TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀሰተኛ መረጃ🔝

ፌክ ፖስት: "ከፊንፊኔ ወደ #መቀሌ ሊገባ ሲል የተያዘ"

ጉግል: "የዚምባብዌ ፋይናንስ ሚኒስትር ቤት ውስጥ የተገኘ 10 ሚልዮን ዶላር"

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ‼️

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሚኒስቴር የማያውቀው የትምህርት ክፍል አለ በሚል በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች የተሰራጨውን መረጃ #አስተባበለ

በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ ስር ዩኒቨርሲቲውና ትምህርት ሚኒስቴር የማያውቀው የትምህርት ክፍል ተገኝቷል የሚል መረጃ ተለቋል።

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር #የቻለ ዩኒቨርሲቲው ማንኛውንም የትምህርት ክፍል የሚከፈተው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተወያይቶበት፣ ማኔጅመንቱና ቦርዱ  አጽድቆት  እና ከትምህርት ሚኒስቴር ፍቃድ ሲያገኝ ብቻ ነው መሆኑን ለfbc ተናግረዋል።

ሁሉም የትምህርት ክፍሎች በዚህ መሰረት የተከፈቱ መሆኑን  የገለፁት ዶክተር የቻለ፥ የፕሮዳክሽን ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍልም በዚሁ መሰረት የተከፈተ መሆኑን አስታውቀዋል።

ሜታል ፕሮዳክሽን ኢንጂነሪንግ የሚል ስያሜ እንደተሰጠውና ይህም ተማሪዎች በልምምድና የተግባር ትምህርት ወቅት በብሄራዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) እድሉን እንዲያገኙ ለማድረግ ነው ብለዋል።

ይህም ተቋሙ ከትምህረት ክፍሉ ጋር በብዙ የሚያገናኘው የስራ አይነት ያለው በመሆኑ ስያሜው በዛ እንዲሰየም መደረጉን ተናግረዋል።

ነገር ግን ይህ ትምህርት ሚኒስቴር ከሚያውቀው ውጪ ስያሜ ስለሚሆን ወደ ትክክለኛው ስያሜ መመለስ አለበት በሚል ውሳኔ ላይ መደረሱን አብራርተዋል።

በዚህም በዩኒቨርሲቲው ሜታል ፕሮዳክሽን ኢንጂነሪንግ የሚለው ስያሜ ቀርቶ ፕሮዳክሽን ኢንጂነሪንግ እንዲሆን ተወስኗል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች እጃቸውን ያስገቡ አካላትን የሚለይ የምርመራ ቡድን ችግሩ ወደ ተከሰተባቸው ሰፍራዎች መላኩን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ። ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በቀጣይም የተገኙ ዉጤቶችን ለሕዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

@Tsegabwolde @tikvahethiopia
ጭልጋ ወረዳ‼️

‹‹በጭልጋ አካባቢ አንድ ሰው ተገድሏል፤ 39 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 50 ቤቶችና 9 ወፍጮ ቤቶች ተዘርፈዋል››

‹‹ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 153 ሰዎች በተጠርጣሪነት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡›› የማዕከላዊ ጎንደር ዋና አስተዳዳሪ
.
.
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ ‹‹በቅማንት ብሔር ስም በህቡዕ ተደራጅተው የሚነግዱ›› የተባሉ ቡድኖች ትናንት ጥቃት አድርሰዋል፡፡ በጥቃቱ ‹‹የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል፤39 ቤቶች ተቃጥለዋል፤ 50 ቤቶችና 9
ወፍጮ ቤቶች ተዘርፈዋል›› ብለዋል የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ብርሃኑ_ጣምያለው፡፡

አቶ ብርሃኑ እንዳሉት ሌሎች 8 ሰዎችም ቆስለዋል፡፡ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 153 ሰዎች በተጠርጣሪነት መለየታቸውንና ወደ ሕግ ለማቅረብ እንደሚሠራም ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል፡፡

አካባቢው ወደ ከፋ ግጭት እንዳያመራ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ከፌዴራል ፖሊስና ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት አካባቢውን የማረጋጋት ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውንም አቶ ብርሃኑ አብራርተዋል፡፡

ግጭቱን ዘገባው በተጠናቀረበት ወቅት ማስቆም የተቻለ ሲሆን ሙሉ በሙሉ የአካባቢውን ሰላም ወደ ቀደመ ሁኔታ ለመመለስ መስተዳድሩ ከሀገር ሽግሌዎችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር አብሮ እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ኅብረተሰቡ የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት ለማደፍረስ የሚጥሩ ኃይሎችን አጥብቆ እንዲያወግዛቸውና ሕግ ፊትም ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት ከመንግሥት ጋር በመሆን የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡አሁን ላይ አካባቢው በመረጋጋት ላይ እንደሆነ ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ🔝

የጅማ ዩኒቨርስቲ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገባቸውን ተቋማት የፊታችን ቅዳሜ ሊያስመርቅ ነው።

ተቋማቱ ለአካባቢው ማህበረሰብም አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውንና ሙሉ ወጪያቸውን በመንግስት በጀት የተሸፈነ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር #ፍቅሬ_ለሜሳ ተናግረዋል፡፡

በእለቱ ከሚመረቁት ውስጥ 30 ሺ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈው የጅማ የህክምና ማዕከል አንዱ ነው፡፡

የህክምና ማዕከሉ ለጎረቤት አገራት ጭምር አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተገነባ ሲሆን ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚችል ሰምተናል፡፡

75 ሺ 400 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውና 40 ሺህ የእግር ኳስ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያለው ስቴዲየምና የስፖርት አካዳሚ በእለቱ ይመረቃል ተብሏል፡፡

አካዳሚው የኢትዮጵያ ስፖርት ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችሉ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚረዳም ተነግሮለታል፡፡

ዘመናዊ የኮንፍረንስና የሲቪክ ማዕከሎች እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች የሰለጠኑ ተማሪዎችም እንደሚመረቁ ታውቋል፡፡

ተቋማቱ ትምህርት እንዲስፋፋ በማስቻል ምርምር እንዲካሄድና የማህበረሰብ አገልግሎት በማበርከት ዩኒቨርስቲው አገራዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣ የሚያግዙ ናቸው ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1 ፎቶ፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አንጋፋው የአቬሽን ባለሙያ ተፈራ መኮንን የአፍሪካ ሲቪል አቬሽን ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ ሆነው መመረጣቸውን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ምስራቅ አፍሪካን ወክለው የተወዳደሩትን ኢትዮጵያዊውን አቶ ተፈራን የመረጣቸው ትናንት በዛምቢያ ሉሳካ ባካሄደው 29ኛው ልዩ ስብሰባው ነው፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ወርቅነህ ገበየሁ የአቶ ተፈራ መመረጥ ኢትዮጵያ በአቬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ የአህጉሪቷን ጥቅሞች በዐለም ዐቀፍ መድረኮች ለማራመድ ያስችላታል፡፡ ተመራጩ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽንን በሃላፊነት የመሩ ሲሆን በአፍሪካና ዐለም ዐቀፍ ሲቪል አቬሽን ድርጅቶች በተለያዩ ሃላፊነቶች ሰርተዋል፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#updat የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደር የነበርው እና እስካሁን በእስር ላይ የነበረው #ሻንቆ_ብርሃኑ ዛሬ እንደተፈታ የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሻንቆ በሽብር ክስ እስካሁን በእስር ላይ ቆይቷል።

©ENF
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፕሬስ መግለጫ🔝

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
Federal Attorney General
ህዳር 25 ቀን 2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ፡ ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳሳቢ ጉዳይ‼️

የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ ተማሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ #እየጨመረ መምጣቱ ተገለፀ።

ባለፉት ዓመታት በተለይ የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ የከፍተኛ ትምህረት ተቋማት ተማሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የፋርማሲ ባለሙያዎች ማህበር የተመሰረተበትን 44ተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ዛሬ በጎንደር ከተማ ውይይት አድርጓል፡፡

‘የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚዎች ቁጥር መጨመርና የፋርማሲስቶች ሚና’ በሚል መሪ ቃል ነው ውይይቱ የተደረገው፡፡

በውይይቱ ላይ እንደተገለፀው ባለፉት ዓመታት በተለይ የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ የከፍተኛ ትምህረት ተቋማት ተማሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ይህም ችግሩን እጅግ አሳሳቢ አድርጎታል፡፡

ውይይቱም ይህንን ቁጥር ከመቀነስና ወጣቱን አምራች ዜጋ ከማድረግ አኳያ የፋርማሲ ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን ሚና መርምሯል፡፡

የአልኮል፣ የሲጋራ፣ የጫትና የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚነት በዓለም እና አገር አቀፍ ደረጃ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝም በውይይቱ ተዳሷል፡፡

በውይይቱ ወቅት እንደተገለፀው በኢትዮጵያ የተጠቃሚዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል:: ለዚህ ደግሞ እንደዋነኛ ምክንያ የተጠቀሱት የአቻ ግፊትና የፖሊሲ መላላት ናቸው፡፡

መንግስት የሚያደርገው ቁጥጥር አነስተኛ መሆኑ የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚዎች ቁጥር እንዲጨምር አስተዋፅኦ አድርጓል። የግለኝነት መስፋፋት ወይም የማህበራዊ ግንኙነት መላላትም በተመሳሳይ ችግሩን አባብሶታል ነው የተባለው፡፡

በፊልምና በድራማ የሚሳተፉ ታዋቂ ግለሰቦችና አማላይ የመጠጥ ማስታወቂያዎችም የሚፈጥሩት ተፅዕኖም በቀላሉ የሚታይ አይደለም
ነው የተባለው፡፡

የችግሩ መፍትሄም በመንስዔነት የተዘረዘሩትን አስቻይ ሁኔታዎች ማስወገድ መሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡

የኢትዮጵያ የፋርማሲ ባለሙያዎች ማሀበር በአሁኑ ወቅት ከ1ሺህ በላይ የሚሆኑ አባላት ያሉት ሲሆን የተመሰረተው የዛሬ 44 ዓመት ህዳር
25/1967 ዓም ነው፡፡ ውይይቱ በሁለት ከተሞች ጎንደርና መቀሌ ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ተካሂዷል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወደ ሳውዲ አረቢያ ሲጓዙ የመን ላይ ታስረው የነበሩ 408 ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችንን ወደ ሀገር መልሷል።

@tsegabwolde @tikahethiopia
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

በሰው መግደል ሙከራ #የተከሰሱት ወንድምማማቾች በእስራት ተቀጡ፡፡
አግዘዉ ዘለቀና እዮብ ዘለቀ የተባሉ 1ኛና 2ተኛ ተከሳሾች በ1996 ዓ.ም የወጣዉን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ እና 27/1/ እና 540 ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ በመተላለፍ በፈፀሙት በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የመግደል ሙከራ ወንጀል የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቢ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡

የወንጀል ዝርዝር ሁኔታው እንዲሚያስረዳዉ የካቲት 12 ቀን 2009 ዓ.ም ከምሽቱ 5፡00 አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታዉ ጉራራ አደባባይ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ የግል ተበዳይ ሀብቶም አርአያን 1ኛና 2ኛ ተከሳሾች ጭንቅላቱ ላይ በዱላ ደጋግመው የመቱትና በቀኝ በኩሉ ህብረ ሰረሰር ዉስጥ ጤናማ ያልሆነ የደም መፍሰስ፣ በግራ በኩል ተቀጥቅጦ የላይኛዉ የአየር መግቢያና መዉጫ ቱቦ እንዲታፈንና
እዲጎዳ፤ የአንገት ዉስጥ ጤናማ ያልሆነ ደም መፍሰስ እንዲያጋጥመዉና ለመራመድና ለመናገር እንዲቸገር፣ በአጠቃላይ የማገገም እድሉ እጅግ አነስተኛ እንዲሆን በማድረጋቸዉ በፈፀሙት በዋና ወንጀል አድጊነት ተካፋይ በመሆን የመግደል ሙከራ ወንጀል ተከሰዋል፡፡

ከሳሽ የፌዴራል አቃቢ ህግ ተከሳሾች ወንጀሉን ስለመፈፀማቸዉ ያስረዱልኛል ያላቸዉን የሰዉና የሰነድ ማስረጃዎችን አያይዞ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡

ክሱን የተመለከተዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቦሌ ምድብ ወንጀል ችሎትም ተከሳሾች ጥፋተኛ ናቸዉ ሲል የቅጣት ዉሳኔዉን አስተላልፏል፡፡ በዚህም መሰረት ወንጀሉ በግብረ አበርነት የተፈፀመ መሆኑ እንደ አንድ የቅጣት ማክበጃ ተይዞ ህዳር 13 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ 2ተኛ የወንጀል ችሎት እያንዳንዳቸዉ በ6 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia