TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኦነግ‼️

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በምርጫ ቦርድ እንዲመዘገብ የቀረበለትን ጥያቄ #አልቀበልም አለ መባሉን #አስተባበለ። ፓርቲው ለምርጫ ቦርድ የምዝገባ ጥያቄ አቅርቤያለሁ ብሏል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ #ቀጀላ_መርዳሳ በአርትስ ቴሌቪዠን ላይ ቀርበው እንደተናገሩት ኦነግ ምርጫ ቦርድ ቀርቤ አልመዘገብም አለ በሚል የሚናፈሱ መረጃዎች #ትክክል_አይደሉም ብለዋል። እንደአቶ ቀጀላ ገለጻ ኦነግ ምዝገባ ለማካሄድ ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርቧል። ነገር ግን የፓርቲዎች ምዝገባ መመሪያ ላይ የሰፈሩት ቅድመ ሁኔታዎች ድርጅቱ ለምርጫ ከሚያደርገው ዝግጅት ጊዜ መጣበብ እና ከድርጅቱ ታሪካዊ አመጣጥ ጋር ሊጣጣሙለት አልቻሉም።

የ45 ዓመታት የምስረታ ታሪክ ያለው ኦነግ በአዲስ ሁኔታ 1500 ሰዎችን አስፈርሞ ለምዝገባ እንዲቀርብ መጠየቁ ድርጅቱን እንደአዲስ የመቁጠር ያህል ነው ያሉት አቶ ቀጀላ ኦነግን በአዲስ አባላትና ደጋፊዎች ማዋቀርም የመስራች አባላቱን ታሪክ መፋቅ ነው ብለዋል።

ኦነግ በአሁኑ ወቅት ወደኢትዮጵያ የመጣው በፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን የተናገሩት ከፍተኛ አመራሩ ይህም በይፋ እውቅና የተሰጠው ድርጅት መሆኑን ይመሰክራል ነው ያሉት።

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ‼️

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ሚኒስቴር የማያውቀው የትምህርት ክፍል አለ በሚል በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች የተሰራጨውን መረጃ #አስተባበለ

በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ ስር ዩኒቨርሲቲውና ትምህርት ሚኒስቴር የማያውቀው የትምህርት ክፍል ተገኝቷል የሚል መረጃ ተለቋል።

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር #የቻለ ዩኒቨርሲቲው ማንኛውንም የትምህርት ክፍል የሚከፈተው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተወያይቶበት፣ ማኔጅመንቱና ቦርዱ  አጽድቆት  እና ከትምህርት ሚኒስቴር ፍቃድ ሲያገኝ ብቻ ነው መሆኑን ለfbc ተናግረዋል።

ሁሉም የትምህርት ክፍሎች በዚህ መሰረት የተከፈቱ መሆኑን  የገለፁት ዶክተር የቻለ፥ የፕሮዳክሽን ኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍልም በዚሁ መሰረት የተከፈተ መሆኑን አስታውቀዋል።

ሜታል ፕሮዳክሽን ኢንጂነሪንግ የሚል ስያሜ እንደተሰጠውና ይህም ተማሪዎች በልምምድና የተግባር ትምህርት ወቅት በብሄራዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) እድሉን እንዲያገኙ ለማድረግ ነው ብለዋል።

ይህም ተቋሙ ከትምህረት ክፍሉ ጋር በብዙ የሚያገናኘው የስራ አይነት ያለው በመሆኑ ስያሜው በዛ እንዲሰየም መደረጉን ተናግረዋል።

ነገር ግን ይህ ትምህርት ሚኒስቴር ከሚያውቀው ውጪ ስያሜ ስለሚሆን ወደ ትክክለኛው ስያሜ መመለስ አለበት በሚል ውሳኔ ላይ መደረሱን አብራርተዋል።

በዚህም በዩኒቨርሲቲው ሜታል ፕሮዳክሽን ኢንጂነሪንግ የሚለው ስያሜ ቀርቶ ፕሮዳክሽን ኢንጂነሪንግ እንዲሆን ተወስኗል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia