TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EOMMARKET

ውበትዎን እና ጤናዎን በቤትዎ ሁነው የሚጠብቁበት ድንቅ ማሳጀር - 
TENS S-780 Luxurious Massager

☎️ 0929181818 / 0909868788
ይምጡ የሽያጭ ማእከሎቻችንን ይጎብኙ፤ ተደስተው ይመለሳሉ !
https://t.iss.one/EOMMarket
አድራሻችን፦
• ቁጥር 1:- መገናኛ, ቤተልሄም ፕላዛ  የሱቅ
                 ቁጥር  G-10 ግራውንድ 
•ቁጥር 2:- ሜክሲኮ, ኬኬር ህንፃ የሱቅ  
                ቁጥር #338
•ቁጥር 3:- አያት አደባባይ , AAT CITY   
                  CENTER G-11 ግራውንድ
𝕵𝖔𝖎𝖓 𝖔𝖚𝖗 𝖈𝖍𝖆𝖓𝖓𝖊𝖑 https://t.iss.one/EOMMarket
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EOTC

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው ልዩ ስብሰባ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በተደራቢነት ተይዘው ለቆዩ ክፍት በኾኑና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ላይ የሚመደቡ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳትን ምርጫ አካሂዷል።

ለኦሮሚያ ክልል 7 አህጉረ ስብከት ፦

1. አባ ሣህለ ማርያም ቶላ - ምዕራብ አርሲ - (ሻሸመኔ) ሀገረ ስብከት
2. አባ ወልደ ገብርኤል አበበ - ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
3. አባ ጥላሁን ወርቁ - ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
4. አባ ዓምደ ሚካኤል ኀይሌ - ሆሮ ጉድሩ ወለጋ - ሻምቡ ሀገረ ስብከት
5. አባ ኀይለ ማርያም ጌታቸው - ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
6. አባ ዘተክለ ሃይማኖት ገብሬ - ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
7. አባ እስጢፋኖስ ገብሬ - ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

ለደቡብ ኢትዮጵያ 2 አህጉረ ስብከት ፦

8. አባ ክፍለ ገብርኤል ተክለ ሐዋርያት - ጌዴኦ አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት

9. አባ ስብሐት ለአብ ወልደ ማርያም - ዳውሮ እና ኮንታ ሀገረ ስብከት ሆነው መመረጣቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህ ተመራጮች መካከል 3ቱ በጥር 14ቱ ሕገወጥ " ሢመት " የተሳተፉ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ምስል ፦ የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@tikvahethiopia
" ቤተሰቦቼ ለእኔ ምንም ቦታ የላቸውም " በሚል ምክንያት ወላጅ አባቱንና ታላቅ ወንድሙን ቤንዚል በመርጨት በቁም ያቃጠላቸው ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ክብረ ደመና ሙሉ ወንጌል አካባቢ ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ተከሳሹ ግለሰብ ከዚህ ቀደም በሌላ ወንጀል ተከሶ ታስሮ የነበረና በፍርድ ቤት ዋስትና የተለቀቀ ሲሆን " ከእናቴ በስተቀር ለእኔ የሚያስብልኝ የለም " በሚል ምክንያት ከሳምንት በፊት በአንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር ቤንዚል በመግዛት አባቱና ታላቅ ወንድሙ የግል ጉዳያቸውን ፈፅመው በመምጣት ቤት ውስጥ ቁጭ ባሉበት እናትዬውን ውሃ አምጭልኝ ብሎ ከቤት መውጣታቸውን ጠብቆ ቤንዚሉን አርከፍክፎባቸው ክብሪት በመለኮስ ማምለጥ እንዳይችሉ በሩን ቆልፎ ለማምለጥ ሲል በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ተጎጂዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመተባበር ወደ ህክምና ቢወስዱም አባትዬው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ታላቅ ወንድሙ በህክምና ላይ ይገኛል።

በተከሳሹ ላይ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጿል።

በቤተሰብ መሀከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በንግግር መፍታት እየተቻለ የወንጀል ተግባር ለመፈፀም መቸኮል የራስንም የሌላውንም የወደፊት ህልም ማጨለም ነውና አለመግባባቶችን በንግግር መፍታት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር መሆኑን ፖሊስ አስገንዝቧል።

ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ከህግ ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችልም ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #NEBE የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በ1,812 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያስፈጸመውንና 849,896 መራጮች ድምፅ የሰጡበትን የወላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ  የውጤት ማዳመሩን ሥራ በዞኑ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሲያከናወን መቆየቱን ገልጿል። በዛሬውም ዕለት ቦርዱ የውጤት  የማመሳከሩንና የማዳመሩን ሥራ በማጠናቀቅ በዞን ደረጃ #የጊዜያዊ ውጤቱን ይፋ አድርጓል።…
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ፦

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል ለመደራጀት ያካሄዱትን የህዝበ ውሳኔ ውጤት በሙሉ ድምፅ አጸድቋል።

ይህም ማለት በኢትዮጵያ 12ኛው ክልል እንዲደራጃ ይሁንታ ሰጥቷል።

በዚህም መሠረት ፦

ላለፉት 30 ዓመታት ገደማ በደቡብ ክልል ሥር ሲተዳደሩ የቆዩት ፦
👉 የዎላይታ ፣
👉 የጋሞ ፣
👉 የጎፋ ፤
👉 የኮንሶ ፣
👉 የደቡብ ኦሞ ፣
👉 የጌዲኦ ዞኖች እንዲሁም
👉 የአማሮ ፣
👉 የቡርጂ ፣
👉 የደራሼ ፣
👉 የአሌ እና የባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች የፌዴራል ሪፐብሊኩ 12ኛ ክልል ሆነው " ደቡብ ኢትዮጵያ " በሚል እንዲደራጁ ምክር ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በሌላ በኩል ፦
👉 የሃድያ ፣
👉 የከንባታ ጠንባሮ ፣
👉 የሀላባ ፣
👉 የሥልጤ ፣
👉 የጉራጌ ዞኖችና እና የየም ልዩ ወረዳ ራሳቸውን መልሰው በማደራጀት #በነባሩ ክልል እንዲቀጥሉ ሲል ምክር ቤቱ ወስኗል።

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለማንኛውም አስተያየት፤ ጥያቄ ወይም ጥቆማ በባንካችን የደንበኞች አገልግሎት መስመር #8292 ላይ ይደውሉ!

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
" EBC የመንግሥት አፍ ያልሆነ መሆን አለበት " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ብሔራዊ የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያ የሆነው EBC " የመንግሥት አፋ ያልሆነ ፤ ለሚያራግቡ እና ለማያስጮሁ ሰዎችም መሳሪያ ያልሆነ መሆን አለበት " ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ የEBC የሚዲያ ኮምፕሌክስን መርቀው ሲከፍቱ ነው።

በዚህ ስነስርአት ላይ ንግግር ያደረጉት ጠ/ሚኒስትሩ ፤ " EBC ለመንግሥት ብቻ የሚያገለግል ሳይሆን ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርግ ሚዲያ እንደምታድረጉት ተስፋ ይደረጋል " ብለዋል።

" EBC ስፒከር አይደለም " ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ " የሚነገርን ድምፅን የሚያጎላ ሳይሆን ድምፅ የሚፈጥር መሆን አለበት ፤ በየቦታው ለማስጮህ ፌስቡክ አለ በቂ ነው ፤ ማስጮህ ሳይሆን የሚጮኸውን ነገር መፍጠር ነው የሚያስፈልገው " ሲሉ ተደምጠዋል።

" መንግሥት ሲያበላሽ ቆንጠጥ አድርጎ የሚጠይቅ ፤ የመንግስት አፍ ያልሆነ ፤ ለሚያራግቡ እና ለሚያስጮሁ ሰዎች መሳሪያ ያልሆነ ፤ የኢትዮጵያን ልዕልና ከፍ የሚያደርግ ፤ የኢትዮጵያን ፍላጎት ከፍ የሚያደርግ ተቋም መሆን አለበት " ብለዋል።

" EBC ከሰፈር ጨዋታ ወጥቶ በአፍሪካ ደረጃ የኢትዮጵያን ታሪክ ፤ የኢትዮጵያን ተፈጥሮ ሃብት ፤ ሊጎበኙ የሚገባቸውን ቦታዎች፣ ያሉትን የስራ እድሎች መግለጥ ይጠበቅበታል " ሲሉ አክለዋል።

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመረቁት ሸጎሌ አካባቢ የሚገኘው የሚዲያ ኮንፕሌክስ እጅግ በጣም ዘመን አፈራሽ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን ያሉት፣ ውስጣዊውም ሆነ ውጫዊ ገፅታ ለስራ እጅግ በጣም ምቹ የሆነ ነው።

ብሔራዊው የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያ EBC የመንግሥት እና የአንድ ፓርቲ ልሳን በመሆን እና የብዙሃንን ድምፅ ያፍናል በሚል የሚተቹት በርካቶች ናቸው።

የ " ኢህአዴግ " ለውጥ ተደርገ በታባለባቸው ጥቂት ወራት ውስጥ ጣቢያው በበርካቶች ዘንድ በሚዲያው ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ለውጥ እንደታየበት ሲገለፅ የቆየ ሲሆን በኃላ ላይ ግን የ " መንግሥት " እንዲሁም የአንድ የገዢ ፓርቲ ድምፅ በመሆንና " ድምፃችን ሊሰማ ይገባል " የሚሉ አካላትን ድምፅ ባለማስተላለፍ እንዲሁም የሚተላለፉ መልዕክቶችን በራሱ መንገድ ቀይሮ በማስተላለፍም ይወቀሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሸዋሮቢት

በሸዋሮቢት የተጣለው የሰዓት ገደብ ዛሬ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በተጣለው ገደብ መሰረት ከምሽቱ 12 ሰዓት አንስቶ ማንኛውም ሰውም ይሁን ተሽከርካሪ ከተማይቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ ማድረግ አይችልም።

በተጨማሪ ፤ አገልግሎት ሰጪዎች የምሽት መዝናኛ ቤቶችን ጨምሮ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

በሌላ በኩል ፥ ትላንት " ባልታወቁ ገዳዮች " የተገደለቱ የከተማው የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ተፈፅሟል።

ቅብራቸው የተፈፀመው በዛው ሸዋሮቢት በሚገኘው እንሰርቱ የሙስሊም መካነመቃብር ነው።

አቶ አብዱ የሁለት ወንድ እና የአንድ ሴት ልጆች አባት እንደነበሩ ተገልጿል።

ፎቶ ፦ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia