TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አርባ ምንጭ⬆️

የኦሮሞ #አባገዳዎች በአርባምንጭ አቀባበል ተደረገላቸዋል። የኦሮሞ አባገዳዎች የጋሞ ሽማግሌዎች ጸቡን ለማብረድ ላደረጉት ጥረት #ምስጋና ለማቅረብ አርባምንጭ ገብተዋል፡፡

የጋሞ ሽማግሌዎች ጸቡን ለማብረድ ላደረጉት ጥረት በኦሮሞ አባገዳዎች ምስጋና ቀርቦላቸዋል፡፡

እንግዶቻቸውን የተቀበሉት #የጋሞ ሽማግሌዎችም ጸብን በጸብ የመመለስ ባህል እንዳሌላቸው ገልጸዋል፡፡

በቡራዩ በተፈጸመው ጥቃት ዙሪያ ከነገ ጀምሮ ውይይት እንደሚያደረግ etv ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
😢ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑርልን😢
.
.
ፍቅር ብቻ ያሸንፋል! ገለቶማ!
@tseabwolde @tikvahethiopia
ኮኮሳ⬆️

"መስቀል ደመራ በምዕራብ አርሲ ዞን ኮኮሳ ከተማ ላይ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ⬇️

እንዃን ለ 2011 የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ እያልን የነባር ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ጥቅምት 5 እና 6 ሲሆን፣ የአዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ከጥቅምት 19 እስከ 21 ድረስ ነው። ስለሆነም በተጠቀሰው ቀን ተማሪዎች በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳዉቃል፡፡

በተጨማሪም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃዎችን ኦሪጂናልና ፎቶ ኮፒ፣ ስምንት ጉርድ ፎቶ-ግራፎች፣ ብርድ ልብስ፣ እና አንሶላ ይዘዉ መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ www.facebook.com/jigjigauniversity ን ይመልከቱ ወይንም [email protected] ላይ ጥያቄዎን ይላኩ፡፡

©ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️የመስቀል ደመራ በዓል በተያዩ የሀገራችን ከተሞች በድምቀት ተከብሯል።

የፎቶዎች ቅደም ተከተል፦

1.ባህር ዳር
2.ወላይታ ሶዶ
3.ሀረር
4.ደሴ
5.እንጂባራ
6.አዲስ አበባ
7.አርሲ ነጌሌ
8.ሀዋሳ

በሁሉም ከተሞች በዓሉ በሰላም ተከብሯል። በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!

የፎቶ ባለቤቶች የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት! 8 ቁጥር ፎቶ፦ ዘመዱ
@tsegabwolde @tivahethiopia
ፎቶ 2⬆️የመስቀል ደመራ በዓል በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች በድምቀት ተከብሯል።

የፎቶዎች ቅደም ተከተል፦

1.አሰላ
2.ደብረ ብርሃን
3.ጅማ
4.መቀለ
5.ጋምቤላ

በሁሉም ከተሞች በዓሉ በሰላም ተከብሯል። በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!

የፎቶ ባለቤቶች የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት!
@tsegabwolde @tivahethiopia
ከጋምቤላ⬆️

"ፀግሽ ጋምቤላ ሰሞኑን የነበረው #ረብሻ ዛሬ #ተረጋግቶ የመስቀል በዓል እንዲህ #በደመቀ ሁኔታ ሁሉም የከተማው ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እና የክልሉ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል በተገኙበት ያለምንም ችግር #በሰላም ተከብርዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ ማስታወቂያ⬆️በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዲስ ለሚገቡ ሁሉም ረዚደንት ሃኪሞች ከራድዮሎጂ በስተቀር የመግቢያ ቀን 20/01/2011 መሆኑ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
GONDAR UNIVERISTY⬇️

"Exam for #postgraduate program in Information Systems, Computer Science and Information technology will be given in 30-1-2011"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ስሞኑን በአዲስ አበባ ከነበረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ታስረው የነበሩ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የአቀባበል ኮሚቴ የነበሩት #ብርሀኑ_ተክለያሬድና #መኮንን_ለገስ ዛሬ ከእስር ተለቀቁ። ግለሰቦቹ የታሰሩት በከተማይቱ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ተጠርጥረው እንደነበርና ምርመራቸውን ጨርሰው መለቀቃቸውን ከቤተሰቦቻቸው ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬዳዋ⬇️

"ሰላም ፀግሽ!! ዴቭ ነኝ ከድሬ ዳዋ፡፡ ዛሬ የደመራ በዓል በሚገርም ሁኔታ በልዩ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ከሌላዉ ግዜ በተለየ ለመጀመሪያ ግዜ የማህበረ ቅዱሳን ድሬ ዳዋ ማዕከል ያሰለጠናቸዉ በገና ደርዳሪዎች ለበዓሉ ልዩ ዉበት ሆነዉ ነበር፡፡የነበረዉ የጥበቃ ሴኩሪቲ ምርጥ ነበር ድሬ ዳዋ ፓሊስ በሚያስደስት ሁኔታ የህዝቡን ደህንነት በመጠበቅ ትልቅ ስራን ነዉ የሰሩት እንዲሁም የደሬ ሙስሊም ወጣቶች ለደመራ የሚሆን በርካታ ችቦ ገዝተዉ አምጥተዋል!!!የድሬ ሰዉ የሰላም ሰዉ መሆኑን በትክክል ያሰየንበት ደማቅ በዓል አክብረን መርኃ ግብሩ በሠላም ተጠናቋል!! የዓመት ሰዉ ይበለን!!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ ፐIKVAH-ETH አባላት ለላካችሁት ፎቶ ከልብ እመሰግናለሁ። የሁሉም ከተማ ድባብ በፎቶ ቢቀርብ ጥሩ ነበር ነገር ግን የኔትዎርክ ደካማነት ያን ከማድረግ አግዶኛል። በሌላ ጊዜ የደረሱኝን ፎቶዎች ሁሉ አንድ ላይ አያይዤ አቀርባለሁ! ፈጣሪ ረጅም እድሜና ጤና ይስጣችሁ!

እስካሁን ባለኝ መረጃ በሁሉም የሀገሪቱ ከተማዎች በዓሉ በሰላም ተከብሯል።

ለእምነቱ ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ⬆️የነባር እና የአዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ይፋ ተደርገዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) #ነገ ድርጅታዊ ስብሰባውን ይጀምራል። ድርጅቱ የፖለቲካ ፕሮግራሙንና ስያሜውን ይቀይራል ተብሎ ይጠበቃል። በርከት ያሉ ነባር የአመራር አባላቱንም #ያሰናብታል ተብሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia