TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኛው‼️

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ሜጄር ጄኔራል #ክንፈ_ዳኘውን ጨምሮ የስድስት ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ እየተመለከተ ነው።

ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ገቢዬ በጡረታ ማገኘው 4 ሺህ ብር ብቻ በመሆኑ መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ ማለታቸውን ተከትሎ በዚህ ጥያቄያቸው ላይ ፖሊስ ተቃውሞውን ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።

የፌደራል ፀረ ሙስና ስነ ምግባር ኮሚሽን ያስመዘገቡትን ሀብት እና እስከ ህዳር 5 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት ድረስ ስሙ ባልተጠቀሰ ባንክ ውስጥ ያላቸው ተቀማጭን በማስረጃነት አቅርቧል።

ጋዜጠኛ ፍጹም የሽጥላ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ ቆሞላታል።

ፖሊስ ለፍርድ ቤት እንዳብራራው፥ ጋዜጠኛ ፍጹም፤ ፍፁም ኢንተርቴይንመንት ለተባለ ድርጅት ባልተገባ ስፖንሰርሺፕ ብር 954 ሺህ 770 ብር የህዝብ ገንዘብ መውሰዷን ገልጿል።

በገንዘቡም የንግድ ድርጅት ከፍተው አፍርተዋል ያፈሩትንም ሀብት ሰውረዋል በሚል መጠርጠሯን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል።

ፍርድ ቤቱ በአሁኑ ወቅትም የሌሎች ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ እየተመለከተ ይገኛል።

ምንጭ ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

ህዳር 8 እና 9 ቀን 2011 በአዲሰ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች  ጉባኤ  የትራፊክ #መጨናናቅ እንዳይከሰት ሕብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠየቀ።

ጉባኤውን ለመታደም በርካታ እንግዶች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ሲሆን እንግዶቹ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በአጀብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት አሽከርካሪዎች ቅድሚያ እንዲሰጡና መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት እስከሚሆኑ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል።

እግረኞችና አሽከርካሪዎች የሞተረኛ ትራፊክና የእሳት አደጋ የአምቡላንስ ሳይረን ድምጽ ሲሰሙ ቀኛቸውን ይዘው በማሳለፍ የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደረጉም ተጠይቋል።

ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ከዛሬ ህዳር 6 ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስኪመለሱ ድረስ ከፓርላማ መብራት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ መስቀል አደባባይ፣ ፍላሚንጎ፣ ኦሎምፒያ፣ ወሎ ሰፈር፣ ጃፓን ኤምባሲ፣ ፍሬንድሽፕ፣ ቦሌ ቀለበት መንገድና ኤርፖርት መንገዶች ግራና ቀኝ አቅጣጫ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው።

ከፓርላማ መብራት – በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ብሄራዊ ቤተ መንግስት፣ በፍል ውሃ- ብሄራዊ ቲያትር -ሜክሲኮ አደባባይ-አፍሪካ ሕብረት አዳራሽ ዙሪያ መንገዶችም እንዲሁ።

ከፓርላማ መብራት – በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን  ፍልውሃና አምባሳደር ቲያትር ዙሪያውን፣ ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ሕብረት ዋናው በር ድረስ ያሉት መንገዶች ላይም ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ- መስቀል አደባባይ -መገናኛ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች በኮካ ኮላ ድልድይ -በአብነት ተክለ ኃይማኖት -ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ ወይም በኤክስትሪም ሆቴል ቴዎድሮስ አደባባይ -አሮጌ ቄራ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙም ተጠቁሟል።

በባልቻ ሆስፒታል -አረቄ ፋብሪካ- ጎማ ቁጠባ- ጥቁር አንበሳ -ኢምግሬሽን -አርማ ጋራዥ -በንግድ ማተሚያ -አሮጌ ቄራ አማራጮችም ተጠቅሰዋል።

ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ሳር ቤት -ጎፋ ማዞሪያ-ቄራ ጎተራ- ጎርጎርዮስ -ቦሌ ሚካኤል- ሩዋንዳ -አትላስ- ዘሪሁን ህንጻ መንገዶችን እንዲጠቀሙም ነው የተገለጸው።

የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች ደግሞ በአትላስ -ዘሪሁን፣ቀለበት መንገድ- ቦሌ ሚካኤል- ሀኪም ማሞ ወደ ጎተራ፣ ቀለበት መንገድ-መገናኛ- ዳያስፖራ አደባባይ-እንግሊዝ ኤምባሲ ፣ ቀለበት መንገድ -መገናኛ- አድዋ ጎዳና -አዋሬ- አራት ኪሎ፣ከፍላሚንጎ-ደንበል ጀርባ ወደ መስቀል ፍላወር መንገዶችን መጠቀም እንደሚቻልም ተጠቅሷል።

ከባድ ተሽከርካሪዎችም ከፓርላማ እሰከ ቦሌ መንገድ እና በአፍሪካ ሕብረት ዙሪያ ያለውን መንገድ መጠቀም ክልክል መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በዱራሜ ከተማ የከምባታ ብሔረሰብ የራሱን ክልል እንዲመሰርት የሚጠይቅ ሰልፍ ነገ እንደሚካሄድ ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከፋ ዞን ምክር ቤት‼️

የካፋ ዞን ምክር ቤት አምስተኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባዔ #ቦንጋ ላይ የተገነባው ብሔራዊ የቡና ሙዚዬም ሥራ እንዲጀምር ወሰነ።

የካፋ ዞን #የክልልነት ጥያቄንም በምክር ቤቱ አባላት ጸድቋል።

የዞኑ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ ግርማ ወልደ ሚካዔል ለኢዜአ እንደገለጹት ጉባዔው በዛሬው ወሎ በሁለት አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አስተሏልፏል ።

ጉባዔው ውሳኔ ካሳለፈባቸው አጀንዳዎች አንዱ በዞኑ ቦንጋ ከተማ ተገንብቶ ለአመታት ሥራ ያልጀመረው ሙዚዬም ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል።

“ከምሁራን የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር ሙዚዬሙ ወደ ሥራ እንዲገባ ውሳኔ ተላልፏል” ብለዋል ።

የካፋ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ ለምክር ቤቱ ቀርቦ በአባላቱ ውይይት ከተደረገበት በኋላ በሙሉ ድምጽ መፅደቁን ምክትል አፈ ጉባዔው ተናግረዋል።

ጉባኤው ነገ የዞኑን የ2010 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ አካላት የሥራ ክንውን በመገምገምና በቀጣይ ዕቅድ ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ አመላክተዋል ።

እንደ ምክትል አፈ ጉባኤው ገለጻ በተለያዩ ምክንያቶች ያልጸደቀውን የዞኑን የ2011 በጀትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሹመትም እንደሚፀድቅ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ሜጀር ጀነራል #ክንፈ_ዳኘው አቅም የለኝም መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ ብለው ያቀረቡት ጥያቄያቸውን ዛሬ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ደብረፂዮን‼️

“ማንም ቢሆን ሰርቆ ትግራይ ክልል እደበቃለሁ ቢል ለሕግ ተላልፎ ይሰጣል” ደብረፂዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር
.
.
"ገና ለገና ስም እንዳይወጣ ተብሎ የሰረቀንና #የተልከሰከሰን ማንም ቢሆን ወደ ሕግ ከማቅረብ ወደኋላ እንደማይል የተናገሩት ርእሰ መስተዳድሩ፣ “ተዋረድን የሚባል ነገር የለም፤ ሁሉም በሰራው ጉድ ሰርቆ እኛ ሥር ከገባ ጎትተን ነው የምናስረክበው፡፡ ከሕዝብ በላይ የሚሆን ሰው ማንም የለም፡፡ ገና ለገና ሥም እንዳያወጡልን ብለን ልንሸፋፍን ? በፍፁም አናደርገውም! #አንጠልጥለን ነው የምንወስደው፡፡ በሕግ፣ በሥነሥርዓት እንዲፈተሽ ማለት ነው፡፡ ሲልከሰከስ ያገኘነውን አሁንም ቢሆን እናስገባዋለን፡፡ ማን ተልከስከስ አለው?” ብለዋል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወንጀለኞችን የማደኑ ስራ ይቀጥላል"

ወንጀለኞችን የማደንና ለህግ የማቅረቡ ሂደት ገና እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ገለፁ።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ለfbc በላከው መግለጫ ላይ እንደተመለከተው፥ መንግስት ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት በሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ሀገርን በመዝረፍና የሀገሪቱን መፃኢ ተስፋ ለማጨለም የሚንቀሳቀሱ አካላትን እንዲሁም የሰኔ 16 የቦምብ ፍንዳታን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን በማቀነባበር የተጠረጠሩትን ተከታትሎ ለህግ ለማቅረብ ተግቶ እየሰራ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት።

መንግስት ይህንን እያደረገ ያለው በአንድ በኩል ባለፉት ዘመናት ህዝቡ በግልፅ ሲጠይቃቸው የነበሩ የፍትህ ጥያቄዎች በመሆናቸውእና በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት ይህንን ለማድረግ ግዴታ ስላለበት እንደሆነም አስረድተዋል።

“የኢትዮጵያ ህዝብ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የፍትህ ጥያቄ ሲያቀርብ ነበር” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ መንግስትም የህዝብ ጥያቄ መመለስ ውዴታው ብቻ ሳይሆን ግዴታውም እንደሆነ ገልፀዋል።

በአንድ ሀገር ውስጥ የመንግስት መኖርን የግዴታ ከሚያደርጉት መሰረታዊ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ፍትህን ማረጋገጥ እንደሆነም ገልፀዋል።

ፍትህ የሚረጋገጠውም ንጹሃን በኩራት ቀና ብለው የሚሄዱበትና ወንጀለኞች ደግሞ የትም የማይደበቁበት ስርዓት መፍጠር ስንችል ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ንፁሃን ዜጎች እንጂ ወንጀለኞች በኩራት የሚኖሩባት ሀገር መሆን የለባትም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ወንጀል የፈፀሙት እንዲቀጡበት፣ ሊፈፅሙ ያሰቡት እንዲጠነቀቁበት፣ እነርሱን ሊከተሉ የሚከጅሉት እንዲማሩበት ሲባል ወንጀለኞችን የማደንና ለህግ የማቅረቡ ሂደት ገና ይቀጥላል፤ #ተጀመረ እንጂ #አልተፈፀመም፤ ዓላማውም በአራቱም አቅጣጫ ሀገሪቱን ከወንጀለኞች ነፃ ማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ወንጀለኞች ጥቅም እስካገኙ ድረስ ወገኔ ለሚሉት አይራሩም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ወንጀለኛ ወገንም ብሄርም፣ ዘርም፣ ሞራልም የለውም ሲሉ አስታውቀዋል።

“ወንጀልና ካንሰር አንድ ናቸው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ካንሰርን በልምምጥ፣ በልመና እና በአማላጅ ማዳን አይቻልም፤ ካንሰርን በዝምታ መመልከትም ሞትን በእያንዳንዷ ቀን በዝምታ እንደ መጋበዝ ነው ብለዋል በመግለጫቸው።

ካንሰር እንደወንጀለኛ ነው ያለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ስለራሱ ካልሆነ ስላለበት አካልም ሆነ ማንነቱን ስላአገኘበት የሰውነት ክፍል ፈፅሞ
እንደማያስብ አስረድተዋል። ካንሰሩ ያንን የሰውነት ክፍል ለመኖሪያና ወደ ሌሎች ለመስፋፊያ ብቻ ነው የሚፈልገው ብለዋል።

ሁሉን ይጎዳል ብቻውን ይጠቀማል በማለት ነው ካንሰርና ወንጀል ያላቸው ቁርኝት በመግለጫቸው ያስረዱት። ይህንንም ቁርኝት የወንጀልና የካንሰር መፈክሩ ሁሉን ለእኔ ሁሉን ወደ እኔ የሚል እንደሆነም ነው ያነሱት።

መግለጫው ካንሰር ስናክም ደህናዎቹ የሰውነት ክፍሎች ለጊዜው ይጎዳሉ በተለይ ካንሰሩ የጀመረበት አካል ክፍል የተጎዳ መስሎ ይታያል፥ እውነቱ ግን ከዚህ በተቀራኒ ነው በማለት ገልፀዋል።

የሰውነት ክፍሎቻችን በጥቂት የካንሰር ሴሎች ምክንያት እርስ በእርሳቸው አይጣሉም፣ አይባሉም፣ አይናከሱም፣ አይካሰሱም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ እንዲያውም ካንሰሩን የጋራ ጠላት አድርገው በአንድነት ሊዋጉት ይነሳሉ ብሏል።

ምክንያቱም ካንሰሩ ከሰውነቱ ክፍል ስሙን እንጂ ሌላውን እንደማይወስዱ ያውቃሉ፤ እዚያ ቦታ መሽጎ ሁሉንም ሊያጠቃ እንደተዘጋጀ ያምናሉ ሲሉ አስረድተዋል።

እንዲሁም በእርስ በእርስ ፍትጊያ ጊዜ ማጥፋት ለካንሰሩ እደሜ መቀጠል መሆኑን ይረዳሉ፤ አብረው ተባብረው ካልተነሱም ዕጣ ፈንታቸው ሞት መሆኑን ይገነዘባሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ስለዚህ ሁሉም በተያዘው የሰውነት ክፍል ላይ ሳይሆን በካንሰሩ ሴል ላይ ለይተው እንደሚዘምቱ ነው ያመለከቱት።

ወንጀል ለፈፃሚው መጀመሪያ ጥቅም ያስገኘለት ቢመስለውም እየቆየ ግን ራሱን እየበላ ሄዶ መሸከም ከማይችልበት ደረጃ ላይ ይደርሳል ብለዋል።

ወንጀል እንደካንሰር ነው ያልነው ለዚህ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ወንጀለኛ የአንድን አካባቢ ህዝብ የሚፈልገው ሊጠቅመው፣ ሊሰራበት፣ ሊታገልለት ወይም ሊያለማለት አይደለም ብለዋል። #አራዊት እንኳን የማይፈፅሙትን ኢሰብዓዊ ድርጊት በሰው ዘር ላይ የሚፈፅም ሰው በምን አንጀቱ ለወገኑ ይራራል፣ በየትኛው ልቡ ለወገኑ
ያስባል በየትኛውስ አእምሮ ለወገኑ ይቆረቆራል ሲሉ የጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ፥ ወንጀለኛ ማሰቢያው ጥቅም ብቻ ነው፤ ጥቅም ካገኘ ይዘርፋል፤ ያጠፋል፤ ይገላል፤ ያሰቃያል ያወድማል በማለት ነው ያብራሩት።

አሁን የተጀመረው ስራ ሀገር የገደሉ ወንጀለኞችን እነርሱ ለሌላው በነፈጉት ፍትህ ፊት የማቅረብ ስራ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥የተያዙ ሰዎችም በተገቢ ደረጃና አያያዝ የሚገባቸውን ፍትህ እንዲያገኙ ይደረጋልም ብሏል፡፡

እያንዳንዱ ማህበረሰብ የተሸሸጉትን ወንጀለኞች አጋልጦ ለህግ በማስረከብ ወንጀል የሚያሳፍር መሆኑን እያሳየ መሆኑን ጠቅሰው፥ የህዝቡ ትብብርም እንደሚቀጥል ተስፋቸውን ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የወንጀለኞች መኖሪያ መሆን ያለባቸው ማረሚያ ቤቶች እንጂ ብሄሮች ብሄረሰቦች አይደሉም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የቅጣቱ ዋና ዓላማ አጥፊዎችን መቅጣትና ድርጊቱን መኮነን ብቻ ሳይሆን ዳግም እንዳይከሰት መከላከልም ጭምር ነው ብለዋል በመግለጫቸው፡፡

ምንጭ፦ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH .apk
4.1 MB
እንኳን ደስ አለን!! TIKVAH-ETH ከቴሌግራም በተጨማሪ በሞባይል መተግበሪያ መጥቷል!!

ያውርዱት እና ስልኮት ላይ ይጫኑት!
በዚህ ቻናል ከምታገኟቸውን መረጃዎች በተጨማሪ የቢዝነስ፣ ስፖርት እና የመዝናኛ ዜናዎች ማግኘት ያስችላችኋል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ችግሩን ለመፍታት እየሰራን ነው‼️TIKVAH-ETH መተግበሪያ ላይ ችግር የገጠማችሁ ችግሩን ለመቅረፍ የጎልደን ጊር ሰዎች እየሰሩ ናቸው። ሌላው ለአይፎን ተጠቃሚዎች በሚቀጥለው ወር ይዘጋጃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ወንጀለኞችን የማደንና ለህግ የማቅረቡ ሂደት ገና ይቀጥላል። መንግስት ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት በሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ሀገርን በመዝረፍና የሀገሪቱን መጻኢ ተስፋ ለማጨለም የሚንቀሳቀሱ አካላትን እንዲሁም #የሰኔ_16 የቦምብ ፍንዳታን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን በማቀነባበር የተጠረጠሩትን ተከታትሎ ለህግ ለማቅረብ ተግቶ እየሰራ ነው፡፡"

▪️ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦብነግ‼️

የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ መንግሥት ወህኒ ቤቶች የተሰቃዩ የኦጋዴን ሱማሌዎችን ጉዳይ እንዲያየው በትዊተር ገጹ ጠይቋል፡፡

ጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ለጣለው ማዕቀብ #የሐሰት ማስረጃ ለማሰባሰብ ሲባል የተመድ የሱማሊያ ማዕቀብ ተቆጣጣሪ ቡድን በርካታ የሱማሌ ተወላጆች በመንግሥት ግርፋት እንዲሰቃዩ አድርጓል ብሏል-ኦብነግ፡፡

በመቶዎች የሚቀጠሩ ዜጎች ዛሬም በጅግጅጋ አካለ ጎደሎ ሆነው ይገኛሉ ሲልም አክሏል፡፡

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው‼️

የብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር በነበሩት ሜጀር ጀኔራል #ክንፈ_ዳኘው በራሳቸው ወይም ጠበቃ አቁመው ለመከራከር ከቤተሰብ ጋር መክረው ለሰኞ ህዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጠ።

ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ‘የ4ሺህ ብር ጡረተኛ በመሆኔ ጠበቃ ለማቆም አቅም የለኝምና መንግስት #ጠበቃ ያቁምልኝ’ ያሉትን ውድቅ በማድረግ በራሳቸው እንዲከራከሩ ውሳኔ ሰጥቷል።

በጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ከባንክ 100 ሺህ ብር ማውጣታቸውንና ይህንን ያህል ገንዘብ በዚሁ ጊዜ ሊጠፋ እንደማይችል፣ የመኖሪያ ቤት፣ 80 ሺህ ብር ዋጋ ያለው መኪናና በባንክ ውስጥ 5ሺህ300 ብር እንዳላቸው ፖሊስ ማስረጃ አቅርቧል።

የተጠርጣሪው ጠበቆች ‘ፖሊስ ያቀረበ ማስረጃ ጠበቃ ለማቆም አያስችልም’ ሲሉ ተከራክረዋል።

ተጠርጣሪው ‘በ2005 ዓ.ም ያስመዘገብኩት ሊወርድ ይችላል። ቤትና መኪና በስሜ የተመዘገበ ምንም የለኝም። ንብረት ካለኝ ይወረስ’ ብለዋል።

ተጠርጣሪው ይህን ቢሉም ፍርድ ቤቱ በራሳቸው ወይም ጠበቃ አቁመው እከራከራለሁ የሚለውን ከቤተሰብ ጋር ተማክረው እንዲቀርቡ ለሰኞ ህዳር 10 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሩ ሰጥቷል።

ከ2002 እስከ 2010 ዓ.ም የብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር በነበሩት ወቅት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጠበቃ ለማቆም አቅም እንደሌላቸው ቃለ ምሃላ መፈጸማቸው አይዘነጋም።

ተከላካይ ጠበቃ እንዲመደብላቸው ትዕዛዝ የሰጠው ችሎቱ መንግስት በሚያቆምላቸው ተከላካይ ጠበቃ በኩል የተጠርጣሪውን ምላሽ ለመስማት ለህዳር ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።

የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ መርማሪ ቡድን እንዳስረዳው ተጠርጣሪው ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው 15 የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ያቀፈውን ሜቴክ ሲመሩ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ወደጎን በመተው በአገርና ህዝብ ሀብት ላይ ከፍተኛ ምዝበራ እንዲደርስ አድርሰዋል በሚል መጠርጠራቸውንም አስረድቷል።

ከተጠቀሱ የወንጀል ድርጊቶች መካከልም ሕጉን ባልተከተለና የድርጅቱን መመሪያ በጣሰ መንገድ በቢሊየን የሚቆጠር የአገር ውስጥና የውጭ ግዥዎች ያለምንም ጨረታ እንዲፈጸም በማድረግ አገራዊ ኪሳራ እንዲደርስ ማድረጋቸውን ጠቅሷል።

ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ ግዙፍ አገራዊ ፕሮጀክቶችን እሰራለሁ በሚል ‘ጨረታ ማወጣት ስራ ማጓተት ነው’ በሚል ፕሮጀክቶቹን ለስጋ ዘመድና በጥቅም ከሚጋሯቸው ሶስተኛ ወገን ለጨረታ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲባክን አድርገዋል በሚል መጠርጠራቸውን አስረድቷል።

በሌላ በኩል ደርጅቱ ከተቋቋመበት ተልዕኮ ውጭ ከኢትዮጵያ ባህር ትራንዚት ሎጀስቲከስ አገልግሎት ደርጅት ከ28 ዓመታት በላይ ያገለገሉና ያረጁ ‘አባይ ወንዝና አንድነት’ የተሰኙ መርከቦችን ብረት ለመጠቀም ግዥ ፈጽሞ ጅቡቱ ወደብ ላይ ለግማሽ ዓመት እንዲቆሙ በማድረግ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንዲከፈል አድርጓል ተብሏል።

በኋላም ዱባይ ከሚገኝ የጋራዥ ድርጅት ከ3 ሺህ ዶላር በላይ ወጭ ለአንድ ዓመት በማስጠገን ህገ ወጥ በሆነ መንገድ በተለይም ቀይ መስመር ተብሎ በሚታወቀው ከኢራን እስከ በርበራ/ሶማሊያ/ ጭነት በማዘዋወር ሲሰሩ ቆይተው ነገር ግን በድርጂቱ ባንክ ሂሳብ አንድም ገንዘብ ገቢ አላደረጉም።

በመጨረሻም እጅግ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጭ የተደረጋበቻው መርከቦች አጅግ በወረደ መጠን ከ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ባልበለጠ ዋጋ አንዲጨሹ ተደርጓል ነው የተባለው።

በሌላ በኩል ከድርጅቱ ሃለፊነት ውጭ ለረጂም ጊዜ አገልግሎው የቆሙና ነዳጃቸውም አገር ውስጥ የሌላ ስድስት አውሮፕላኖችን ከእስራኤል በመግዛትና ደጀን አቬሽን የሚል በማቋቋም ካለምንም ጥቅም ከፍተኛ ብክነት አንዲደርስ አድርገዋል፣ አስራ ሁለት የሚሆኑ ደረጃቸው የወረዱ ሚግ-23 አውሮፓለኖችን ለአገልግሎት አበቃለሁ በሚል ግዥ በመፈጸምም ያለምንም ጥቅም እስካሁን ድርስ እንዲቀመጡ አድርጓል።

በሌላ በኩል በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ የወዳደቁ ብረቶችን አገልግሎት የሚሰጡትን አገልግሎት ላይ አንዳይውሉ፣ የሚወገዱትንም አንዳይወገዱ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ  ሃብት አላግባብ እንዲባክን አድርገዋልም ተብሏል።

እንደ ያዮ ማዳበሪያ ፋብሪከ አይነት ፕሮከጅቶችም ካለምንም አዋጭ ጥናትና የባለሙያ ያልታገዙ እቅዶችን እየተመራ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲባክን አድርጓል፣  ካለምንም አዋጭነት ጥናት በድርጅቱ የተመረቱ ቁሳቁሶችም ገዥ በማጣት ለዓመታት አላግባብ ተከማችተዋል ብሏል።

ከአስር ስኳርና የማደባሪያ ፍብሪካዎችን ለመገንባት የተረከበው ሜቴክ ማከናወን ባለመቻሉ አንዳንዶቹ ለሌላ ድርጅት እንዲሰጡ መደረጉን የገለጸው መረማሪ ፖሊስ፣ ድርጅቱ ለፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ የሚሆን በቢሊየን ከፍተኛ ገንዘብ ተረክቦ ነገር ግን ፕሮጀክቶቹ ሳይከናወኑ ገንዘቡም ከድርጅቱ የባንክ ሂሳብ አንደሌላ አስረድቷል።

በአጠቃለይ ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በራሳቸው ትዕዛዝ ኮርፖሬሽኑ ከህግ ወጭ ግዥዎችን በመፈጸም፣ ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና የጥቅም ተጋሪ ሶስተኛ ወገንን ለመጥቀም ሲሉ ከፍተኛ ምዝበራ አድርሰዋል በሚል በከባድ የሙስና ወንጀል መጠርጠሩን ለችሎቱ አስተድቷል።

ከዚህም በተጨማሪ ተጠርጣሪው በህግ አንደሚፈለጉ እያወቁ ከአገር ለመውጣት ሲሞክሩ ጠረፍ ላይ ሁመራ አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስረድቷል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ወደናተ በደረሰው የሞባይል መተግበሪያ ላይ ያላችሁን አስተያየት እንዲሁም ሊስተካከል ይገባል የምትሉት ነገር ካለ ይህን bot ተጠቅማችሁ አስተያየታችሁን ማድረስ ትችላላችሁ @tikvahethbot
Forwarded from Dawit Abraham
ኩኩሉ የሞባይል ጌም (በኢትዮጵያ የመጀመሪያው 3ዲ ሞባይል ጌም)!! ይህች ምስኪን ዶሮ በአመት በዓል ማለዳ የቢላ ሲሳይ ልትሆን ነው። ከታሰረችበት እንድታመልጥና እግሬ አውጭኝ ብላ እንድትሮጥ ይርዷት! ጌሙን ለመጫወት ከስር ያለዉን አባሪ ይከተሉ!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.qenetech.kukulu
የሚሸጥ ቦታ የአክስዮን ድርሻ
የአክስዮን አባላት ብዛት = 29
የቦታ ስፋት = 650 ካሬ ሜትር
አድራሻ = ቡልጋርያ አስፋልት ዳር
የግንባታ ሁኔታ = ዲዛይን አልቋል,2 Basement +Ground +13, mixed used apartment and  ግንባታ ከ 2 ወር በኋላ ይጀምራል

ሁሉም አባላት 1 አፓርትመነት(ባለ 2 መኝታ 120 ካሬ ሜትር)  ይደርሳቸዋል እና ቀሪው አፓርትመነት ና ሱቆች ለባለ አክስዮኖች ይከፋፈላል. 
የሚገባው ሰው በሚሸጠው ሰው የሚተካ ነው
የግንባታ ወጪ ከሚገዛዉ ሰው ነው
የግንባታ ወጪ አከፋፈል 1st 300 ሺ, 2nd 300 ሺ .እንደዛ ይቀጥላል.....
አጠቃላይ የግንባታ ወጪ ግምታዊ ከአንድ ባለ አክስዮን የሚጠበቀው 2 ሚልየን.በተለያየ ግዜ የሚከፈል::

የአክስዮን መሸጫ ዋጋ = 1.9 ሚልዮን ብር

0913602806 (Adil)