TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ThomasSankara በቶማስ ሳንካራ ግድያ ተባባሪ በመሆን አስራ አራት ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ከ34 ዓመታት በፊት ነበር የወቅቱ የቡርኪና ፋሶ ፕሬዝዳንት ቶማስ ሳንካራ " የአፍሪካው ቼ ጉቬራ" አስደንጋጭ የሆነ ግድያ የተፈጸመባቸው። የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኙ ሳንካራ እአአ ጥቅምት 15/1987 በተካሄደ መፈንቅለ መንግሥት ነው በወታደሮቹ በጥይት ተገደሉት። እንሆ ከ34…
#ThomasSankar

የቶማስ ሳንካራ የፍርድ ሂደት ዛሬ ይቀጥላል።

የወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በተካሄደባት ቡርኪና ፋሶ ለሳምንት ተቋርጦ የነበረው የቶማስ ሳንካራ ግድያ የፍርድ ሂድት ዛሬ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊው ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ጄነራል ጊልበት ዲንዴሬ ነፃ መውጣቱን የሚገልጹ ወሬዎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ ሀሰተኛ ናቸው ሲል ወድቅ በማድረግ አሁንም በማካ እስር ላይ እንደሆኑ አረጋግጧል።

#Update

የሳንካራ ግድያ ክስ በዋና ከተማዋ ዋጋዱጉ በሚገኘው ወታደራዊ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኞ ይቀጥላል ተብሎ ነበር።

ፍርድ ቤቱ የፍርድ ሂደቱ መታገዱን አሳውቋል። " ህገ መንግስቱ ወደ ቦታው ከተመለሰ በኋላ የፍርድ ሂደቱ ይቀጥላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የሳንካራ ስም ዛሬም ድረስ ለምን ተደጋግሞ ይነሳል ?

ቶማስ ሳንካራ ምድር ላይ ለ37 ዓመታት ብቻ የተራመደ ነገር ግን በማእበል የማይጠፋ ዱካ አሳርፎ ያለፈ የዘመናችን አፍሪካዊ አብዮተኛ ነው።

በቅኝ ግዛት ወቅት "አፐር ቮልታ" ትባል የነበረችውን በርሀማ ደሀ ሀገሩን "ቡርኪና ፋሶ" ወደሚል ይፋዊ መጠሪያ የቀየረ፣ ተበታትነው ይኖሩ የነበሩትን ህዝቦቿን "ቡርኪናቤ" የተሰኘ የጋራ ማንነት እንዲጋሩ ያደረገ፣ ለዜጎቹ ህይወት የሚገደው ባለራዕይ መሪ ነበር።

ለምዕራባውያን ኃያላን ሀገራት ጫና ፍፁም ሳይንበረከክ በታደመባቸው ዓለምአቀፋዊና አፍሪካዊ ስብሰባዎች ላይ ሁሉ ዓለምን በማናለብኝነት ሲመዘብሩ ከነበሩ ሀገራት መሪዎች ጋር ጎሮሮ ለጎሮሮ ሲተናነቅ ያሳለፈ፣ ለጥቁር ህዝቦች እና በደል ላጎበጣቸው ምንዱባን ልሳን ሆኖ ያለፈ፣ ዓለም ከማይረሳቸው አብዮተኞች መካከል ጎልቶ የሚታወስ አፍሪካዊ እንቁ ነው።

"የራስን የተፈጥሮ ሀብት በራስ ጉልበት ማልማት" በሚለው የሀገሩን ህዝብ ባነቃነቀ ዘመቻ ያስመዘገባቸው አስደናቂ ድሎች አፍሪካ የራሷን ተፈጥሯዊ እድገት እንድታድግ ለማይፈልጉት ምእራባውያን ሀገራት እንደ ስጋት እንዲቆጠር አድርጎት ነበር።

ድሎት የማያሸንፈው ቆፍጣናው ወጣት ወደ ፕሬዝዳንትነት ከመጣ ጊዜ አንስቶ የቅንጦት ኑሮን ኖሮ አያውቅም። ከህዝብ ጋር የዩኒፎርሙን እጅጌ ከፍ አድርጎ ስሚንቶ የሚያቦካ፣ አካፋና ዶማ አንስቶ ጥቁር ላብ በግንባሩ እስኪንዠቀዠቅ ድረስ ሰርቶ የሚያሰራ፣ ድሆች ያለ ልኬት የሚሳሱለት መሪ ነበር።

አካሄዱ ባስፈራቸው ምዕራባውያን መሪዎች እና ስልጣን ባናወዛቸው የቅርብ ጓዶቹ በአጭር ቢቀጭም ተራማጅ ሀሳቦቹና ያስመዘገባቸው ተጨባጭ ለውጦች ዛሬም ድረስ ስሙ ተደጋግሞ እንዲነሳ አስችሎታል።

(ከሰለሞን ዳኜ - ቶማስ ሳንካራ ጥቁሩ አብዮተኛ)

@tikvahethiopia
#NewsAlert

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጡረታ እንደሚወጡ ማሳወቃቸውን ተከትሎ አሜሪካ በአዲስ አበባ ለሚገኘው ኤምባሲ አዲስ ሰው በተወካይነት በኃላፊነት ቦታ ላይ መድባለች።

አሜሪካ በአዲስ አበባ ላለው ኤምባሲዋ ትሬሲ አን ጃኮብሰንን ነው በጊዜያዊነት በኃላፊነት ቦታ ላይ ያስቀመጠችው።

አሜሪካዊቷ ዲፕሎማት ትሬሲ አን ጃኮብሰን በቱርክሜኒስታን፣ ታጂኪስታንና ኮሶቮ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል፤ በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዓለም አቀፍ ድርጅት ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ፀሀፊ ሆነውም አገልግለዋል።

@tikvahethiopia
#Update

የ2ኛው ዘር የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ነገ ይጀመራል።

በፀጥታ ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ፈተናቸውን መውሰድ ይጀምራሉ።

#AmharaRegionEB

• 37 ሺህ 55 ተማሪዎችን ለፈተና ይቀመጣሉ።

• ፈተናው በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደርና በደሴ ከተማ አስተዳደር ሙሉ በሙሉ ይሰጣል።

• በዋግ ኽምራ ከአበርገሌ ወረዳ በስተቀር በሁሉም ወረዳዎች፣ በሰሜን ሸዋ ዞን 3 ወረዳዎች እና በሰሜን ጎንደር ዞን በአንድ ጣቢያ ፈተናው ይሰጣል።

• በኦሮሚያ ክልል ከምስራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተፈናቅለው ለመጡ 220 የክልሉ ተወላጅ ተማሪዎች በቡሬ ከተማ በተዘጋጀ የፈተና ጣቢያ ፈተናው ይሰጣል።

• ለብሔራዊ ፈተና ከሚቀመጡት ተማሪዎች መካከል 34 ሺህ 970 የሚሆኑት መደበኛ ተማሪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ የግል ተፈታኞች ናቸው።

• ፈተናው በአጠቃላይ በ129 ጣቢያዎች ይሰጣል።

• ለፈተናው የሚያስፈልጉ ቁሶችና የመፈተኛ ወረቀቶች ወደተዘጋጁ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተጓጉዘው አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገ ነው።

#OromiaRegionEB

• በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ አራት ዞኖች በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይካሄድ የቀረው የ2013 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል።

• በቄሌም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች በ17 ወረዳዎች 55 ትምህርት ቤቶች ከ21 ሺ በላይ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የተሰጠውን ፈተና በጸጥታ ምክንያት አልወሰዱም።

• ፈተና ተፈትነው ውጤት በመጠባበቅ ላይ ላሉና እስካሁን በትዕግሥት ፈተናውን ለመውሰድ የተጠባበቁ ተማሪዎች ምስጋና ቀርቧል።

• በሁለተኛው ዙር የተፈታኞች ቁጥር አነስተኛ በመሆኑ ውጤት ለመግለጽ ብዙ እንደማይቆይ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በአንደኛው ዙር በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ዛሬ ፈተናቸውን ጀምረዋል።

መልካም ፈተና!

@tikvahethiopia
#MohammedrafieAbaraya

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የውጭ ፖሊሲ እና ዴፕሎማሲ ተንታኝ የነበሩት አቶ ሙሐመድራፊዕ አባራያ የጠ/ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሆነው መሾማቸው በዛሬው ዕለት ተሰምቷል።

@tikvahethiopia
#AU2022Summit

እስካሁን የየት ሀገር ሚኒስትሮች ገቡ ?

ነገ ለሚጀምረው የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች የሚሳተፉበት የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ የተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ናቸው።

እስካሁን የገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፦

🇿🇼 ፍሬድሪክ ሻቫ (ዝምባብዌ)
🇸🇹 ኤዲቴ ራሞስ ቴንዡዋ (የሳዖቶሜና ፒሪንሲፔ)
🇨🇲 ሌዡን ቤላ ቤላ (ካሜሩን)
🇹🇩 ማህማት ዜኑ ሸሪፍ (ቻድ)
🇨🇮 ካንዲያ ካሚስኮ ካማራ (ኮትዲቯር)
🇸🇴 አብዲሳድ ሙሴ አሊ (ሶማሊያ)
🇨🇬 ዢያን ክላውዴ ጋኮሶ (የሪፐብሊክ ኮንጎ)
🇳🇪 ሀሱሚ ማሹዱ (ኒጀር ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)
🇿🇦 ዶ/ር ናለዲ ፓንዶር (ደቡብ አፍሪካ)
🇸🇳 አሲታ ቶል ሳል (ሴኔጋል)
🇲🇷 እስማኤል ኡልድ ሼክ አህመድ (ሞሪታኒያ)
🇩🇯 ሙሀሙድ አሊ የሱፍ (ጂቡቲ)
🇱🇾 ናጅላ አልማንጉሽ (ሊቢያ)
🇦🇴 ሜንዶንካ ኤስሜራልዳ ዢያን ክላውዴ ጋኮሶ (አንጎላ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር)

@tikvahethiopia
#NewsAlert

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና እንደሚሰጥ ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ በተቋማት ተጠያቂነትና የመረጃ ፍሰትን ለመዘርጋት እንዲሁም ውጤታማ እና ቀልጣፋ ሥራ እንዲያከናወኑ ያስችላል በተባለ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ መዋቅር ላይ ያተኮረ ነው።

በመንግስትም ሆነ በግል የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ወደሚፈለገው ደረጃ ከፍ ለማድረግ በቀጣይ የትምህርት ዘመን የመውጫ ፈተና ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ሊሰጥ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

#MoE

@tikvahethiopia
#GendaRira

9 የፌዴራል ፖሊስ አባላት በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

በባሌ ዞን ጎባ ወረዳ ልዩ ስሙ ገንዳ ሪራ በተባለ ስፍራ በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጎባ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋው የደረሰው በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 9:00 ሰዓት ገደማ ነው።

አደጋው ከደሎ መና ወደ ሮቤ ዶዘር እየጎተተ ሲጓዝ ከነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ክሬን ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሮቤ ወደ ደሎ መና በመጓዝ ላይ ከነበረው የፖሊስ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በደረሰው የተሽከርካሪ አደጋ 9 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ህይወት ሲያልፍ ፥ በአራቱ ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው ክሬኑን ሲያሽከረክር የነበረው ረዳት በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ አሳውቋል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ተብሏል።

ከባድና ቀላል አደጋ የደረሰባቸው የፖሊስ አባላት ጎባ ሪፌራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ተፈርዶበታል !

በገቢዎች ሚንስቴር ውስጥ የኦዲት ባለሙያ ሆኖ ሲሰራ 1.5 ሚሊየን ብር ጉቦ ለመቀበል ተስማምቶ ግማሽ ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘው ተከሳሽ በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።

መላኩ ሸዋረጋ የተባለው ተከሳሽ በገቢዎች ሚንስቴር አዳማ ቅ/ፅ/ቤት የኦዲት ባለሙያ ሆኖ ሲሰራ አንድ ሚሊየን ብር በባንክ አካውንት እንዲገባለትና 5 መቶ ሺህ ብር ደግሞ በጥሬው ለመቀበል ተስማምቶ በቦሌ ክፍለ ከተማ ካፒታል ሆቴል ገንዘብ ሲቀበል የተገኘው ተከሳሽ በፈፀመው ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል በፅኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

ተከሳሹ የተጣለበትን የስራ ኃላፊነቱን ተጠቅሞ ኽርበርግ ሮዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለው ድርጅት የ2 ዓመት የንግድ ስራ ትርፍ ግብር ብር 66‚616‚818 ብር ከ93 ሳንቲም አንዲከፍል ሲወሰንበት የድርጅቱ የአስተዳደር ሰራተኛ የሆነችው 1ኛ የዐቃቤ ህግ ምስክር በውሳኔው ላይ ለቅ/ፅ/ቤቱ ቅሬታ ታቀርባለች፡፡

ተከሳሹ በበኩሉ የቀረበውን ቅሬታ ውሳኔውን ዝቅተኛ በሆነ መልኩ መወሰን እንደሚቻልና ለዚህም ብር 1‚000‚000 ብር በባንክ ለመቀበልና ቀሪውን 500‚000 ብር ደግሞ እጅ በእጅ ለመቀበል ከተደራደረና ከተስማማ በኋላ ጥቅምት 24/3013 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ካፒታል ሆቴል ውስጥ 500‚000 ብሩን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

በፈፀመው ጉቦ መቀበል የሙስና ወንጀል በፍትሕ ሚኒስቴር ክስ መስርቶበታል።

በከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ በአንደኛ የሙስና ወንጀል ችሎት የቀረበው ተከሳሽ መላኩ ሸዋረጋ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎበት በ4 ዓመት ከ10 ወር ፅኑ እሥራት እና በ2500 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል።

እንዲሁም በጉቦ የተሰጠው ገንዘብ ለተበዳይ እንዲመለስ ዐቃቤ ህግ በጠየቀው መሰረት ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ ገንዘቡ ለተበዳይ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡

ምንጭ፦ ፍትህ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#AU

የአፍሪካ ህብረት ሰንደቅዓላማ ...

የአፍሪካ የራሱ ሰንደቅዓላማ ያልነበረው ሲሆን በ2004 ግን መለያ ሰንደቅዓላማ አዘጋጅቶ ነበር።

በ8ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እኤአ ጥር 29 እና 30 ቀን 2007 በአዲስ አበባ ሲካሄድ ነባሩን ሰንደቅዓላማ የሚተካ አዲስ የህብረቱ ሰንደቅዓላማ እንዲዘጋጅ ውሳኔ ተላለፈ።

በወቅቱ የሊቢያ መሪና የህብረቱ ሊቀመንበር ሙአመር ጋዳፊ የሚመራው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኃላፊነቱን ወስዶ ለህብረቱ ሰንደቅዓላማ ንድፍ መስራት ለሚፈልጉ ጥሪ አቀረበ።

የኮሚሽኑን ጥሪ ተከትሎ ከ19 የአፍሪካ ሀገራት ከ100 በላይ ግለሰቦች፣ ከዳያስፖራ 2 ግለሰቦች ከ100 በላይ ንድፎችን አስገቡ።

የሰንደቅዓላማ ንድፎቹ በባለሙያዎች ተመዘኑ። በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆነው የግራፊክ ጠቢብ ያዴሳ ቦጂያ ያቀረበው ንድፍ አሸናፊ ሆነ።

ያሸነፈው የያዴሳ ንድፍ ሰንደቅዓላማ እንዲሆን እኤአ ጥር 31 ቀን 2010 በአዲስ አበባ በተካሄደው 14ኛው መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተወሰነ።

ያዴሳ ቦጂያ ያረቀቀውና አሁን በስራ ላይ ያለው የህብረቱ ሰንደቅዓላማ አረንጓዴ መደብ፣ በ55 ወርቃማ ኮከቦች የተከበበችና በነጭ የፀሐይ ጨረሮች ላይ ያረፈች አረንጓዴ የአፍሪካ ካርታን የያዘ ነው።

የአፍሪካ ካርታ በአረንጓዴ መወከሉ አህጉራዊ ተስፋን ለማሳየት ሲሆን፣ ነጭ የፀሐይ ጨረሮች ደግሞ አፍሪካውያንን ከተቀረው ዓለም ጋር በወዳጅነት፣ በጋራ የመኖር ግልፅ ፍላጎትን የሚያሳይ ነው።

አረንጓዴው የአፍሪካ ካርታ በ55 ወርቃማ ኮከቦች የተከበበ ሲሆን ተምሳሌትነቱ 55ቱን የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራትን፥ የአፍሪካን ፀጋዎችና ብሩህ ተስፋን የሚያሳይ ነው።

Credit : #ኢዜአ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA #FRANCE

ፈረንሳይ በኢትዮጵያ የመልሶ ማቋቋም ጥረቶችን እንዲሁም የታቀደውን ብሔራዊ ውይይት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን ገለፀች።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የፈረንሳይ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ፍሬደሪክ ክላቪየርን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ ሁኔታ፣ በቀጠናዊ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያካሄደ ስላለው የሰላም ጥረት ለልዩ ልዑኩ ገለፃ አድርገዋል።

በዚህ ረገድ ወሳኝ አገራዊ ጉዳዮችን ለመፍታት እና በህዝብ መካከል መግባባት ለመፍጠር ያለመ የብሔራዊ ውይይት ኮሚሽን መቋቋሙን ጠቅሰዋል።

ከፍተኛ የሆኑ የፖለቲካ ሰዎች ከእስር መፈታታቸው የውይይት መድረኩን ስኬታማነት እንደሚያፋጥነው ገልፀዋል።

ምንም እንኳን መንግስት ወታደሮቹ ወደ ትግራይ እንዳይገቡ መከልከሉ የሰላሙን ጥረት እንደሚያጠናክር ቢገለፅም ህወሓት በአጎራባች ክልሎች ላይ እያደረሰ ያለው አዲስ ጥቃት የሚጠበቀውን የሰላም ጥረት እንዳይቀንስ ስጋት ፈጥሯል ብለዋል።

ልዩ መልዕክተኛው ሀገራቸው ፈረንሳይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት አሳውቀዋል።

ሀገራቸው ፤ የመልሶ ማቋቋም ስራዎችን እና በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የታቀደውን ሁሉን አቀፍ ውይይት ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ደብረፅዮን በቢቢሲ ኒውስ ሀወር ላይ ቀርበው ምን አሉ ? የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ዛሬ ከቢቢሲ ኒውስ ሀወር ጋር በነበራቸው ቆይታ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር በሌሎች አካላት አማካኝነት (ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ) ንግግርና ውይይት መደረግ መጀመሩን ገልፀዋል። በዚህም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል። ከፌዴራል መንግስት ጋር በሌሎች አካላት አማካኝነት (በUN ፣AU…
#Update

መንግስት በቅርቡ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በተናገሩት ንግግር ላይ ምላሽ ሰጠ።

የኢትዮጵያ መንግስት ከትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሓት) ጋር ድርድር አለመጀመሩን ዛሬ አስታውቋል።

የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ባለፈዉ ሳምንት ከቢቢሲ ኒውስ ሀወር ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በሌሎች አካላት (ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ) ንግግር መጀመራቸውን አስታዉቀዉ ነበር።

ዶክተር ደብረፅዮን የተጀመረው ንግግርም "ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እያሳየ " መሆኑን ገልፀው ነበር።

የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ዶቼቨለ) በሰጡት ቃል የኢትዮጵያ መንግስት ሰላምን ለሚያመጣ ለየትኛዉም አማራጭ በሩ ክፍት ነዉ ብለዋል።

ነገር ግን እስካሁን ድረስ ከህወሓት ጋር የተደረገ ንግግር የለም ሲሉ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአንደኛው ዙር በፀጥታ ችግር የ12ኛ ክፍል ፈተና መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች ዛሬ ፈተናቸውን ጀምረዋል። መልካም ፈተና! @tikvahethiopia
#Update

የመጀመሪያው ቀን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።

ፈተናው በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተሰጥቷል።

#Amahra

በአማራ ክልል ከ37 ሺ በላይ ለሆኑ ተማሪዎች ዛሬ ፈተና ሲሰጥ ውሏል። ፈተናው በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ ዋግኸምራ፣ ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖችና በደሴ ከተማ ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን 3 ወረዳዎች፣ በሰሜን ጎንደር ዞን በ1 የፈተና ጣቢያ ፈተናው ነው የተሰጠው።

በሌላ በኩል ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ተፈናቅለው ለመጡ 220 ተማሪዎችም በልዩ ሁኔታ በቡሬ በተቋቋመ የመፈተኛ ጣቢያ ተፈትነዋል።

#OromiaRegion

በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ ዞን በ12 ወረዳዎች በ42 የፈተና ጣቢያዎች 14,228 ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸው ፤ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከተጠበቁት 16,608 ተማሪዎች መካከል 1, 243 በተለያዩ ምክንያቶች ፈተና ላይ አለመቀመጣቸው ተገልጿል።

በምዕራብ ወለጋ የቤጊ እና ቆንደላ ወረዳዎች 1,137 ተማሪዎች በአራት የፈተና ጣቢያ ፈተናው ላይ የተቀመጡ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች 931 ተማሪዎች ፈተናው ላይ እንዳልተቀመጡ ተገልጿል።

#Afar

በአፋር ክልል ፈተናውን ይወስዳሉ ተብለው ከተጠበቁት 257 ተማሪዎች 154 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ጀምረዋል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን አንፃራዊ ሠላም ተመዝግቦባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሲሰጥ ውሏል።

• የሁለተኛው ቀን ፈተና ይቀጥላል።

መረጃ ፦ ኢብኮ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የአማራክ ክልል ትምህርት ቢሮ

ፎቶ ፦ የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ የወልዲያ ከተማ ፣ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮዎች ፣ የቤ/ጉ ክልል ትምህርት ቢሮ

@tikvahethiopia