#DireDawaUniversity
በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በጊዚያዊነት ተመድበው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ነባር ተማሪዎች " ግቢው ውጡ አለን " ሲሉ ቅሬታቸውን አድርሰውናል።
ተማሪዎቹ "ግቢውን ለቀን እንድንወጣ ተነግሮናል"፣ "የምግብ አገልግሎትም ተቋርጦብናል" ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀርባሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት መገርሳ ቃሲም (ዶ/ር) ተከታዩን ምላሽ ሰጠውናል።
"መደበኛ ነባር ተማሪዎች በግቢው መቆየት የሚችሉት እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ብቻ ነው። ከሰኔ 30 በኋላ ዩኒቨርሲቲው የክረምት ተማሪዎችን ይቀበላል። በመሆኑም መደበኛ ነባር ተማሪዎችን የምናቆይበት አሰራር የለም።"
"በኮቪድ-19 ምክንያት የተደራረቡና የምንቀበላቸው 5 ሺህ የሚሆኑ የክረምት ተማሪዎች አሉብን። በቅርቡ የተቀበልናቸው የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ነው የሚገኙት። ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ የበጀት እጥረት ገጥሞናል።"
በመሆኑም ሁሉም መደበኛ ነባር ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ተቋሙ በአካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት ነው የሚሰራው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲውን ውሳኔ ሊያከብሩ ይገባል ብለዋል።
More : @tikvahuniversity

TIKVAH-ETHIOPIA
#SUDAN #DrWorknehGebeyhu የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በሱዳን የአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ዋና ፀሀፊው በስራ ጉብኝታቸው ከሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን አሳውቀዋል። በውይይቱ ኢጋድ ማክሰኞ ዕለት በኬንያ፣ ናይሮቢ…
#Update
እጅግ በጣም በወሳኝ ሰዓት ይደረጋል ያተባለው የኢጋድ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል።
በዚሁ ስብሰባ ላይ የአባል ሀገራት መሪዎች ናይሮቢ እየገቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።
ናይሮቢ ከደረሱ መሪዎች መካከል የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የሱዳኑ ወታደራዊ አስተዳደር መሪ እና የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ይጠቀሳሉ።
ከኢጋድ ስብሰባ ጎን ለጎን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን በወቅታዊ ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
የዛሬው የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እጅግ በጣም በወሳኝ ሰዓት የሚደረግ ስብሰባ ሲሆን የቀጣናው ጉዳይ ላይ በመሪዎች አማካኝነት ይመከርበታል።
መሪዎች ቀጠናውን በሚያሳስቡ ጉዳዮች ላይ ፣ ለሰላም እና ደህንነት እንቅፋት ስለሆኑ ጉዳዮች ፣ በድርቁ ሁኔታ ላይ በጥልቀት ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Photo Credit : IGAD & PMOEthiopia
@tikvahethiopia

Photo
#SUDAN
ሲቪል አስተዳደሩን ገልብጠው ሙሉ በሙሉ ስልጣን ከተቆጣጠሩ ጊዜ አንስቶ በሱዳናውያን ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እያስተናገዱ ያሉት ሌ/ጄነራል አብዳልፈታህ አልቡርሃን ጦሩ ቦታውን እንደሚለቅ ተናግረዋል።
ትላንት ሰኞ ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን በቴሌቫዥን ቀርበው የሱዳን ጦር ኃይል አገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ለማድረግ ቦታውን ይለቃል ብለዋል።
የአገሪቱ ጦር ኃይል ሱዳን ወደ ዴሞክራሲ ለምታደርገው ሽግግር እንቅፋት እንደማይሆንና ምርጫ እንዲደረግ ወስኖ እየሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ጨምረውም በአገሪቱ ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማብቃት ከሲቪል ቡድኖች ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ ጦር ሠራዊቱ የሚያደርገውን ተሳትፎ እንደሚያቋርጥ አሳውቀዋል።
ነገር ግን አገሪቱ ውስጥ ምርጫ ስለሚደረግበት እንዲሁም ጦር ኃይሉ ሥልጣን ስለሚያስረክብበት ሂደት የጊዜ ሰሌዳ ምንም አላሉም።
በሱዳን ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰረት የሚጠይቁት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሠራዊቱ ከፖለቲካው እንዲወጣ በመጠየቅ ለወራት የዘለቀ ተቃውሞ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል ሲል ቢቢሲ ፅፏል።

#ችሎት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቅ በፍርድ ቤት ብይን ተሰጠ። የ ሳምንታዊው “ ፍትሕ ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የ100 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብይን ተሰጥቷል። ፍርድ ቤቱ ብይኑን በአብላጫ ድምጽ ያስተላለፈው በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ…
" ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አልተፈታም " - ቤተሰቦቹ
የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን እንዲያከበር ጠየቁ።
ትናንት ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ100 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ መወሰኑ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም ቤተሰቦቹ ለዋስትና የተጠየቀውን ብር አስይዘው የመፈቻ ወረቀቱን ይዘው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ሦስተኛ) ቢሄዱም ፍቺውን የሚያስፈፅም አካል ባለመኖሩ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገንን ሳይፈታው እንዳሳደረው ገልፀዋል።
በዛሬው ዕለትም ቤተሰቦቹ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ሦስተኛ) ቢገኙም እስካሁኑ ሰዓት ድረስ አራት የሚሆኑ መርማሪ ፖሊሶች፥ የመርማሪ ፖሊስ ሀላፊዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሩን ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀዋል።
በዚህም እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤቱ የወሰነው የፍቺ ጉዳይ መቋጫ አላገኘም ብለዋል።
የሚመለከታቸው አካላት ህግ እና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲከበር ጫና እንዲፈጥሩ ጠይቀዋል።
Via Tariku Desalgn

#Update እጅግ በጣም በወሳኝ ሰዓት ይደረጋል ያተባለው የኢጋድ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል። በዚሁ ስብሰባ ላይ የአባል ሀገራት መሪዎች ናይሮቢ እየገቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል። ናይሮቢ ከደረሱ መሪዎች መካከል የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የሱዳኑ ወታደራዊ አስተዳደር መሪ እና የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ይጠቀሳሉ። ከኢጋድ ስብሰባ ጎን ለጎን ጠ/ሚ ዶ/ር…
#SUDAN #ETHIOPIA
የኢትዮጵያ እና የሱዳን ጉዳይ !
ኢትዮጵያ እና ሱዳን በመካከላቸው ያሉ ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸው ገለፁ።
ኬንያ ፤ ናይሮቢ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል-ቡርሃን ጋር ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " ሁለቱ ሀገራት በሰላማዊ መንገድ ሊሠሩባቸው የሚችሉ በርካታ የትብብር መሠረቶች እንዳሏቸው አረጋግጠናል " ብለዋል።
" ያለን ትሥሥር ከየትኛውም መከፋፈል የሚበልጥ ነው " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " ሁለታችንም ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮችን #በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኝነታችንን ገልጸናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

#ዝርፊያ
የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች በተለያየ ጊዜ ዘረፋን ጨምሮ እስከ ግድያ የሚደረስ ወንጀል ይፈፀምባቸዋል።
ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ሰምተናል።
ከሰሞኑን አንድ በዚሁ በኤሌክቶኒክ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ሚሰራ ሰራተኛ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት አመክቷል።
ስሙ ሚኪያስ ተፈሪ የተባለው ወንድማችን ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራባትን መኪና ይዞ ቆሞ ሥራ ሲጠባበቅ ነበር (ባለፈው ረቡዕ ምሽት)።
ከአገግልሎት ሰጪ ድርጅቱ ተደውሎ ከሳሪስ ጀሞ ሥራ እንዲሄድ ይጠየቃል ፤ የድርጅቱን ትእዛዝ ተቀብሎ ሦስት ሰዎችን አሳፍሮ ወደታዘዘበት ጀሞ ይሄዳል።
ደንበኞቹ ያሉበት ጀሞ ደረሱ። " ሂሳብ ስንት ቆጠረ?" ብለው ጠየቁ። ሂሳቡን ነገራቸው። እነርሱ ግን በያዙት ስለት አስፈራርተው መኪናውን ነጥቀው ተሰውሩ።
ሚኪያስ ቤተሰቡን የሚያስተዳድርበትን መኪና በዚህ መንገድ ተነጥቋል። ሚኪያስ ለፖሊስ ጣቢያ ድርጊቱን አሳውቋል። እስከዛሬ ሰኞ ድረስ አንዳችም ፍንጭ አልተሰማ።
መኪናው ከላይ በፎቶው የተያያዘ ሲሆን ታፋልጉት ዘንድ ጥሪ አቅርቧል ፤ (0922875988)
በሌላ በኩል ፤ በመሰል ስራ ላይ እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩ ወገኖች በተደጋጋሚ የሚሰሙት ዝርፊ እና ወንጀል ለስራቸው ስጋትን እየፈጠረ መሆኑን በመግለፅ የደህንነት ጉዳይ ይታሰብበት ፤ ወንጀለኞችንም ተከታትሎ አድኖ መያዝ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

#AASTU
የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች " ትምህርት ስለተጠናቀቀ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ እንደተባሉና ችግር ላይ መሆናቸውን" ገልጸውልናል።
በተለይ ከትግራይ ክልል የመጡ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ትራንስፖርት አለመኖሩ እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶችን በማንሳት መቸገራቸውን ያስረዳሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ የጠየቅናቸው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አለምእሸት ገብረወልድ ተከታዩን ምላሽ ሰጠውናል።
"መደበኛ ነባር ተማሪዎች እስካሁን በግቢው ነው የሚገኙት። ማንም የወጣ ተማሪ የለም።"
"የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በጉዳዩ ዙሪያ እየመከሩ ነው። የትኞቹ ተማሪዎች ናቸው መቆየት ያለባቸው በሚለው ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እየተወያዩ ነው።"
"ዩኒቨርሲቲው የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች የትኞቹ ናቸው የሚለውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ውሳኔው እንደሚያሳውቅ" ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የነዳጅ ድጎማ !
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በአዲሱ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ሥርአት ተጠቃሚ የማይሆኑ ተቋማትና ተሽከርካሪዎች በ4 ወራት ጊዜ ውስጥ ከመንግሥት የሚያገኙት የነዳጅ ድጎማ ሙሉ ለሙሉ ተነስቶ ዋጋውን ራሳቸው እንደሚሸፍኑ አስታውቋል።
ለ3 ወራት ግን መንግስት ከሚገዙት ነዳጅ ውስጥ ከ25 እስከ 75 በመቶ ዋጋ እንደሚደጉም ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል።
በሌላ በኩል ፤ ድጎማ የሚደረግላቸው የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ድጎማ ደግሞ በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ እንደሚነሳ ተገልጿል።
በዚህም መንግሥት በየስድስት ወሩ ተፈፃሚ በሚያደርገው ሥርዓት መሰረት 10 በመቶ ድጎማን እያነሳ የሚሄድ ሲሆን በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ በድጎማ የሚደገፋ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ የሚወጡ ይሆናል ተብሏል።
መረጃው የኢትዮ ንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እና WMCC ነው።

የነዳጅ ዋጋ 📈
ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።
በዚህ መሰረት ፦
👉 ቤንዚን በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም
👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም
👉 ኬሮሲን በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም
👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 53 ብር ከ10 ሳንቲም
👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ37 ሳንቲም
👉 የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 98 ብር ከ83 መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከላይ የተገለጸው የቤንዚን ፣ የኬሮሲን እና የነጭ ዋጋ ላይ ለህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ወይም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች 15 በመቶ በመንግስት እንዲደጎሙና ቀሪውን 10 በመቶ እንዲከፍሉ በማድረግ የድጎማ መጠኑን በቴሌ ብር ተመላሽ እንዲሆንላቸው ይደረጋል ተብሏል።
የተደረገው የዋጋ ማስተካከያ የተደረገባቸው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዝርዝር ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ሁሉ ተግባራዊ ይሆናል።
ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

#Oromia
የኢትዮጵያ ህ/ተ/ምክር ቤት አባሉ እና የብልፅግና ፓርቲው አባል ዶ/ር ሃንጋሳ ኢብራሂም ትላንት ምሽት በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ በአፋን ኦሮሞ (በጥቂቱ በአማርኛ) ያደረጉት ንግግር ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።
የም/ቤት አባሉ፤ 1:48:57 በፈጀው ንግግራቸው በኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና በኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ቢሮ ላይ ጠንካራ የሆነ ውንጀላ አሰምተዋል፤ በክልሉ ለሚሞቱ ንፁሃን እና ለፀጥታው ችግር አመራሮችን ወንጅለው ፌዴራል መንግስት ወደ እስር ቤት እንዲያስገባቸው ጥሪ አቅርበዋል።
የም/ቤት አባሉ ንግግር ከፍተኛ ትኩረትን የሳበው በምርጫ ተወዳደረው የህ/ተ/ም/ቤት አባል መሆናቸው ከዚህም አልፎ የብልፅግና ፓርቲ አባል መሆናቸው ነው።
ዶ/ር ሃንጋሳ ኢብራሂም በክልሉ ለንፁሃንን ሴቶች፣ ህፃናት፣ እናቶች ጭፍጨፋ ከፕሬዜዳንቱ፣ ከክልሉ የብልፅግና ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አንስቶ ተጠያቂ አድርገዋል።
የም/ቤት አባሉ "ክልሉ ውስጥ ሁለት አይነት ሸኔ ነው ያለው" ያሉ ሲሆን እውነተኛው ሸኔና ሳቦታጅ ሸኔ ነው ብለዋል። "ሳቦታጁ ሸኔ የሚመራው በኦሮሚያ ክልል አመራር ነው። የኦሮሚያው ክልል አመራር እና የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ቢሮ ከእነአመራራቸው ከነካቢኔዎቻቸው ካልተፈረካከሱ በቀር በጭራሽ ሞት፣ ግድያ በኦሮሚያ ሊቆም አይችልም" ብለዋል።
ለሚናገሩት ነገርም ተጨባጭ መረጃ እንዳለቸው ገልፀዋል።
"የሀዘን መግለጫ ቋቅ አለን" ያሉት የምክር ቤት አባሉ የዶ/ር ዐቢይ አስተዳደር የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኢሌ ላይ የወሰደውን አይነት እርምጃ በኦሮሚያም እንዲወስድ እና ክልሉ በአዲስ አመራር እንዲመራ ጠይቀዋል።
እስካሁን ከክልሉ ሆነ ከፓርቲው የተባለ ነገር የለም።
ያንብቡ : telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-07-06

ዛሬ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ መሆን ጀመረ።
ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ፤ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በመላው ሀገሪቱ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡
የነዳጅ ድጎማውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መተግበሪያ በልፅጎ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።
በዚህም መሠረት በቴሌ ብር በኩል አገልግሎቱን ለማግኘት የተመዘገቡ ከ160,000 በላይ ተሸከርካሪዎች ከዛሬ ሰኔ 29 /2014 ጀምሮ መተግበሪያውን በመጠቀም ይስተናገዳሉ ተብሏል።
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ ነዳጅ ፍጆታ ተቀራራቢ የሊትር መጠን ግምት በጥናት ተለይቷል። ይህም እያንዳንዱ ተሸከርካሪ የሚጠቀመውን የነዳጅ መጠን ያገናዘበ ስሌት በመቀመጡ ተሽከርካሪዎቹ ያለ ብክነት የታለመ የነዳጅ ድጎማን ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ የህዝብ ትራንስፖርት ተሸከርካሪዎች ብቻ ዕለታዊ የነዳጅ መጠን ፦
👉 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በቀን 7 ሊትር
👉 መለስተኛ የከተማ ታክሲ (ላዳ) በቀን 25 ሊትር
👉 ሚኒባስ ታክሲ በቀን 65 ሊትር
👉 መለስተኛ አውቶብስ በቀን 94 ሊትር
👉 የከተማ አውቶብስ በቀን 102 ሊትር
👉 የሕዝብ አውቶብስ በቀን 25 ሊትር
👉 ሀገር አቋራጭ አውቶብስ በቀን 65 ሊትር መሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ፦ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር