TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ ቤት በመንግሥት ተቋማት በርካታና ሰፋ ያሉ የኦዲት ክፍተቶችን በኦዲት ሪፖርት ማረጋገጡን አስታውቋል። ባለፈው ፤ ማክሰኞ ለፓርላማው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት ቀርቦ ነበር። ይህ ሪፖርት እንደሚያመለክተው የ2014 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው የኦዲት ሥራ 6 ተቋማት አስተያየት ለመስጠት ያልተቻለባቸው ሲሆኑ 19 ተቋማት ደግሞ…
#ኦዲት

" በ86 የመንግስት መስሪያ ቤቶች 6 ቢሊዮን 838 ሚሊዮን 886 ብር ተመላሽ እንዲደረግ ሙያዊ አስተያየት ቢሰጥም 0.65 በመቶው ብቻ ነው ተመላሽ የሆነው " - የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት

የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ክርስትያን ታደለ ፤ የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለ ዓለማ እያዋለ ባለመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የብሔራዊ ስጋት እየሆነ ስለመጣ የፍትህ ተቋማት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳሰቡ።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ይህ ያሳሰቡት ከቀናት በፊት የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለፓርላማው የ2014 ዓ/ም የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ ክንዋኔ ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ነው።

" የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለት ዓለማ በትክክል እንዲውል ዋና ኦዲተር መ/ቤት እያደረገ ያለውን ጥረት የሚበረታታ ነው " ያሉት አቶ ክርስቲያን " የክዋኔ ኦዲት ስራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ የሪፖርቱን ተአማኒነት እና ተቀባይነትን ማረጋገጥ ይገባል " ብለዋል።

ዋና ኦዲተር የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድ እና ሪፖርት በወቅቱ በመገምገም የተሻለ ውጤት እንዲመጣ በይበልጥ ጥረቱን አጠናክሮ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

አቶ ክርስቲያን ፤ " አስፈጻሚው አካል ለኦዲት ግኝቶች ትኩረት ባለመስጠት የገንዝብ የመመለስ ምጣኔው በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ፤ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተቋማትን በመቆጣጠርና ተጠያቂነትን ማስፈን ይጠበቅበታል " ብለዋል።

" የመንግስት እና የሕዝብ ኃብት ለታለመለ ዓለማ እያዋለ ባለመሆኑ ሙስና እና ብልሹ አሰራር የብሔራዊ ስጋት እየሆነ የመጣ በመሆኑ የፍትህ ተቋማት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው " ሲሉም አሳስበዋል።

የፌደራል የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ በበኩላቸው ፤  " በ86 የመንግስት መ/ ቤቶች 6 ቢለዮን 838 ሚሊዮን 886 ብር ተመላሽ እንዲደረግ ሙያዊ አስተያየት ቢሰጥም 0.65 በመቶው ብቻ ተመላሽ በመደረጉ የሚፈለገውን ለውጥ እያመጣ አይደለም።  " ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ኦዲተሯ ፤ በተወሰኑ የመንግስት እና የህዝብ ሃብት ባባከኑ የስራ ኃላፊዎች ላይ የገንዘብ ቅጣት እና የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እርምጃ በገንዘብ ሚኒስቴር መወሰዱን ሲናገሩ ተደምጠዋል።

#HoPR

@tikvahethiopia
" የባይደን አስተዳደር የወሰደው እርምጃ የአሜሪካ እና የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ዕርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መላክን ለማስቀጠል መንገድ የሚከፍት ነው " - ፎሬይን ፖሊሲ ድረገፅ

አሜሪካ ፤ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈችውን ፍረጃ ማንሳቷን " ፎሬይን ፖሊሲ " ዘግቧል።

የፕሬዜዳንት ባይደን አስተዳደር ፤ " ኢትዮጵያ አሁን ላይ በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውስጥ እየተሳተፈች አይደለችም " በሚል ለኮንግረሱ ማሳወቁ ተነግሯል።

ይህ ውሳኔ የአሜሪካ እና የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ዕርዳታ ወደ #ኢትዮጵያ መላክን ለማስቀጠል መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል።

አሜሪካ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ጋር የነበራት ግንኙነት መሻከሩ ፤ በተለይ የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን መጣሏ የሚዘነጋ አይደለም።

አሁን ላይ ከሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ የባይደን አስተዳደር የወሰደው እርምጃ ዋሽንግቶን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል እየሰራች ባለችበት ወቅት መሆኑን ፎሬይን ፖሊሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ያንብቡ : https://foreignpolicy.com/2023/06/29/ethiopia-tigray-war-human-rights-violations-designation-biden-us-government/

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ " BRICS " ን የመቀላቀል ጥያቄ  !

ኢትዮጵያ ሩስያ፣ ቻይና፣ ሕንድ ፣ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪካ የመሰረቱትን " BIRCS " የተሰኘውን ስብሰብ / ጂዮፖለቲካዊ ጥምረት ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርባለች።

ላቀረበችው ጥያቄ በጎ ምላሽ እንደምትጠብቅም አሳውቃለች።

ይህን ጥያቄ በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምን አሉ ?

አምባሳደር መለስ ዓለም ፦

" አሁን እየተለወጠ ባለው የዓለማችን ሁኔታ አንፃር ፤ እየተቀያየረ ባለው የዓለማችን ሁኔታ አንፃር እና የኃይል አሰላለፍ አንፃር ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማረጋገጥ የሚረዱንን የሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋሞች አባል እንድንሆን እንሰራለን።

ከእነዚህም አንደኛው BRICS ነው ፤ ጥያቄ ቀርቧል ፤ በዚህ መሰረት ብራዚል፣ ሩስያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ አባል የሆኑበት የዚሁ አካል አባል ለመሆን በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ጥያቄ ቀርቧል።

ጥያቄያችን በጎ ምላሽ ያገኛል ብለን እናስባለን። "

@tikvahethiopia
#Super_Dunamis_Raw_Material

JOIN 👉 https://t.iss.one/dunamisRM

> RAW MATERIAL SUPPLIER & POLYMER TRADE CONSULTANCY

ለማንኛውም አይነት የፕላስቲክና ኬሚካል ፋብሪካዎች ጥሬ እቃ አናቀርባለን።

ለውሀና ጁስ፣ ለስፖንጅ፣ ለሳሙና ፋብሪካ

ጥሬ እቃ አስመጪነት ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ሙያዊ የማማከር አገልግሎት : ቴሌግራም - https://t.iss.one/dunamisRM

ይደውሉ የሚፈልጉትን ጥሬ እቃ በቅልጥፍና ከደጅዎ እናደርሳለን

ስልክ፡ +251911428276/ +251902454776
#ጥናት

በሶስት ክልሎች ሲዳማ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵካ በተደረገ የሰላም ልኬት የናሙና ጥናት የክልሎቹ ተወላጆች በሌላ ክልል ተወላጆች ላይ ያላቸው እምነት 14 በመቶ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል።

የክልሎቹ ጎሳዎች ወይም ተወላጆች እርስ በእርስ ያላቸው እምነት 48 በመቶ ብቻ ነው ተብሏል።

በሶስቱም ክልሎች 801 ሰዎችን ፣ 101 የቀበሌ አስተዳደሮችን እና 101 የሀገር ሽማግሌዎችን በናሙናነት ተወስደዋል።

ጥናቱ እንዲካሄድ ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር ከኢንተርፒስ በጋራ ሆነው ነው።

በዚሁ ጥናት ፤ የኢትዮጵያ ሰላም ጥናት ልኬት (Peace Index) በሶስቱ ክልሎች ከአስር ፤ 6.7 እንደሆነ ተመላክቷል።

በግለሰብ በቤተሰብ፣ በህብረተሰብ እና በወሰን መካከል ያለው የሰላም ልኬት ውጤት ይለያያል ተብሏል።

ጥናቱን ያቀረቡት ተመራማሪ ፤ ሙሉ ተካ  ፤ " መለኪያው ከ0 - 10 ነው ፤ በግለሰቦች ውስጥ ያለው ሰላም 8.1 ነው። በቤተሰብ ጋር 7.1 ነው። ማህበረሰብ ጋር 6.3 ነው ፤ በአካባቢ ድንበሮች 5.4 ነው " ብለዋል።

እነዚህ ሶስቱ ክልሎች በአንፃራዊነት ሰላማዊ የነበሩ እና ሆነው የቆዩ ክልሎች ናቸው ነጥባቸው ግን ትልቅ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ አሁን የተመዘገበው ውጤት የአንድ ችግር አለመላካች ነው ያሉ ሲሆን " የጥናቱ አንድምታ አሁን መተንተን አይቻልም። መጠንቀቅ አለብን ከዚህ አንድምታውን እና ድምዳሜውን መስጠት አቸጋሪ ነው ፤ ይሄ ጥናት መነሻ ነው " ብለዋል።

በሶስቱ ክልሎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በሌላው ጎሳ ላይ ያላቸው እምነት 14 በመቶ፣ በሌላ ሃይማኖት ላይ ያላቸው እምነት 14 በመቶ እና በሌሎች ክልሎች ላይ ያላቸው እምነት 13 በመቶ ብቻ መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል።

የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም በበኩላቸው ፤ እንዲህ አይነት ጥናት በሁሉም ክልሎች ተጠንቶ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ያሉ ሲሆን እንዲህ አይነት ጥናት መደረጉ ችግሮችን በግምት ከመለየት ይልቅ ሳይንሳዊ በመሆነ መንገድ በመለየት መፍትሄ ለመስጠት ይረዳል ሲሉ አሳውቀዋል።

ጥናቱን በተመለከተ ክልሎቹ ምን አሉ ?

ያንብቡ : https://telegra.ph/Sheger-FM-06-30

Credit : Sheger FM 102.1

@tikvahethiopia
" የሃጫሉን ግድያ የፈጸሙትን ታውቃለችሁ አውጡልን " - ወ/ሮ ፋንቱ ደምሴ

ትላንት በ " አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን " አዘጋጅነት የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ የተሰዋበት ዝክር እና የሃጫሉ አዋርድ ተካሂዷል።

በዚሁ ዝግጅት ላይ የአርቲስት ሃጫሉ ባለቤትና የሃጫሉ ፋውንዴሽን ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ ንግግር ያደረገች ሲሆን በንግግሯም ከባለቤቷ ግድያ ጋር በተያያዘ ዛሬም ድረስ ፍትሕ እንዳልተገኘ በመግለፅ ቅሬታ አቅርባለች።

ወ/ሮ ፋንቱ ፤ " አንተ ከተለየን ጊዜ ጀምሮ ለሦስት ዓመታት ያህል  ያንተን እውነታ ወይም ያንተን ፍትህ አላየሁም " ብላለች።

" በአካል ጥለን ከሄድክ ጀምሮ እኔና ልጆቻችን ያላንተ ሀሳብ፣ ናፍቆት እና ፍቅር በስተቀር እውነትንና የሰውን ደም በምትመጠው ሀገር ላይ እየኖርን ይኸው ሶስት አመታትን አስቆጥረናል " ስትል በሀዘን ስሜት ተናግራለች።

ወይዘሮ ፋንቱ በአርቲስት ሃጫሉ ሞት ጋር በተያያዘ ተጠርጥራ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ነፃ የተለቀቀችው ሴት ላይ ያላትን ቅሬታ አሰምታለች።

በተጨማሪ ፤ " መንግስትም ሆነ ሌላው አካላት የሃጫሉን ግድያ የፈጸሙትን ታውቃለችሁ አውጡልን " ስትል ጠይቃለች።

" አሁንም፣ ወደፊትም ከፈጣሪ በታች ያንተ እውነት የገደሉህ ፣ ያስገደሉህን እና ከአንተ ጋር የነበረችው ልጅ ጋር ነው ያለው። ለኔ ማንም ንፁህ አይደለም " ብላለች።

ወ/ሮ ፋንቱ በሃጫሉ ግድያ እጃቸው ያለበት ብዙ መሆናቸውን በመግለፅ " እውነታውን አውጡልኝ  " ስትል ጥሪ አቅርባለች።

" ለሃጫሉ ፍትህ አልሰፈነችም " ያለችው ወ/ሮ ፋንቱ " የእሱ እውነታ አለመውጣቱን ሁላችሁም ታውቃላችሁ፤ በሀይማኖታችሁ ፀልዩልን " ብላለች።

Via @tikvahethAFAANOROMOO

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ ውስጥ ትላንት እና ዛሬ " ሲኖ ትራክ " እየተባለ በሚጠራው የጭነት ተሽከርካሪ የተገጩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።

ዛሬ ከቀኑ 5:37 በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሰሜን ሆቴል ፊትፊት " ሲኖ ትራክ " እየተባለ የሚጠራው የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበረን የ50 ዓመት ጎልማሳ በመግጨቱ ሕይወቱ ማለፉ ተገልጿል።

ትናንት ምሽት ደግሞ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ጣፎ 2ኛ በር አካባቢ መንገድ በማቋረጥ ላይ የነበረ የ44 ዓመት ጎልማሳ በዚሁ " ሲኖ ትራክ " በሚባለው የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ተገጭቶ ሕይወቱ አልፏል።

መረጃው የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ነው።

@tikvahethiopia
ዛሬ ያለ ዋስትና አምኖ ማን ያበድራል?
እንደራስ በቴሌብር ገመናዎን ሸፍኖ ያበድርዎታል!

በ10፣ 25 እና 60 ቀናት የመመለሻ ጊዜ አማራጮች አሉት
ብድር የሚጠይቁበት ሞባይል ስልክ  የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኝነት ቆይታ ከ3 ወራት በላይ መሆን
የቴሌብር አገልግሎት ደንበኝነት ቆይታዎ ከ3 ወራት በላይ መሆን
የሁለቱ አገልግሎቶች (የኢትዮ ቴሌኮም እና ቴሌብር) አጠቃቀም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት እየታየ እስከ ከፍተኛው የብድር ጣራ 15,000 ብር የማግኘት እድል ይኖርዎታል።

ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ

(ኢትዮ ቴሌኮም)
አፖሎ ዘመደ ብዙ ነው። ከየትኛውም አማራጭ ወደ አፖሎ አካውንትዎ ገንዘብ ተቀማጭ አድርገው ቀለል ብሎት ይገበያዩ ::

ስለ አፖሎ የዲጅታል ባንክ መተግበሪያ አጠቃቀም እና የተለያዩ መረጃዎች ለማግኘት የአፖሎ የቴሌግራም ቻነልን ይቀላቀሉ።
https://t.iss.one/apollodigitalproduct
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all