TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ExitExam

" የሚሰጠው ሞዴል ፈተና በጥያቄ ክብደቱም ሆነ በብዛቱ ከዋናው የመውጫ ፈተና ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ለሁሉም የግል እና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 29/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የሙከራ ፈተናው ከ168 ሺህ ለሚበልጡ ዕጩ ምሩቃን እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና በመስጠት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

የሙከራ ፈተናው ተማሪዎች የራሳቸውን መለያ ቁጥር እና የይለፍ ቃል ተጠቅመው በቀላሉ መፈተን እንዲችሉና ከፈተና ስርዓቱ ጋር እንዲተዋወቁ የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል።

ለሁሉም የግልና የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጥያቄ ክብደቱም ሆነ በብዛቱ ከዋናው የቅድመ ምረቃ መውጫ ፈተና ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሞዴል ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 29/2015 ዓ.ም በተመሳሳይ ጊዜ እንደሚሰጥም ኃላፊው ገልጸዋል።

የ2015 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም በተመሳሳይ ጊዜ በኦንላይን እንደሚሰጥ ይታወቃል።

Via @tikvahuniversity
" ምንም ጉዳይ ቢሆን ገንዘብ ፈጥኖ ከመስጠት ተቆጠቡ " - የአዲስ አበባ ፖሊስ

ሳትታገት " ታግቻለው " ብላ የፍቅር ጒደኛዋን 500 ሺህ ብር የጠየቀችው ተከሳሽ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ተጠርጣሪዋ ግለሰብ የማታለል ወንጀሉን የፈፀመችው በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ9 ጎሮ አይሲቲ አካባቢ ነው።

ግለሰቧ  ለቦታ መያዣ ተብለው ከተሰሩ የጎጆ ዳስ ውስጥ ታግቻለሁ በማለት የፍቅር ጒደኛዋን አምስት መቶ ሺህ ብር  እሱ በማያውቀው ስልክ መክፈል አለብሽ ተብያለሁ በማለት መልዕክት ስትልክለት እንደነበር  እና የግል ተበዳይ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መያዟ፤ የላከችው መልዕክትም ሃሰት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

ህብረተሰቡ መሰል የወንጀል ተግባር ሰለባ ላለመሆን ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እና ምንም ጉዳይ ቢሆን ገንዘቡን ፈጥኖ ከመስጠት በመቆጠብ ለአቅራቢያው ፖሊስ ጥቆማ ሊያደርግ እንደሚገባ መልዕክት ተላልፏል።

Via Addis Ababa Police

@tikvahethiopia
የአንድ ሰው ግድያ ፈረንሳይን በተቃውሞ እየናጣት ነው።

በፈረንሳይ ሀገር ፓሪስ አቅራቢያ ባለፈው ማክሰኞ ዕለት አንድ የ17 ዓመት ታዳጊ በፈረንሳይ ፖሊስ መገደሉን ከተትሎ ፈረንሳያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ።

ናሄል ኤም የተሰኘው ታዳጊ በቅርብ ርቀት በፖሊስ ተተኩሶበት የተገደለ ሲሆን ግድያው " የትራፊክ መብራት ጥሷል " በሚል የተፈፀመ መሆኑ ተነግሯል።

ግድያውን የፈፀመው የፖሊስ አባል ፤ ሽጉጡን የመዘዘው ሕይወቱ አደጋ ላይ እንዳለ ስለተሰማው እንደሆነ ተናግሯል።

የታዳጊውን ግድያ ተከትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ግን ሀገሪቱን እየናጣት ነው።

የታዳጊ መኖሪያ በሆነችው የፓሪስ አካባቢ የሚገኙ ባለሥልጣናት ሥፍራውን ለቀው ከወጡ ቀናት አልፈዋል።

በርካቶች ወደ አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን በዚህ መሃል ዝርፊያን ጨምሮ የአመፅ ተግባራት መፈፀማቸው ተመላክቷል።

ምንም እንኳን ታዳጊውን የገደለው የፖሊስ መኮንን ክስ ቢመሰረትም አመጹ በመላው አገሪቱ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።

- በሊል እና ማርሴ ከተሞች በርካታ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ለእሥር በቅተዋል።

- ናንቴር በተሰኘችው ታዳጊው በሚኖርባት ከተማ አንድ ባንክ ያለበት ሕንፃ በእሳት ተቃጥሏል።

- በማህበራዊ ሚዲያ በርካታ ሥፍራዎች በእሣት እየጋዩ ታይተዋል።

- በፓሪስና በሌሎች ከተማዎች የአውቶቡስና ባቡር ትራንስፖርት በሃገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽት 3 ሰዓት ጀምሮ ተቋርጧል።

- አንዳንድ ከተሞች ሰዎች ምሽት እንዳንይንቀሳቀሱ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥለዋል።

- የፈረንሳይ መንግሥት አመፁን ለመግታት 40 ሺህ የፖሊስ ሠራዊት በሃገሪቱ አሰማርቷል።

- ማክሰኞ እና ረቡዕ ምሽት በነበሩ ተቃውሞዎች በርካታ ተሽከርካሪዎችና ሕንፃዎች በእሳት ጋይተዋል።

- የሟች እናት ሐሙስ ዕለት የጠሩት ሰልፍ በርካታ ግጭቶችን አስከትሏል።

ማን ምን አለ ?

የፈረንሳይ የሃገር ውስጥ ሚኒስትሩ ዤራልድ ዳርማኒን ፥ " ረቡዕ ማታ 170 የፖሊስ መኮንኖች ጉዳት እንደደረሰባቸውና 180 ሰዎች በቁጥጥር ውለዋል። " ብለዋል።

የፈረንሳይ ጠ/ሚ ኤሊሳቤት ቦርን ፤  " በ17 ዓመቱ ታዳጊ ሞት የተነሳ የተፈጠረውን ስሜታዊነት እንረዳለን። " ያሉ ሲሆን " ግን ምንም ነገር ለአመፅ ምክንያት ሊሆን አይችልም። " ሲሉ ተናግረዋል።

የታጊው ናሄል ጠበቃ ያሲን ቦዝሩ በበኩላቸው ፤ " ሃገራችን የምትከተለው ሕግ የፖሊስ መኮንኖች የሚጠብቅ ነው። ይህ ደግሞ ያለመከሰስ ባሕልን ያዳብራል። " ሲሉ ተችተዋል።

ታዳጊውን የገደለው ፖሊስ ሽጉጡን የመዘዘው ሕይወቱ አደጋ ላይ እንዳለ ስለተሰማው እንደሆነ የተናገረ ሲሆን ጠበቃዎቹ ደንበኛቸው ድርጊቱን የፈፀመው " ሕጉን በተከተለ መንገድ ነው " ብለዋል።

#Video ከላይ የተያያዙት ቪድዮዎች የታዳጊውን ግድያ እሱን ተከትሎ በፈረንሳይ የተቀጣጠለውን ተቃውሞና አመፅ የሚያሳዩ ናቸው። (ከተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የተገኙ)

Credit : BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአንድ ሰው ግድያ ፈረንሳይን በተቃውሞ እየናጣት ነው። በፈረንሳይ ሀገር ፓሪስ አቅራቢያ ባለፈው ማክሰኞ ዕለት አንድ የ17 ዓመት ታዳጊ በፈረንሳይ ፖሊስ መገደሉን ከተትሎ ፈረንሳያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ። ናሄል ኤም የተሰኘው ታዳጊ በቅርብ ርቀት በፖሊስ ተተኩሶበት የተገደለ ሲሆን ግድያው " የትራፊክ መብራት ጥሷል " በሚል የተፈፀመ መሆኑ ተነግሯል። ግድያውን የፈፀመው የፖሊስ አባል ፤…
#France

በአንድ የፖሊስ አባል በተገደለ አንድ የ17 ዓመት ታዳጊ ሀገራቸው በከፍተኛ ተቃውሞና አመፅ ውስጥ የምትገኘው የፈረሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የውጭ ሀገር ስብሰባቸውን አቋርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ፕሬዜዳንቱ በብራስልስ የአውሮፓ ህብረት ጉባኤ እየታደሙ የነበረ ሲሆን በታዳጊው ግድያ ሀገሪቱ በተቃውሞ መናጧን ተከትሎ ስብሰባቸውን ጥለው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኃላ ከባለሥልጣኖቻቸው ጋር አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል።

ካሳለፏቸው ውሳኔዎች መካከልም ፤ አንዳንድ የሚከናወኑ ዝግጅቶች እንዲሰረዙ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ለዘረፋ የሚጠሩ ጥሪዎች ላይ ክትትል እንዲደርግ የሚሉት ይገኙበታል።

በተጨማሪ ፕሬዝዳንቱ ተቃውሞውን ለመቆጣጠር አሁን ከተሰማሩት 40 ሺህ የፀጥታ አካላት ተጨማሪ እንደሚሰማሩ አሳውቀዋል። ወላጆች ልጆቸውን ከጎዳና ላይ አመፅ እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

ፕሬዜዳንት ማክሮን ፤ " በአንዳንድ ሰፈሮች የአንድ ጎረምሳ ሞት ተቀባይነት በሌለው መልኩ ለሌላ ነገር ውሏል " ሲሉ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።

በፈረንሳይ የአንድ የ17 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ አባል መገደሉን ተከትሎ ለተከታታይ ቀናት በሀገሪቱ ብርቱ ተቃድሞ እና አመፅ እየተካሄደ ይገኛል። በተከሰተው አመፅ በተለያዩ ከተሞች በርካታ ተሽከርካሪዎች ጋይተዋል፣ ህንፃዎች ተቃጥለዋል፣ በፖሊስ እና በተቃውሞ አራማጆች ማካከል ግጭት ተፈጥሮ ሰዎች ተጎድተዋል፤ በርካቶችም ታስረዋል።

@tikvahethiopia
#ተጠንቀቁ

UNICEF 2,800 ሰራተኞችን ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል ?

UNICEF ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወረውን አይነት ምንም የቅጥር ማስታወቂያ #አላወጣም

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምትመለከቱት አይነት ሀሰተኛ የቅጥር ማስታወቂያ በስፋት እየተዘዋወረ ነው።

ማስታቂያው UNICEF በትግራይ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ለሚገኙ ዜጎች በ3 የስራ መደቦች የተመዘገቡ ሰራተኞችን አሰልጥኖ ለመቅጠር ይፈልጋል የሚል ነው።

በዚሁ ሀሰተኛ የቅጥር ጥሪ ፤ በባችለር ዲግሪ ፣ በማንኛውም ትምህርት መስክ ፣ በ0 ዓመት ፣ በ24,700 ብር ደመወዝ 2,800 ሰራተኞች እንደሚፈለጉ ይገልጻል።

በጣም የሚያስገርመው የስራው አመልካቾች የሚያመለክቱበት ሀሰተኛ አድራሻ የተቀመጠ ሲሆን በዚሁ አድራሻ ተመዝጋቢዎች የማመልከቻ ፎርም ሲሞሉ 1,000 ብር በCBE Birr ወይም በTelebirr ቀድመው እንዲከፍሉ ይጠይቃል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ይህ ፍፁም ሀሰተኛ እንዲሁም በርካታ ወጣቶችን ለማጭበርበር እየተደረገ ያለ እንቅስቃሴ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከUNICEF ተጨማሪ መረጃ ያገኘ ሲሆን በኦንላይን እየተሰራጨ ያለው ሀሰተኛ የቅጥር ማስታወቂያ መሆኑን ገልጿል።

UNICEF የስራ ዕድል የሚያስተዋውቀው በይፋዊ ድረገፁ unicef.org/careers/ ላይ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል። ከዚህም ባለፈ በየትኛውም የቅጥር ሂደት ገንዘብ እንደማያስከፍል እንዲሁም የባንክ መረጃን እንደማይጠይቅ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#BirhanBank

ለማንኛውም አስተያየት፤ ጥያቄ ወይም ጥቆማ በባንካችን የደንበኞች አገልግሎት መስመር #8292 ላይ ይደውሉ!

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc

እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
#MoE

ሀገር አቀፉ የ " ጤና ኢግዚቢሽን " በአዲስ አበባ ፤ በብሔራዊ ሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ይገኛል።

የጤና ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ በጤናው ዘርፍ በሚኒስቴሩ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች በሚኒስቴሩ በኩል የቀረቡ ሲሆን ሌሎች የግል እንዲሁም የመንግስት ተቋማትም በኤግዚቢሽኑ ተገኝተዋል።

ሰኔ 14 በተከፈተውና እስከ ሐምሌ 13 በሚቆየው በዚህ ኤግዚቢሽን ለህጻናትና ለተማሪዎች የሚሆኑ ዴስኮች፤ የኢትዮጵያ ባህላዊ ህክምናን የሚያስረዱ በተለያዩ እጸዋት ላይ የተደረጉ ምርምሮች ማሳያ፤ ስለ አጠቃላይ የሆስፒታል አገልግሎት እንዲሁም የዲጂታል የጤና ሥርዓቶች ላይ ማብራሪያ እንዲሁም ጉብኝት ማድረግ ይቻላል።

በተለይ በጤናው ዘርፍ ለተሰማሩ ፤ ወደፊት በጤና ትምህርት ውስጥ ማለፍ ለሚፈልጉና በትምህርት ላይ ለሚገኙ #ተማሪዎች እንዲሁም በሚኒስቴሩ ያሉ እንቅስቃሴዎችን መረዳት ለሚፈልጉ ጎብኚዎች በኤግዚቢሽኑ ቢሳተፉ እንደሚያተርፉ የጤና ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

@tikvahethiopia