#Bambasi
ከወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ጋር በተያያዘ #በባምባሲ ወረዳ የሰዓት እላፊ ታውጇል።
ወረዳው ፤ " የስጋት ቀጠና " ከሆኑ አካባቢዎች (ምዕራብ ወለጋ) ጋር ተጎራባች በመሆኑ ጥፋት ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላትን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሰዓት እላፊ መታወጅ ማስፈለጉን ገልጿል።
በወረዳው አንዳንድ ስጋት ሊሆኑ ሚችሉ ተጨባጭ ምልክቶች ስለታዩ እና የፀጥታ ችግር ካለባቸው አጎራባች አካባቢዎች ያለውን እንቅስቃሴ መቆጣጠር በማስፈለጉ ከጥቅምት 21/2015 ጀምሮ የሰዓት እላፊ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ተመላክቷል።
በዚህ መሰረት፦
- እግረኞች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም።
- ሞተር ሳይክሎችና 3 እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 1:00 - ንጋቱ 12:00 ሰዓት እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም።
- ማንኛውም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሻይ ቡና፣ ምግብ፣ ሪስቶራንት፣ መጠጥ ቤቶች እና ወ.ዘ.ተ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ማድረግ አይችሉም።
* ለጸጥታ ስራ ከሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ወላድ ከሚያንቀሳቅሱ አንቡላንሶች ዉጭ ማንኛዉም ተሸከርካሪ ከ1፡00 በኋላ ሲንቀሳቀሱ ያሉባቸውን ችግሮች በ 0574410224 ለጸጥታ አካሉ ማሳወቅ ግድ ይላቸዋል ፤ ሳያሳውቁ መንቀሳቀስ አይፈቀድም፡፡
ህብረተሰብ የሰዓት እላፊውን በጊዜ ወደ ቤቱ በመግባት የጸጥታ ሃይሉ ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።
ማንኛውም ለጸጥታ ስጋት የሚሆነ አጠራጣሪ ነገሮችን በ0574410224 መጠቆም እንደሚቻል ተመላክቷል።
በሌላ በኩል ፤ ማንኛውም የጸጥታ አካል ከተመደበው መደበኛ ሠራዊት ውጪ የተጣለውን የሰዓት እላፊ ገደብ አልፎ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ በቁጥጥር ስር እንደሚውል ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።
@tikvahethiopia