TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.7K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኦሮሚያ ክልል‼️

በኦሮሚያ ክልል #በህገ_ወጥ_መንገድ የተያዙ 15 ሺህ 582 የቀበሌ ቤቶችን በፍተሻ ማግኘቱን የክልሉ ከተማ እና ቤቶች ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በክልሉ ከተማ እና ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች ልማት እና ማስተላለፍ ዳይሬክተር አቶ ባይሳ ሂርኮ በፍተሻ ከተገኙት ቤቶች ውስጥ 80 በመቶዎቹ መኖሪያ መሆናቸውን ገልጸው፥ ቀሪዎቹ የንግድ ቤቶች ናቸው ብለዋል፡፡

ቢሮው እነዚህ የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት አቅም ለሌላቸው ዜጎች መተላለፋቸውን ለfbc አስታውቋል።

በክልሉ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፥ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የመስጠት ተግባሩ ይበለኝ የሚያሰኝ ቢሆንም አሁንም በሚገባ እንዳልተሰራበት ተናግረዋል፡፡

አቶ ባይሳ አስተያየቱ ትክክል መሆኑን የገለፁ ሲሆን፥ በኃላፊነት የሚሰሩ ከተሞች እንዳሉ ሁሉ ኃላፊነትታቸውን በአግባቡ የማይወጡ ስለመኖራቸውም ጠቁመዋል።

በቅርቡ እየተሰራ ባለው የመለየት ስራ የደረሳቸውን ጥቆማ ተከትሎ በተደረገ ማጣራት ሦስት እና አራት ፎቅ እያላቸው በመንግስት ቤት የሚኖሩ ግለሰቦች እንዳሉም ገልጸዋል፡፡

እስካሁን በተሰራው ስራ የምዕራብ አርሲ ትንንሽ ከተሞች፣ ቦረና ዞን እና ሆለታ ስራቸውን በአግባቡ እየሰሩ የሚገኙ ሲሆን፥ በሌሎች ከተሞች ጀምሩ ያለ ቢሆንም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ ባይሳ አብራርተዋል።

ከሆለታ በስተቀር ችግሩ በስፋት የሚታይባቸው በኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች ሰፊ ስራ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል።

ከዚህ ባለፈ የተመለሱ ቤቶችን ኮሚቴ በማቋቋም ኃላፊነት በተሞላበት እና ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የመስጠት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የተደራጀ መረጃ አለመኖር እና የህግ ክፍተት መኖር በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮች እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

አዋጁም የተከራዮችን አቅም ባገናዘበ መልኩ ለንግድ ቤት እስከ አምስት አመት ለመኖሪያ ቤት ደግሞ ከአምስት እስከ 10 ዓመት ብቻ መከራየት የሚያስችል አሰራር መዘርጋት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ረቂቅ አዋጁ ከግንቦት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። አቶ ባይሳ ሂርኮ በክልሉ 664 ከተሞች በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተወረሱ፣ በማዘጋጃ ቤት የተሰሩ የቁጠባ ቤቶች እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የተሰሩ እና ባለቤት የሌላቸው ከ114ሺ በላይ ቤቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

እስካሁን ከ53 ሺህ በላይ ሰነድ አልባ የመንግስት ቤቶች ካርታ ተሰርቶላቸው ሰነድ እንዲኖራቸው መደረጉንም አንስተዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia