TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የነዋሪዎችድምፅ

“ በጣም አንገብጋቢ የሆነው የጤና ችግር ነው፡፡ ሆስፒታል ስለሌለ እናቶች ሪፈር ሲባሉ ደም እየፈሰሳቸው መንገድ ላይ ይሞታሉ ” - ነዋሪዎች

በአማራ ክልል፣ በሰሜን ጎንደር ዞን የበየዳ ወረዳ ነዋሪዎች፣ “ በክልሉ በሚካሄደው የተኩስ ልውውጥ ከሚደርስብን ግፉ በተጨማሪ የጤና፣ የመብራት፣ የትራንስፖርትና የኔቶርክ አገልግሎት ባለመኖራቸው በከፋ ስቃይ ውሰጥ ነን ” ሲሉ አማረዋል፡፡

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ የወረዳው ነዋሪዎች፤ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጡ ባለድርሻ አካላትን በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ እንዳላገኙ፣ በመጨረሻም በሚዲያ በኩል ምሬታቸው ለማሰማት እንደተገደዱ አስረድተዋል፡፡

ስለተማረሩባቸው ጉዳዮች ነዋሪዎቹ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ በበየዳ ወረዳ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ናቸው ያሉት፡፡ በጣም አንገብጋቢ የሆነው የጤና ችግር ነው፡፡ በወረዳው ሆስፒታል ስለሌለ እናቶች ሪፈር ሲባሉ ደም እየፈሰሳቸው መንገድ ላይ ይሞታሉ፡፡

ይህ የሚሆነው ሆስፒታል ባለመኖሩ ከበየዳ ወደ ደባርቅ ሪፈር ሲባሉ ነው፡፡ ከወረዳው ወደ ዞኑ ለመሄድ መንገዱ ሩቅ ከመሆኑ መንገድ የሚወልዱ እናቶች አሉ፡፡ በወረዳው ጤና ጣቢያ ብቻ ነው ያለው።

ሌላው ደግሞ፣ በወረዳው መብራት የለም፡፡ በጀነሬተር ከቀኑ 2 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት፤ ከምሽቱ ከ12 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት ነው የሚሰራው፡፡ አሁን ደግሞ ከግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ጠፍቷል፡፡

ለአንድ ወር ብቻ በጀኔሬተር ይሰራል፡፡ ከዚያ በኋላ ለ4 ወራት ይጠፋል፡፡ አንድ ስልክ አንድ ጊዜ ብቻ ቻርጅ ለማድረግ 25 ብር እንከፍላለን፡፡ በጣም ስቃይ ላይ ነን፡፡ በጨለማ ውስጥ እያደርን ነው፡፡

የትራንስፖርት ችግርም አለብን፡፡ ከወረዳው እስከ ደባርቅ ለ60 ኪ.ሜ መንገድ 350 ብር ለመክፈል እንገደዳለን፡፡ ይህ ክፍያ ለአንድ ጉዞ ብቻ ነው፡፡ ታሪፍ የለውም፤ እንደፈለጉ ነው ህዝቡን የሚበዘብዙት፡፡

ሁለት አውቶብሶች ብቻ ናቸው ያሉት፡፡ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ቁጥር ደግሞ ብዙ ነው፡፡ የተሳፋሪ ወንበር ለማግኘት ለደላላ 50 ብር መክፈል ግድ ይላል፡፡

ለዚያውም ከ50 በላይ ሰዎችን መያዝ በማይችል ተሽከርካሪ እስከ 90 ተሳፋሪዎችን አጭቀው በመጫን ነው፡፡ በዚህም ህፃናት፣ ነብሰ ጡሮች፣ አረጋዊያን እንኳ ተጨፍለቀው ነው የሚጓዙት፡፡ በጣም ይሰቃያሉ፡፡

እንዲሁም ከድል ይብዛና ልዋሬ መካከል ያለው መንገድ 27.3 ኪ.ሜ ነው፡፡ ለዚህም ነዋሪዎች ለትራንስፖርት ከ200 - 250 ብር ይጠየቃሉ፡፡ በዚህ ልክ በደል እየደረሰብን መሆኑ በጣም ያሳዝናል፡፡

በሌላ በኩል፣ በወረዳው ወደ ከ25 ቀበሌዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በ18 ቀበሌዎች የኔትወርክ አግልግሎት የለም፡፡ እኛ የበየዳ ነዋሪዎች ግን እንደ ማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ግብር እየከፈልን፣ መሰረተ ልማት እያለማን ነው፡፡ ሆኖም መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠቱ በጣም አሳዝኖናል፡፡

ባለድርሻ አካላትን ስንጠይቅም መልስ እንኳን በአግባቡ አይሰጡንም፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ፈጣን ምላሽ የማይጠን ከሆነ ወደ ሌላ አቅጣጫ ለማምራት እንገደዳለን፡፡ ነገሩ ወደ መጥፎ ሁኔታ ከማምራቱ በፊት ለችግሩ በአፋጣኝ ምላሽ ይሰጠን፡፡

የተከበረው የኢትዮጵያ ህዝብ በደላችንን፤ ብሶታችን ይወቅልን ”
ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቲክቫህም፤ ለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጥ ወደ ሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ተደጋጋሚ ሙከራ ቢደረግም፣ ስልክ ለማንሳትም ሆነ መልዕክት ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡

አስተዳዳሩ ለሚያስተዳድረው ህዝብ ቅሬታ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ በመሆን ኃላፊነቱን የሚወጣ ከሆነ በድጋሚ የምንጠይቀው ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የህዝብድምጽ የአማራ ህዝብ አስተማማኝ ሰላምን ካጣ ዓመታት አልፈዋል። በየጊዜው የሚያገረሸው የተኩስ ልውውጥ የሰዎችን ህይወት መቅጠፉን ቀጥሏል። በክልሉ ያሉ ሲቪል ሰዎች በሰላም ወጥቶ መግባት ቅንጦት እንደሆነ ይናገራሉ። የኢኮኖሚውና የሰላም እንቅስቃሴውም ከሌሎች ክልሎች አንጻር እየተዳከመ ይገኛል። ከዚህ ቀደም የሀገርና የውጭ ቱሪስት የሚጎርፍባቸው አካባቢዎች ዛሬ ሰው አይታይባቸውም። በዚህ…
🔈 #የነዋሪዎችድምፅ

“ ግድያና እገታ የሚፈጸመው መሀል ከተማ ላይ ነው፡፡ ለዛውም ፖሊስ ጣቢያ ባለበት አጠገብ፡፡ ዛሬ ህዝቡ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቷል፡፡ ፖሊስና ሚሊሻ ወደ ህዝቡ ነው የተኮሰው ” - ነዋሪዎች

በአማራ ክልል፣ ጎንደር ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች በተለይ ከሦስት ወራት ወዲህ " በታጠቁ አካላት አማካኝነት ግድያ፣ እገታና ዝርፍያ " በመበራከቱ ሰቆቃ ላይ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ድርጊቱ የሚፈጸመው በከተማው ምንም አይነት የተኩስ ልውወጥ በማይደረግበትና አገር ሰላም በተባለበት ወቅት እንደሆነ፣ የጸጥታ አካላት ቅሬታው ከነዋሪዎቸ ቢቀርብላቸውም ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠታቸው ጥቃቱ እንደተባባሰ አስረድተዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ምን አሉ ?

- ኧረ የፍትህ ያለህ ! አገራችን ይሄው ሆነ፡፡ ታዲያ አገራችንን ትተን የት እንሂድ ? ሞትና እገታ በቃ እንደ ደና አደርክ ሁሌም የምንሰማው ቃል ሆነብን እኮ፡፡

- የታጠቁ አካላት ሌሊት የተኩስ ሩምታ ይከፍታሉ፡፡ የነዋሪዎችን ቤትም ሰብረው ይገባሉ፡፡ ከዚያ ሰዎቹን በማስፈራራት አግተው ይወስዳሉ፡፡ እንደገና ታጋቾቹን ለመልቀቅ እስከ 3 ሚሊዮን ብር ይጠይቃሉ፡፡ ገንዘቡ ተልኮም ታጋቾቹን ይገድሏቸዋል፡፡

- ሁሌም ሌሊት ላይ በጣም ይተኮሳል፡፡ እናም ተኩስ ከተሰማ የሆነ ሰው እየታገተ እንደሆነ ይታወቃል ከድርጊቱ መደጋገም ተነሳ፡፡

- የ ‘ፋኖ’ ታጣቂዎች በከተማው የሉም። ከተማው ላይ ያለው ሚሊሻ ነው፡፡ ፖሊሶች ራሱ ከተማ ላይ ሲንቀሳቀሱ አይታዩም፡፡

- ጎንደር ላይ ፋኖም፣ መከላከያም የለም፤ ስለዚህ ጦርነት የለም፡፡ እገታ፣ ግድያና ዝርፊያው የሚፈጸመው በከተማው ጦርነት እየተካሄደ ሆኖ እንኳ አይደለም፡፡

- እንዲህ የሚያደርጉትን አካላት ማንነት ሌሊት ስለሚመጡ በደንብ ማወቅ አይቻልም፡፡

- በየቀኑ በመኪና እየመጡ አጥር ዘለው ይገባሉ፡፡ ግቢ ከበው ሌሎች ሙሉ አባበሎቻቸውን አስገብተው ነዋሪዎቹን አግተው ይወስዳሉ፡፡ እንደዚህ መሆን ከጀመረ ሦስት ወራት አስቆጥሯል፡፡

- አጋቾቹ ገንዘብ ሲጠይቁ የታጋች ቤተሰብ በባንክ ነው ገንዘብ የሚልከው፡፡ በባንክ ነው የሚላክላቸው። ስለዚህ እነርሱን ማግኘት ለምን አልተሻለም ? ሙሉ መረጃው ባንክ ላይ አለ።

- የጸጥታ አካላት በቀበሌ ሰብስበውን ነበር፡፡ ሁሉም ሰዎች ‘ እናንተ የምታመጧቸው ሚሊሾች ናቸው እንዲህ የሚያደርጉን፡፡ ' ነው ያሉት።

- ትላንት ከሚሊሻ በተተኮሰ ጥይት አንድ ልጅ ተገድሏል፡፡

- ግድያና እገታ የሚፈጸመው መሀል ከተማ ላይ ነው፡፡ ለዛውም ፖሊስ ጣቢያ ባለበት አጠገብ፡፡ ዛሬ ህዝቡ ሰላመዊ ሰልፍ ሲወጣ ፖሊስና ሚሊሻ ወደ ህዝቡ ተኩሷል ፒያሳ ላይ። ሰዎችም ተጎድተዋል። ተገድለዋል።

- እንዲህ የሚያደረገው የነዋሪው ሥነ ልቦና እንዲጎዳ፣ ተስፋ እንዲቆርጥ ነው፡፡ ፍላጎታቸው ገንዘብ ብቻ አይደለም፤ ምክንያቱም ገንዘብ ከተላከ በኋላም ታጋቾቹን ይገድሏቸዋል፡፡

- ጡት እንኳን ጠብታ ያልጨረሰች ኖላዊት የተባለች ህፃን ልጅ በአጋቾች ታግታ አጋቾቹ 1 ሚሊዮን ተጠየቀባት ፤ አቅም የለንም ሲሉ 500 ሺህ አደረጉ ከዛ  200 ሺህ ብር ከተቀበሉ በኃላገድለዋት አስክሬኗን በር ላይ ጥለዋል። ለማን እንጩህ ፤ የት እንሂድ ?

- በቅርቡ ደግሞ እናት እና ልጅን ለማፈን ብለው ለሊት ቢመጡም አልመች ስላላቸው ገለዋቸው ሂደዋል። የፍትህ ያለህ።

- ባለሃብቱ ከከተማው እየወጣ ነው ፤ ሌላውም ይህን ሽሽት በቻለው አቅም ወደ አዲስ አበባ እየገባ ነው። እዚህ የቀረው መሄጃ ቢያጣ ነው።

- ባለሀብቱ እየወጣ ሲያስቸግራቸው አጋቾቹ ያገኙትን አፍነው ለምናቹ አምጡ ማለት ጀምረዋል። የሚጠይቁት 1 እስከ 3 ሚሊዮን ብር ነው ሚጠይቁ ደሀም ያዙ ሀብታም ይህን ነድ የሚጠይቁት።


ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ወደ ከተማው እና የክልሉ ጸጥታ አካላት ሙከራ ብናደርግም ስልክ ላመንሳት ፈቃደበኛ አልሆኑም፡፡

ምላሽ ከሰጡ በድጋሚ የምንጠይቃቸው ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት🚨 ዛሬም ድረስ የሰው ህይወት የሚቀጠፍባቸው የመስቃን እና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች " በፈጣሪ ስም መፍትሄ ይፈለግልን ፤ ተሰቃየን ህይወታችን በሰቀቀን መግፋት ደከመን " ሲሉ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርበዋል። " ተደጋጋሚ እርቅ ይፈጸማል ግን ሳይቆይ ያገረሽና ደም ይፈሳል፣ ሰው ይገደላል የምንገባበት አጣን ድምጻችን ይሰማ " ብለዋል። ከሰሞኑን በመስቃን እና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች…
🔈 #የነዋሪዎችድምፅ

በመስቃንና ማረቆ እየሆነ ያለው ምንድን ነው ?

በማረቆ እና መስቃን መካከል ለዓመታት በሚስተዋለው ግጭት ግድያና መፈናቀል ሊቆም እንዳልቻለ ነዋሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

አሁንም ከፍተኛ የሆነ የበቀል ሥሜት ስላለ ሥጋት እንዳለባቸው ገልጸው፣ የሚመለከታቸው ባለድረሻ አካላት ለጉዳዩ እልባት እንዲሰጡት ጠይቀዋል፡፡

የማረቆ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች ምን አሉ ?

“ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በምሽት ንፁሃንን ይገድላሉ። ከሳምንት በፊትም ግድያ ነበር። በጣም ግራ የሚያጋባ ወቅት ነው፡፡

መገደሉ፣ መፈናቀሉ እየተለመደ መጣ፡፡ ምን እናድርግ ?

ነገሩ ለረጅም ጊዜ ትክክለኛ መፍትሄ ሳያገኝ የግጭት ቀጠና በመሆኑ ጉዳዩ እያሳሰበው ግማሹ የአይምሮ እና ለተለያዩ የህመም አይነቶች እየተዳረገ ይገኛል፡፡

የችግሩ ምንጭ የማረቆ ህዝብ የጠየቀው የ9 ቀበሌ የማካለል ጉዳይ ነው፡፡

ጥያቄው ለብዙ አመታት ሲሆን፣ በዚህ ረጅም ዓመት በህግ አግባብ ከክልል ምክር ቤት እስከ ፌደሬሽን ሲጠየቅ ቆይቷል፡፡

ግጭቱ ከተቀሰቀሰ ግን ከአምስት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡

ለዚህ ግጭት ዋና ተጠያቂ ተብለው የሚወሰዱት ከጉራጌ ዞን እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮችና የጸጥታ አካላት ናቸው።

በምሽት በሀሰተኛ ጥቆማና ጥርጣሬ ወጣቱን እያሳደዱት ስለሆነ ነገሩ ትኩረት ያስፈልገዋል ” ብለዋል፡፡

የምሥራቅ መስቃን ነዋሪዎች በበኩላቸው ፥ ከማረቆ ተፈናቅለው ወደ መስቃን የመጡ ወገኖች እንዳሉ ገልጸው፣ ችግሩ ያለው ሰላም ከማይፈልጉ ኃላፊነት ላይ ያሉ አካላት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ግድያም በተለያየ ጊዜ እንደሚፈጸም ጠቁመዋል።

“ በማረቆ ተወላጆች ከስምንት በላይ ቀበሌዎች ተወስደውብናል ” የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ ለዚህ ድርጊትም ኃላፊነት ላይ ያሉ አካላትን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡

አንድ ስለጉዳዩ ያጫወቱን በምሥራቅ መስቃን የሚገኙ የእድሜ ባለጸጋ፣ “ ሁለቱ ብሔረሰቦች ተስማምተው መኖር እንዳይችሉ እያደረጉ ያሉት የፖለቲካ ትርፍ የሚፈልጉ አካላት ናቸው ” ብለዋል፡፡

በሁለቱ ወረዳዎች መካከል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር የተከሰተው በ2010 ዓ/ም ሲሆን፣ በ2014 ዓ/ም እርቀ ሰላም እንዲወርድ ተደርጎ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ ከእርቀ ሰላሙ ወዲህም ችግር አገርሽቶ በየጊዜው ሞትና መፈናቀሉ ሊቆም አልቻለም፡፡

የሚመለከታቸው አካላት ምን እየሰሩ እንደሆነ ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አልተሳካም፡፡ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆኑ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የነዋሪዎችድምፅ

የሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ ህንጻ ቤቶች ባለቤቶች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር የነዋሪዎች ይዞታ መሆኑ እየታወቀ ለሶስተኛ ወገን ተላልፏል ያለው ይዞታ ጉዳይ ፍርድ ቤት ድረስ የደረሰ ነው።

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው ጉዳዩን የተከታተለው።

ከሳሽ ሆኖ የቀረበው ደግሞ ታሌሮ ኃ/የተ/የግል ማህበር ነው። ክስ ያቀረበው በሰንጋ ተራ የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች ኃ/የተ/ የህብረት ስራ ማህበር ላይ ነው።

ከሳሽ ያቀረበው ክስ ፥ ተከሳሾች በኃይል ገብተው የተሰጠኝን ከ600 ካ.ሜ በላይ የሆነ ቦታ ለመንጠቅ የብረት አጥር በማጠር ሁከትም ፈጥረዋል የሚል ነው።

" በሁከቱ ምክንያት ለደረሰብኝ ጉዳትና ኪሳራ ከነወለዱ ተከሳሾች እንዲተኩ ይወስንልኝ " የሚል ነው።

ከዚህ ጋር የሰነድ ማስረጃ አቅርቧል።

የሰንጋ ተራ የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች ኃ/የተ/ የህብረት ስራ ማህበር በበኩሉ ፦
-  ከሳሽ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ያቀረበበት ይዞታ በእጃ አደርጎ ወይም በይዞታው ስር አድርጎ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሲያዝበት የነበረ ይዞታ አይደለም።
- ከሳሽ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ይዞታ ይዞት አያውቅም።
- ከሳሽ ባያያዙት ካርታ ላይ ከተረጋገጠው ይዞታ ውጭ የሆነ ይዞታ ነው። ይዞታው በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በክ/ከተማው መሬት ልማት ማኔጅመንት በኩል ካሳ ተከፍሎብት የሰንጋ ተራ የጋራ ህንፃ ነዋሪዎች ማህበር ይዞታነት የተካለለ ነው፡፡

ስለሆነም ከሳሽ በእጁ በማይገኝ ይዞታ የራሱ ባልሆነና በይዞታው ስር ባልነበረ ይዞታ ላይ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጿል።

ሌላው ከሳሽ የፕላን ስምምነት የተሰጠው አሁን ክርክር በተነሳበት ይዞታ ላይ ሳይሆን አስቀድሞ በነበረው ይዞታ ላይ እንደሆነ አመልክተዋል።

በከሳሽ ይዞታ በማስረጃነት ከተያያዘው ካርታ ላይ መረዳት እንደሚቻለው ባለ 7 ፎቅ ህንጻ የሰራው በ1685 ካ/ሜ ይዞታ ላይ ነው  እንጂ በክሱ ላይ እንደተገለጸው በካርታ ከተያያዘው ይዞታ ውጭ ባለው 600 ካ/ሜ በላይ በሆነው ይዞታ ላይ አይደለም ብለዋል።

ክሳሽ የሁከት ይወገድ ክስ ያቀረበው በህጋዊ መንገድ ከያዘው ይዞታ ውጪ በሆነው በ600 ካ/ሜ ይዞታ ላይ ነው ይህም በእጁ አድርጎ የማያዝበት በመሆኑ ክሱ ተገቢነት የለውም ብለው ተከራክረዋል።

የሰንጋ ተራ የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች ኃ/የተ/ የህብረት ስራ ማህበር  ፦
° በከሳሽ ይዞታ ወስጥ በመግባት የሰራነው አጥር የለም፤
° ይዞታው የከሽ ስለመሆኑም የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ማስረጃም የለም።
° አጥር የሰራነውም በይዞታችን ስር አድርገን እየተጠቀምንበት ባለው ይዞታ እና ስልጣን ካው አካል የተሰጠንን የግንባታ ቦታ ፕላን እና የአጥር ግንባታ ፈቃድ በመያዝ በህጋዊ መንገድ ነው።
° በከሳሽ በኩል የቀረቡት ሰነዶች ለክርክሩ መነሻ በሆነው ይዞታ በ600 ካ.ሜ በላይ የሆነው ይዞታ ላይ ባለይዞታነቱን የሚያስረዱ ማስረጃዎች አይደሉም።
° ' ማስፋፊያ ጠይቄ ተስጥቶኛል ' ካለም አግባብ ባለው አካል የተሰጠው ለመሆኑ ሊያረጋግጥ የሚችል ማስረጃ ማቅረብ ሲገባው አላቀረበም።

ክሱ ውድቅ ይሁን ፤ በቂ ወጪና ኪሳራ እንዲከፈለን ሲሉ ጠይቀዋል።

የልደታ ክ/ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ጣልታ ገብቶ እንዲከራከር ይታዘዝልን በማለትም ለፍርድ ቤት አመልክተው ነበር።

ማህበሩ በማስረጃነት የሰነድ ማስረጃ እና የሰው ምስክር አቅርቧል።

ፍርድቤቱ የልደታ ክ/ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ጣልቃ ገብቶ እንዲከራክር በ29/10/13 ዓ.ም ላይ ትእዛዝ የሰጠ ቢሆንም ጣልቃገብ የሰጡት መልስ ባለመኖሩ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎ ክስ በሌሉበት ተሰምቷል።

ፍርድ ቤት በሁለቱም በኩል የቀረቡ ዶክመንቶችን ከተመላከተ በኃላ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል መጣራት አለበት በማለት የአዲስ አበባ የመሬት ይዞታ አስተዳደር ፅ/ቤት ከልደታ ክ/ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ግራ ቀኙ በተገኙበት ይዞታው በከሳሽ ስራ መሆን አለመሆኑን በማጣራት ምላሽ እንዲልክ አዟል።

በኃላም የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፥

" የቅየሳ መሳሪያ ይዘን በቦታው ላይ በአካል ተገኝተን ልኬት ልንወስድ ዝግጅት እያደረግን እያለ ከሳሽ ጥያቄያቸው በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በያዙት 1685 ካ.ሜ ይዞታቸው ላይ ሳይሆን በካርታ ከያዙት ውጭ ተጨማሪ የቦታ ማስፋፋት ጥያቄ መሆኑን በቃል ያስረዱን ሲሆን በዚህም ልኬት ሳናከናውን ተመልሰናል። ጥያቄያቸው አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሻ በመሆኑ ለሚመለከተው አካል አመልክተናል። " የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።

ፍ/ቤቱም በምላሽ የቀረበው የስነድ ማስረጃ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ይዞታ ከሳሽ በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በያዙት 1685 ካ.ሜ ይዞታቸው ላይ ሳይሆን በካርታ ከያዙት ውጭ ተጨማሪ የቦታ ማስፋፋት ጥያቄ መሆኑን እና አስተዳደራዊ ውሳኔ የሚሻ መሆኑን ያሳያል ብሏል።

በዚህም ምላሽ የሚያስረዳው ለክርክሩ መነሻ የሆነው ይዞታ የከሳሽ ይዞታ አለመሆኑን እንደሆነ በግልጽ አስቀምጧል።

ከሳሽ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ይዞታ በእጁ አድርጎ በእዉነት እያዘዘበት መሆኑ እና ይዞታዉን በህግ አግባብ ያገኘዉ መሆኑ በማስረጃ ያልተረጋገጠ በመሆኑ የከሳሽን ክስ ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም።

ውድቅም በማድረግ ወስኗል፡፡

ይህ ውሳኔ በተሰጠበት ሁኔታ ቆይቶ እና አረሳስቶ በሚመስል ሁኔታ ቦታው በፖሊስ ኃይል ታግዞ ታጥሯል።

የሰንጋ ተራ የጋራ ህንጻ ነዋሪዎች ኃ/የተ/ የህብረት ስራ ማህበር የማጠር ተግባሩና እየተፈጸመ ያለው ከህግ ውጭ የሚደረግ ድርጊት ይቁም በሚል ይመለከታቸው ያላቸው ቢሮችን ለማነጋገር ቢጥርም ሰሚ አላገኘም።

አሁንም ቦታው ታጥሮ ይገኛል።

(ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው የፍርድ ቤት ውሳኔና ሌሎች ዶክመንቶች ከላይ ተያይዘዋል)

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM