TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን‼️

ህዳር 8 እና 9 ቀን 2011 በአዲሰ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች  ጉባኤ  የትራፊክ #መጨናናቅ እንዳይከሰት ሕብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠየቀ።

ጉባኤውን ለመታደም በርካታ እንግዶች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ሲሆን እንግዶቹ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በአጀብ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት አሽከርካሪዎች ቅድሚያ እንዲሰጡና መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት እስከሚሆኑ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል።

እግረኞችና አሽከርካሪዎች የሞተረኛ ትራፊክና የእሳት አደጋ የአምቡላንስ ሳይረን ድምጽ ሲሰሙ ቀኛቸውን ይዘው በማሳለፍ የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደረጉም ተጠይቋል።

ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ከዛሬ ህዳር 6 ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስኪመለሱ ድረስ ከፓርላማ መብራት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ መስቀል አደባባይ፣ ፍላሚንጎ፣ ኦሎምፒያ፣ ወሎ ሰፈር፣ ጃፓን ኤምባሲ፣ ፍሬንድሽፕ፣ ቦሌ ቀለበት መንገድና ኤርፖርት መንገዶች ግራና ቀኝ አቅጣጫ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው።

ከፓርላማ መብራት – በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ብሄራዊ ቤተ መንግስት፣ በፍል ውሃ- ብሄራዊ ቲያትር -ሜክሲኮ አደባባይ-አፍሪካ ሕብረት አዳራሽ ዙሪያ መንገዶችም እንዲሁ።

ከፓርላማ መብራት – በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን  ፍልውሃና አምባሳደር ቲያትር ዙሪያውን፣ ከንግድ ምክር ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ እስከ አፍሪካ ሕብረት ዋናው በር ድረስ ያሉት መንገዶች ላይም ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ- መስቀል አደባባይ -መገናኛ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች በኮካ ኮላ ድልድይ -በአብነት ተክለ ኃይማኖት -ጌጃ ሰፈር ጎማ ቁጠባ ወይም በኤክስትሪም ሆቴል ቴዎድሮስ አደባባይ -አሮጌ ቄራ አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙም ተጠቁሟል።

በባልቻ ሆስፒታል -አረቄ ፋብሪካ- ጎማ ቁጠባ- ጥቁር አንበሳ -ኢምግሬሽን -አርማ ጋራዥ -በንግድ ማተሚያ -አሮጌ ቄራ አማራጮችም ተጠቅሰዋል።

ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ሳር ቤት -ጎፋ ማዞሪያ-ቄራ ጎተራ- ጎርጎርዮስ -ቦሌ ሚካኤል- ሩዋንዳ -አትላስ- ዘሪሁን ህንጻ መንገዶችን እንዲጠቀሙም ነው የተገለጸው።

የቦሌ መንገድ ተጠቃሚዎች ደግሞ በአትላስ -ዘሪሁን፣ቀለበት መንገድ- ቦሌ ሚካኤል- ሀኪም ማሞ ወደ ጎተራ፣ ቀለበት መንገድ-መገናኛ- ዳያስፖራ አደባባይ-እንግሊዝ ኤምባሲ ፣ ቀለበት መንገድ -መገናኛ- አድዋ ጎዳና -አዋሬ- አራት ኪሎ፣ከፍላሚንጎ-ደንበል ጀርባ ወደ መስቀል ፍላወር መንገዶችን መጠቀም እንደሚቻልም ተጠቅሷል።

ከባድ ተሽከርካሪዎችም ከፓርላማ እሰከ ቦሌ መንገድ እና በአፍሪካ ሕብረት ዙሪያ ያለውን መንገድ መጠቀም ክልክል መሆኑንም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia