TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአለም ባንክ(አጃምባ)🔝

"አለም ባንክ በተልምዶ አጃምባ ከሚባለው ሰፈር መኖሪያ ቤታቸው ሃሙስ እለት የፈረሰባቸው ሲሆን እስካሁን ድረስ ባቅራቢያቸው የሚገኘው ፋኑሄል ቤ/ክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው ነው ሚገኙት።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
 የሰላም አምባሳደር እናቶች🔝

“በሀገር ዙሪያ የሚሰማው የእርስ በርስ ግድያ፣ ግጭትና ማፈናቀል አሰጋን፣ አስጨነቀን” የሚሉ እናቶች ሰላም እንዲሰፍን፤ በሀገሪቱ የታየው የዴሞክራሲ ጅምር እንዳይደናቀፍ ለመማፀን ኢትዮጵያን እየዙሩ ነው፡፡

ከባህር ዳርና መቀሌ መልስ ያነጋገርናቸው 22 የሰላም አምባዳር እናቶች አፋር፣ አዲስ አበባ፣ አዋሳ እያሉ ሊቀጥሉ መሆኑን ለVOA ገልፀዋል፡፡

እንዴት ተነሳሱ? እስካሁን ለተደማጭነት ያዩት ተስፋ ምን ይሆን?

ምንስ እንቅፋት ይሆነናል ብለው ያሰጋሉ?

ለጊዜው ከ22 ሦስቱን VOA በስልክ አግኝቶ አነጋግሯል፡፡ ከትግራይ ክልል ወይዘሮ ጃኖ ንጉሠ፤ ከአማራ ክልል ወይዘሮ ገነት ታደሰ፤ ከኦሮሚያ ክልል ወይዘሮ አዱኛ መሐምድ...

©VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጭልጋ ወረዳ‼️

በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለፀ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ #ብርሃኑ_ጣዕምያለው በሰጡት መግለጫ፥ በጭልጋ አካባቢ በአራት ቀበሌዎች ላይ በተቀሰቀሰ #ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን አስታውቀዋል።

በግጭቱ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና በስምንት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

በተጨማሪም 30 መኖሪያ ቤቶችና 9 ወፍጮ ቤቶች መቃጠላቸውን የገለፁ ሲሆን፥ በ50 ቤቶች ላይ ደግሞ ዘረፋ መፈፀሙን ነው የገለፁት።

ህዳር 24 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት አክራ ጎጥ ላይ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ታጣቂዎች ግጭት ማስነሳታቸው ነው የተነገረው።

የዚህ ድርጊት ዋና አስተባባሪ ተብለው የተጠረጠሩ 49 ግለሰቦች የተለዩ ሲሆን፥ #በቁጥጥር ስር ለማዋል የክልሉና የፌዴራል የፀጥታ ሀይሎች ከህብተሰቡ ጋር እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

በተጨማሪም 84 የመካከለኛ ደረጃ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ ነው ተብሏል።

አከባቢውን ለማረጋጋትና ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ የክልሉና የፌዴራል የፀጥታ አካላት ርብርብ እያደረጉ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ፋባ ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዛሬ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፎች ዛሬ ህዳር 25/03/2011 ዓ.ም. ተድርገዋል።

ፎቶ፦ elu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠገዴ  ወረዳ‼️

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ  ተቀብሮ የነበረ #የእጅ_ቦምብ ፈንድቶ የሁለት ህፃናት ህይወት  ሲያልፍ በስድስቱ ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን ፓሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፓሊስ መመሪያ ሀላፊ ኮማንደር #እንየው_ዘውዴ፥ ቦምቡ በጠገዴ ወረዳ ቡሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አቅራቢያ በግምት በ350 ሜትር ርቀት የተከሰተ ነው ብለዋል።

ሀላፊው ኤፍ 1 የተባለ የእጅ ቦንብ ህፃናት ተማሪዎች ዋርካ ስር ሆነው እያነበቡ በነበረበት ወቅት መፈንዳቱንና ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።

በፍንዳታው ስምንት ህፃናት የመቁሰል አደጋ እንዳጋጥሟቸውና  ሁለቱ ሆስፒታል እንደደረሱ ህይወታቸው እንዳለፈ ገልፀዋል።

ፈንድቶ ጉዳት ያደረሰው ቦንቡ መሬት ውስጥ ተቀብሮ መቆየቱን ኮማንደሩ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ🔝

"በአሁኑ ሰአት በወለጋ ዩኒቨርስቲ ማለትም ከ5:30-7:30 በጣም አለመረጋጋት አለ እንዳውም ብሎክ 714 እና 722 ሁለት ተማሪዎችተመተው ነቀምቴ ሪፈራል ሆስፒታል ሄደዋል ነው። ግቢው እንዳለ በክልል ፖሊሶች ተከቧል ተማሪዎችም ወደ ጫካ እየገቡ ነው። እኛም በጣም ፈርተን ዶርም ተቀምጠናል። አብዛኛው ተማሪም እያለቀሱ ይገኛሉ በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነው። ካፌ ውስጥም በመግባት ተማሪዎችን ደብድበዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የሴኔጋሉ ተወካይ የአውሮፓዊያኑ 2019 የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ፡፡ ኮሊ ሴክ የተባሉት እኚ በድርጅቱ የሀገረ ሴኔጋል ተወካይ ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉም ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንደሚኖሯቸው ተነግሯል፡፡

@tsegabwolde @tikahethiopia
ነቀምት‼️

ዛሬ በነቀምቴ ከተማ የቴሌኮም አገልግሎት መቋረጡ ኢትዮ ቴሌኮም ተናግሯል፡፡ ከማለዳው 12፡45 ጀምሮ አገልግሎቱ መቋረጡ ታውቋል፡፡

ለነቀምቴ ከተማም የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጠው የኮር ሳይት በኤሌክትሪክ ሀይል መቋረጥ ምክንያት አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻለ ተሰምቷል፡፡

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ነቀምት ከተማ የተቋረጠውን አገልግሎት መላ ለመስጠትም ኢትዮ ቴሌኮም በስፍራው ባለሙያዎችን ልኳል፡፡ ለዚህም ህዝቡን #ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ🔝በተቋሙ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት አሁን መረጋጋቱን እና ግቢው ወደሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተመለሰ እንደሆነ በግቢው ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ለTIKVAH-ETH ባደረሱት መልዕክት አሳውቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia