ፎቶ⬆️ክቡር ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ እና ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ በዛሬው የደመራ ስነ ስርዓት ላይ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን⬇️
ለሱዳን በተሰጠው መሬት ላይ እጀዎት አለበት እየተባለ የሚነሳው ሀሳብ ምን ያክል እውነታ አለው? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ የብአዴን ሊቀመንበር አቶ #ደመቀ_መኮንን ምላሽ ሰጡ፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን ‹‹ብዙዎቹ እንዲህ አይነት ቅሬታ ሲመጣ ለምን ግልጽ አላደረገም ምላሽስ ለምን አልሰጠም የሚሉ ሀሳቦችን ሲሰጡ ሰምቻለው፡፡ በዚህ ላይ #ግልጽ ማድረጉ ጠቃሚ ነው ብየ አስባለሁ፡፡
ከሱዳን ጋር የሚያዋስነው ድንበርን በተመለከተ ከሚኒሊክ ጀምሮ ሲሰራ የቆየ አካሄድ አለ፤ ይሁን እንጅ ከሚነሳብኝ ቅሬታ አንፃር በወቅቱ ጉዳዩ ሲፈጸም እኔ የነበርኩት #እንግሊዝ ሀገር ነው፡፡
ብዙ ጊዜ ሲወራ የምሰማው ደመቀ ለሱዳን መሬት ሰጥቶ ከፍተኛ ሹመት አገኘ የሚል ነው ፤እውነታው ግን እኔ በክልሉ #ከፍተኛ የስልጣን እርክን ባገለገልኩበት 14 ዓመታት ያክል ባስመዘገብኩት ከፍተኛ ውጤት ተንተርሶ ድርጅቴ ነው ለከፍተኛ የስልጣን እርክን እንድደርስ ድምጽ የሰጠኝ፡፡ በወቅቱ የተሰጠኝን የፌዴራል ስልጣን ለኔ አይገባም ሌሎች ቢሆኑ የሚል ሀሳብ ባቀርብም ድርጅቱ በአብላጫ ድምጽ ይህን ኃላፊነት እንድወጣ ስለጠየቀኝ ብቻ ኃላፊነቱን ለመወጣት ስል ነው የተቀበልኩት እንጅ እንደሚወራው አይደለም›› ብለዋል፡፡
‹‹ምንም እውነታ የሌለው የተቀነባበረ #የስም_ማጥፋት ዘመቻ ነው የተፈጸመብኝ፡፡ይህ ሆን ተብሎ አንገቴን እንድደፋ እና አመራርነቴም ተቀባይነትን እንዳያገኝ የተደረገ ሴራ ነው፡፡››
በኔ በኩል #ጉድለት የምለው ድርጅቱን እየመራሁ መሬት ላይ የተፈጸመውን ስህተት አለማወቄ ነው፡፡ አንድም መሬት #አልተሰጠም እየተባለ የተካሄደው የድንቁርና አካሄድ እኔም ድርጅቱም ልንማርበት የሚገባ ነው፡፡ በእርግጥ ስለስም ማጥፋቱ በተወሰነ መጠን በብአዴን ስብሰባ ላይ የተነገረ ቢሆንም የሚያዳምጥ ግን አልነበረም፡፡ አቶ #አያሌው_ጎበዜ በወቅቱ ርዕሰ መስተዳድር በሆኑበት ወቅት በእኔ ተፈርሞ ለሱዳን የተሰጠ መሬት እንደሌለ ግልጽ አድርገውም ነበር፡፡
በወቅቱ በስራ ላይ የሌሉ መሪዎችን #በሀሰት ወሬ መቀባት ድርጅትንም ይጎዳል፤ ተቀባይነትንም ያሳጣል፤ ከዚህም ልንማርበት ይገባል፡፡
የእኛ አመራርነት ጎልቶ እንዳይወጣ ለማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች ተጠቅመውበታል ነው ያሉት፡፡
አለአግባብ ለሱዳን የተሰጠውም መሬት ተገቢ አይደለም የሚል አቋም ነው ያለን፤ ወደፊትም ማስተካከያ እንዲወሰድበት እየተሰራም ነው፡፡ የተፈረመ ካለም መስተካካል አለበት የሚል አቋም ይዘን እየሰራን ነው፤ ጉዳዩ በፌደራል እንዲታይም ከፍተኛ ጥረት እያደረግን ነው ብለዋል የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን፡፡
ምንጭ፦ የአማራ መገናኛ ብዙሀን ድርጅት

ለጥያቄዎቻችሁ መልስ‼️
ዛሬን ጨምሮ ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ጥያቄዎች ቀርበውልኛል፦
"ምንድነው የምትንዘባዘበው መረጃ ከሌለህ ትርኪ ምርኪ ነገር ለምን ትፖስታለህ?"
"ትንንሽ ጉዳዮችን ለምን ትፅፋለህ?"
"አንተ የመንግስት አጨብጫቢ ነህ?"
"አንተ ከዚህ ብሄር ነህ #መሰለኝ ለዚህኛው ታደላለህ..." እና ሌሎችም።
እንዲሁም አስተያየት መሰል ብዙ ስድቦች ይደርሱኛል።
.
.
በመሰረቱ ይህን ቻናል ለህዝብ ጥቅም እና ለመረጃ ልውውጥ የከፈትኩት ነው። ከየትኛውም ወገን ንፁህ ነው። እኔም ከየትኛውም ወገንተኝነት 1000000% ንፁህ ነኝ። እኔ ራሴን የሁሉም ሰው አድርጌ ነው የምቆጥረው። ለሁሉም የሰው ፍጡር እጅግ በጣም ትልቅ ክብር ነው ያለኝ! የኔ መስፈርት ሰው መሆን ላይ ነው። በመሆኑም መረጃዎች ሲላኩልኝ መጀመሪያም መጨረሻም የማየው ከየትኛው ወገን፣ ከየትኛው ብሄር፣ ከየትኛው ሀይማኖት ተከታይ ሰዎች ተላከልኝ ሳይሆን ይህን መረጃ ባሰራጨው ለተከበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ይጠቅመዋል? የሚል ጥያቄ ነው የማነሳው።
በፍፁም ያለአንዳች ግብ እዚህ ገፅ ላይ የሚለጠፈው ፅሁፍ የለም። በተለይ ቻናሉ ለሰላም የሚሰራ ነው። ይህ ማለት ችግር ሲፈጠር ይደብቃል ማለት አይደለም። መረጃዎቹ ሁሉ እንዲመቱልኝ የምፈልገው ግብ አለ። የአያንዳንዱን ከተማ እንቅስቃሴ ሰላም መሆኑን ሰው በሰላም እየተንቀሳቀሰ እለታዊ ተግባሩን መፈፀሙን የሚገልፁ ፅሁፎችን የምለጥፈው መቀለ ሆኖ ስለ ወለጋ፤ ባህር ዳር ሆኖ ስለ ሀዋሳ፤ ሞያሌ ሆኖ ስለ ቤንሻንጉል ጉዳይ መሰማት ስላለበት ነው። ለኛ ስናነባቸው ትንሽ እና ተራ የሚመስሉን ነገሮች ብዙ ሺዎችን በእንቅስቃሴያቸው እንዳገዛቸው በቂ ማረጋገጫ አለኝ።
ይሆነ ቦታ ወጣቶች የሚሰሩትን ጥሩ ስራ ሳቀርብ ሌላውም በነጋታው አስቦት ያድራል። እዚህ ከተማ እንዲህ አይነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተከናወነ፣ ተከበረ የምለውም በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ስላለው ነው።
ከዚህ ቀደም የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚያከብሩትን በዓል እንዲሁም የክርስትና እምነት ተከታዮች የሚያከብሩትን በዓላት በየከተማው በየቀበሌው #በሰላም ስለመከበሩ የማበስረው የዚህን ቻናል ግብ ለማሳካት ነው። 😁ብችል የእያንዳንዱን ሰው ሰላማዊ ውሎ ብዘግብ ደስ ይለኛል።
እና ወዳጆቼ በሰላም ተከበረ በሰላም አለቀ የሚሉ ቃላቶች ማደጋገማቸውን እንደትንሽነት እና እንዳላዋቂነት አትቁጠሩት ትልቅ ትልቅ ጥቅም አላቸው።
ሌላው ከናተ የሚመጡት መረጃዎች እውነት ስለመሆናቸው ፈጣሪ ታማኞች አድርጎ ስለፈጠራችሁ አያሳስበኝም።
መረጃዎች #እንደወረዱ የሚቀርቡት በፍፁም የኔ እጅ እንዳይገባበት ነው። መረጃ ስትልኩልኝ ነጥብ አላስተካክልም። የላካችሁትን አቅርባለሁ። ይህ እኔ ምፈነጭበት እና እራሴን ማስተዋውቅበት መድረክ አይደለም። ይሄ የናተ ገፅ ነው! የፃፋችኋትን #ምንም ኢዲት ሳላደርግ ቃል በቃል አቀርባለሁ። ወደፊትም በዚሁ ቀጥላለሁ።
ማጠቃለያው፦ እዚህ ቤት #ትንሽ ጉዳይ የለም! ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩባት ምድር ምንም የማልፈው ነገር የለም። ይህ አቋሜ ነው። ደረጃ እና ጥራት እያሉ መመፃደቅ አይሰራም። ከእናተ ቤት ተነስተን እንስከ ሀገር ድረስ መረጃዎችን እንዳስሳለን። ለማቅራራት እና ዝነኛ ወይም ገንዘብና ስልጣን ባላቸው ሰዎች ለመወደድ አይደለም የምሰራው! እኔም ሆንኩ ቻናሉ ለእያንዳንዱ ጥቃቅን ጉዳይ info እንሰጣለን። ይህን ማድረግ ትንሽነት እና አለማወቅ ከሆነ ትንሽ እና አላዋቂ ሆኜ ልሙት!
.
.
አዎን የተላከ ሁሉ አይቀርብም! መረጃ ሲላክ ለአካባቢው እና ለሌላ ቦታ ይህ ነገር ይጠቅማል?? የሚለውን ጠይቄ ነው። ሌላው በውስጥ በኩል መረጃ የምሰጣቸው አሉ።
.
.
TIKVAH-ETH ለዝና የሚንቀሳቀስ አይደለም! ለሰላም፣ ለፍቅር እና ለተስፋ ነው የሚሰራው።
እዚህ የሰበሰበን ሰውነት ነው፤ ከዛም ኢትዮጵያዊነት! ነፁ ኢትዮጵያዊ ደግሞ እራሱን የሚያውቅ ሁሉንም የሰው ፍጡር እንደራሱ የሚያይና #የሚያከብር ነው።

ክፍል 1-ኃላፊነት የጎደለው የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የሚያስከፍለው ዋጋ!
ሐሳብን በነፃነት መግለጽ የዴሞክራሲ ማዕከላዊ መርህ ነው፡፡ ይህ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ #መብት ደግሞ በይበልጥ እንዲተገበርና እንዲከበር ካደረጉ የታሪክ ክስተቶች፣ የቅርብ ጊዜውና ትልቁ ተጠቃሽ የማኅበራዊ ሚዲያ ነው፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያ በባህርይው በማዕከላዊነት የሚደረግ የይዘት ቁጥጥር ባለመኖሩ፣ ተጠቃሚዎች የሚፈልጉትን ጉዳይ ያለማንም ገምጋሚነትና አርታኢነት በመቶ ሺሕዎች ለሚቆጠሩ ተጠቃሚ ተከታዮቻቸው በአነስተኛ ወጪ ያስተላልፋሉ፡፡ ይህም ሳንሱር እንዲጠፋ የሚደረገው ትግልና ክርክር እርባን አልባ እንዲሆን በማድረግ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እሳቤ፣ ይህን ያህል ይሄዳል ተብሎ ያልተጠበቀበት ደረጃ አድርሶታል፡፡
በዚህም ምክንያት የማኅበራዊ ሚዲያው ለዴሞክራሲ ልምምድ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሚና እንደሚጫወት ዕሙን ነው፡፡ ዛሬ አንድ ግለሰብ በስልኩ የሚያደርገው ግንኙነት እ.ኤ.አ. በ1980ዎቹ ሮናልድ ሬገን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሳሉ ያደርጉት ከነበረው እንደሚልቅ፣ ከ20 ዓመታት በፊት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ቢል ክሊንተን ያገኙት ከነበረው መረጃ የበለጠ አንድ የ13 ዓመት ታዳጊ በስልኩ እንደሚያገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ መረጃ ኃይል ነውና በዚህ ዘመን በቀላሉ የሚገኝ መረጃ ለዴሞክራሲ ልምምድ ብሎም በመረጃ ላይ የተመረኮዘ ውሳኔ ለመስጠት ትልቁን ሚና ይጫወታል፡፡ ከመሪዎቹ የሚገዳደር መረጃ እጁ ጫፍ ላይ የያዘ ዜጋ የመንግሥትት ተጠያቂነት እንዲኖር ለማድረግ ይችላልና፡፡ ከአንድ የዓለም ጫፍ የተከሰተን ጉዳይ ማግኘትና መተንተን፣ ከዚያም ለውሳኔ መዘጋጀት ከኢንተርኔት ዘመን አስቀድሞ የደኅንነት ተቋማት ተግባር ነበር፡፡ አሁን ግን ከደኅንነት ተቋማት በማይተናነስ ደረጃ ማንኛውም ዜጋ መረጃ አለው፡፡ ይህም መንግሥት የሚወስዳቸውን ዕርምጃዎች እየተከታተሉ ለምን? እንዴት? ለማን ተወሰኑ? በሚሉ ጥያቄዎች ማረምና ተጠያቂነትን ማምጣት ይቻላል፡፡
ይሁንና በ1980ዎቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ሬገንና ከ20 ዓመታት በፊት በተመሳሳይ ሥልጣን ላይ የነበሩት ክሊንተን ያገኟቸው የነበሩ መረጃዎች፣ አሁን ላይ ማንም ከሚያገኛቸው መረጃዎች የሚለዩበት አንድ ነጥብ አለ፣ ተዓማኒነት፡፡ ፕሬዚዳንቶቹ ለሚያስተላልፏዋቸው ውሳኔዎች እንዲረዷቸው መረጃዎቹን ከታማኝ ምንጮች ያገኛሉ፡፡ ለመተንተን ይረዳቸውም ዘንድ ከባለሙያዎች ጋር ይነጋገራሉ፡፡ ነገር ግን አሁን ላይ ከስልኮቻችን፣ በተለይም ከማኅበራዊ ሚዲያ የምናገኛቸው መረጃዎች ተዓማኒነታቸው አናሳ በመሆኑ የሚተላለፉ ውሳኔዎች አደገኛ እንዲሆኑ ያደርጋሉ፡፡
ለዚህ የቅርብ ጊዜ ማሳያ የሚሆነው በማይናማር (በርማ) በሮሂንጂያ የእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የተፈጸመው #ግድያ ነው፡፡ በዚህች የደቡብ ምሥራቅ እስያ አገር የሚኖሩና እንደ አገሪቱ ዜጎች የማይቆጠሩት የሮሂንጊያ ማኅበረሰብ እ.ኤ.አ. በ2016 በአገሪቱ ወታደሮች በተፈጸመባቸው ጥቃት ከአሥር ሺሕ በላይ ሰዎች ሲሞቱባቸው፣ ከ700 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ለመሰደድ በቅተዋል፡፡ በዚህች አብዛኛው ማኅበረሰብ #ዜናም ሆነ ተያያዥ መረጃዎችን ከማኅበራዊ ገጾች በተለይም #ከፌስቡክ እንደሚያገኝ በሚገለጽባት አገር፣ በሮሂንጂያ ማኅበረሰብ ላይ የተፈጸመው በደል ‹በዓለማችን እጅግ በጣም የተጨፈጨፉ ሰዎች› በመባል እንዲታወቅ ያደረገ ጥፋት እንዲፈጸም ያደረገው #በፊስቡክ የሚለቀቅ መረጃ ነበር፡፡
በማይናማር የቡድሂስት መነኩሴ የሆኑት #አሺን_ዊራቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተከታይ ያላቸው ሲሆኑ፣ ይኼንን የተከታዮቻቸውን መብዛት ለበጎ ሳይሆን የውሸት መረጃዎችን በማሠራጨት ለበርካቶች #ሞት መንስዔ ሆነዋል፡፡ እኚህ የማይናማር ቢን ላዲን በመባል የተሰየሙት መነኩሴ ለተከታዮቻቸው ሙስሊም የሆነ አንድ ባለድርጅት አሠሪ፣ የቡድሂስት እምነት ተከታይ የሆነችን ሴት ደፍሯል የሚሉ የሐሰት ማስረጃ ቢያስራጩም ተጠያቂ አልሆኑም ነበር፡፡ ፌስቡክም በተደጋጋሚ ሪፖርት ቢደረግለትም እ.ኤ.አ. እስከ 2018 ድረስ ዕርምጃ ባለመውሰዱ ከፍተኛ ጥፋት እንዲፈጸም ምክንያት ሆኗል፡፡
በዚህ የማኅበራዊ ሚዲያዎች በተንሰራፉበት ዓለም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በማደግ ላይ ያሉና አብዛኛው ኅብረተሰብ ያልተማረ በሆነባቸው አገሮች፣ የማይናማር ዕጣ ፈንታ ሊደገምባቸው እንደማይችል ማረጋገጫ እንደሌለ ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ፡፡ ይህ በተለይ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፈር ካልተበጀለት #አጥፊነቱ ሊከፋ ይችላልም ይላሉ፡፡
.
.
ክፍል ሁለት 6:00 ላይ🔄
ምንጭ፦ ሪፖርተር

TIKVAH-ETHIOPIA via @like
ዳዊት ፅጌ የባላገሩ አሸናፊ ፦ መስከረም 17 በመጨረሻው ዙር በሚሊኒየም አዳራሽ በተደረገው ውድድር ስለ ጥላሁን ገሰሰ የሰራው በሺ የሚቆጠሩ ተመልካቾችን ከመቀመጫቸው አስነስቶ ያስጨበጨበ ስራ....
"በዘመን ድልድይ ላይ ድምፅህ ይሻገራል
ግን ባካል ተለይህ ሞት ለማን ይቀራል"
💚💛❤️ጥላሁን ገሰሰ💚💛❤️
"በዘመን ድልድይ ላይ ድምፅህ ይሻገራል
ግን ባካል ተለይህ ሞት ለማን ይቀራል"
💚💛❤️ጥላሁን ገሰሰ💚💛❤️
የሲዳማ ዞን አስተዳደር⬇️
የዞናችን ሕዝቦች ከዚህ እንደቀደመው ሁሉ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ ነቅቶ እንዲጠብቅና ለረጅም ዓመታት ያጎለበተውን እንግዳ ተቀባይነት ባህሉን እንዲያሳይ የሲዳማ ዞን አስተዳደር አሳሰበ።
እንደሚታወቀው ከፊታችን መስከረም 18-21/2011 ዓ.ም የዴኢህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ እና ከመስከረም 23-25/2011 ዓ.ም የኢህአዴግ ድርጅታዊ #ጉባዔ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል። በእነዚህ ጉባኤዎች የጉባኤ ተሳታፊ እንግዶች ፣ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ከሀገር ውስጥና ውጭ ታላላቅ ሚዲያዎች የሚታደሙበት ጉባዔ በመሆኑ እንግዶችን ለመቀበል የሲዳማ ዞንና #የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል በሀገራችን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ተስፋ ሰጪና የመላው ዞናችን ሕዝብ #ተስፋ ያለመለመ በመሆኑ ሕዝባችንን ከለውጡ ጎን እንዲሰለፍ አስችሏል። ይህ የለውጥ ህደት ያልተመቻቸው እየፈነጠቀ ያለውን የተስፋ ብርሃን ለማጨለም በተለያዩ ጊዜያት በዞናችንም ሆነ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ በለውጥ #አደናቃፊ ኃይሎች የተቀነባበረው ትንኮሳና መሰሪ ዓላማቸው በፀጥታ ኃይሉና በሕዝባችን ብርታት
እየመከነ በዞናችን ውስጥ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር መቻሉ አንዱ ማሳያ ነው።
ጉባዔዎቹ #በሰላም መጠናቀቅ የሕዝባችንን ሰላም ወዳድነቱን፣ እንግዳ ተቀባይነቱን ከማጉላት ባሻገር የሲዳማ ሕዝብ ለጠየቀው ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ እንዲያገኝና በሀገራችንም የተጀመረው የለውጥ ጅማሮን ለማስቀጠል ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ መሆኑ ይታመናል። በመሆኑም አልፎ አልፎ የለውጥ አደናቃፊ ኃይሎች በኀብረተ ሰቡ ውስጥ ስጋት ለመፍጠር በሚያደርጉት ትንኮሳ ሳይደናበር መላው ሕዝባችን ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እኩይ ዓላማቸውን እንዲያመክንና ለጉባዔው በሰላም መጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የሲዳማ ዞን አስተዳደር ጥሪውን ያቀርባል።
መስከረም,16/2011 ዓ.ም
ሀዋሳ,ሲዳማ

#update የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ #ብናልፍ_አንዱዓለም እንደገለጹት ብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት #በባሕር_ዳር ከተማ ያካሂዳል፡፡
©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሞተራይዝድ ዊልቼር በመስቀል በዓል #በስጦታነት አበርክተዋል።
Source:-Fitsum Arega,Chief of Staff, Prime Minister's Office - FDRE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Source:-Fitsum Arega,Chief of Staff, Prime Minister's Office - FDRE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰው ክቡር ነው! #ፈጣሪን ካከበርክ ሰውን #ታከበራለህ። ሰውን ስታከብር ብሄሩን፣ ማንነቱ፣ ቋንቋውን፣ ባህሉን እና ሀሳቡን እንዲሁም የኔ መገለጫ ነው የሚለው ነገር ሁሉ ታከብራለህ። የቱንም ያህል #ልዩነት ቢኖር #ሰውነት ሁሉንም ልዩነት ባዶ ያደርገዋል። ሰውነት #ይቅደም! ሰው እንደሰው ከተከበረ የሰውየው የሆኑ ነገሮች ሁሉ ይከበራሉ። አክቲቪስት ነን ባዮች፤ ፖለቲከኞችም ጭምር በዚህ ወቅት ከምንም ነገር በፊት ለወጣቱ ልታስተምሩት የሚገባው ስለሰው ክቡርነት መሆን አለበት። ሰው ሲከበር #ግጭት አይኖርም፤ ሰው ሲከበር ጥላቻና ክፋት አይኖርም! ሰው መሆን ይከበር!
.
.
#ETHIOPIA
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
.
.
#ETHIOPIA
ፀጋአብ ወልዴ~ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ክፍል 2-ኃላፊነት የጎደለው የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የሚያስከፍለው ዋጋ!
ማኅበራዊ ሚዲያ በኢትዮጵያ፦
በኢትዮጵያ እያደገ የመጣው የኢንተርኔት ተደራሽነትና የስማርት ሞባይል ስልኮች መስፋፋት ከፍተኛ የሆነ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዕድገት እንዲኖር አድርጓል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ እንደሚያሳየው፣ አጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 67.5 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 65.7 ሚሊዮን የሚሆኑት የሞባይል ተጠቃሚ ናቸው፡፡ 17.8 ሚሊዮን ደግሞ የኢንተርኔትና የዳታ ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 1.2 ሚሊዮን የመደበኛ ስልክ ደንበኞች ናቸው፡፡ ምንም እንኳን የኢትዮጵያ የስማርት ስልኮች ተጠቃሚነት ከዓለማችን የመጨረሻው ቢሆንም (ከአጠቃላይ የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች አራት በመቶው ብቻ የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች ናቸው)፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር እያደገ ነው፡፡ ሆኖም ከዓለም አንፃር አናሳ ነው፡፡
ኩዋርትዝ አፍሪካ በየካቲት ወር 2010 ዓ.ም. ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አጠቃላይ የሞባይል ተጠቃሚዎች ቁጥር ብዙ ቢሆንም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር ግን ከአራት ሚሊዮን አይበልጥም፡፡ ይሁንና እያደገ በመጣው የተጠቃሚዎች ዕድገት በመሳብ ግለሰቦችም ሆኑ የመንግሥትና የግል ተቋማት ማኅበራዊ ሚዲያ ወደ መጠቀም አዘንብለዋል፡፡ በዚህም በአነስተኛ ወጪ መረጃዎችን ለበርካቶች ተደራሽ ያደርጋሉ፡፡
በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ከሚውሉ የማኅበራዊ ሚዲያዎች በቀዳሚነት የሚነሳው ፌስቡክ ሲሆን፣ 93.7 በመቶ የሚሆነው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ የፌስቡክ ተጠቃሚ ነው፡፡ በመቀጠል ዩቲዩብ፣ ፒንተረስት፣ ትዊተር፣ ጉግል ፕላስና ሊንክደን ይከተላሉ፡፡
በዓለም እንደሚታየው ሁሉ የማኅበራዊ ሚዲያው በሁለት ወገን የተሳለ ሰይፍ በኢትዮጵያም ራሱን እየገለጠ ነው፡፡ ማኅበራዊ ሚዲያን ሥራቸውን ለማስተዋወቅ፣ ጠቃሚ ማረጃዎችን ለማቀበል፣ ለማዝናናት፣ አገራቸውንና አካባቢያቸውን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙበት እንዳሉ ሁሉ፣ የጥላቻ መልዕክቶችን ለማሠራጨት፣ #ዘረኝነትን ለመስበክ፣ ሃይማኖትና ብሔርን #ለማንቋሸሽ፣ #ለመሳደብና #ለፀብ ለማነሳሳት የሚጠቀሙበት ትንሽ አይደሉም፡፡ ፌስቡክና የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚሰጡትን ሐሳብን ያለገደብ የመግለጽ መብት በመጠቀም፣ የአንድ ወገን በደሎችን ብቻ የሚያጎሉ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ሳይታክቱ የሚሠሩ በርካቶች ናቸው፡፡
በርካታ ተከታዮች ኖረዋቸው ለእነዚህ ተከታዮቻቸው ለፀብ የሚያነሳሱ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች፣ እነዚህ መልዕክቶቻቸው የሚያደርሷቸው ጥፋቶች እነርሱ ላይ ጉዳት ስለማያስከትሉ ሰዎች እየሞቱ፣ ንብረቶች እየወደሙና በርካቶች ከቀዬአቸው እየተፈናቀሉ በምቾት የጥፋት ሥራዎቻቸውን ያከናውናሉ፡፡
ይኼንን በማድረጋቸውም ለማኅበረሰብ መብት ተቆርቋሪ ተደርገው ይቆጠራሉ፣ የነፃ አውጪነትን ማዕረግን ይሸለማሉ፡፡ ይህ በተለይ የፖለቲካ አክቲቪስት ነን በማለት ጎራ ለይተው የቃላት ጦርነት እያደረጉ፣ በአካል ጦርነቶችን በማነሳሳት የሚሠሩ የማኅበራዊ ድረ ገጾች ተጠቃሚዎች ላይ በጉልህ ይታያል፡፡ በአንዱ ጎራ የእኔ ብሔር ተጠቃ አጥቂውም የእገሌ ብሔር ነው እያሉ ጣት ሲቀሳሰሩ፣ ለበርካታ ዓመታት ተዋልዶና ተፋቅሮ በኖረ ማኅበረሰብ ዘንድ ጠላትነትን ይዘራሉ፡፡ ይህ ድርጊት የማይናማር ቢን ላዲን የተባለን ግለሰብ በደቡብ ምሥራቅ እስያ እንደፈጠረ ሁሉ፣ ተመሳሳይ አዛሳኝ ታሪክ በኢትዮጵያ ሊደገም እንደማይቻል ምንም ማስተማመኛ እንደሌለ ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ከልማታቸው እኩል ለዴሞክራሲና እንደ መናገር ላሉ መርሆች ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ዕሙን እንደሆነ ባለሙያዎች ቢስማሙም፣ ከሰላም የሚበልጥ የለምና የሕዝቦችን አብሮ የመኖርና ሰላም የሚያደፈርስ ጉዳይ ከተከሰተ መላ ሊባልና ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚያስፈልግ ያትታሉ፡፡
የክፋት ዓላማ ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ባገኙት አጋጣሚ ፍርኃትን በመንዛት ከፍተኛ ጥፋት ለመፍጠር የሚችል የጥፋት ሠራዊት እንደሚገነቡ፣ ዴሞክራሲን ፈተና ላይ ሊጥሉ እንደሚችሉ የማኅበራዊ ሚዲያ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ክፉ ሐሳብ ያላቸው ተጠቃሚዎች ደግሞ የሕግ፣ የሥነ ምግባር ወይም የሞራል ተጠያቂነት ስለሌላቸው ያለ ገደብ የበላይነታቸውን ይዘው ሁሉንም ለግል ጥቅማቸው ሲሉ እንደሚያደርጉም ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ይህ ለኢትዮጵያም ሊሠራ የሚችል ነው፡፡
.
.
ክፍል 3 ይቀጥላል🔄

#update ደመራ ከማብራት ስነ ስርዓት ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ምንም አይነት የእሳት አደጋ #እንዳልተከሰተ የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላለከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ገልጿል።
©ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
©ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ETV Zena Live! የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ 12ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የመክፈቻ ስነ ስርዓት በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።
📌የድርጅቱ ጉባኤ ‹‹የለውጡ ቀጣይነት ለአማራ ህዝቦች ተጠቃሚነትና ዴሞክራሲያዊ አንድነት›› በሚል መሪ መልዕክት ነው የሚካሄደው።