"ለኢትዮጵያውያን #ከሶሪያ የተላኩ መልእክተኞች"!
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሶሪያ ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ #ምፅዋት ሲለምኑ የሚያሳይ ምስል በብዛት እየተሰራጨና share እየተደረገ ይገኛል።
አዎን ቢገባን ብናስተውለው እነዚህ ሶሪያኖች እኛ ሐገር የተላኩት ከፈጣሪ መልእክተኛ ሆነው ነው። አሁንም ልብ ካልገዛን፣ ጥላቻን ትተን ይቅርታን ካልተላበስን፣ መለያዬትን ትተን አንድነትን ካልያዝን፣ የጦርነት አታሞ/ ከበሮ መደለቅ ካላቆምን እንደ እነዚህ ሶሪያኖች ትሆናላችሁ ተጠንቀቁ ሲል ነው የላከልን፤ ከእንግዲህ መለያየትን፣ ዘረኝነትን የምትሰብኩ የጦርነት ነጋሪን የምትጎስሙ #ጦርነት ናፋቂዎችና እነሱን ተከትላችሁ የምታብዱ ተከታዮቻቸው ፈጣሪ ከዚህ በላይ ወርዶ አይነግራችሁምና ልብ ግዙ።
አንደበታችሁ ሰላምን ያውራ፣ እግራችሁ ወደ ጥፋት ሳይሆን ወደ ሰላም መንገድ ያቅኑ፣ እጆቻችሁ የመሳሪያ ቃታን ሳይሆን በሐሳብ የምታሸንፉበት እስክርቢቶን ይያዙ። ኢትዮጵያ ፈርሳ ላትፈርስ ተለያይተን ላንለያይ ትዝብት ላይ አትውደቁ። ጉልበታችሁንም አትጨርሱ።
©Kibrom Adhanom Ghebreyesus
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ፈረንሳይ‼️
በፈረንሳይ #ሰትራስቡርክ ከተማ አንድ ታጣቂ በፈጸመው ጥቃት የአራት ሰዎች ህይዎት ማለፉ ተገለፀ።
ታሪካዊ በሆነው የገና ገበያ ማዕከል ውስጥ #ክሌበር_አደባባይ አካባቢ ጥቃቱ እንደፈመው ነው የተገለፀው። በዚህ ጥቃት የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉንና በ12 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።
የአካባቢው ፖሊሶችም ጥቃት ለማስቆም ከታጣቂው ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸው ነው የተገለፀው። በዚህ ሂደት ላይም ጥቃቱን የፈፀመው ታጣቂ መጠነኛ ጉዳት ከደረሰበት በኃላ ከቦታው መሰወሩ በዘገባው ተመላክቷል።
ይሁን እንጂ የወንጀሉን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ለማዋል የከተማዋ ፖሊሶች አሰሳ መጀመራቸውን አስታውቀዋል። በከተማዋ የተፈፀመው ጥቃትም ከሽብር ድርጊት ጋር የተያያዘ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ምንጭ፦አናዶሉ(በfbc)

#update በጋሞ ክልል ምስረታ ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ አስቸኳይ ጉባኤ የጠራው የጋሞ ጎፋ ዞን ምክር ቤት ጥያቄውን በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፡፡
©ኢትዮጵየ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©ኢትዮጵየ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰበር መረጃ‼️በመጪው እሁድ፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ ሕግ ፊት እንዲቀርቡ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተሰማ፡፡
ምንጭ፦ ሸገር 102.1(የኔነህ ሲሳይ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ ሸገር 102.1(የኔነህ ሲሳይ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ🔝በከተማይቱ ያለው ውጥረት አሁንም ያልረገበ ሲሆን እስከ ቅርብ ሰዓት ድረስ ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር። የትራንስፖርት እና የንግድ እንቅስቃሴ #እንደተቋረጠ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ5 ተማሪዎች ህይወት አልፏል‼️
በቅርቡ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በግለሰቦች ደረጃ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት የቡድን መልክ በመያዝ ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች #ተዛምቶ የአምስት ተማሪዎች ህይወት ማለፉን የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየመከሩ ናቸው።
በምክክር መድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ናቸው።
ምክክሩ ሲጀመር የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር #ሂሩት_ወልደማሪያም እንደተናገሩት፤ በዩኒቨርሲቲዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት ለሰው ህይወት መጥፋት ጭምር የዳረገ ጉዳት ደርሷል።
በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በግለሰቦች ደረጃ የተፈጠረ አለመግባባት ወደ #ቡድን መልክ በመቀየር በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተዛምቶ የነገ ተስፋ የሆኑ አምስት ተማሪዎችን ህይወት ቀጥፏል ብለዋል።
ችግሩን ለማርገብና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ታልሞ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ግጭት ወደተከሰተባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተንቀሳቅሰው ባከናወኑት ተግባር አንጻራዊ ሰላም እንደመጣ ዶክተር ሂሩት ተናግረዋል።
አሁን ባለድርሻ አካላት በሚያደርጉት ምክክር ዘላቂ የሆነ ሰላም ሊያረጋግጥ የሚችል ሃሳብ እንደሚፈልቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ

ሎቄ🔝በዶክተር #ወላሳ_ላዊሶ የሚመራው የሲዳማ ምሁራን ቡድን ከዛሬ 17 ዐመታት በፊት ልዩ ስሙ #ሎቄ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ በመንግስት #የፀጥታ_ሀይሎች ህወይታቸውን ያጡ ዜጎች ቤተሰቦቻቸውን በአካል በመሄድ ጎብኝተዋቸዋል።
ፎቶ፦ ታሪኩ ለማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ፦ ታሪኩ ለማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደትን ሰላማዊ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካል ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ተባለ። በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የመማር ማስተመሩን ሂደት በሚያውኩ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦችን በሚጠቁም ጥናት ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ጨምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️
በምሰራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ #መርመርሳ በተባለው አካባቢ ዛሬ ጠዋት ባጋጠመው የተሽከርካሪዎች ግጭት የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር #አስቻለው_ዓለሙ እንደገለፁት ዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ተኩል አከባቢ አደጋው የደረሰው ከአዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ 16 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ አዳማ ሲጓዝ የነበረ ሃይሩፍ የህዝብ ማመለለሻ ተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ይጓዝ ከነበረ ዋልያ አገር አቋራጭ የህዝበ ማመላለሻ አውቶቡስ ጋር መርመርሳ በተባለው አካባቢ በመጋጨታቸው ነው።
በአደጋው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት 01289 ሃይሩፍ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ሾፌሩን ጨምሮ 9 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸውን አልፏል።
በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት 97486 ዋልያ አገር አቋራጭ አውቶቡስ ውስጥ ከነበሩ ተሳታፊዎች መካከል የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ኮማንደሩ ተናግረዋል።
በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው ሌላ በአራት ሰዎች ላይ ከባድ በሶስት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን አመልክተው ተጎጂዎቹ በአዳማ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
“የአደጋው መንስኤ አለአግባብ ደርቦ ለማለፍ መሞከርና ቅድሚያ አለመስጠት ነው” ያሉት ኮማንደር አስቻለው የአውቶቡሱ ሾፌር ለጊዜው ባለመገኘቱ ፖሊስ ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን አስረድተዋል።
ምንጭ፦ ena

AAU🔝
"የአለም HIV ADIS ቀን በAAU ማንዴላ አዳራሽ ዲ/ን ዳንኤል ክብረትና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት "ለ HIV ይበልጥ ተጋላጭ ነን እንመርመር ራሳችንን እንወቅ " በሚል መርህ ቃል በድምቀት ተከብራል ምርመራውም በ AAU ግቢ ውስጥ በስፋት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ (ዮሴፍ ከበደ - AAU )"

ኦሮሚያ ክልል‼️
በኦሮሚያ ክልል #በህገ_ወጥ_መንገድ የተያዙ 15 ሺህ 582 የቀበሌ ቤቶችን በፍተሻ ማግኘቱን የክልሉ ከተማ እና ቤቶች ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በክልሉ ከተማ እና ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች ልማት እና ማስተላለፍ ዳይሬክተር አቶ ባይሳ ሂርኮ በፍተሻ ከተገኙት ቤቶች ውስጥ 80 በመቶዎቹ መኖሪያ መሆናቸውን ገልጸው፥ ቀሪዎቹ የንግድ ቤቶች ናቸው ብለዋል፡፡
ቢሮው እነዚህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት አቅም ለሌላቸው ዜጎች መተላለፋቸውን ለfbc አስታውቋል።
በክልሉ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፥ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የመስጠት ተግባሩ ይበለኝ የሚያሰኝ ቢሆንም አሁንም በሚገባ እንዳልተሰራበት ተናግረዋል፡፡
አቶ ባይሳ አስተያየቱ ትክክል መሆኑን የገለፁ ሲሆን፥ በኃላፊነት የሚሰሩ ከተሞች እንዳሉ ሁሉ ኃላፊነትታቸውን በአግባቡ የማይወጡ ስለመኖራቸውም ጠቁመዋል።
በቅርቡ እየተሰራ ባለው የመለየት ስራ የደረሳቸውን ጥቆማ ተከትሎ በተደረገ ማጣራት ሦስት እና አራት ፎቅ እያላቸው በመንግስት ቤት የሚኖሩ ግለሰቦች እንዳሉም ገልጸዋል፡፡
እስካሁን በተሰራው ስራ የምዕራብ አርሲ ትንንሽ ከተሞች፣ ቦረና ዞን እና ሆለታ ስራቸውን በአግባቡ እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን፥ በሌሎች ከተሞች ጀምሩ ያለ ቢሆንም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ ባይሳ አብራርተዋል።
ከሆለታ በስተቀር ችግሩ በስፋት የሚታይባቸው በኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች ሰፊ ስራ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል።
ከዚህ ባለፈ የተመለሱ ቤቶችን ኮሚቴ በማቋቋም ኃላፊነት በተሞላበት እና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የመስጠት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የተደራጀ መረጃ አለመኖር እና የህግ ክፍተት መኖር በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
አዋጁም የተከራዮችን አቅም ባገናዘበ መልኩ ለንግድ ቤት እስከ አምስት አመት ለመኖሪያ ቤት ደግሞ ከአምስት እስከ 10 ዓመት ብቻ መከራየት የሚያስችል አሰራር መዘርጋት የሚያስችል ነው ተብሏል።
ረቂቅ አዋጁ ከግንቦት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። አቶ ባይሳ ሂርኮ በክልሉ 664 ከተሞች በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሱ፣ በማዘጋጃ ቤት የተሰሩ የቁጠባ ቤቶች እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የተሰሩ እና ባለቤት የሌላቸው ከ114ሺ በላይ ቤቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
እስካሁን ከ53 ሺህ በላይ ሰነድ አልባ የመንግስት ቤቶች ካርታ ተሰርቶላቸው ሰነድ እንዲኖራቸው መደረጉንም አንስተዋል።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ