TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MesiratEthiopia

🌟 በቅርቡ መውሰድ ያለባችሁ ስልጠናዎች 🌟
የግል በጀት አወጣጥ መሠረታዊ ነገሮች (Basics of Personal Budgeting) 👇
📅 መስከረም 10, 2017 ዓ.ም
🕒 ከቀኑ 8:00 እስከ 11:00 ሰዓት
🔗 Register Here: https://forms.gle/t2KczdEpPrNstvjz5

መሠረታዊ መብቶች (Fundamental Rights) 👇
📅 መስከረም 15, 2017 ዓ.ም
🕒 ከቀኑ 8:00 እስከ 11:00 ሰዓት
🔗 Register Here: https://forms.gle/Vk2Yd44t8Cnba6Jm6

የንድፍ አስተሳሰብ (Design Thinking) 👇
📅 መስከረም 20, 2017 ዓ.ም
🕒 ከቀኑ 8:00 እስከ 11:00 ሰዓት
🔗 Register Here: https://forms.gle/6aurE6Q8nAZQdNz18
ይህ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ!
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት🚨 ዛሬም ድረስ የሰው ህይወት የሚቀጠፍባቸው የመስቃን እና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች " በፈጣሪ ስም መፍትሄ ይፈለግልን ፤ ተሰቃየን ህይወታችን በሰቀቀን መግፋት ደከመን " ሲሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርበዋል። " ተደጋጋሚ እርቅ ይፈጸማል ግን ሳይቆይ ያገረሽና ደም ይፈሳል፣ ሰው ይገደላል የምንገባበት አጣን ድምጻችን ይሰማ " ብለዋል። ከሰሞኑን በመስቃን እና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች…
🔈 #የነዋሪዎችድምፅ

በመስቃንና ማረቆ እየሆነ ያለው ምንድን ነው ?

በማረቆ እና መስቃን መካከል ለዓመታት በሚስተዋለው ግጭት ግድያና መፈናቀል ሊቆም እንዳልቻለ ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

አሁንም ከፍተኛ የሆነ የበቀል ሥሜት ስላለ ሥጋት እንዳለባቸው ገልጸው፣ የሚመለከታቸው ባለድረሻ አካላት ለጉዳዩ እልባት እንዲሰጡት ጠይቀዋል፡፡

የማረቆ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ምን አሉ ?

“ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በምሽት ንፁሃንን ይገድላሉ። ከሳምንት በፊትም ግድያ ነበር። በጣም ግራ የሚያጋባ ወቅት ነው፡፡

መገደሉ፣ መፈናቀሉ እየተለመደ መጣ፡፡ ምን እናድርግ ?

ነገሩ ለረጅም ጊዜ ትክክለኛ መፍትሄ ሳያገኝ የግጭት ቀጠና በመሆኑ ጉዳዩ እያሳሰበው ግማሹ የአይምሮ እና ለተለያዩ የህመም አይነቶች እየተዳረገ ይገኛል፡፡

የችግሩ ምንጭ የማረቆ ህዝብ የጠየቀው የ9 ቀበሌ የማካለል ጉዳይ ነው፡፡

ጥያቄው ለብዙ አመታት ሲሆን፣ በዚህ ረጅም ዓመት በህግ አግባብ ከክልል ምክር ቤት እስከ ፌደሬሽን ሲጠየቅ ቆይቷል፡፡

ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ግን ከአምስት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡

ለዚህ ግጭት ዋና ተጠያቂ ተብለው የሚወሰዱት ከጉራጌ ዞን እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮችና የጸጥታ አካላት ናቸው።

በምሽት በሀሰተኛ ጥቆማና ጥርጣሬ ወጣቱን እያሳደዱት ስለሆነ ነገሩ ትኩረት ያስፈልገዋል ” ብለዋል፡፡

የምሥራቅ መስቃን ነዋሪዎች በበኩላቸው ፥ ከማረቆ ተፈናቅለው ወደ መስቃን የመጡ ወገኖች እንዳሉ ገልጸው፣ ችግሩ ያለው ሰላም ከማይፈልጉ ኃላፊነት ላይ ያሉ አካላት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ግድያም በተለያየ ጊዜ እንደሚፈጸም ጠቁመዋል።

“ በማረቆ ተወላጆች ከስምንት በላይ ቀበሌዎች ተወስደውብናል ” የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ ለዚህ ድርጊትም ኃላፊነት ላይ ያሉ አካላትን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

አንድ ስለጉዳዩ ያጫወቱን በምሥራቅ መስቃን የሚገኙ የእድሜ ባለጸጋ፣ “ ሁለቱ ብሔረሰቦች ተስማምተው መኖር እንዳይችሉ እያደረጉ ያሉት የፖለቲካ ትርፍ የሚፈልጉ አካላት ናቸው ” ብለዋል፡፡

በሁለቱ ወረዳዎች መካከል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር የተከሰተው በ2010 ዓ/ም ሲሆን፣ በ2014 ዓ/ም እርቀ ሰላም እንዲወርድ ተደርጎ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ ከእርቀ ሰላሙ ወዲህም ችግር አገርሽቶ በየጊዜው ሞትና መፈናቀሉ ሊቆም አልቻለም፡፡

የሚመለከታቸው አካላት ምን እየሰሩ እንደሆነ ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አልተሳካም፡፡ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆኑ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዕለታዊ ዛሬ ንግድ ባንክ የዶላር መግዣ ላይ ጭማሪ በማድረግ ወደ 108 ብር ከ0728 ሳንቲም አስገብቷል። መሸጫው 119 ብር ከ9608 ሳንቲም ነው። በአቢሲኒያ ባንክ አንዱ ዶላር 108 ብር ከ0729 ሳንቲም መግዣ ፤ 121 ብር ከ0416 ሳንቲም መሸጫ ተቆርጦላታል። በወጋገን ባንክ የዶላር መግዣው 115 ብር ከ0121 ሳንቲም ነው። አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ደግሞ አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ107…
#ዶላር

የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ከፍ ያለ ጭማሪ አሳይቷል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ7 ቀናት ጭማሪ ያልታየበት ወጥ የምንዛሬ ዋጋ ነበር።

ባንኩ ዛሬ ሲያገበያይበት የነበረው የምንዛሬ ዋጋ ከፍ ያለ ጭማሪ የታየበት ነበር።

አንዱ የአሜሪካ ዶላር መግዣው ወደ 112 ብር ከ3957 ሳንቲም ደርሷል።

የመጫው ዋጋም 124 ብር ከ7592 ሳንቲም ገብቷል።

በፓውንድ ላይም ጭማሪ ተመዝግቧል።

አንዱ ፓውንድ መግዣው 141 ብር ከ6314 ሳንቲም ተቆርጦለት ውሏል። መሸጫው 157 ብር ከ9487 ሳንቲም ነበር።

ዩሮ መግዣው 125 ብር ከ0177 ሳንቲም መሸጫው 138 ብር ከ7697 ሳንቲም ሆኖ ውሏል።

የUAE ድርሃም መግዣው 30 ብር ከ6030 ሳንቲም መሸጫው 33 ብር ከ9693 ሳንቲም ገብቷል።

#Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የመመዝገቢያ ቀናት ከጳጉሜ 5/2016 ዓ.ም - መስከረም 8/2017 ዓ.ም ድረስ ነው " - የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንጋፋዉ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ /ም  ለቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች ለመቀበል መዘጋጀቱን አሳውቆናል። ዩኒቨርሲቲው ለ2017 ቅድመ ምረቃ ትምህርት በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል ከፍለዉ ለሚማሩ እንዲሁም በማታ በተከታታይ መርሃ ግብር…
#AAU

ራስ ገዙ አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል በመጀመሪያ ዲግሪ በ2017 ዓ/ም መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎች ያቀረበው ጥሪ ነገ ያበቃል።

በ2017 ዓ/ም በቅድመ ምረቃ መደበኛ መርሃ ግብር በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  የተማሪዎች ምደባ እንደማይኖር  ይታወቃል።

በመንግስት ስኮላርሺፕ እንዲሁም በግል ከፍለው በዩኒቨርሲቲው መማር ለሚፈልጉ በሙሉ የአ.አ.ዩ  የሚያወጣውን የመግቢያ ፈተና (UAT) እንዲሁም ሌሎች መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲው ድረ ገጾች ፦
➡️ www.aau.edu.et
➡️ https://portal.aau.edu.et ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ ይችላሉ።

የመመዝገቢያ ቀኑ ነገ መስከረም 8/ 2017 ዓ.ም ያበቃል።

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት ወደፊት ይገለጻል።

በመንግስት ስኮላርሽፕ ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመማር የሚያያዘው ማስረጃ ምንድነው ?

በቀን መደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለማመልከት ከተጠየቁት መስፈርቶች አንዱ የቤተሰብ የገቢ መጠንን የሚገልፅ ማስረጃ ማያያዝ ነው።

በዚህ መሰረት ፦

1. ከወረዳ/ቀበሌ ወይም መስሪያ ቤት ስለገቢያቸዉ ዝቅተኛነት የሚገልፅ ማስረጃ ከሚመለከተዉ ከወረዳ ወይም ቀበሌ ወይም መስሪያ ቤት ዘርፍ ኃላፊ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

2. የቤተሰቡ ኃላፊ ጡረታ ላይ የሚገኙ መሆናቸዉን የሚገልፅ ደብዳቤ ወይም የታደሰ የጡረተኝነት መታወቂያ ወይም የባንክ ደብተር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

https://t.iss.one/TikvahUniversity/12317

(Addis Ababa University)

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በሀሰተኛ የብር ኖት ግብይት የፈፀሙ 2 ተጠርጣሪዎች እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ገብርኤል አካባቢ መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 12፡ 30 ሰዓት ላይ ነው።

ግለሰቦቹ ከአንድ ሸቀጣ ሸቀጥ መሸጫ እና ዘይት አከፋፋይ ከሆነ ሱቅ ውስጥ በርከት ያለ ባለ 20 ሊትር ዘይት ለመግዛት ተስማምተው ያስጭናሉ።

በኋላም ሒሳብ ሲከፍሉ ገንዘቡ ከባንክ እንደወጣና ህጋዊ ለማስመሰል አሽገው 42 ሺህ 350 ብር ለነጋዴው ይከፍሉታል፡፡

ሆኖም የግል ተበዳይ ገንዘቡ ሀሰተኛ መሆኑን ተጠራጥሮ በአካባቢ ነዋሪዎች ትብብር እንዲያዙ አድርጓል።

ተጠርጣሪዎቹ የግል ተበዳይ መጠራጠሩን ሲረዱ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 30791 ተሽከርካሪ በመጠቀም ለማምለጥ ቢሞክሩም በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ሊያዙ ችለዋል።

ግብይት ሊፈፅሙበት ከነበረ 42 ሺህ 3 መቶ 50 ብር ውስጥ 39 ሺህ 4 መቶ ሃሰተኛ ብር እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተደረገ እንደሆነ ፖሊስ ገልጿል።

@tikvahethiopia
" በጣም አስቸጋሪ የሚባለውን መንገድ ተከትለን በእግር፥ በመኪና እና በሞተር ሳይክል ነው የወጣነው " - ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው

ለወራት በእስር ላይ ከቆዩ በኃላ ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው እና በላይ ማናዬ ወደ ሙያቸው መመለስ ስላልቻሉ ከአገር መሰደዳቸውን ተናገሩ።

ሁለቱ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ከአገር ለመውጣት ከነሐሴ 28፤ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለአስራ አንድ ቀናት መጓዛቸውን ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

እንዴት ከአገር ወጡ ?

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ፥ " በጣም አስቸጋሪ የሚባለውን መንገድ ተከትለን በእግር፥ በመኪና እና በሞተር ሳይክል ነው የወጣነው። የነበሩብን የጉዞ እገዳዎች እና ክትትሎች መደበኛውን የጉዞ መንገድ እንድንጠቀም አላስቻለንም። " ሲል ተናግሯል።

ሁለቱም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በጸጥታ ኃይሎች ከታሰሩ በኋላ አንድ ጊዜ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ነው ከእስር የተለቀቁት።

ከእስር ከተለቀቁ 3 ወራት ገደማ በኋላ ደግሞ አገር ጥለው ተሰድደዋል።

ከአገር ተሰዶ ለመውጣት ምክንያት ያሉት ምንድነው ?

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ፦

" ከእስር ስንወጣ ያናገሩን የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ሰዎች እና የፌደራል ፖሊስ አባል ከዚህ በኋላ የምናደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚከታተሉን ገልጸውልናል። ይህ የመጀመሪያ ምክንያት ነው።

ወደ ሙያችን መመለስ ስላልቻልን ያለውን ችግር እና አፈናም መስበር የምንችልበት አቅም ስለሌለን ከአገር ወጥተናል።

ያንን ማድረግ የምንችለበት ዕድል ልናገኝ የምንችለው ከሀገር ስንወጣ ነው፥ መጀመሪያ ሕይወታችንን ማትረፍ አለብን በሚል ነው። በመንግሥት በኩል ሊገድሉን የሚችሉበት ዕድል ነበራቸው በተደጋጋሚ በእስር ቤት ውስጥ የሚነግሩን ያንን ነው።

መውጣቱ ሕይወትን ለማትረፍ ያሰብነው ነው፤ ቀጥሎ ደግሞ በሙያችን ለመስራት ያስችለን ይሆናል ብለን የገመትነው ነው።

በሙያችን መስራት ነው ዕቅዳችን በሀገር ውስጥ ካሉ ችግሮች አንጻር ስንሰራ የነበረውን ስራ የማስቀጠል ፍላጎት ነው ያለን። "

መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF #Tigray በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም አለ። በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል። የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ…
#Tigray

" ... የቆየው አመራር በአካልና በስልክ ስልጣን ለማስረከብ ቢጠየቅም ፍቃደኛ መሆን አልቻለም  " -  አዲሱ የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተኽላይ ፍቓዱ 

በቅርብ በትግራይ ጊዜያዊ አስታዳደር የተሾሙት  የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተኽላይ ፍቓዱ " የቆየው አመራር በአካልና በስልክ ስልጣን ለማስረከብ ቢጠየቅም ፍቃደኛ መሆን አልቻለም " ሲሉ ተናገሩ።

ይህን ያሉት ከቢቢሲ ትግርኛ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ነው።

አቶ ተኽላይ ፥ በፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋዊ ደብዳቤ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ከተሾሙ ሁለት ሳምንት መቆጠሩን ተናግረዋን።

ነገር ግን የቆየው አስተዳደር በአካልም ሆነ በስልክ የስልጣን ርክክብ ለማደረግ ቢጠየቅም ፍቃደኛ መሆን አልቻለም።

" በመንግስት በጀት የመንግስት ተፃፃራሪ ሆኖ መቆም ሽፍትነት ነው " ያሉት አቶ ተኽላይ " ከዚህ በኋላ መንግስት ሕግና ስርዓት ለማስከበር ይገደዳል " በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡

በቅርቡ የተከሰተው የህወሓት መሰነጣጠቅ ተክትሎ በየቀኑ አዳዲስ ክስተቶች በመታየት ላይ ይገኛሉ።

(ለማስታወስ)

በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው ተተኪ የሚባሉ 16 የማእከላዊ ኮሚቴ  አባላት ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ያልሰጡትን 14ኛው ጉባኤ አካሂደዋል፡፡

14ኛው ድርጅታዊ ጉባኤው ህጋዊ አይደለም ያሉት ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በጉባኤው የስራ አሰፈፃሚ አድርጎ የመረጣቸው የደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ሊያ ካሳና የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተኽላይ ገ/መድህን ምትክ አዳዲስ የዞን አስተዳዳሪዎች ሹመዋል፡፡

የዶ/ር ደብረፅዮኑ ህወሓት መስከረም 6 /2017 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ 14ኛ ጉባኤው ያልተሳተፉት የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙባቸው 16 የማእከላይ ኮሚቴ  አባላት ከአባልነትና ከድርጅታዊ የስራ ሃላፊነታቸው ማባረሩን አሳውቋል።

የእነ ዶክተር ደብረፅዮኑ ህወሓት " ከአባልነትና ከድርጅት ሃላፊነት አባርሪያቸዋለሁ " ብሎ መግለጫ ካወጣባቸው 16 የድርጅቱ የማእከላይ ኮሚቴ 5 አሁንም በጊዚያዊ አስተዳደሩ እውቅናና ተቀባይነት ያላቸው የትግራይ ደቡባዊ ፣ ደቡባዊ ምስራቅ ፣ ምስራቅ ፣ ማእከላዊ ፣ ሰሜናዊ ምዕራብና የምዕራብ ዞኖች ዋና አስተዳዳሪዎች ናቸው፡፡

በእነ ዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው ህወሓት በቅርቡ ባካሄደው ጉባኤ የማእከላይ ኮሚቴ አመራር በመሆን ከተመረጡት መካከል ይትባረክ ኣማሃና ኤልያስ ካሕሳይ የመቐለ ከተማ ዋናና ምክትል በመሆን በማስተዳደር ላይ ይገኛሉ በሃላፊነት ይቀጥሉ ይሆን ? በቀጣይ የምናየው ይሆናል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በፕሮፌሰር በየነ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። ፕሮፌሰር በየነ ረዘም ላለ ጊዜ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውንም ጠቁመዋል። " በኢትዮዽያ ገንቢ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ምልክት ነበሩ " ሲሉም ገልጸዋል።  @tikvahethiopia
#ProfessorBeyenePetros

" ከጠዋቱ 2 ሰዓት በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ የለቅሶ እና ሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል " - ሀድያ ዞን

የጉምቱው ፖለቲከኛ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ስርዓተ ቀብር ነገ ይፈጸማል።

የፕሮፌሰሩ አስክሬን በህክምና ሲረዱ ከቆዩበት ኬንያ ናይሮቢ ትላንት ምሽት ነው አዲስ አበባ የገባው።

የቀብር ስርዓቱን ለማስፈጸም የተቋቋመ አብይ ኮሚቴ ሊኢብኮ በሰጠው ቃል ፤ የፕሮፌሰሩ ስርዓተ ቀብር በአዲስ አበባ ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የሙያ ባልደረቦቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም አሳውቋል።

በሌላ በኩል በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ነገ ሐሙስ ከጠዋቱ 2 ሰዓት በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ የለቅሶ እና ሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል።

መላው የዞኑ ነዋሪ ሕዝብ  በተገለፀው ሰዓት እና ቦታ በመገኘት በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን እንዲገልጽ ጥሪ ቀርቧል።

ፕሮፌሰር በየነ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ዕንቁ ምሁራን መካከል ከቀዳሚቹ ተርታ ይጠቀሳሉ። ከዚህ ባለፈ በሀገሪቱ የፖለቲካ ውስጥ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት ነበሩ፡፡

ነፍስ ይማር !

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ጉቦ በመቀበል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ሰራተኞቹ የግብር መጠንን በመቀነስ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ጉቦ በመቀበል ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ መርማሪ ያቀረበውን የጥርጣሬ መነሻንና የተጠርጣሪ ጠበቃ መከራከሪያ ነጥቦችን ተመልክቷል።

ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው የታዩት ተጠርጣሪዎች ፦

የአ/አ ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ ሃብታሙ ግዲሳ፣

የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር ስምረት ገ/እግዚአብሔር፣

የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር ዮሴፍ ባቡ፣

የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር አቤኔዘር ቶሎሳ፣

ከፍተኛ ግብር ከፋይ የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር ለሚ ሲሌ

ገንዘብ ተቀባይ ባለሙያ ወ/ሮ መቅደስ አረጋዊ ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ የተሰጣቸውን የስራ ኃላፊነትን ወደ ጎን በመተው ከግብር ከፋይ ግለሰቦች ጋር በጥቅም በመመሳጠር ከግብር ከፋይ ድርጅቶች " ግብር እንቀንስላችኋለን " በማለት በመደራደር ከ100 ሚሊየን ብር የግብር መጠንን ወደ 13 ሚሊየን ብር ዝቅ በማድረግ ግብርን በመቀነስ ከተለያዩ ድርጅቶች በተለያዩ መጠኖች ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ጉቦ ተቀብለዋል በማለት መርማሪ ፖሊስ የጥርጣሬ መነሻውን ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አቅርቧል።

መርማሪ ፖሊስ በባንክ ሂሳባቸው የጉቦ ገንዘብ ገቢ የተደረገላቸው ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን የሚያሳይ ማስረጃ መሰብሰቡን በማመላከት ተጨማሪ ግብረ አበር ለመያዝና ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ማስረጃዎች አሰባስቦ ለመቅረብ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ በበኩሏ ደንበኞቿ በመርማሪ ፖሊስ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት " አልፈጸሙም " በማለት በመከራከር የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቃለች።

መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ቢወጡ ማስረጃ ሊያሸሹ ይችላሉ በማለት በጠበቃቸው የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ እንዲደረግ በመጠየቅ ተከራክሯል።

የፖሊስ የጥርጣሬ መነሻን እና ግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የምርመራ መዝገቡ ጅምር በመሆኑ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ለፖሊስ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን በማመን የተጠርጣሪ የዋስትና ጥያቄን በማለፍ ለፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

መረጃው የኤፍ ቢ ሲ ነው።

@tikvahethiopia