TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኦብነግ‼️

የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ መንግሥት ወህኒ ቤቶች የተሰቃዩ የኦጋዴን ሱማሌዎችን ጉዳይ እንዲያየው በትዊተር ገጹ ጠይቋል፡፡

ጸጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ለጣለው ማዕቀብ #የሐሰት ማስረጃ ለማሰባሰብ ሲባል የተመድ የሱማሊያ ማዕቀብ ተቆጣጣሪ ቡድን በርካታ የሱማሌ ተወላጆች በመንግሥት ግርፋት እንዲሰቃዩ አድርጓል ብሏል-ኦብነግ፡፡

በመቶዎች የሚቀጠሩ ዜጎች ዛሬም በጅግጅጋ አካለ ጎደሎ ሆነው ይገኛሉ ሲልም አክሏል፡፡

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ለደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሚሊዮን_ማቲዎስ ደብዳቤ ጻፈ በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሠራጨው ደብዳቤ #የሐሰት መሆኑን ጽህፈት ቤቱ ገለፀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃው “በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሠራጨው ደብዳቤ የሐሰት መሆኑን ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ማሳወቅ እፈልጋለሁ” ብሏል።

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ እንዲህ ያለ ደብዳቤ እንዳልጻፉ ማሳወቅ እንወዳለን” ብሏል ጽህፈት ቤቱ።

በዚህ አጋጣሚ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እንዲህ የመሰሉ የሐሰት ዜናዎችን እያጣሩና #በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ ሲልም ጥሪውን አስተላልፏል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለብፁዕነታቸው የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም ሐሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አሳወቀች።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ #ደቡብ_አፍሪካ ሊያደርጉ የነበረውን ጉዞ መሰረዛቸውን ተከትሎ #የሐሰት_ዜና በመሰራጨት ላይ እንደሚገኝ ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፦
- በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጆሐንስበርግ መንበረ ጵጵስና ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የተመሠረተበት ፳፭ኛ ዓመት በዓል ላይ ለመገኘት፣
- ቅዳሴ ቤቱን ለማክበር
- በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን ለመባረክ
-  ምዕመናንን ለማስተማር ዛሬ ከቅዱስነታቸው ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ መርሐ ግብር ይዘው ነበር።

ይሁን እንጂ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ካለባቸው ተደራራቢና አስቸኳይ ሥራዎች አንጻር ለ10 ቀናት ሙሉ ፦
° ከጽ/ቤታቸው ርቀው መቆየት በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የዕለት ተዕለት ሥራዎች ላይ ክፍተት እንዳይፈጠር በመስጋታቸው
° ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊውና ምክትል ሥራ አስኪያጁ በሌሉበት ሁኔታ ለበርካታ ቀናት ከጠ/ጽሕፈቱ ርቀው ከተጓዙ ሥራዎች ስለሚበደሉ ቀደም ሲል ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ሐዋርያዊ ጉዞ ከቅዱስነታቸው ጋር በጥሞና በመወያየት #ለመሰረዝ መገደዳቸው ተነግሯል።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በአንዳንድ ማኅበራዊ ገጾች ፈጽሞ እውነትነት በሌለው መንገድ " ብፁዕነታቸው ወደ ኤርፖርት እንዳይሔዱ እንደተከለከሉ እንዲሁም ፓስፖርታቸው እንደተያዘ " በማስመሰል የሚሰራጨው ዜና ፍፁም መሰረተ ቢስና የሐሰት ዜና መሆኑን ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ከታቀደው ሐዋርያዊ ጉዞ ለመቅረት የተገደዱት በተደራራቢ ሥራ ምክንያት  መሆኑን እና የብፁዕነታቸው ፓስፖርትም ለጉዞ ሲባል ቀደም ብሎ ከሚመለከተው አካል መጥቶ በልዩ ጽሕፈት ቤቱ ጉዳይ አስፈጻሚ እጅ የሚገኝ መሆኑን ገልጻለች።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ከብፁዓን አባቶች ጋር ሆነው በዛሬው ዕለት ደቡብ አፍሪካ ፤ ጁሐንስበርግ ከተማ በሰላም የገቡ ሲሆን ምዕመናንም አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ደቡብ አፍሪካ ፦ https://telegra.ph/EOTC-05-10

@tikvahethiopia