TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NBE : ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፤ ባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ግብይት ይፋ አድርጓል።

ንግድ ባንኮች የአጭር ጊዜ ማለትም ለአንድ ቀን ወይም ለሰባት ቀናት መቆየት የሚችል ገንዘብ መበደርና ማበደር የሚችሉ መሆናቸውንም አብስሯል።

በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት መጀመሩ ፦

➡️ ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ጉድለትን በመሸፈን ወይም ትርፍ ገንዘብን ለሌሎች ባንኮች በማበደር የገንዘብ ፍሰትን በብቃት እንዲያስተዳደሩ ያስችላቸዋል።

➡️ የገንዘብ ግብይቱ የአጭር ጊዜ ማለትም የአንድ ቀን ወይንም የሰባት ቀናት የመክፈያ ጊዜ ያላቸው ብድሮችን ያካትታል ፤ ይህ ባንኮች የአጭር ጊዜ የገንዘብ ጉድለትን በመሸፈን ወይም ትርፍ ገንዘብን ለሌሎች ባንኮች በማበደር የገንዘብ ፍሰትን በብቃት እንዲያስተዳደሩ ያስችላቸዋል።

➡️ የገንዘብ እጥረት ስጋትን በመቀነስና በተረጋጋ የወለድ ተመን ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ሲል ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።


በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የግብይት መድረክ ላይ ብቻ እንዲሆ ብሔራዊ ባንክ ፈቅዷል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

#NBE

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኦርቶዶክስተዋሕዶ " ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው የጥቅምት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ…
#ቅዱስሲኖዶስ

" በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለም !! ... ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን የሰላም ጥሪ እናቀርባለን " - ቅዱስ ሲኖዶስ

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቋል።

ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።

የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ተሰጥቷል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ 

ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡ "


(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት)

/ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል /

@tikvahethiopia
ሕብር ሙዳይ የቁጠባ ሒሳብ

ሙዳይ ተቀማጭ ሒሳብ በአነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች የሚከፍቱት የቁጠባ ሒሳብ ሲሆን፤ አገልግሎቱ የቁጠባ ባህልን ለማዳበር አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቆጣቢዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ በመሆኑ ደንበኞችን ለማበረታታት በነፃ የገንዘብ ቁጠባ ሣጥኖች የሚሰጥበት የቁጠባ ሒሳብ ነው፡፡

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞  ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡
🤳 በቀላሉ አዳዲስ መረጃዎች  እንዲደርስዎ የቴሌግራም ገፃችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፡፡ https://t.iss.one/HibretBanket
🌐 ሌሎች የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን linktr.ee/Hibret.Bank ይጎብኙ፡፡

#HibirMudai #savings #financialwellness
🎁 ቴሌብር ሱፐርአፕ ይጠቀሙ፤ ተጨማሪ ስጦታዎችን ያግኙ!

🚀 ገና ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/uecbbr ሲጭኑ በ 100ሜ.ባ ስጦታ እንቀበልዎታለን!
💥 የመጀመሪያውን ግብይት ሲፈጽሙ ደግሞ የ15 ብር ስጦታ ይበረከትልዎታል!

በተጨማሪም በቴሌብር 100 ብር እና ከዚያ በላይ የሞባይል አየር ሰዓት ሲሞሉ 25%፣ ከ100 ብር በታች ሲሞሉ 15% እንዲሁም ጥቅል ሲገዙ 10% ተጨማሪ ስጦታ ያገኛሉ፡፡

▶️ ለተጨማሪ፡ https://youtu.be/l7sSDPhPig4 ይመልከቱ!

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኋላ ብቻ ባልመከኑ ተተኳሾች ከ51 በላይ ወገኖች ሲቀጠፉ ፤ ከ286 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ሰለባ ሆኗል " - በትግራይ ማእከላይ ዞን የየጭላ አበርገለ ወረዳ የፀጥታ ፅ/ቤት በትግራይ በነበረው አውዳሚ እና አሰቃቂ ጦርነት ወቅት ተቀብረው እና ተጥለው ያልመከኑ ተተኳሾች የንፁሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፍና አካል ማጉደል ቀጥለዋል። በየጭላ አሸርገለ ወረዳ የእምባ…
#ትግራይ

ያልመከነ ተተኳሽ ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወት ቀጠፈ።

ጥቅምት 21 /2017 ዓ.ም በትግራይ ማእከላይ ዞን አበረገለ ጭላ ወረዳ ስምረት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ዘገልዋ መንደር ውስጥ ባልመከነ ተተኳሽ  ሶስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸው ጠፍቷል።

ህይወታቸው የጠፋው ባል እና ሚስት ከ5 ዓመት ልጃቸው ጋር ነው።

የወረዳው ፓሊስ አከባቢው በትግራዩ ጦርነት ከባድ ውግያ የተካሄደበት ከመሆኑ  ጋር ተያይዞ ያልመከኑ ተተኳሾች አደጋ ሲያደርሱ ቆይቷል እያደረሱም ይገኛሉ ብሏል።

ፓሊስ እንዳለው ህይወቱ የተቀጠፈው ህፃን ወድቆ ያገኘውን ተተኳሽ ወደ ቤቱ ወስዶ ከእሳት በማነካካቱ ፈንድቶ ሦስቱ የቤተሰቡ አባላት ወድያውኑ ሞተዋል።

በወረዳው ከፕሪቶሪያ ስምምነት ወዲህ ብቻ ባልመከኑ ተተኳሾች የአሁኑን ጨምሮ ከ53 ሰዎች በላይ መሞታቸው ያስታወቀው የሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት በበኩሉ አሁንም የሚመለከተው አካል አከባቢው ካልመከኑ ተተኳሾች በማፅዳት ህዝቡ እንዲታደግ ተማጽኗል። 

መረጃው  ከወረዳው የህዝብ ግንኙነት ፅህፈት ቤት ነው የተገኘው። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
#ኮንታ

ዛሬ በኮንታ በደረሰ የመሬት መሸራተት አደጋ 6 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በቀበሌው ትናንት ምሽት የጣለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ ዛሬ ጠዋት 2 ሠዓት ላይ የመሬት መንሸራተት መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት ሲሆን ከአንደኛው ቤተሰብ አራት እንዲሁም ከሌላኛው ቤተሰብ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

መረጃው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

@tikvahethiopia
#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል ፣ ሰሜን ሸዋ ዞን ወጫሌ ወረዳ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

ዛሬ ጥዋት ወጫሌ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩን ጨምሮ በርካቶች ነው የተገደሉት።

የወጫሌ ወረዳ አጎራባች ይሆነው አለልቱ ወረዳ ፥ የቀድሞው የወረዳው አሁን ደግሞ የወጫሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጉሴ ኮሩ መገደላቸውን አረጋግጧል።

ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡ አንዲት ነዋሪው " የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ ብዙዎች ህይወታቸው አልፏል። የጉዳቱ መጠን እስካሁን የተጣራ አይመስለኝም " ብለዋል።

ጉዳት የደረሰባቸው ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷል።

የወረዳው ዋና ከተማ ሙከጡሪ ከአዲስ አበባ 82 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተቀራረቦ እንደመነጋገር የመሰለ ነገር የለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ምሽት ብዙዎችን ያነጋገር መልእክትና ፎቶ በይፋዊና በተረጋገጠ የX ገጻቸው ላይ አጋርተዋል። ፎቶው ከደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ጋር አብረው ያሉበት ነው። አቶ ጌታቸው ፤ " ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም ለመቀራረቡ እኛ እንቀርባለን ብላችሁ እኛን ለማገናኘት…
ፎቶ ፦ የህወሓት አመራሮች ዛሬ በመቐለ ከተማ ፊት ለፊት ተገናኝተዋል።

የፊት ለፊት ግንኙነቱ በክልሉ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች የተመራ ነበር።

ጥዋት በመቐለ ኖርዘርን ስታር ሆቴል አዳራሽ  የነበረው የፊት ለፊት ውይይት ግማሽ ቀን የፈጀ እንደነበር ታውቋል።

የሃይማኖት አባቶቹ ፥ " ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ ባቀረብናላቸው ጥሪ መሰረት ተገናኝተው ችግራቸውን በፓለቲካዊ እና በህጋዊ አሰራር እንፈታለን ብለውናል " ሲሉ አብስረዋል።

ሁለቱ ቡድኖች በመወከልና በመምራት በፊት ለፊት ውይይቱ የተገኙት ጌታቸው ረዳ እና ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ለሚድያ የሰጡት መግለጫ የለም።

አቶ ጌታቸው ረዳ እና ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ከቀናት በፊት ተገናኝተው አብረው የተነሱትን ፎቶ አቶ ጌታቸው በ X ገጻቸው ላይ አጋርተው መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia