TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Monkeypox (Ethiopia) በኢትዮጵያ ፤ በዝንጀሮ ፈንጣጣ ሳይያዙ አልቀሩም ተብሎ #የተጠረጠሩ 2 ሰዎች ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጋቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ምንም በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር / ኬዝ ካለበራቸው አሁን ላይ የተጠረጠሩ ኬዞችን ለዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ካደረጉ 7 ሀገራት አንዷ ናት ተብሏል (ሀገራቱ ኢትዮጵያ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ሞዛምቢክ ፣…
#Update

ጤና ሚኒስቴር " የዝንጀሮ ፈንጣጣ " በሽታ በኢትዮጵያ አልተከሰተም የተለየም ሰው የለም ሲል አሳወቀ።

ሚኒስቴሩ የሪፖርተር ጋዜጣን ዘገባም ትክክለኛ እንዳልሆነ ገልጿል።

" የዝንጀሮ ፈንጣጣ በኢትዮጵያ ተከስቶ ሁለት ሰዎች ተለይተዋል (ኳረንቲን ገብተዋል) የሚል መረጃ በሪፖርተር ጋዜጣ ወጥቶ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ነው " ያለው ሚኒስቴሩ " በሽታው በሌሎች ሀገራት ቢከሰትም በኢትዮጵያ እስካሁን የተያዘም ሆነ የተለየ ሰው የለም " ብሏል።

የሚዲያ አካላት ያልተረጋገጠና በሚመለከተው አካል ያልቀረበ መረጃን ከማሰራጨት ይቆጠቡ ሲልም አሳስቧል።

ወቅታዊ የጤና መረጃዎችን እንዲሁም የማህበረሰቡ የጤና ስጋት የሚሆኑ ወረርሽኞችን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ከጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ ማግኘት ይገባል ብሏል።

ሪፖርተር ጋዜጣ ትላንት ታትሞ በተሰራጨው እትሙ በኢትዮጵያ ከዝንጀሮ ፈንጣጣ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች ተለይተው መቀመጣቸውን አስነብቧል።

ጋዜጣው ስማቸውን እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የጤና ሚኒስቴር ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ባስነበበው ዘገባው የግለሰቦቹ ናሙና ወደ ውጭ ሀገር መላኩን አመልክቷል።

ነገር ግን ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ የተያዘም ሆነ የተለየ (ኳራንቲን) የገባ ሰው የለም ሲል የሪርተር ጋዜጣን ዘገባ ስህተት መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በድሃ ጎኔ ያሳደኩት ልጄ ነው " ከቀናት በፊት ማንነታቸውን እስካሁን መለየት ባልተቻሉ አካላት የተወሰደው ገጣሚ በላይ ቀበለ ወያ እስካሁን ያለበት እንደማይታወቅ ቤተሰቦቹ አመልክተዋል። እናት ፦ " ልጄን በሰላም መልሱልኝ የወሰደ አካል፤ መንግስትም ይሁን ሌላም አካል ከሆነ ልጄን በሰላም መልሱልኝ። በድሃ ጎኔ ያሳደኩት ነው። በደሃ ጎኔ ነው ያሳደኩት ጥፋት ካለው አይጠየቅ አይደለም ፤ ጥፋት ካለው…
" ያለበት እስካሁን አልታወቀም "

የገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ቤተሰቦች ልጃቸው አሁንም የት እንዳለ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልፀዋል።

በልጃቸው አድራሻ አለመታወቅ ሳቢያ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ የወደቁት ቤተሰቦች ልጃቸውን የወሰደ አካል በሰላም እንዲመልስ እየጠየቁ ይገኛሉ።

" ጥፋት ካለበት አይጠየቅ እያልን አይደለም " ያሉት ቤተሰቦቹ መንግስት አስሮትም ከሆነ አድራሻውን እንዲያሳውቃቸው ህግን ባከበረ መልኩ እንዲሰራ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው።

ገጣሚው በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ እንደተወሰደ ከተሰማ ዛሬ 6ኛ ቀኑ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ዛሬ ጥዋት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ነው ከመኖሪያ ቤቱ የተወሰደው " ጠበቃ ታደለ ገ/መድህን ከጥቂት ቀን በፊት በዋስ ከእስር የተለቀቀው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ዛሬ በድጋሚ መታሰሩን ለማወቅ ተችሏል። ጠበቃ ታደለ ገ/መድህን ፥ ዛሬ ጥዋት ከመኖሪያ ቤቱ ሲቪል የለበሱ የፀጥታ አካላት እንደወሰዱትና ወዴት እንደወሰዱት እንደማያውቁ ገልፀዋል፤ ያለበትን ቦታ ለማወቅም እያፈላለጉ መሆኑን አክለዋል። በሌላ መረጃ…
" ተጨንቀናል ያሉበትን አሳውቁን " ቤተሰቦች

ከቀናት በፊት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከቤቱ የተወሰደው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እስካሁን ያለበትን ማወቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቹ ገለፁ።

ቤተሰቦቹ ዛሬ በላኩልን መልዕክት ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ/ም 7 ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከቤቱ ከወሰዱት በኃላ እስካሁን ድረስ ያለበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ አስረድተዋል።

" ፌዴራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ ብንፈልገውም ልናገኘው አልቻልም ፤ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ብናመለክትም ከፌዴራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ ውጭ እንደሆኑ ነው የነገረን " ሲል አሳውቆናል ሲሉ ገልፀዋል።

ቤተሰቦች በያየሰው ሽመልስ ቦታ አለመታወቅ ከፍተኛ ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ገልፀው የወሰዳቸው አካል ያለበትን ብቻ እንዲያሳውቃቸው ተማፅነዋል።

ጋዜጠኛ ያየሰው ከጥቂት ቀናት በፊት ነበር በ10 ሺ ብር ዋስ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲለቀቅ ወስኖለት የተለቀቀው። ከዚህ በኃላ ነው በድጋሚ የተያዘው።

በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በተወሰደ ከአንድ ቀን በኃላ ጋዜጠኛ አበበ ባዩ ምሽት 4:30 ሲቪል በለበሱ ሰዎች የተወሰደ ሲሆን ቤተሰቦቹ እሱንም እካሁን ማግኘት እንዳልቻሉ አመልክተዋል።

ፌዴራል ፖሊስ እና አ/አ ፖሊስ መጠየቃቸውን ነገር ግን እንዳላገኙት ፤ ያለበትን ለማወቅም ለኢሰመኮ ቢያመለክቱም ያለበትን ለማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀዋል።

የአበበ ባዩ ቤተሰቦችም ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ገልፀው የወሰዳቸው አካል ያለበትን ቦታ እንዲያሳውቃቸው ተማፅነዋል።

ጋዜጠኛ አበበ ባዩ ከጥቂት ወራት በፊት ለእስር ተዳርጎ መፈታቱ የሚታወስ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ገባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል። ፓርቲው ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ ነው። ዛሬ እና ነገ በሚቆየው የፓርቲው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲውን መሪ ጨምሮ ለከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ምርጫ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪ ጉባኤው በተለያዩ ጉዳዮች ተወይያቶ ውሳኔ ያሳልፋል ፤ በሀገራዊ ጉዳዮች…
#Update

ኢዜማ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች እየመረጠ ነው።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ትላንት ቅዳሜ ሰኔ 25/2014 ዓ/ም የጀመረውን አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ገባኤው በዛሬው ዕለት ቀጥሏል።

በአሁን ሰዓት የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች የመምረጥ ሂደት እየተካሄደ እንደሚገኝ ታውቋል።

Photo Credit : EZEMA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኢዜማ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች እየመረጠ ነው። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ትላንት ቅዳሜ ሰኔ 25/2014 ዓ/ም የጀመረውን አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ገባኤው በዛሬው ዕለት ቀጥሏል። በአሁን ሰዓት የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች የመምረጥ ሂደት እየተካሄደ እንደሚገኝ ታውቋል። Photo Credit : EZEMA @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ከፍተኛ አመራሮችን ለመምረጥ ሚስጥራዊ የድምፅ አሰጣጥ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ፓርቲውን ለመምራት እየተወዳደሩ የሚገኙት እጩዎች ባለፉት ሳምንታት ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበረ ሲሆን ዛሬ የመጨረሻው ውጤት የሚለይበት ነው።

በተለይም ደግሞ ለፓርቲው መሪነት የሚወዳደሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና አቶ አንዱአለም አራጌ ውጤትን በርካታ የፓርቲው ደጋፊዎች የሚጠብቁት ነው።

Photo Credit : EZEMA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢዜማ የኢዜማ የአመራሮች ምርጫ ውጤት እስካሁን (ምሽት 4:18 ድረስ) ይፋ ያልሆነ ሲሆን ፓርቲው ቆጠራው እንደተጠናቀቀ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል። የጉባኤው አባላት የአመራሮችን ምርጫ ውጤት እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ተከታትለን እናሳውቃለን ! @tikvahethiopia
#Update

ኢዜማ ውጤት ይፋ ማድረግ ጀመረ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው የአመራሮች ምርጫ ፦

- አቶ አበበ አካሉ - የኢዜማ ዋና ፀሀፊ
- ዶ/ር ጫኔ ከበደ - የኢዜማ ሊቀመንበር
- ዶ/ር አማኑኤል ኤርሞን - ምክትል ሊቀመንበር
- አቶ አንድነት ሽፈራውን የፋይናንስ ኃላፊ አድርጎ መርጧል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜማ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢዜማ የኢዜማ የአመራሮች ምርጫ ውጤት እስካሁን (ምሽት 4:18 ድረስ) ይፋ ያልሆነ ሲሆን ፓርቲው ቆጠራው እንደተጠናቀቀ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል። የጉባኤው አባላት የአመራሮችን ምርጫ ውጤት እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ተከታትለን እናሳውቃለን ! @tikvahethiopia
#NewsAlert #ኢዜማ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ መሪ ፤ አርክቴክት ዮሐንስ ደግሞ ምክትል መሪ ሆነው ተመረጡ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ምርጫ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋን እና አርክቴክት ዮሐንስ መኮንንን የኢዜማ #መሪ እና #ምክትል_መሪ አድርጎ መርጧል፡፡

በጉባኤው ላይ ወደ 900 ገደማ የፓርቲው አባላት ያተሳተፉ ሲሆን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ 549 ድምፅ ማግኘታቸው ተገልጿል።

ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ለመሪነት የተወዳደሩት አቶ አንዱአለም አራጌ 326 ድምፅ ነው ያገኙት። አቶ አንዱአለም ከፓርቲው ምስረታ አንስቶ የፓርቲው ምክትል መሪ ሆነው ቆይተዋል።

ለምክትል መሪነት የተወዳደሩት አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን በጉባኤው የተመረጡ ሲሆን ለቦታው በተፎካካሪነት ቀርበው የነበሩት አቶ ሀብታሙ ኪታባ ነበሩ።

@tivahethiopia