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) በዚህ ሳምንት ሐሙስ በይፋ ትጥቅ ይፈታል።
.
.
በቅርቡ በመንግስት እና ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) መካከል በአምቦ በተደረገው ስምምነት መሠረት እርቁን ተግባራዊ ለማድረግ የተመረጠው የቴክኒክ ኮሚቴ ሥራውን በተግባር መጀመሩን የቴክኒክ ኮሚቴው አባል አቶ #ጀዋር_መሀመድ አስታውቀዋል።
.
.
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምናና የኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ለሁለት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርገዋል።
.
.
#የኢፌዲሪ_አየር_ሃይል በሶማሊያ ከባይደዋ በስተምስራቅ 75 ኪሎ ሜትር ላይ ቡርሃይቤ በተባለ የአልሻባብ ይዞታ ላይ ጥር 16 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሱን የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
.
.
ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተዉን #አለመረጋጋት ተከትሎ የከተማዉ ፖሊስ ኮሚሽን 308 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያካሄደ ነዉ፡፡

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ፣ etv፣ fbc፣ VOA፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት፣ የጠ/ሚ ፅ/ቤት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ አብመድ
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia