TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለBiT ተማሪዎች‼️

ቀን 26/01/2011 ዓ.ም

በባህር ዳር ዩንቨርስቲ ለባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ #ማራዘሙን የገለፀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በ2010 ዓ.ም ማጠቃለያ ፈተና ላልወሰዳችሁ ( ለ1ኛ፤2ኛ እና የ3ኛ ዓመት Holistic ፈተና ተፈታኝ ) የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች #የማይመለከት መሆኑን አውቃችሁ ኢንስቲትዩቱ ባወጣላችሁ የመግቢያና የፈተና መርሃ ግብር መሰረት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

ምንጭ፦ የBiT የፌስቡክ ገፅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ ጥቆማ‼️

ከአዲስ አበባ ወደ ሱሉልታ በሚወስደው መንገድ ሚዛን ጋር የመኪና ግጭት አደጋ ደርሷል። የሚመለከተው አካል ወደስፍራ እንዲሄድ ከቦታው ጥሪ ቀርቧል።

ቻናላችን የደረሰውን ጉዳት አጣርቶ ያሳውቃል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ⬆️የተማሪዎች የመግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጎንደር⬆️

"ዛሬ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 127 ወንድ እና 31 ሴት ተማሪዎችን በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል። በፕሮግራሙ ላይ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ እና ክቡር ዶ/ር አርቲስት መሃሙድ አህመድ በክብር እንግድነት ተገኝተው ነበር። ተማሪ ፍሬህይወት በከፍተኛ ነጥብ የወርቅ ተሸላሚ ሆናለች። "

©Dave ከጎንደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደብረ ማርቆስ⬇️

"በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው በከሠዓቱ መርሃ ግብር የአመቱን የስራ ሪፖርት የሚያቀርብ ሲሆን አጠቃላይ የተቋማት የተማሪዎች ህብረት አዲስ የምርጫ ደንብ ውይይት ተደርጎበት ከተወሰነ በኋላ MoE ከፍተኛ ትምህርት ድኤታ ይፀድቃል። ጎን ለጎንም በሰላማዊ መማር ማስተማር፣ መልካም አስተዳደር፣ ልዩ ድጋፍ ስለሚሹ ተማሪዎችን በተመለከተ እና ሀገራዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተደርጎ ለተማሪዎች ህንረት ተልዕኮ የሚሰጥ ይሆናል። ጉባኤው "እኛ ተማሪዎች ሀገራችን በምታደርገው የላውጥ ጉዞ ሚናችን የጎላ ነው!" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።"

©መሌ ከWKU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ‼️ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ተራዝሟል። ነገእ ግን 2ኛ አመት እና ከዚያ በላይ የመደበኛ ጤና ተማሪዎች ጥቅምት 1 እና 2 ወደተቋሙ እድትገቡ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ⬆️

"ፀግሽ መስከረም 27 በአካባቢያችን ወረዳ 4 የሚገኙ ውጤታማ ተማሪዎችን "ውጤታማ ተማሪዎችን በማበረታት ለተሻለች ኢትዮጵያ እንትጋ" በሚል መሪ ቃል እንሸልማለን:: በእለቱ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ #ኤፍሬም የወረዳ አመራሮች የሃይማኖት አባቶች አቲስቶች የሚገኙ ይሆናል። በከተማችን የላይበራሪ አጠቃቀማችንን የንባብ ባህላችንን አስመልክቶ ግሩም ዶክመንተሪ ይቀርባል። የዚህ ግሩፕ አባላትንም ጋብዘናል። አድራሻ መሳለሚያ ወርዳ 4 ወጣት ማእከል አዳራሽ፦ ኢትዮ የልማትና መረዳጃ እድር ከቀድሞ 01 ወጣት ተስፋ መረዳጃና የልማት ማህበር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ።እናመሰግናለን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባህር ዳር⬆️

የኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ ጉባዔ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች፣ ከያንያን፣ የመብት ተሟጋቾች እና የማኅበራዊ ሚዲያው ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተሳታፊ ሁነዋል፡፡ ‹‹ማኅበራዊ ሚድያ ለኢትዮጵያ አበርክቶቹ፣ ይሁንታዎች እና መርገምቶች›› የሚል የመነሻ ጽሑፍ በሥነ-ጽሑፍ ተመራማሪው ቴዎድሮስ አደላው ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopja
#update የቴክኒክ እና ሙያ መግቢያ⬆️

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ በ2011 ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ #ነጥብን ይፋ አድርጓል፡፡

ኤጀንሲው #ዛሬ እንዳስታወቀው በየዓመቱ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተፈታኞች መካከል የሥራ ገበያውን መሰረት በማድረግ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መቀበያ መስፈርት ተመርኩዞ የመቁረጫ ነጥቡን ይፋ እንዳደረገ አመልክቷል፡፡

በዚህም መሰረት በ2010 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል 725 ሺህ 652 የሚሆኑት ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት በመደበኛው ዘርፍ እንደሚገቡ ኤጀንሲው አመልክቷል፡፡

ከዚህም ውስጥ 230 ሺህ 828 ሴቶች ናቸው፡፡ በመምህራን ኮሌጅ እንዲሁም በፖሊስና መከላከያ ማሰልጠኛ ተቋማት የሚገቡት ቁጥር በዚህ መግለጫ አለመካተቱም ተመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia