#HadiyaZone
የሆሣዕና ከተማ ከንቲባ አቶ አብርሃም መጫ የሃዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ።
ዛሬ የሀዲያ ዞን ምክር ቤት አስቸካይ ጉባዔ አካሂዶ አቶ አብርሃም መጫን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።
አቶ አብርሃም መጫ የዞኑን ህዝብ በታማኝነትና በትጋት ለማገልገል በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለማላ ፈጽመዋል።
አቶ አብርሃም መጫ የዞኑ አስተዳዳሪ ሹመት ከመቀበላቸው በፊት የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ በመሆን ሲያገለግሉ እንደነበር የዞኑ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
እባካችሁ ወላጆች ልጆቻችሁን ጠብቁ ! በአዲስ አበባ በትናንትናዉ እለት ሁለት ታዳጊዎች ወንዝ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስን ዋቢ አደርጎ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል። ታዳጊዎቹ ለሞት የተዳረጉት ኳስ ለማወጣት ወደ ወንዝ በመግባታቸዉ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል። አደጋዉ የደረሰዉ ትናንት 9፡00 አካባቢ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስር በተለምዶ "…
ወላጆች ልጆቻችሁን ጠብቁ !
ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ዋና እንዋኛለን ብለው ወንዝ ውስጥ ከገቡ 2 ልጆች የአንዱ ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገልጿል።
ህይወቱ ያለፈው የ12 ዓመት ታዳጊ መሆኑ ተነግሯል።
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ " .. ወረዳ አንድ ለቡ አርሴማ አካባቢ ነው በአንድ ወንዝ ውስጥ እድሜያቸው የ8 እና የ12 ዓመት ታዳጊዎች ዋና ለመዋኘት በሚል ነው ወንዝ ውስጥ ገብተው ዋና ሲዋኙ የ12 ዓመት ታዳጊው ህይወቱ አልፏል።
የ8 ዓመቱ ታዳጊ በአካባቢው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተረባርበው እሱን ከነህይወቱ አውጥተውታል።
ጥሪው ለኛ ቢመጣም እኛ ከመድረሳችን በፊት ህይወቱ የተረፈውን የ8 ዓመት ታዳጊ እና የሞተውን ልጅ የአካባቢው ህብረተሰብ አውጥተውታል " ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።
በዚህ ወር ብቻ ዋና ለመዋኘት በሚል ወንዝ ከገቡት 3 ልጆች ህይወታቸው አልፏል።
የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ፤ ወላጆች አሁን ትምህርት ቤት የሚዘጋበት ወቅት በመሆኑ ታዳጊዎች ወደ ወንዝ እንዳይሄዱ ማድረግ በከተማው ያሉ ገደላማ እና ውሃ የሚያቁሩ ቦታዎችን መከለያ በማበጀት ልጆችን ከአደጋ መጠበቅ ይገባል ሲል ማሳሰቡን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

#ችሎት
የቀድሞ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና ሌሎችም በሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው የመርከብ ግዢ እና እርሻ መሳሪያ ክስ ላይ የመከላከያ ምስክርነታቸው በአካል ቀርበው እንዲያሰሙ #በድጋሚ ታዘዘ።
ቀደም ሲል በቨርቹዋል ቴክኖሎጂ እንዲመሰክሩ ታዞ የነበረው ትዛዝ ተቀይሮ ነው በአካል ቀርበው እንዲመሰክሩ የታዘዘው።
ከሁለት ወር በፊት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ሜ/ጀ ክንፈ ዳኘው የእርሻ መሳሪያና የመርከብ ግዢ ሙስና ክስ ላይ በተቆጠሩበት የመከላከያ ምስክርነት በተደጋጋሚ እንዲቀርቡ ትዛዝ ተሰጥቶ ባለመቅረባቸው ምክንያት ታስረው እንዲቀርቡ መታዘዙ ይታወሳል።
" መጥሪያ ሳይደርሰኝ ታስሬ እንደበር የተሰጠው የፍርድ ቤት ትዛዝ ተገቢ አይደለም " ሲሉ ከኢትዮጲያ ውጪ እንደሚገኙና የስራ ጫና እንዳለባቸው አመላክተው በአካል ለመቅረብ እንደሚቸገሩ በመግለጽ ባሉበት ቦታ የምስክርነት አሰማሙ ቨርቹዋል ቴክኖሎጂ እንዲሆንላቸው ጠይቀው ነበር።
ያንብቡ : https://telegra.ph/Tarik-Adugna-07-04
Credit : Journalist Tarik Adugna

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤት ብይን ተሰጠ።
የ ሳምንታዊው “ ፍትሕ ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የ100 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ተሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ብይኑን በአብላጫ ድምጽ ያስተላለፈው በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንዳይደር አስነብቧል።

#እናት_ፓርቲ #ድርድር
እናት ፓርቲ የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነት በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ ለማድረግ የታሰበውን ድርድር እንደሚገፍ ገልጾ ነገር ግን በሁለቱ ፓርቲዎች (ብልፅግና እና ህወሓት) መካከል የሚደረግ እንዳይሆን ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብሏል።
ፓርቲው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በላከልን መግለጫው ነው ይህን ያለው።
እናት ፓርቲ ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውና ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀረው ጦርነት ምን አልባት ኢትዮጵያ በታሪኳ ከጋጠሟት ጥፋቶችና ውድመቶች ሁሉ ከቀዳሚዎቹ ሊቆጠር የሚችል ነው ብሏል።
ጦርነቱ ሰዋዊ፣ ቁሳዊ፣ ሥነ ልቡናዊና ድፕሎማሲያዊ ጉዞን ለብዙ አሥርት ዓመታት ወደኋላ መልሷል ያለ ሲሆን ይህ ጦርነት ሊያመጣ የሚችለው ምስቅልቅልና ዳፋ አሳስቦት በእርቅና ሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሽምግሌዎችን ከማፈላለግ ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሷሳ።
አሁንም ያ ውድመትና ውረድ እንውረድ ዳግም እንዳይከሰት ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት የታየው መነሳሳት በደስታ የሚመለከተው ኩነት መሆኑን ገልጿል።
በመጀመሪያ ችግሩ እንዳይከሰት ብንከላከለው ጥሩ ነበር ከተከሰተ በኋላ የውጭ አካል ገብቶ በድርድር መልክ ከሚፈታ ይልቅ በሀገሬው ባህል በእርቅና ይቅርታ ቢፈታ መልካም ነበር ሲል ገልጿል።
ይህ ድርድር ብዙ ውስብስብ ጉዳዮችን ተሸክሞ የሚደረግ ነው ያለው ፓርቲድ ስለሆነም ሂደቱ ከቅድመ ድርድር ጀምሮ ዘለቄታዊ መፍትሔ በሚያመጣ መልኩ ታቅዶ ካልተፈጸመ እና የውጭ ኃይሎችን "አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት መከላከል ካልተቻለ ጅብ ፈርቶ ዛፍ ብወጣ፣ ነብር ቆየኝ” ዓይነት መሆኑ አይቀሬ ነው ሲል አስጠንቅቋል።
ፓርቲው ለድርድሩ ውጤታማነት ወሣኝ ናቸው ያላቸውን ነጥቦችን አንድ በአንድ ዘርዝሮ በመግለጫው አስቀምጧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

" ከሟቾች መካከል ሴቶች እና ህፃናት ይገኙበታል " - የቲክቫህ አባል
ዛሬ በቄለም ወለጋ ለምለም ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል።
እሱና ቤተሰቦቹ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ አባል ዛሬ የተፈፀመው ጭፍጨፋ እጅግ በጣም አሳዛኝ እንደነበር ገልፆ በርካታ ሰው ተገድላል፤ ሴቶች እና ህፃናትም ይገኙበታል ብሏል።
በአካባቢው ኔትዎርክ ይሰራ ነበር አሁን ላይ እየሰራ አይደለም ቤተሰቦቼ ቦታው ላይ ነበሩ አምልጠው ማቻራ የምትባል አካባቢ ገብተዋል ፤ ሲል ገልጿል።
ጥቃቱን እስካሁን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አረጋግጠዋል ፤ " ጨፍጫፊዎቹ የሸኔ ቡድን " ናቸው ብለዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " የጸጥታ አካላት ከሚያደርሱበት ዱላ የፈረጠጠው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በዜጎች ላይ አደጋ እያደረሰ በመሸሽ ላይ ነው " ብለዋል።
" በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል " ሲሉ ፅፈዋል።
" በዜጎቻችን ላይ በደረሰው መከራ እያዘንን ይሄንን አሸባሪ ቡድን እስከመጨረሻው ተከታትለን ከህዝባችን ጋር እናስወግደዋለን። " ሲሉም አክለዋል።
ከጥቂት ቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ መንግስት በይፋ ባመነው ብቻ ከ300 በላይ ሰዎች መጨፍጨፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ ተገድለው የተቀበሩ በአንድ አካባቢ ብቻ እስከ 600 እንደሚደርስ ቤተስቦቻቸው እዛው ያሉ የቲክቫህ አባላት መናገራቸው አይዘነጋም። አንዳድን ተቋማት ቁጥሩን ከዚህም ከፍ ያደርጉታል።
አሁንም ንፁሃን ፣ ምንም ስለፖለቲካ የማያውቁ ህፃናት፣ ሴቶች እየተገደሉ ሲሆን ከቀናት በፊት የነበረው የንፁሃን ጭፍጨፋ ሰሞነኛ አጀንዳ ሆኖ አልፎ ነበር።
በድጋሚ የመንግስት ተቀዳሚው ተግባሩ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ በመሆኑ ለንፁሃን ዜጎች ጥበቃ ሊደረግ ይገባል።

" እባካችሁ እየተጠነቀቃችሁ አሽከርክሩ " - የአለታ ጩኮ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት
በትራፊክ አደጋ እስካሁን ቁጥራቸውን በትክክል መለየት ያልተቻለ ወገኖቻቸችን ህይወት አለፈ።
ዛሬ በሲዳማ ክልል አለታ ጩኮ ከተማ መግቢያው ላይ ዛሬ በደረሰ አደጋ የጉዳቱን መጠን ማወቅ ባይቻልም ከፍተኛ የሚባል ጉዳት ደርሷል።
የአለታ ጩኮ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በፎቶም አስደግፈው በላኩት መልዕክት አንድ በተለምዶ ዶልፊን እያተባለ የሚጠራው የህዝብ ማመላለሻ መኪና (ከሀዋሳ አቅጣጫ ሲመጣ የነበረ) እና " ሰላም ባስ " (ከሞያሌ አቅጣጫ ሲመጣ የነበረ) ተጋጭተው በደረሰው እጅግ በጣም ዘግናኝ አደጋ የሰዎች ህይወት አልፏል፤ ጉዳትም ደርሷል ብለዋል።
አጠቃላይ የጉዳቱን መጠን ግን እንደማያውቁ አስረድተዋል።
ቤተሰቦቻችን የሰውን ህይወት ኃላፊነት ወስደው መኪና የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች በጥንቃቄ እንዲያሽከረርኩ አደራ ብለዋል።
#Biruk #Ephrem

" ከሟቾች መካከል ሴቶች እና ህፃናት ይገኙበታል " - የቲክቫህ አባል ዛሬ በቄለም ወለጋ ለምለም ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል። እሱና ቤተሰቦቹ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ አባል ዛሬ የተፈፀመው ጭፍጨፋ እጅግ በጣም አሳዛኝ እንደነበር ገልፆ በርካታ ሰው ተገድላል፤ ሴቶች እና ህፃናትም ይገኙበታል ብሏል። በአካባቢው ኔትዎርክ ይሰራ ነበር አሁን ላይ እየሰራ አይደለም ቤተሰቦቼ…
የቄለም ወለጋው ጥቃት ...
" ... ጥቃት አድራሾቹ እጅግ በጣም የታጠቁ እና የተደራጁ ናቸው።
እዛ ያለው ማህበረሰብ ምስኪን ገበሬ ነው የዕለት ጉርሱን ዳፋ ቀና ብሎ የሚያገኝ ነው።
መብራት እንኳን በቅጡ የሌለው አካባቢ ነው። ከቦቀሎ እና ማሽላ እንጀራ በዘለለ የማይበላ ፤ በኑሮው የተጎሳቆለ ማህበረሰብ ነው እንኳን ጥይት እና ገጀራ ሊገባው ! እጅግ ምስኪን ማህበረሰብ ነው ።
ሰው ወዳድ ናቸው ፤ እንግዳም ተቀባይ ናቸው ፤ ያላቸውን አውጥተው የሚያስተናግዱ ናቸው። ፍርድ ከላይ ነው ፤ ፍርድ ከአላህ ነው ለዛ ማህበረሰብ ይሄ አይገባውም ነበር።
በሚያሳዝን ሁኔታን የማህበረሰቡን ሮሮ፣ ጩኸት ማን እንደሚሰማው አናውቅም። ጥቃት አድራሾቹን ማን ሃይ እንደሚላቸውም አናቅም።
ለማን አቤት እንደምንል ግራ የሚገባ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ባለፈው ከፍ ብሎ ጊምቢ አካባቢ በጣም ብዙ ሰው በተሰመሳሳይ ሁኔታ ተጨፍጭፏል።
ዘር እየተመረጠ ሰው የሚጨፈጨፍበት ጊዜ ላይ ደረስን ፤ ለማን አቤት እንደምንል አናውቅም " - በአከባቢው ቤተሰቦቹ ያሉ የቲክቫህ አባል ከተናገርው በጥቂቱ
ከላይ ያለው መልዕክት እየተላኩት ካሉ በርካታ መልዕክቶች አንዱ ነው። ቤተሰቦቻቸው እዛ ያሉ የቲክቫህ አባላት መልዕክት እየላኩ ነው።
ዛሬ ጭፍጨፋ በተፈፀመበት አካባቢ አስክሬን የመሰብሰብ ስራ እየተሰራ ሲሆን ፤ መከላከያውም በቦታው አለ ተብሏል።
እጅግ በርካታ ሰዎች ፤ ምንም ማያውቁ ምስኪን ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ የተጨፈጨፉት። በርካቶች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ መቻራ መሄዳቸውን ለማውቅም ተችሏል።
አሁንም አጠቃላይ ቀጠናውን ደህንነት ማረጋገጥ ካልተቻለ ሌላ ጥቃት ይፈፀማል የሚል ስጋት አይሏል።
(ውድ ቤተሰቦቻችን መልዕክቶችን አደራጅተን እንደጨረስን እንልካለን)

" በትንሹ 150 ሰዎች ተገድለዋል "
ቢቢሲ አፍሪካ ዛሬ ማምሻውን ይዞት በወጣው ዘገባ በኦሮሚያ ክልል፣ ሀዋ ገለን ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት በትንሹ 150 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።
ቢቢሲ አፍሪካ ፤ የአይን እማኞች ጥቃቱ በሀዋ ገላን ወረዳ መፈፀሙን እንደገለፁለትና በአካባቢው ላይ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር አክሏል።

" በትንሹ 150 ሰዎች ተገድለዋል " ቢቢሲ አፍሪካ ዛሬ ማምሻውን ይዞት በወጣው ዘገባ በኦሮሚያ ክልል፣ ሀዋ ገለን ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት በትንሹ 150 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል። ቢቢሲ አፍሪካ ፤ የአይን እማኞች ጥቃቱ በሀዋ ገላን ወረዳ መፈፀሙን እንደገለፁለትና በአካባቢው ላይ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ እንደነበር አክሏል። @tikvahethiopia
#EHRC
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በሃዋ ገላን ወረዳ (መንደር 20 እና መንደር 21) ላይ ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ ንፁሀን ዜጎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ መፈጸሙን ሪፖርት እንደደረሰው ገልጿል።
ኮሚሽኑ ሁኔታውን እየተከታተለ መሆኑና እና ከአካባቢው ተርፈው የሸሹ ሰዎችን ማረጋገሩን አመልክቷል።
ኮሚሽኑ ጥቃቱ ያደረሱት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ሸኔ) አባላት መሆናቸውንና ግድያውም ከጥዋት አንስቶ መጀመሩን ምንጮቼ አመልክተዋል ብሏል።
ኢሰመኮ የመንደር 20 እና መንደር 21 ነዋሪዎች በዋናነት የአማራ ብሄር ተወላጆች መሆናቸውን መረዳቱንም ገልጿል።
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ወደ አካባቢው መድረሳቸው ተነግሯል ያለው ኢሰመኮ ነዋሪዎቹ ግን ወደ ሌላ ቦታ ሄደው መጠለላቸውን ቀጥለዋል ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።
የኢሰመጉ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ " በአካባቢው የቀጠለው የጸጥታ ችግር እና በነዋሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ብሔር ተኮር ግድያ በአስቸኳይ መቆም አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።
ተጨማሪ የንፁሃንን ሞት ለመከላከል መንግስት የፀጥታ ኃይሉን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

" ያለበት እስካሁን አልታወቀም " የገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ቤተሰቦች ልጃቸው አሁንም የት እንዳለ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልፀዋል። በልጃቸው አድራሻ አለመታወቅ ሳቢያ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የወደቁት ቤተሰቦች ልጃቸውን የወሰደ አካል በሰላም እንዲመልስ እየጠየቁ ይገኛሉ። " ጥፋት ካለበት አይጠየቅ እያልን አይደለም " ያሉት ቤተሰቦቹ መንግስት አስሮትም ከሆነ አድራሻውን እንዲያሳውቃቸው ህግን ባከበረ መልኩ…
#Update
ለቀናት ያህል የት እንደነበር ያልታወቀው ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ትላንት ምሽት ወደቤቱ መመለሱ ታውቋል።
ገጣሚ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ፤ " ከልዑል እግዚአብሔር ቀጥሎ ላዘናችሁልኝ ፣ ለራራችሁልኝ ፣ ለተጨነቃችሁልኝ ፣ ድምፅ ለሆናችሁኝ ሁሉ ከልቤ አመሠግናለሁ ። በህይወት ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ ። ደህና ነኝ " ኢትዮጵያ ለዘልዓለም ትኑር " ሲል ፅፏል።
ገጣሚው በማን ፣ እንዴት እንደተወሰደ እንዲሁም የት እንዳነበረ በዝርዝር አልፃፈም።
ባለፉት 7 ቀናት ያለበት ባለመታወቁ እናት እና አባቱ አጠቃላ ቤተሰቦቹ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ወድቀው እንደነበር እና መንግስትም ሆነ ሌላ አካላ ልጃቸውን በሰላም እንዲመልስላቸው ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።