TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አስቸኳይ~ነቀምት‼️

ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል #የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በ03፣ 04 እና 07 ቀበሌ፤ በነቀምት የመምህራን ማሰልጠኛ፣ ዳንዲ ቦሩ ኮሌጅ፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በነቀምት ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ። እነኚህ ወገኖቻችን ድጋፍ እና እገዛ ያስፈልጋቸዋል። ሁላችንም ከጎናቸው እንሁን!

#ሼር #SHARE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
⬆️ከላይ ያለውን መልዕክት በፌስቡክ ገፃቹ ላይ በመለጠፍ ተባባሩኝ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ የንግስ በዓል እየተከበረ ይገኛል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ የ11ኛው የኢሕአዴግ ጉባዔ ኦፊሴላዊ መሪ ቃል “ሃገራዊ አንድነት፤ ለሁለንተናዊ ብልፅግና"
.
.
The official motto of the 11th EPRDF Congress is “National Unity for Comprehensive Prosperity.

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወሎ ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም የነባር ተማሪዎችን የመግቢያ ቀናት ይፋ አድርጓል።

🗓ጥቅምት 5 እና 6
🔹በቅጣት ጥቅምት 7
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ህወሃት⬇️

ህወሓት በቀጣይ ግንባሩን የሚመሩ ድርጅቱን #ስራ_አስፈፃሚ አባላት መረጠ፡፡

በዚህም መሰረት፦

1. ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል-ሊቀመንበር
2. ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሄር- ም/ ሊቀመንበር
3. አቶ ጌታቸው ረዳ
4. አቶ አለም ገብረዋህድ
5. አቶ አስመለሽ ወልደስላሴ
6. ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
7. ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም
8. አቶ ጌታቸው አሰፋ
9. ዶ/ር አዲስ አለምባሌማ በቀጥታ በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባላነት ህወሓትን የሚወከሉ ሲሆን፣
10. አቶ በየነ ምክሩ እና
11. ዶ/ር አክሊሉ ኃይለሚካኤልን ጨምሮ አስራ አንዱ አባላት ህወሓትን በስራ አስፈፃሚነት የሚያገለግሉ መሆናቸው ተዘግቧል።

ግንባሩ ዛሬ ባካሄደው ምርጫም 55 አባላት ያሉት የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ ተካሂዷል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
BiT⬆️በተማሪዎች ህብረት የተረጋገጠ አዲሱ የBiT ተማሪዎች የጊዜ ሰሌዳ ከላይ የምትመለከቱት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቀዊተ ሸኖ ⬇️

ከነቀምት ወደ አርጆ በመጓዝ ላይ በነበረ ሚኒባስ ላይ በደረሰ አደጋ የ10 ሰዎች #ህይወት አለፈ።

በትናንትናው ዕለት በምስራቅ ወለጋ #ከነቀምት ወደ #አርጆ ከተማ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒ ባስ ላይ #ቀዊተ_ሸኖ በተባለ ቦታ ላይ በደረሰ አደጋ የ10 ተሳፋሪዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ሌሎች 3 ተሳፋሪዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ሚኒባሱ ኮድ 3 80 85 ኢት 4 ከሆነ ተሳቢ ካለው ሲኖትራክ ጋር የመታጠፊያ ከርብ ላይ የተጋጨ ሲሆን፥ የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ እንደሚገኝ የምስራቅ ወለጋ የትራፊክ ደህንነት ሃላፊ ኢንስፔክተር ፍሮምሳ ሰለሞን ለFBC ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የሰኔ 16 የቦምብ ጥቃትን በመሩ፣ ባቀነባበሩና የፋይናንስ ድጋፍ ባደረጉ ግለሰቦች ላይ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ #አጠናቋል። በዚህም መሰረት ጥቃቱን በማቀነባበር፣ በመምራትና በፋይናንስ በመደገፍ የተሳተፉ ግለሰቦች ማንነትና የምርመራ #ውጤቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ በሚቀጥለው ሳምንት #መግለጫ እንደሚሰጥ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ #ብርሃኑ_ጸጋዬ ተናግረዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አቶ #መላኩ_ፋንታ ፣ ጄኔራል #አሳምነው_ፅጌ ለአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት በእጩነት ከቀረቡ ሰዎች መካከል መሆናቸው ታውቋል። በተጨማሪ አቶ ንጉሱ ጥላሁንም ዕጩ ናቸው።

ምንጭ፦የኢትዮጵያ ፕሬሥ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update አዴፓ 75 የማዕከላዊ ኮሚቴ #እጩ አባላቱን ጥቆማ አካሂዷል። ከተመራጭ 65 አባላት ውስጥ 13 ለአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስራ እፈፃሚ እና 9 ለኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ይመረጣሉ፡፡ የምርጫው ቆጠራ እየተካሄደ እንደሚገኝ የአማራ መገናኛ ብዙሀን ድርጅት ዘግቧል። ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል፡፡

1. አቶ ደመቀ መኮንን
2. አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
3. ዶክተር አምባቸው መኮንን
4. አቶ ሲሳይ ዳምጤ
5. አቶ ዘለቀ አንሉ
6. አቶ ጥላሁን ወርቃየሁ
7. አቶ ፈንታ ደጀን
8. አቶ አብርሃም አያሌው
9. አቶ ተፈራ ወንድምአገኘሁ
10. አቶ ፀጋ አራጌ
11. አቶ ተመስገን ኃይሉ
12. አቶ መሃመድ አብዱ
13. አቶ ኃይሉ ግርማይ
14. ዶክተር ወርቅነህ አዳነ
15. አቶ ብርሃኑ ጣምያለው
16. አቶ ግዛት ዓብዩ
17. ዶክተር መለሰ መኮነን
18. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
19. ወ/ሮ አየለች አሳየ
20. አቶ እዘዝ ዋሴ
21. አቶ ሙሉቀን ዓየሁ
22. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
23. አቶ ምግባሩ ከበደ
24. አቶ ሻምበል ከበደ
25. አቶ ታደሰ ገ/ፃድቅ
26. አቶ ዓለሙ ጀምበሬ
27. አቶ ዮሐንስ ቧያለው
28. አቶ አህመድ ሃሰን
29. አቶ አምሳሉ ደረጀ
30. ወ/ሮ አስናቁ ደረስ
31. አቶ መላኩ አለበል
32. አቶ ላቀ አያሌው
33. አቶ ደሴ ጥላሁን
34. አቶ አየን ብርሃን
35. ዶክተር ይናገር ደሴ
36. አቶ ምስራቅ ተፈራ
37. አቶ ያረጋል ሃይሉ
38. አቶ ብናልፍ አንዷለም
39. አቶ ተፈራ ደርበው
40. አቶ አሊ መኮነን
41. አቶ አገኘሁ ተሻገር
42. ወ/ሮ ፈንታይቱ ካሴ
43. አቶ ንጉሱ ጥላሁን
44. አቶ ሞላ መልካሙ
45. ሲ/ር ብዙአየሁ ቢያዝን
46. አቶ አብርሃም አለኸኝ
47. ቀለምወርቅ ምህረቴ
48. አቶ ጎሹ እንዳላማው
49. ዶክተር ንጉሴ ምትኩ
50. ዶክተር አምላኩ አስረስ
51. ዶክተር ስዩም መስፍን
52. አቶ ዘመዴ ተፈራ
53. ዶክተር ኃይለማሪያም ብርቄ
54. አቶ ካሳ አበባው
55. ወ/ሮ ራቢያ ይማም
56. ወ/ሮ እናታለም መለሰ
57. አቶ መላኩ ፈንታ
58. አቶ ስዩም መኮንን
59. ዶክተር ጥላየ ጌቴ
60. አቶ ጃንጥራር አባይ
61. አቶ ፍቃዴ ዳምጤ
62. ወ/ሮ ሱቢያ ደሳለኝ
63. አቶ አሰማኸኝ አስረስ
64. ዶክተር ጥላሁን መሃሪ
65. ዶክተር አህመዲን መሃመድ
66. አቶ እንዳወቅ አብየ
67. አቶ ወንዳለ ሃብታሙ
68. ዶክተር ይልቃል ከፋለ
69. ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ
70. አቶ ፍስሃ ወ/ሰንበት
71. ወ/ሮ ወርቅሰሙ ማሞ
72. አቶ ባዘዘው ጫኔ
73. ዶክተር ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል
74. ጀኔራል አሳምነው ፅጌ
75. ወ/ሮ ፈንታየ ጥበቡ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለተማሪዎች‼️የዩኒቨርሲቲ ምደባ መጥቷል እየተባለ የሚወራው ወሬ #ውሸት ነው። እስካሁን በዚህ ጉዳይ ኤጀንሲው ያለው ነገር የለም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጨፌ ኦሮሚያ በዚህ ሳምንት መጨረሻ #አስቸኳይ ስብሰባውን እንደሚያደርግ ተገለፀ። አስቸኳይ ስብሰባውን ከመስከረም 25፣ 2011 ጀምሮ በአዳማ ከተማ በጨፌ አደራሽ እንደሚሰበሰብ ተገልጿል። ለዚህም የጨፌ አባላት በሙሉ መስከረም 24 2011 ዓ.ም በአዳማ ጨፌ ኦሮሚያ አደራሽ እንዲገኙ የጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ ቤት አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ጌታቸው አሰፋ
አቶ ጌታቸው አሰፋ‼️ኢሳት የተባለው ቴሌቪዥን እና አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ ከወራት በፊት የቀድሞው የመረጃና ደህንነት ሀላፊ አቶ ጌታቸው የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው እና ሀገር ጥለው መሸሻቸውን ዘገበው ነበር። እኔም ሁለቱን ምንጮች ጠቅሼ ዘገባውን አቅርቤላችሁ ነበር። እንሆ ነገሩ ሁሉ ሌላ ሆኖ ተገኝቷል፦ የእስር ትዕዛዝ ወጣባቸው፤ ሀገር ጥለው ጠፉ የተባሉት አቶ ጌታቸው የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው #ተመርጠዋል

ጋዜጠኛ አለምነህ ዛሬ እንደፃፈው አቶ ጌታቸው ሀገር ጥለው መሸሻቸውን የሰማሁት ከአስተማማኝ ምንጭ ነበር ብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🙏ስለትብብራችሁ አመሰግናለሁ!
#update BBC-ቤንሻንጉል⬇️

በቤንሻንጉል ጉምዝ በተፈጠረ ግጭት ከ50 ሺህ ሰዎች በላይ #ሲፈናቀሉ የሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተሰማ።

መስከረም 16/2011 ዓ.ም የካማሼ ዞን አመራሮች ከምዕራብ ኦሮሚያ አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ ጋር የነበራቸውን ስብሰባ አጠናቅቀው እየተመለሱ በነበሩ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና የፀጥታ ኃይሎች ላይ በተከፈተው ተኩስ የ4 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በተወሰኑ ከኦሮሚያ ጋር በሚዋሰኑ ስፍራዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች #መሞታቸውን፣ መፈናቀላቸውን ቤቶች መቃጠላቸውን የቤንሻንጉል ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አበራ ባይታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በተለይ በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ ስር ሳይ ዳለቻ ቀበሌ ግጭት የነበረ ሲሆን በግጭቱም 75 ቤቶች ተቃጥለዋል ብለዋል። በዚሁ ወረዳ ጅጋንፎይ ቀበሌ በጭበጭ በምትባል አካባቢ ላይ ቤቶች መቃጠላቸውን ጠቅሰው ሌሎች ቀበሌዎችም ላይ ተመሳሳይ ግጭቶች መከሰሰታቸውን ተናግረዋል።

በበሎይ ጅጋንፎ ሶቤይ ከተማ ላይ በርካታ ሰዎች ተፈናቅለዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በሶጌ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች ልቢጋ፣ ሳይ ዳላቻ፣ ታንካራ ቀበሌዎች በርካታ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አስረድተዋል።

"በተንካራ 105 ቤቶች ተቃጥለዋል 3 ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል" ያሉት መስተዳድሩ በበጭበጭ 1 ሰው መሞቱንና አንገርባጃ ቀበሌ 2 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አስረድተዋል። እንደ ክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለፃ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ እና በስጋት ምክንያት ወደ ጫካ የገቡ ሰዎች ያሉ ሲሆን ቁጥራቸው ምን ያህል ነው የሚለውን ግን የተጠናቀረ መረጃ የለኝም በማለት ሳይናገሩ ቀርተዋል።

የተፈናቀሉት ሰዎች ከቤንሻንጉል ብቻ ሳይሆን ክልሉን ከሚያዋስኑት የኦሮሚያ ቀበሌዎችም እንደሆነ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ሳስጋ ወረዳ ዱራበሎ፣ ካምፕ፣ በሎበሬዳ፣ ስምንተኛ ከሚባሉት ቀበሌዎች በስጋት ምክንያት ወደ ነቀምትና በሎበሬዳ ወደሚገኙ ማዕከሎች #ተፈናቅለው እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታከለ ቶሎሳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቤንሻንጉል ክልል የኦሮሚያ አዋሳኝ ቀበሌዎች በተከሰተው ግጭት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 12 ደርሷል። ከዚህ በተጨማሪም 14 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን እነዚህም በሳስጋ ወረዳ ጤና ጣቢያና በነቀምት ሆስፒታል ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ ከሆነ ቀያቸውን ጥለው ወደ ኦሮሚያ የተሰደዱ ሰዎች ቁጥር 50 ሺህ ደርሷል። እነዚህ ሰዎች የተፈናቀሉት ከበሎይ ጅጋንፎና ያሶ ሲሆን ከኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ደግሞ ሀሮ ሊሙ፣ ሶጌና ሳስጋ አካባቢዎች ነው።

አቶ ታከለ ጨምረውም ከእነዚህ አካባቢዎች የሚፈናቀሉ የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆችች ቁጥር በየእለቱ እየጨመረ መሆኑን ገልፀዋል። የተፈናቀሉት ሰዎች ሳስጋ ወረዳ፣ ነቀምት ከተማ፣ ሀሮ ሊሙ ወረዳና ጉቶ ጊዳ ወረዳ ውስጥ ኡኬ ከተማ ተጠልለው እንደሚገኙ ጨምረው አስረድተዋል።

በምሥራቅ ወለጋ የሀሮ ሊሙ ወረዳ ኮሙኑኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸው አቶ #ዱጋሳ_ጃለታ ከቤንሻንጉል ክልል 7 ቀበሌዎች 20 ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን እስካሁን ባላቸው መረጃ በወረዳው ብቻ 5 ሰዎች ሞተዋል።

2 #ነፍሰጡር እናቶች መንገድ ላይ መውለዳቸውን የተናገሩት አቶ ዱጋሳ ህፃናት፣ እናቶችና አቅመ ደካሞች የመኪና መንገድ ባለመኖሩ የተነሳ ለመሸሽ አዳጋች እንደሆነባቸውም ጨምረው አስረድተዋል።

በቤንሻንጉል ክልል #ግጭት በተከሰተባቸው በበሎይ ጅጋንፎይ ወረዳ #ሦስት አካባቢዎች እንዲሁም በካማሼ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሰፍረው እንደሚገኙ የተናገሩት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በተለያየ ጊዜ ምርት በሚደርስበት አካባቢ በክፍፍል ወቅት በተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚነሱ ነገር ግን እነዚህን ወስዶ #ብሄር ተኮር ግጭት ነው ማለት እንደማይቻል አስረድተዋል።

የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ የሆኑት አቶ ታከለ ቶሎሳ በበኩላቸው እስካሁን ድረስ 40 ሰዎች ከቤንሽንጉል 5 ሰዎች ደግሞ ከኦሮሚያ #በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ለተፈናቀሉ ሰዎች የአካባቢው ማህበረሰብ #እርዳታ እያደረገላቸው መሆኑን ከመንግሥት ደግሞ አስፈላጊው ድጋፍ እየተጠበቀ እንደሆነ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ BBC የአማርኛው አገልግሎት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ እየተሰራጨ ያለው የመግቢያ ቀን እስካሁን ድረስ በዩኒቨርሲቲውም ሆነ በተማሪዎች ህብረቱ የተረጋገጠ አይደለም። የተማሪዎች ተወካዩ ካላይ ያለውን ምላሽ ሰጥቶበታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የደኢህዴን 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት #ምርጫ እያካሄደ ነው፡፡ 70 አባላት ተጠቁሞ የድምፅ ቆጠራ እየተካሄደ ሲሆን እጩዎች :-

1. ጓድ ማስረሻ በላቸው
2. ጓድ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል
3. ጓድ የሺዋስ አለሙ
4. ጓዲት ሙፈርያት ካሚል
5. ጓድ አንተነህ ፍቃዱ
6. ጓዲት ማርታ ሉዊጄ
7. ጓድ ሺሰማ ገብረስላሴ
8. ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው
9. ጓድ ሚሊዮን ማቴዎስ
10. ጓዲት ፋጤ ሰርሜሎ
11. ጓድ ጥበቡ ዪሃንስ
12. ጓድ ሙሉጌታ ተፈራ
13. ጓድ ደሴ ዳልኬ
14. ጓድ ዘይኑ ጀማል
15. ጓድ ኢንጂነር የማታም ቸኮል
16. ጓድ ዶክተር ቴክሌ ሌዛ
17. ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዪ
18. ጓድ ቃሬ ጫዊቻ
19. ጓዲት ስምረት ግርማ
20. ጓዲት ህይወት ሃይሉ
21. ጓድ መለሰ አለሙ
22. ጓድ ኤልያስ ሽኩር
23. ጓድ አክሊሉ ታደሰ
24. ጓድ ሃይለማርም ተስፋዪ
25. ጓድ አብዱልፈታ የሱፍ
26. ጓድ ተስፋዪ በልጅጌ
27. ጓድ እርስቱ ይርዳው
28. ጓድ ታምራት ዲላ
29. ጓዲት አስቴር ዳዊት
30. ጓዲት ኢ/ር ሌላ አለም ገ/ዮሐንስ
31. ጓድ ክፍሌ ገ/ማሪያም
32. ጓድ አያሌው ዝና
33. ጓድ ዘይኑ ቢታ
34. ጓድ አክሊሉ ለማ
35. ጓድ ሞገስ ባልቻ
36. ጓድአስራት አለማየሁ
37. ጓድአ/ር ምስጋናው አረዳ
38. ጓድ ተስፋዬ ይገዙ
39. ጓድ አብይ አንዳሞ
40. ጓድ አለማየሁ ባውዲ
41. ጓድ ጥላሁን ከበደ
42. ጓድ ዶ/ር ደመቀ አጪሶ
43. ጓድ አብራሃም ማርሻሎ
44. ጓድ ከበደ ሳህለ
45. ጓዲት መሰረት መስቀሌ
46. ጓድ ስኳሬ ሹዳ
47. ጓድ ኃ/ብርሃን ዜና
48. ጓድ አማኑኤል አብደላ
49. ጓድ ምትኩ ካሳ
50. ጓዲት ሂክማ ሐይረዲን
51. ጓድ አሰፋ አቢዩ
52. ጓድ ተፈራ ሞላ
53. ጓድ ፍቅሬ ግዛው
54. ጓድ አስራት አሰፋ
55. ጓድ ታከለ ነጨ
56. ጓድ ኢ/ር ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ
57. ጓድ ዋዱ ዳና
58. ጓድ ኡስማን ሱሩር
59. ጓድ አያኖ በራሶ
60. ጓድ አማኑኤል አብረሃም
61. ጓድ ተዘራ ወ/ማሪያም
62. ጓዲት ሄለን ደበበ
63. ጓድ ደገቶ ኩምቤ
64. ጓድ ፍፁም አረጋ
65. ጓዲት አለምፀሐይ ጳውሎስ
66. ጓድ ገ/መስቀል ጫላ
67. ጓድ አልጋየሁ ጅሎ
68. ጓድ በላይ ኮጆአብ
69. ጓድ ብሌን ግዜወርቅ
70. ጓድ ዶ/ር ተሸመ ታደሰ
ናቸው ፡፡ ውጤቱን ዛሬ ምሽት ይፋ ይደረጋል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ #በስደት ላይ ከሚኖሩ #ኤርትራውያን መካከል150 ተማሪዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብተው የመማር ዕድል እንደሚያገኙ በኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia