"ሀክ ተደርጌ ነው"
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ይፋዊ የተረጋገጠ የፌስቡክ ገፅ ላይ የተጋራው የአንድ ግለሰብ አካውንት መልዕክት በበርካቶች ዘንድ ውግዘት ያደረሰ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ "ሀክ ተደርጌ ነው" ብሏል።
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ በፌስቡክ ገፁ ላይ ያጋራው ከላይ የተያያዘውን "Adisalem Desta" የተባለ ግለሰብ ፅሁፍ ሲሆን ፅሁፉ " የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ኃይሎች በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚቀርበውን ጥሪ ቸል በማለት የዘር ጭፍጨፋ ጦርነታቸውን እያባባሱ ነው / መላውን ትግራይ በመቆጣጠር የዚህን ሳምንት በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደውን የሰላም ንግግር የትጥቅ ማስፈታት ስነስርዓት ለማድረግ ነው ። " የሚሉና ሌሎች ሀሳቦች የያዘ ነው።
ይኸው ፅሁፍ በገፁ ላይ ለ25 ደቂቃ ያህል የቆየ ሲሆን እጅግ በርካታ ሰዎች በአስተያየት መስጫው ላይ ከፍተኛ ውግዘት እና ተቃውሞ አሰምተዋል።
" ዓለም አቀፉ ተቋም የህወሓትን ቡድን ፕሮፖጋንዳ በግልፅ ማሰራጨቱን፣ ተቋሙ በሽብርተኝነት የተፈረጀውን ህወሓትን የመደገፍ አላማ እንዳለው፣ በዚህ ድርጊቱም ሊያፍር እንደሚገባ " በመግለፅ ድርጊቱን ኮንነዋል።
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ልዑክ በገፁ ላይ የነበረው ፅሁፍ የጠፋ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ ገፁ " ተጠልፎ/ሀክ ተደርጎ " እንደነበር ገልጿል።
ልዑኩ፤ "ዛሬ አካውንታችን እንደተጠለፈ እና ፖስት እንደተደረገ ለማሳወቅ ይወዳል" ያለ ሲሆን "ይህ የአውሮፓ ህብረት / በኢትዮጵያ የአውሮፓ ልዑክ ይፋዊ መልዕክት አይደለም" ብሏል።
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ልዑክ አካውንቱን መልሶ መቆጣጠሩን አመልክቶ ከጠለፋው (ሀክ መደረጉ) ጋር በተያያዘ ያለውን ሁኔታ እየመረመረ መሆኑን ገልጿል።
"ሀክ ተደርጌ ነው" ባለበት ፅሁፉ የአስተያየት መስጫውን #ቆልፎታል።
@tikvahethiopia

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
" ... ህወሓቶች የሀገሪቱን ሕገ መንግስት እንዲያከብሩ ፤ እና እንደ ኢትዮጵያ አንድ #ክልል እንዲንቀሳቀሱ ለማሳመን እየሞከርን ነው " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት በሚካሄደው ሂደት ከባድ የውጭ ጣልቃ ገብነት እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ከCGTN ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ሰላምን ለማምጣት ባለው ሂደት " የውጪ ጣልቃ ገብነት " ቢኖርም የሰላም ስምምነት እንደሚደረስ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።
" በእርግጥ ከግራም ሆነ ከቀኝም በርካታ ጣልቃ ገብነቶች የሚኖሩ ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ይሆናል " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " ኢትዮጵያውያን መረዳት ያለባቸው የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን መፍታት አንደምንችል " ነው ሲሉ አክለዋል።
" ህወሓት የሀገሪቱን #ህገመንግስት እንዲያከብር ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አንድ ክልል እንዲንቀሳቀስ ለማሳመን ጥረት እያደረገን ነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " ፍላጎታችንን መገንዘብ የሚችሉ ከሆነ እና የራሱን ህገመንግስት የሚያክብር እና በህጉ መሰረት የሚንቀሳቀስ ከሆነ ሰላም ይሰፍናል ብየ አስባሁ " ብለዋል።
(ሙሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከላይ ተያይዟል)

TIKVAH-ETHIOPIA
#DigitalLottery አድማስ ሎተሪ ወጣ ! የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአድማስ ሎተሪ ዕጣ ዛሬ መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ/ም በብሔራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በሕዝብ ፊት መውጣቱን አሳውቋል። ዛሬ የወጣው ሁለተኛው ዙር ነው። 👉 የ1.5 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር ፦ 003111908205 👉 የ800 ሺህ ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር ፦ 003098506207…
#DigitalLottery
አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ጥቅምት 22/205 ዓ/ም በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል።
1.5 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 004159786369 ሆኖ ወጥቷል።
👉 1.5 ሚሊዮን ብር - 004159786369
👉 800 ሺህ ብር - 004412460260
👉 350 ሺህ ብር - 004223166354
👉 200 ሺህ ብር - 004429482613
👉 160 ሺህ ብር - 004095740673
👉 120 ሺህ ብር - 004374280736
(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)

#Update ትላንት ለሊት አሜሪካ ሰኞ ሊደረግ ከታቀደው የሰላም ንግግር ጋር በተያያዘ መግለጫ አውጥታለች። በዚህ መግለጫ በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ክልል ባለስልጣናት መካከል በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሊደረግ የታቀደውን የሰላም ንግግር በደስታ እንደምትቀበለው ገልፃለች። አሜሪካ ፤ " ደቡብ አፍሪካ ውይይቱን ስላስተናገደች እናደንቃለን " ያለች ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን…
#USA
ትላንት ለሊት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ መግለጫ ሰጥተው ነበር በዚህ መግለጫቸው ስለ ደቡብ አፍሪካድ የሰላም ንግግር አንስተው ነበር።
ምን አሉ ?
- የሰላም ንግግር 4 ጉዳዮችን ለማሳካት ያለመ ነው።
1ኛ. በአስቸኳይ ግጭት ማቆም፣
2ኛ. የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን በሙሉ ማቅረብ፣
3ኛ. የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ ተጨማሪ እርምጃዎችን መውሰድ
4ኛ. #የኤርትራን_ጦር ከሰሜን ኢትዮጵያ ማስወጣት ነው።
- በደቡብ አፍሪካ እየተደረገ ያለው ንግግር በአራቱ ግቦች ላይ ልዩነቶችን ለማጥባብ ይረዳል።
- የፕሬዜዳንት ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር በደቡብ አፍሪካው ንግግር ላይ እየተሳተፉ ነው። እሳቸው ‘ተሳታፊ እና ታዛቢ’ ሆነው ይቀጥላሉ።
- የሰላም ንግግሩ ሁለቱ የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ልዩነቶቻቸውን ለማጥበብ እና 4ቱ ግቦች ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲያመጡ ዕድል ይሰጣቸዋል።
- የውይይቱ መራዘም ተወያይ አካላት በመካከላቸው የተራራቀ አቋም ይዘው ደቡብ አፍሪካ ማቅናታቸውን ያመላክታል።
- የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ውይይቱን መቀጠላቸው ለመነጋገር ያላቸውን ፍላጎት ያሳያል።
- ተቀምጦ ለመወያየት ፈቃደኛ ሆነው መቀጠላቸውን ልዩነታቸውን የሚነጋገሩበት እና በመካከላቸው ያለውን ርቀት ለማጥበብ የሚነጋገሩበት ይሆናል።
ምንጭ፦ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

" ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ "
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሶስተኛ (3) ተከታታይ አመት ከቢዝነስ ትራቭል ሪደርስ አዋርድ የ2022 " ምርጥ አፍሪካ አየር መንገድ " ሽልማት ማሸነፉን አሳውቋል።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሶስተኛ (3) ተከታታይ አመት ከቢዝነስ ትራቭል ሪደርስ አዋርድ የ2022 " ምርጥ አፍሪካ አየር መንገድ " ሽልማት ማሸነፉን አሳውቋል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ #በህይወት አለ። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አንጋፋው የሀገራችን አርቲስት ክቡር ዶክተር አሊ ቢራ " አረፈ / ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው። ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ባጋጠመው የጤና እክል የተነሳ በአዳማ ጄነራል ሆስፒታል ለላፉት ቀናት #የሕክምና_ክትትል እየተደረገለት ይገኛል። የ75 ዓመቱ አርቲስት አሊ…
" መሰል ሀሰተኛ መረጃ ሲነዛ በዚህ ወር ብቻ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው "
ዛሬ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ " ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " እየተባለ ሲናፈስ የነበረው መረጃ #ሀሰተኛ ነው።
በክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ላይ መሰል ሀሰተኛ መረጃ ሲነዛ በዚህ ወር ብቻ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
ከወራት በፊት ተመሳሳይ ሀሰተኛ ወሬ መሰራጨቱ እና ቤተሰቦቹን እጅጉን መጉዳቱና ማሳዘኑ የሚዘናጋ አይደለም።
ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ባጋጠመው የጤና እክል የተነሳ በአዳማ ጄነራል ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።
እንዲህ ያለው ነውር በሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያ ላይ እጅግ እየተደጋገመ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚከተሏቸው ትልልቅ የማህበራዊ ሚዲያዎችም ሰለባ እየሆኑ ነው።
አንዳንድ ጊዜ " ፈጥነን መረጃ አደረስን " ለማለት ያህል ፤ እንዲሁም የዩትዩብ ብር ለማግኘት / ላይክ ለመሰብሰብ ሲባል የሰዎችን ህይወት መረበሽ እና መበጥበጥ ከህሊና ያፈነገጠ ተግባር ነው።

#የፀጥታ_ችግር
ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፤ አሶሳ ከተማ 96 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኘው ማና ሲቡ ፤ መንዲ ከተማ (ምዕራብ ወለጋ) እና አካባቢው ላይ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ መኖሩና ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።
አንድ በአካባቢው ላይ ቤተሰቦቹ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል፤ ከትላንት ወዲያ ሰኞ ታጣቂዎች ከማለዳ ጀምሮ ቶክስ በመክፈት ወደመንዲ ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት በመንግስት መ/ቤቶችና ተቋማት ላይ ጥፋት ሲያደርሱ እንደነበር አመልክቷል።
ባንኮችም ተዘርፈዋል።
በከተማው የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ እንደሆኑና ከአሶሳ-መንዲ የህዝብ ትራንስፖርት ሙሉ ለሙሉ እንደተቋረጠ በክስተቱ ንፁሃን ሰዎች እየተገደሉ ገልጿል።
መንዲ እና አካባቢው ከባድ ሁኔታ ላይ ነው ያሉት ያለው የኸው የቤተሰባችን አባል "ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዛት ያላቸው የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው ወደ ከተማ ዘልቀው ገብተው ጥፋት ያደረሱት" ሲል አስረድቷል።
ከአሶሳ ጋር የሚያገናኘውን ዋናውን አስፓልት በመቆረጡ ነዋሪው ትልቅ ስጋት ላይ እንደሆነ ገልጾ " የንፁሃን ደም ከመፍሰሱ በፊት መንግስት ፈጣን መፍትሄ እንዲሰጥ እንፈልጋለን " ብሏል።
" ብዙ ዘመዶቼ እዛ ስላሉ እኔም ጨንቀት ላይ ነኝ " ሲል ሀሳቡን አጋርቷል።
የምዕራብ ወለጋ ዞን የአስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደበላ ኦላና ደግሞ " ከሰኞ ጀምሮ እስከ ትላንት ማክሰኞ ድረስ የፀጥታ ኃይሉ እና ታጣቂዎች እየተዋጉ ነው " ሲሉ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።
አቶ ደበላ በአካባቢው ከሰኞ ጀምሮ ተኩስ እንደነበርና #ከተማው ውስጥም ተኩስ እንደነበር አመልክተዋል።
ታጣቂዎቹ ወደ ከተማ ዘልቀው ሳይገቡ እንዳልቀረ ጥርጣሬ እንዳላቸውም ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ገልፀዋል።

#Bambasi
ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ #በባምባሲ ወረዳ የሰዓት እላፊ ታውጇል።
ወረዳው ፤ " የስጋት ቀጠና " ከሆኑ አካባቢዎች (ምዕራብ ወለጋ) ጋር ተጎራባች በመሆኑ ጥፋት ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሰዓት እላፊ መታወጅ ማስፈለጉን ገልጿል።
በወረዳው አንዳንድ ስጋት ሊሆኑ ሚችሉ ተጨባጭ ምልክቶች ስለታዩ እና የፀጥታ ችግር ካለባቸው አጎራባች አካባቢዎች ያለውን እንቅስቃሴ መቆጣጠር በማስፈለጉ ከጥቅምት 21/2015 ጀምሮ የሰዓት እላፊ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ተመላክቷል።
በዚህ መሰረት፦
- እግረኞች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም።
- ሞተር ሳይክሎችና 3 እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 - ንጋቱ 12:00 ሰዓት እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም።
- ማንኛውም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሻይ ቡና፣ ምግብ፣ ሪስቶራንት፣ መጠጥ ቤቶች እና ወ.ዘ.ተ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም።
* ለጸጥታ ስራ ከሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ወላድ ከሚያንቀሳቅሱ አንቡላንሶች ዉጭ ማንኛዉም ተሸከርካሪ ከ1፡00 በኋላ ሲንቀሳቀሱ ያሉባቸውን ችግሮች በ 0574410224 ለጸጥታ አካሉ ማሳወቅ ግድ ይላቸዋል ፤ ሳያሳውቁ መንቀሳቀስ አይፈቀድም፡፡
ህብረተሰብ የሰዓት እላፊውን በጊዜ ወደ ቤቱ በመግባት የጸጥታ ሃይሉ ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።
ማንኛውም ለጸጥታ ስጋት የሚሆነ አጠራጣሪ ነገሮችን በ0574410224 መጠቆም እንደሚቻል ተመላክቷል።
በሌላ በኩል ፤ ማንኛውም የጸጥታ አካል ከተመደበው መደበኛ ሠራዊት ውጪ የተጣለውን የሰዓት እላፊ ገደብ አልፎ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ በቁጥጥር ስር እንደሚውል ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

#Update ከአላማጣ እስከ ቆቦ የሚገኙ አካባቢዎች ዳግም #የኤሌክትሪክ_ኃይል ማግኘታቸው ተገልጿል። የኤሌክትሪክ ኃይል ያገኙት ፦ - አላማጣ፣ - ኮረም፣ - ዋጃ፣ - ጥሙጋ እና ቆቦ ከተሞች ናቸው። ከአላማጣ እስከ ላሊበላ የተዘረጋውን የ66 ኬ.ቪ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ በአካባቢው ያሉ ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ…
#Update
ለረጅም ጊዜ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባት የቆየችው ላሊበላ ከተማ ዛሬ እንደገና የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳገኘች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።
ከላሊበላ ከተማ በተጨማሪ ላስታ ወረዳና ሙጃ ከተማ ኤሌክትሪክ እንዳገኙ ተገልጿል።
እነዚህን አካባቢዎች መልሰው ኃይል ያገኙት በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የአላማጣ - ላሊበላ የ66 ኬ.ቮ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ሲደረግ የነበረው የጥገና ስራ መጠናቀቁን ተከትሎ መሆኑ ተመላክቷል።

Photo
#Update | #Pretoria
የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ ከሰዓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ስላለው " የሰላም ንግግር " ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ እንደሚሰጡ ተነግሯል።
ኦባሳንጆ ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት #ሰላማዊ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ስላለው የሰላም ንግግር በተመለከተ በፕሪቶሪያ ሆነው ነው መግለጫውን የሚሰጡት።
ባለፈው ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ/ም በደቡብ አፍሪካ የጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር እሁድ እንደሚጠናቀቅ ቢገለፅም ለተጨማሪ ቀናት ተራዝሞ የሰላም ንግግሩ እንዲቀጥል ተደርጓል።
በዚህ ሁሉ ጊዜ የሰላም ንግግሩ ይዘት ፣ አጀንዳ እና የደረሰበት ደረጃ በተመለከተ ምንም መረጃ ሳይወጣና የንግግሩ አመቻቾች አጠቃላይ ሂደቱ ከሚዲያዎች በራቀ ሁኔታ እንዲሄድ አድርገዋል። ዛሬ ከሰዓት ግን ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የሰላም ንግግሩን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋዊ መግለጫ ይሰጣሉ።
ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ የዛሬውን የሰዓት መግለጫ በተመለከተ ይህን መረጃ ያገኘነው ከDICRO South Africa ነው።