TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update | #Pretoria

የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ ከሰዓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ስላለው " የሰላም ንግግር " ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ እንደሚሰጡ ተነግሯል።

ኦባሳንጆ ፤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት #ሰላማዊ መፍትሄ ያገኝ ዘንድ በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ስላለው የሰላም ንግግር በተመለከተ በፕሪቶሪያ ሆነው ነው መግለጫውን የሚሰጡት።

ባለፈው ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ/ም በደቡብ አፍሪካ የጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የሰላም ንግግር እሁድ እንደሚጠናቀቅ ቢገለፅም ለተጨማሪ ቀናት ተራዝሞ የሰላም ንግግሩ እንዲቀጥል ተደርጓል።

በዚህ ሁሉ ጊዜ የሰላም ንግግሩ ይዘት ፣ አጀንዳ እና የደረሰበት ደረጃ በተመለከተ ምንም መረጃ ሳይወጣና የንግግሩ አመቻቾች አጠቃላይ ሂደቱ ከሚዲያዎች በራቀ ሁኔታ እንዲሄድ አድርገዋል። ዛሬ ከሰዓት ግን ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የሰላም ንግግሩን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋዊ መግለጫ ይሰጣሉ።

ውድ ቤተሰቦቻችን ፤ የዛሬውን የሰዓት መግለጫ በተመለከተ ይህን መረጃ ያገኘነው ከDICRO South Africa ነው።

@tikvahethiopia