TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ሞሳድ " ኢራን ውስጥ ገብቶ አንድን ግለሰብ ጠልፎ መወሰዱ ተሰማ።

ለመገናኛ ብዙሃን እምብዛም መረጃ የማይሰጠው የእስራኤሉ የስለላ  ድርጅት "ሞሳድ" ቆጵሮስ ውስጥ እስራኤላውያንን ለመግደል አቅዷል የተባለ ቡድን መሪ ነው ተብሎ የተጠረጠረን ግለሰብ ኢራን ውስጥ ዘልቆ በመግባት ለመያዝ መቻሉን አስታውቋል።

"ሞሳድ" በእስራኤላውያን ዜጎች ላይ ቆጵሮስ ውስጥ ግድያን ሊፈጽም ስለነበረው ገዳይ ቡድን ለቆጵሮስ ባለሥልጣናት መረጃ መስጠቱን እና ጥቃት ፈጻሚ ህዋሱም እንዲበተን መደረጉን አመልክቷል።

"ሞሳድ" ባወጣው መግለጫ ላይ ተካሄደ ያለውን ተልዕኮ "በኢራን ግዛት ውስጥ የተፈጸመ ልዩ ድፍረት የተሞላበት" በማለት ገልጾታል።

አንድ ከፍተኛ የሞሳድ ከፍተኛ ባለሥልጣን፤ "በየትኛውም የዓለም ክፍል ውስጥ በሚገኙ አይሁዳውያን እና እስራኤላውያን ላይ የሽብር ጥቃትን የሚያስፈጽሙ ባለሥልጣናትን የኢራን ግዛትን ጨምሮ ባሉበት ቦታ ሁሉ እናገኛቸዋለን" ስለማለታቸው ተነግሯል።

ይህ የሞሳድ ኦፕሬሽን ለረጅም ዘመናት በጠላትነት ሲፈላለጉ በነበሩት እስራኤል እና ኢራን መካከል ያለው ተዘዋዋሪ ፍልሚያ መቀጠሉን ያመለክታል ተብሏል።

እስራኤል ቆጵሮስ ውስጥ ዜጎቿን ለመግደል በኢራን አማካይነት ተቀነባብሮ ነበር ያለችውን ሴራ ከገለልተኛ ወገን #ማረጋገጥ ያልተቻለ ሲሆን ከኢራንም ሆነ ከቆጵሮስ በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።

በ "ሞሳድ" የተያዘው ግለሰብ ምን አለ ?

በእስራኤል ባለሥልጣናት ይፋ በተደረገ ቪዲዮ ላይ ዋነኛ ተጠርጣሪ እንደሆነ የተገለጸው ዩሴፍ ሻሃባዚ የተባለ ግለሰብ ከኢራን ውጭ ለ " ሞሳድ " ወኪሎች በፋርስ ቋንቋ ሲናገር አሳይቷል።

በዚህ ቪድዮ፥ ግለሰቡ አንድ እስራኤላዊ ነጋዴን ለመግደል በቱርክ ቁጥጥር ሥር ወዳለው ሰሜን ቆጵሮስ በመግባት በሕገወጥ መንገድ ወደ ደቡቡ ክፍል መግባቱን ያስረዳል።

የግለሰቡን አድራሻና ፎቶግራፍ በኢራን አብዮታዊ ዘብ ውስጥ ያለ አዛዡ እንደላከለት ተናግሯል።

"ግለሰቡን እዚያ መኖሩን እና የት ሊሄድ እንደሆነ ካወቅኩ በኋላ ዕቅዴ እንቅስቃሴ የሌለበት እና ጸጥ ያለ ሁኔታ ሲፈጠር በጥይት መግደል ነበር" በማለት ሲናገር ይሰማል።

ግለሰቡ ኢላማው የሆነውን እስራኤላዊ ከለየ እና የመኖሪያ ቤቱን ፎቶ ካነሳ በኋላ፣ በፖሊስ እየተፈለገ መሆኑ ስለተነገረው ከቆጵሮስ በመውጣት ወደ ኢራን ተመልሷል ተብሏል።

በሞሳድ ከኢራን ተይዞ የወጣውና ግድያውን ሊፈጽም እንደነበር ሲያምን በቪዲዮ የተቀዳው ግለሰብ በአስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ቃሉን እየሰጠ ይሁን አይሁን ግልጽ አይደለም።

ግለሰቡ መቼ ተያዘ ?

"ሞሳድ" ግለሰቡን ከኢራን ግዛት ውስጥ መቼ እና ከየት ቦታ ይዞ እንዳወጣው እንዲሁም ቆጵሮስ ውስጥ ሊፈጸም የነበረው ጥቃት ለመቼ ታስቦ እንደነበር ዝርዝር መረጃ አልሰጠም።

የእስራኤል እና ኢራን ግንኙነት...

እስራኤል፤ ኢራንን ለረጅም አመታት እንደ ዋነኛ ጠላቷ አድርጋ ትቆጥራታለች።

የኢራን መንግሥት እስራኤልን ለማውደም የሚያደርገውን ተደጋጋሚ ዛቻና ጥቃት የሚፈጽሙባትን ታጣቂ ቡድኖችን ትደግፋለች በሚል ነው እንደጠላት የምታያት።

እስራኤል ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያዎችን ለመገንባት እየጣረች መሆኗን ታምናለች።

በቅርብ ዓመታት እስራኤል በኢራን የኑክሌር ተቋማት ላይ ተከታታይ ጥቃቶችን የፈጸመች ሲሆን በርካታ የኢራን የኑክሌር ሳይንቲስቶችን በመግደል ትከሰሳለች።

ከ5 ዓመት በፊትም የሞሳድ ወኪሎች በኢራን ዋና ከተማ የሚገኝ የሰነዶች ማከማቻን ሰብረው በመግባት ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የኑክሌር መረሃ ግብርን ሰነዶች መዝረፋቸውን እስራኤል አሳውቃ ነበር።

ኢራን ምን አለች ? 👉 telegra.ph/MOSAD-07-01

(BBC, NuR)

@tikvahethiopia
#Update

የመውጫ ፈተና ላይ የሚፈፀሙ የደንብ ጥሰቶች እንደ ችግሩ ስፋት እና ጥልቀት የትምህርት ማስረጃ መከልከል ፣ ጥሰት የፈፀመው ተማሪ ድጋሚ ለፈተና እንዳይቀመጥ የማድረግን እርምጃ ሊያካትት እንደሚችል ተጠቁሟል።

ባለፍው ሰኞ ሰኔ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ፤ በበየነ መረብ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከመንግስት ዩኒቨርስቲ አመራሮችና ባለቤቶች ጋር ዉይይት አደርጎ ነበር።

በዚህ ውይይት ማጠቃለያ ላይ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2015 ዓ/ም ከሚሰጠው የመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ የጋራ ሊደረጉ የሚገባቸው ጉዳዮችን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀምጧል።

ይኸውም ፦

- ለመዉጫ ፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን በተመለከተ በ2015 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር የትምህርት ዘመን ትምህርታቸዉን ያጠናቀቁ ወይም ተመዝግበው በመማር ላይ ያሉ እና ከዚህ በፊት ለህግና ጤና መዉጫ ፈተና ቀርበዉ ያላለፉ ተማሪዎች ይሆናሉ፡፡ ይህም ሆኖ ከዚህ በፊት ዝርዝራቸዉ ከተላከውና መለያ ኮድ ከተሰጣቸዉ ውጭ አንደ አዲስ የሚላክና የሚካተት ተማሪ አይኖርም ተብሏል።

- በመዉጫ ፈተና ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ማለትም በትራንስክሪፕት ላይ የመዉጫ ፈተና የወሰዱበት ወር፣ ዓመትና ከ100 ያስመዘገቡት በግልጽ የሚጻፍ ይሆናል።

- በመዉጫ ፈተና ወቅት ለሚያጋጥሙ ፈተና ደንብ ጥሰቶች ሊወሰዱ የሚገቡ የዲሲፕሊን እርምጃዎችን በተመለከተ በዩኒቨርስቲዎች የዲሲፕሊን እርምጃ አወሳሰድ አሰራር የሚታይ ሆኖ የዲሲፕሊን እርምጃዉ እንደ ችግሩ ስፋትና ጥልቀት የትምህርት ማስረጃ መከልከል፣ ድጋሚ ለፈተና እንዳይቀመጥ ማድረግ እና ሌሎች እርምጃዎችን ሊያካትት እንደሚችል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

- በመዉጫ ፈተና አንድ ላይ የተጠቃለሉ (Merged Programs) ፕሮግራሞችን በተመለከተ በጋራ (በወል) የተዘጋጁ በአንድ ወይም የተለያዩ ሁለትና ከዚያ በላይ ስያሜ የሚጠሩ ፈተናዎች ያሉ ሲሆን ሌሎች ፕሮግራሞችን በተመለከተ በተቋማት የተሰጣቸዉ ስያሜ አጠራርን ይዘዉ የተዘጋጁ መሆናቸዉን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ለግል እንዲሁም ለመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ  ፤ ተመሳሳይ ፈተና እንዲኖራቸው የሆኑ ፕሮግራሞች እንዲሁም በስያሜያቸው ፈተና የተዘጋጀላቸው ፕሮግራሞችን በአባሪ አድርጎ በዝርዝር አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለግል እና ለመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከውን ደብዳቤ የተመለከተና ትክክለኝነቱንም ከሚመለከተው የትምህርት ሚኒስቴር አካል ያረጋገጠ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለማሳወቅ ይወዳል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
#COOP

From the first ring to the final solution, our call center agents are your dedicated problem-solving partners, ensuring a seamless experience and leaving you with a smile that lasts.

Call on 609 for your inquiries!

Follow us on https://t.iss.one/coopbankoromia

#Coopbank #Bank #Ethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የባይደን አስተዳደር የወሰደው እርምጃ የአሜሪካ እና የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ዕርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መላክን ለማስቀጠል መንገድ የሚከፍት ነው " - ፎሬይን ፖሊሲ ድረገፅ አሜሪካ ፤ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈችውን ፍረጃ ማንሳቷን " ፎሬይን ፖሊሲ " ዘግቧል። የፕሬዜዳንት ባይደን አስተዳደር ፤ " ኢትዮጵያ አሁን ላይ በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውስጥ እየተሳተፈች…
" የAGOA ጉዳይ በተለየ መልኩ ይታያል " - አሜሪካ

የዋይት ሀውስ የብሄራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ በሰጡት ቃል ፤ አሜሪካ ፤ ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ እያስመዘገበች ነው ያሉትን መሻሻል ከግምት ውስጥ በማስገባት የተወሰኑ የእርዳታ ገደቦችን እንዳነሳች አሳውቀዋል።

ቃል አቀባዩ መሻሻሉ የታየው የኢትዮጵያ መንግሥት እና የትግራይ ክልል ኃይሎች ግጭት የማቆም ስምምነት ከተፈራረሙ ህዳር ወር አንስቶ መሆኑን ተናግረዋል።

" የምግብ ዕርዳታን ባለበት እንደቆመ በአንዳንድ የእርዳታ ዓይነቶች ላይ ገደቦችን እያነሳን ነው " ያሉት ኪርቢ " ይህ ውሳኔ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ድጋፋችንን ለማጠናከር ያሉትን አማራጫቾች ያሰፋዋል ብለን እናምናለን። " ሲሉ ታናግረዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዕርዳታው ሰላም እና እርቅን ይደግፋል ሲል አሳውቋል።

" ለኢትዮጵያ የሚደረገው እርዳታ መቀጠል የጦርነት / ግጭት ማቆም ስምምነቱን የበለጠ ለመደገፍ እና በሽግግር ፍትሕ እና በተጠያቂነት ላይ ለሚደረገው ጥረት ለመደገፍ እንዲሁም ዘላቂ ሰላምና ዕርቅን ለማጎልበት ነው " ሲሉ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።

" በምዕራብ ትግራይ ከክልሉ ውጭ በሆኑ ታጣቂዎች ስለሚፈፀሙ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ ሪፖርቶች ያሉንን ስጋቶችን ማንሳትና መናገር እንቀጥላለን፤ መንግስት ሰላማዊ ዜጎችን እንዲጠብቅና አጥፊዎችንም በህግ እንዲጠየቅ እናሳስባለን " ብለዋል።

አሜሪካ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ኢትዮጵያን ከAGOA ተጠቃሚነት ማገዷ የሚዘነጋ አይደለም። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ቃል አቀባዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የዋይት ሀውስ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል አቀባይ የAGOA ጉዳይ በተለየ ሁኔታ እንደሚታይ ገልጸዋል።

የአሜሪካ የንግድ ተወካይ ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ለAGOA ተጠቃሚነት ብቁ መሆናቸውን የሚያሳይ ዓመታዊ ግምገማን እንደሚመራ ቃል አቀባዩ አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ https://www.reuters.com/world/us-lifts-some-restrictions-ethiopia-after-human-rights-improvements-white-house-2023-06-30/

@tikvahethiopia
AI ኮድ ያድርጉ!

የአይኮግ ኤኒ ዋን ካን ኮድ የ2023 የክረምት ኮዲንግ ምዝገባ ተጀምሯል።

የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ሃምሌ 3 ስለሚጀመር፣ አሁኑኑ ይመዝገቡ!

በኦንላይን-4000ETB
አዲስ አበባ (በአካል)-5,500 ETB ብር ብቻ በመክፈል ልጅዎን ያስተምሩ።

ለመመዝገብ: በስልክ ቁጥራችን
+251904262728/251901379478 በመደወል

ዌብሳይታችንን በመጎብኘት
https://icogacc.com/register

ወይም ቴልግራም ቦት ይጠቀሙ
@iCogACCsummercamp_bot

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችንን ይከተሉ
Facebook: facebook.com/icogacc

Instagram: instagram.com/icogacc
Twitter: twitter.com/icog_acc
Linkedin: linkedin.com/company/icog-anyone-can-code/
#Sport

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሻምፒዮን ሆነ።

በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመራው የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ለተከታታይ ሁለተኛ አመት ለአስራ ስድስተኛ ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮን መሆናቸውን ዛሬ አረጋግጠዋል።

አንድ ነጥብ ብቻ ያስፈልጋቸው የነበሩት ፈረሰኞቹ በሀያ ዘጠነኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸናፊ ያደረጉ ሁለት ግቦች ቸርነት ጉግሳ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቶጓዊው የፊት መስመር አጥቂ እስማኤል ኦሮ አጎሮ በሀያ አምስት ጎሎች የሊጉን ከፍተኛ ግብ አግቢነት እየመራ ይገኛል።

እስማኤል ኦሮ አጎሮ ከዚህ በተጨማሪም በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ ከፍተኛ የምንጊዜም ሁለተኛ ግብ አስቆጣሪነትን ከጌታነህ ከበደ ጋር መጋራት ችሏል።

የሊጉ #ሪከርድ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እነማን ናቸው ?

1. አቡበከር ናስር :- 2⃣9⃣ ጎሎች

2. ጌታነህ ከበደ :- 2⃣5⃣ ጎሎች

2. እስማኤል ኦሮ አጎሮ :- 2⃣5⃣ ጎሎች

4. ዮርዳኖስ አባይ :- 2⃣4⃣ ጎሎች

ተጨማሪ https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport  
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት ግድና ብቸኛው አማራጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ " - የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አንገብጋቢ ባሏቸው የሠራተኞች ጥያቄዎች ላይ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኮንፌዴሬሽኑን አመራሮች እንዲያነጋግሩ ጥያቄ አቀረበ፡፡ ኮንፌዴሬሽኑ በዘንድሮው የሜይ ዴይ በዓል ላይ በአደባባይ ሊያነሳቸው የነበሩ ጥቄያዎችን…
" እኛ አሁንም የሠራተኞች የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ሳይስተካከል ዝም አንልም " - የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ

ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወስነው የደመወዝ ቦርድ እንዲቋቋም ለዓመታት ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ባለማግኘቱ ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) አስታወቀ፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ 1156/2011 ዝቅተኛ የደመወዝ የሚወስነውን " የደመወዝ ቦርድ " ማቋቋም እንደሚገባ መደንገጉን፣ ይሁን እንጂ ለዝቅተኛ ተከፋዮች የኑሮ ሁኔታን የዋጀ የአከፋፈል ሥርዓት ያስተካክላል ተብሎ ሲጠበቅ ዓመታት ያስቆጠረው " የደመወዝ ቦርድ " የማቋቋም ድንጋጌ፣ አሁንም ጆሮ ዳባ መባሉን የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ገልጸዋል፡፡

ኢሠማኮ ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ደጅ ቢጠናም፣ አሁንም የዝቅተኛ ሠራተኞች ጉዳይ ምላሽ ማግኘት አለመቻሉን አቶ ካሳሁን አስረድተዋል፡፡

ተገቢውን ቅደም ተከተል በመከተል በሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ትኩረት እንዲያገኝ ኢሠማኮ ጥያቄ ቢያቀርብም፣ ምላሽ ባለማግኘቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕልባት እንዲገኝ አቤቱታ ማቅረቡን አክለዋል፡፡  

ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጥያቄው መቅረቡን ገልጸው፣ " የሚሰጡትን ምላሽ እየተጠባበቅን ነው " ብለዋል፡፡

ኢሠማኮ በየዓመቱ በሚከበረው የላብ አደሮች ቀን (ሜይ ዴይ) በኑሮ ውድነት ምክንያት በሠራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና መፍትሔ እንዲያገኝና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ምጣኔ እንዲሻሻል፣ በሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ሊያቀርብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም ሳይሳካለት መቅረቱ ይታወሳል፡፡

በሰላማዊ ሠልፉ ሊነሱ የታሰቡ ጥያቄዎች ለሚመለከታቸው አካላት ቢቀርቡም የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ ወደ ሥራ እንዲመለስ ከመፍቀድ በዘለለ ወሳኙ የሠራተኞች የህልውና ጥያቄ መፍትሔ እንዳልተሰጠው ፕሬዚዳንቱ አስረድተዋል፡፡

" እኛ አሁንም የሠራተኞች የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ሳይስተካከል ዝም አንልም " ያሉት ፕሬዚዳንቱ " ሌሎች ሕጋዊ አማራጮችን በመጠቀም መፍትሔ ለማግኘት እንሠራለን " ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አስፈጻሚ ተካልኝ አያሌው (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የደመወዝ ቦርድ ማቋቋም የራሱ የሆነ አሉታዊም አዎንታዊ ጎን አለው ብለዋል፡፡

የደመወዝ ቦርድ ማቋቋም ከሥራ አጥነትና ከኑሮ ውድነት አኳያ፣ ለሚተላለፈው ኢኮኖሚው መቋቋም ይችላል የሚለውን ጉዳይ ለማየት ጥናት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎ ሚኒስቴር አገር አቀፍ የኢኮኖሚው ሁኔታ ተፅዕኖ መፍጠር አለመፍጠሩን በጥናት ከመለየት በተጨማሪ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አንድ ግለሰብ ለመኖር የሚያስፈልገው ወርኃዊ ገቢ ጭምር እየታየ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

" የደመወዝ ቦርድ ማቋቋም አሁን ካለው አገራዊ ሁኔታ አንፃር መታየት ስላለበት፣ በድጋሚ ጥናት እየተደረገበት ነው " ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንፃር አስቸጋሪና ውስብስብ በመሆኑ፣ ቦርዱን ለማቋቋም እንደገና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል የሚወሰንባቸውን አካባቢዎች ለመለየት ዳሰሳ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

የደመወዝ ቦርድ ለማቋቋም አሁን ባሉ አገር አቀፍ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊና የፖለቲካዊ ሁነቶች አስቻይና ከልካይ ሁኔታዎችን ያማከለ እንዲሆን ያለመ ብሔራዊ የዳሰሳ ጥናት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መረጃው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
በ10 ሴኮንድ በሲቢኢ ብር ከፍያዎን ፈፅመው ነዳጅ ይቅዱ!
=================
እርስዎ ብቻ ወደ ነዳጅ ማደያ ከመምጣትዎ አስቀድመው

• የሲቢኢ ብር አገልግሎትዎ በአግባቡ እንደሚሠራ ያረጋግጡ፣
• ሲቢኢ ብርን መጠቀም ካልጀመሩም ወደ *847# በመደወል፣ ወይም የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ በራስዎ ይመዝገቡ፤ በተጨማሪም
• በሲቢኢ ብር አካውንትዎ በቂ ገንዘብ መኖሩን ያረጋግጡ እንጂ

በ10 ሴኮንድ ብቻ ነዳጅ ቀድተው ይመለሳሉ!

ስለ ሲቢኢ ብር አገልግሎት በቂ መረጃ ለማግኘት ወደ 951 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ!
*****
የሲቢኢ ብር መተ
ግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#ኢትዮጵያ

በሀገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ለ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ እና ከተማ አቀፍ ፈተና ይቀመጣሉ።

ፈተናው በክልሎች እንዲሁም በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሰኔ 26 እና ሰኔ 27 /2015 ዓ/ም እንደሚሰጥ ከየክልሉ ትምህርት ቢሮዎች ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በዘንድሮው ዓመት በሚሊዮን ሚቆጠሩ ተማሪዎች ፈተናው ላይ የሚቀመጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ግዙፎቹ የኢትዮጵያ ክልሎች ኦሮሚያ እና አማራ በድምሩ ከ830 ሺህ በናይ (አማራ 347,666 ፤ ኦሮሚያ 484,994) ተማሪዎችን ፈተና ላይ ያስቀምጣሉ።

በደቡብ ክልል ከ200 ሺህ በላይ ፣ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ75 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተና ላይ የሚቀመጡ ሲሆን በሌሎች ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ በርካታ ሺዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።

እንደ ክልል ትምህርት ቢሮዎች መረጃ በአጠቃላይ በመላው ሀገሪቱ ፈተናውን የሚወስዱት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ናቸው።

ነገ መሰጠት የሚጀምረው ፈተና ሙሉ ቀን (ጠዋት እና ከሰዓት) እንደሚሰጥ የታወቀ ሲሆን ተፈታኞች እርሳስ፣ ላጲስ እና ማስመሪያ ብቻ ወደ ፈተና ማዕከላት ይዘው መሔድ ይችላሉ።

ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌት፣ ጆሮ ማዳመጫ፣ ዲጂታል ሰዓት እንዲሁም ማንኛውንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን ይዞ በፈተና ማዕከላት መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ወላጆችም ልጆቻችሁ የተከለከሉ ቁሳቁሶችን ይዘው ወደ መፈተኛ ጣቢያ እንዳይሄዱ ክትትል አድርጉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EOTC

በቅርብ ቀናት በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ ልዑክ ወደ መቐለ እንደሚጓዝ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ዓርብ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ/ም ባካሔደው መደበኛ ስብሰባ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ የልዑካን ቡድን በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ክልል ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ እንዲጓዝ ውሳኔ አስተላልፏል።

ልዑካን ቡድኑ ወደ መቐለ የሚጓዘው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ የተወሰነውን የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስና በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓንሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር መሆኑ ታውቋል።

ወደ መቐለ በሚደረገው ጉዞ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው የሰላምና አቀራራቢ ኮሚቴ አባላት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር አብረው ይጓዛሉ።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
#ኤክሶደስ

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ!

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት፤ አድራሻችን 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን። ስልክ ቁጥር 0979099909/ 0911039377
  √በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ በሀገራችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ለ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ እና ከተማ አቀፍ ፈተና ይቀመጣሉ። ፈተናው በክልሎች እንዲሁም በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ሰኔ 26 እና ሰኔ 27 /2015 ዓ/ም እንደሚሰጥ ከየክልሉ ትምህርት ቢሮዎች ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በዘንድሮው ዓመት በሚሊዮን ሚቆጠሩ ተማሪዎች ፈተናው ላይ የሚቀመጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ግዙፎቹ የኢትዮጵያ…
የ8ኛ ክፍል ክልልና ከተማ አቀፍ ፈተና ዛሬ ሰኞ መሰጠት ተጀምሯል።

ፈተናው ለሁለት ቀናት ይሰጣል።

በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች (አ/አ እና ድሬዳዋ) እንዲሁም በክልሎች በሚሰጠው በዘንድሮው ዓመት የ8ኛ ክፍል ፈተና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ይፈተናሉ።

ፎቶ ፦ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

@tikvahethiopia