TIKVAH-ETHIOPIA
#Update እንሆ ከ3 ዓመት በኃላ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ወደ በረራ ተመልሷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ3 ዓመታት በኋላ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራ በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑን አስታውቋል። የሙከራ በረራውን ያከናወነው ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ባካሔደው የደርሶ መልስ በረራ ነው። ለሙከራ በረራው እ.አ.አ በ2018 የቦይንግ አውሮፕላን በረራ መቆጣጠሪያ ክፍሉ…
#EthiopianAirlines
በአፍሪካ ታላቁ እና የአህጉሪቱ የአቪየሽን መሪ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ " ቦይንግ 737 ማክስ " አውሮፕላኑን ዛሬ ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም ዳግም ወደ አየር መለሰ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ፣ የአየር መንገዱ የማኔጅመንት አባላት፣ የቦይንግ የስራ ኃላፊዎች፣ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ጋዜጠኞች እና የአየር መንገዱ ደንበኞች በዚህ የመጀመሪያ በረራ ላይ መታደማቸው ተገልጿል።
አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን ወደ አገልግሎት መመለስ አስመልክተው ፥ “የበረራ ደህንነት የአየር መንገዳችን ተቀዳሚና ወሳኝ ጉዳይ ነው፤ እያንዳንዷ የምንሰራት ስራና የምንወስናት ውሳኔ በበረራ ደህንነት አብይ ጉዳይ የተቃኘ ነው። በዚህ መርህ ላይ በመመስረት ነው ዛሬ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላናችንን ወደ አገልግሎት የመለስነው።" ብለዋል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጊኒ ቢሳው መዲና በተኩስ ስትናጥ ነበር።
በጊኒ ቢሳው ርዕሰ መዲና በሀገሪቱ መንግስት መቀመጫ አቅራቢያ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ተነግሯል።
በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ ሰዎች ዛሬ ማክሰኞ ቤተ መንግስቱን መክበባቸው ነው የተሰማው።
ይህ የሆነው ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ኢምባሎ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ኑኖ ጎሜስ ናቢያም በካቢኔ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ሄደው በነበረበት ወቅት ሳይሆን እንዳልቀረ ተገልጿል።
በነበረው ሁኔታ የተደናገጡ ሰዎች ከአካባቢው ሲሸሹ መታየቱን፣ የንግድ እንቅስቃሴ መቋረጡ ፣ ባንኮች መዘጋታቸውንና ወታደሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ደግሞ በጎዳናዎች ላይ ሲዘዋወሩ መታየታቸውን AFP ዘግቧል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጊኒ ቢሳው ዋና ከተማ ግጭት መኖሩን የሚገልፁ ዜናዎች በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።
አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆምና የሀገሪቱ የዲሞክራሲ ተቋማት ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ ጠይቀዋል።
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ECOWAS ባወጣው መግለጫ በቢሳው ክስተቱን " የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ " ሲል በመጥራት አውግዟል።
በምዕራብ አፍሪካ ውስጥ ያሉት ሦስት ሀገራት - ማሊ ፣ ጊኒ እና ቡርኪናፋሶ - ከ18 ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት አጋጥሟቸዋል።
@tikvahetheng

220131_humanitarian_bulletin_final (2).pdf
244.5 KB
#UN
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (UNOCHA) ፦
• በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለው ግጭት በህብረተሰቡ ህይወት እና ኑሮ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እያሳደረ እና የሰብአዊ ፍላጎቶችን እያሳደገው ይገኛል።
• በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ፣ ምዕራብ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ያለው ያልተረጋጋ የጸጥታ ችግር (የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጎራባች አካባቢዎችን ጨምሮ) በርካቶችን ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ እያደረገ ነው።
• በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ከ250,000 በላይ ሰዎች የእህል ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። እስካሁን ያለው ምላሽ በቂ አይደለም፤ ሽፋኑም ውስን ነው።

#Oromia, #WestGuji 📍
በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በሸኔ በመከበቡ ውሎ መግባት አስቸጋሪ መሆኑን አመለከቱ።
ነዋሪዎች የታጣቂ ቡዱን በርካታ የወረዳውን ቀበሌዎችን መቆጣጠሩን በመግለፅ ሰዎች እንደሚገደሉ፣ ንብረትም እንደሚወድም እና እንደሚዘረፍ ገልፀዋል።
ወረዳው ነዋሪ ፦
" ያለንበት ሁኔታ አሰቃቂ እና ተስፋ የሌለው ነው።
በአሁን ጊዜ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ነን። ታጣቂዎች ቤት አይሉ ማህበረሰቡ የሚገለገልባቸው የመንግስት ተቋማንት እያቃጠሉ እና እያወደሙ ነው።
በየቀኑ የ4 እና 5 ሰዎች መገደል ይሰማል። አርሶ አደር በከብቶቹ መሃል ይገደላል።
ተሽከርካሪ እንደልብ አይንቀሳቀስም ይዘረፋል። ለማን አቤት እንደምንል አናውቅም እያለቅን እየተሰቃየን ነው። "
ሌላ ነዋሪ ፦
" ከወረዳው ከታጣቂዎች ንፁህ የሚባለው ሁለት ቀበሌ ብቻ ናቸው።
እዚህ ደረጃ ከደረሰ ቆይቷል። የወረዳ የፀጥታ ኃላፊን ጨምሮ ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሻዎች፣ የቀበሌ ሊቀመንበሮች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አልቀዋል "
የገላና ወረዳ አስተዳደሪ አቶ ሞርከታ ሴሮ ፦
" እነዚህ ታጣቂዎች የሸኔ ታጣቂዎች ናቸው።
እንቅስቃሴያቸውን መግታት አልቻልንም ስለዚህ ችግሩ በጣም እየከፋ በመምጣቱ እኛም ለመንግስት አካል አመልክተናል።
በተለይ የወታደር ኃይል ገብቶ ይህን ኃይል እንዲመታው እና ህብረተሰቡ በነፃነት ወጥቶ እንዲገባ የሚደረግበትን ሁኔታ እየፈጠርን ነው።
ሁኔታው ትንሽ ከበድ ይላል። እውነቱን ለመናገር የወረዳው ብዙ ቀበሌዎች ላይ ገብተዋል።
የመከላከያ ሰራዊት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይገባሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገርን ነው። "
ያንብቡ : https://telegra.ph/Gelana-Woreda-02-01

Telegraph
Gelana Woreda
#ገለና_ወረዳ በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በሸኔ በመከበቡ ውሎ መግባት አስቸጋሪ መሆኑን አመለከቱ። ነዋሪዎች የታጣቂ ቡዱን በርካታ የወረዳውን ቀበሌ መቆጣጠሩን በመግለፅ ሰዎች እንደሚገደሉ፣ ንብረትም እንደሚወድም እና እንደሚዘረፍ ገልፀዋል። ከወረዳው ከታጣቂዎች ንፁህ የሚባለው ሁለት ቀበሌ ብቻ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች ነገሩ እዚህ ደረጃ ከደረሰ መቆየቱንና የወረዳ የፀጥታ…
#ETHIOPIA
የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 👉 7,696
• ቫይረሱ የተገኘባቸው 👉 319
• ህይወታቸው ያለፈ 👉 6
• ከበሽታው ያገገሙ 👉 576
• ፅኑ ታማሚዎች 👉 252
በኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 465,477 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል 7,343 ህይወታቸው አልፏል፤ 399,021 ከበሽታው አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው 59,111 ሰዎች ናቸው።
በኢትዮጵያ ክትባት መሰጠት ከጀመረ አንስቶ የተከተቡ ዜጎች 9,372,085 ደርሰዋል።

የአንቶኒዮ ጉተሬዝ ጥሪ ... #ETHIOPIA
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አርብ ጥር 27 በቻይና ቤጂንግ ከተማ በሚጀመረው የክረምት ኦሎምፒክ ላይ ለመገኘት ወደ ቦታው ከመጓዛቸው በፊት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
ጉተሬዝ በመግለጫቸው ፥ በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም ወገኖች የኦሎምፒክ መንፈስን ተንተርሰው በአፋጣኝ ግጭት እንዲያቆሙ ተማፅነዋል።
ክፍለ ዘመናትን በተሻገረው የኦሎምፒክ ባህል መሰረት በየትኛውም አካባቢ የሚገኙ ተፈላሚ ወገኖች ውድድሮቹ እስኪጠናቀቁ ድረስ ግጭት እንዲያቆሙ ጥሪ እንደሚቀርብ አስታውሰዋል።
ዋና ፀሀፊው በኢትዮጵያ በቀጠለው ግጭት እና ደም መፋሰስ የሀገሪቱ ህዝቦች ስቃይ ቀጥሏል ሲሉ ተደምጠዋል።
ሁሉም ወገኖች የኦሎምፒክ መንፈስን ተከትለው ህይወትን እንዲያድኑ፣ ልዩነቶቻቸውን እንዲፈቱ እና ለእውነተኛ ሰላም መንገድ እንዲፈልጉም ጥሪ አቅርበዋል።
አንቶኒዮ ጉተሬዝ የግጭቱ መቆም ለተቸገሩ ህዝቦች ሰብዓዊ እርዳታን ለማድረስ እንደሚያስችል ፤ ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን የሚያሳትፈውንና እጅግ አስፈላጊ የሆነውን አካታች ውይይት ለማካሄድ መንገድ የሚጠርግ ነው ብለዋል።
የቤጂንግ የክረምት ኦሎምፒክ ከጥር 27 እስከ የካቲት 13/2014 ዓ/ም ይካሄዳል።
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

#Oromia ከቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት እና ፈንታሌ ወረዳዎችን በሚያዋስን እና ካራ ወይም ሞቶማ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ 14 ሰዎች ተገድለዋል። ከሟቾቹ መካከል የከረዩ አባ ገዳ ከድር ሃዋስ ቦሩ ይገኙበታል። የክልሉ መንግሥት አባ ገዳ ከድር ሃዋስን የገደለው "ሸኔ" ነው በማለት በሽብርተኛ ቡድንነት የተሰየመውን ታጣቂ ቡድንን ከሷል። የሟች ቤተሰብ እና የአካባቢው ነዋሪ በበኩላቸው…
" በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ ግድያ የፈጸሙና ያስፈጸሙ የፀጥታና የአስተዳደር አባላት ላይ ተገቢው የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ለፍትሕ ሊቀርቡ ይገባል " - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ ግድያ የፈጸሙና ያስፈጸሙ የፀጥታና የአስተዳደር አባላት ላይ ተገቢው የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ለፍትሕ ሊቀርቡ ይገባል ብሏል።
ኮሚሽኑ ይህን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።
ኢሰመኮ በምርመራ አሰባሰብኩኝ ባለው እና አገናዘብኩኝ ባላቸው ማስረጃዎች 14 የከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት በኅዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በመንግስት የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በግዳጅ ወደ ጫካ ቦታ ተወስደውና የፀጥታና የአካባቢ አስተዳደር ሰዎች ባሉበት፣ ጭካኔ በተሞላው ሁኔታ በጥይት ተመተው የተገደሉ መሆኑንና ይህም ከሕግ ውጭ የተፈጸመ ግድያ (extra judicial killing) ስለመሆኑ በምክንያታዊ ሁኔታ አሳማኝ (reasonable ground to believe) ሆኖ ማግኘቱን ገልጿል።
በተጨማሪም፣ በግዳጅ ከተወሰዱት 23 የጅላ አባላት መካከል አንድ ሰው ሞጆ ከተማ በሚገኝ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ካምፕ ውስጥ በቁጥጥር ስር እያለ ሕይወቱ አልፎ ያለምንም ምርመራ አስክሬኑን ቤተሰቦቹ እንዲወስዱና እንዲቀበር መደረጉ ከዚሁ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ተጨማሪ ከሕግ ውጭ የተፈጸመ ግድያ (extra judicial killing) መኖሩን በምክንያታዊ ሁኔታ አሳማኝ (reasonable ground to believe) ሆኖ ማግኘቱን ኢሰመኮ ከአሳውቋል።
* ኢሰመኮ የላከልን ሙሉ መግለጫ ከላይ ተይያዟል።

" በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ ግድያ የፈጸሙና ያስፈጸሙ የፀጥታና የአስተዳደር አባላት ላይ ተገቢው የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ለፍትሕ ሊቀርቡ ይገባል " - ኢሰመኮ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ ግድያ የፈጸሙና ያስፈጸሙ የፀጥታና የአስተዳደር አባላት ላይ ተገቢው የወንጀል ምርመራ ተደርጎ ለፍትሕ ሊቀርቡ ይገባል ብሏል። ኮሚሽኑ ይህን ያለው ዛሬ ባወጣው…
ከኢሰመኮ ሪፖርት ፦
ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ለስራ ወደፈንታሌ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ሄደው ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አከባቢ ወደመተሃራ በመመለስ ላይ የነበሩ የፀጥታ አባላት ላይ በወረዳው ሀሮ ቀርሳ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኢፍቱ በተባለ ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት የ11 ፖሊስ አባላት ሕይወት ማለፉና ቢያንስ 17 ሌሎች የፖሊስ አባላት መቁሳለቸው ታውቋል።
ይህንን ተከትሎ ህዳር 22 ቀን 2014 በግምት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጥቃቱን ያደረሱ ተጠርጣሪዎችን ለመፈለግ በፈንታሌ ወረዳ ጡጢቲ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዴዲቲ ካራ ከሚባል የከረዩ ሚችሌ አባገዳዎችና የጅላ አባላት የመኖሪያ ሰፈር የደረሱ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች 39 የጅላ አባላትን በቁጥጥር ስር አውለዋል።
በእነዚህ ፀጥታ አባላት ቁጥጥር ስር ከዋሉ የከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት መካከል 16 ሰዎች ወደ ጨቢ አኖሌ ጫካ ተወስደው14ቱ ሰዎች በጥይት ተመተው ተገድለዋል።
በዚህም፦
-የከረዩ አባገዳ #ከዲር_ሀዋስ
-ኦዳ ጫርጨር
-ቦሩ ፈንታሌ
-ፈንታሌ ቦሩ
-ቁምቢ ጉራቻ (ቃሉ ናቸው)
-ቦሩ ፈንታሌ
-ቡላ ፈንታሌ
-ሮባ ሀዋስ
-ቦሩ ጎዳና
-ጂሎ ደዲኦ
-ቡላ ፈንታሌ
-ቡልጋ ቦረኡ
-ጂሎ ዲዶ እና ቦሩ ጂሎን ጨምሮ 14 የከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት መሬት ላይ እንዲተኙ ተደርገው በጥይት ተመተው ተገድለዋል።
የሟቾችን አስከሬን ለማንሳት ግድያው ወደ ተፈጸመበት ቦታ የሄዱ ሰዎች በቦታው በነበሩ ፖሊሶች እንዳያነሱ በመከልከላቸው ፤ አስከሬኖቹ ለበርካታ ሰዓታት ሳይነሱ መቆየታቸውንና የፈነዱና በከፊል በዱር እንስሳ የተበሉ እንደነበሩ አስከሬኖቹን ያነሱና የቀበሩ ሰዎች ገልጸዋል።
አስከሬኖቹ ከጀርባ በኩል ወገባቸውና ጭንቅላታቸው ላይ በጥይት ተመተው መገደላቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች ነበሩባቸው።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፦
" ... በከረዩ የሚችሌ ገዳ አባላት ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸሙና ያስፈጸሙ ሰዎችን እንዲሁም በፖሊስ አባላት ላይ የግድያና የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል የፈጸሙትን ሰዎች በሕግ ተጠያቂነት ለማረጋገጥ ተገቢው የወንጀል ምርመራ በአፋጣኝ ሊደረግ እንደሚገባ ኮሚሽኑ ምክረ ሃሳብ አቅርቦ ነበር።
ስለ ጠቅላላው የነገሩ ሁኔታ እውነቱን በመግለጽ ፍትሕ በማረጋገጥና የተጎዱ ሰዎችን በመካስ ላይ የተመሰረተ አስፈላጊ ተግባራትን በማከናወን የማኅበረሰቡን ሰላም እና ደኅንነት እንዲመለስ ማድረግ ይጠበቃል "

Photo
Kereyu Incident Investigation Report.pdf
460.6 KB
ሙሉ ሪፖርት : በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ግድያ ላይ የተደረገ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የተላከ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia
@tikvahethiopia
#Update
40ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ጉባኤ ጀምሯል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚሳተፉበት 40ኛው የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ “የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ አቅም መገንባት፣ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማትን ማፋጠን” በሚል መሪ ቃል ይመክራል።
የአስፈጻሚ ም/ቤቱ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ በሚካሔደው 35ኛው የሕብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይም ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ሕብረት የአስፈጻሚ ምክር ቤት በሕብረቱ አባል አገራት የጋራ ፍላጎት የሆኑ የፖሊሲ ጉዳዮችን የሚያስተባብርና ውሳኔ የሚሰጥ ነው።
ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

#AmharaRegion
የአማራ ክልል በኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልሎች በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ አካባቢዎች የሚሆን የእንስሳት መኖ ድጋፍ አድርጓል።
ክልሉ ትላንት በኦሮሚያ ክልል ጎጂና ቦረና አካባቢዎች በድርቅ ለደረሰው ጉዳት የእንስሳት መኖ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ወደ ሶማሊ ክልል በማቅናት ድጋፍ አድርጓል።
በኦሮሚያ እና በሶማሊ ክልል የተከሰተው አስከፊ ድርቅ በርካታ እንስሳትን መፍጀቱ እንዲሁም በርካታ ወገኖችን ለከፍተኛ ችግር መዳረጉ ይታወቃል።

#ችሎት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ታስረው እንዲቀርቡ ትዛዝ ተሰጠ። ከህዳር 4 ቀን 2011ዓ/ም ጀምሮ በስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሜቴክ ዳሪክተር ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘውን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ከዕርሻ መሳሪያ ግዢ ጋር ተያይዞ በዓቃቢህግ በቀረበባቸውባቸው የሙስና ክስ የመከላከያ ማስረጃ ማሰማት መጀመራቸው ይታወሳል። በዚህም መሰረት በሀምሌ 11ቀን 2013 ዓ/ም የገንዘብ ሚኒስትሩ…
#ችሎት
የኢጋድ ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እና አምባሳደር ድሪባ ኩማ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸው ፍርድ ቤቱ አዘዘ።
የመጥሪያ ትዛዙን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
በነ ሜ/ጀነራል ክንፈ ዳኘው የመርከብ ግዢ የሙስና ክስ ላይ በመከላከያ ምስክርነት ፍርድ ቤት ቀርበው እንዲመሰክሩ ነው መጥሪያ እንዲደርሳቸው የታዘዘው።
በጥር 23 ቀን በነበረው የችሎቱ ቀጠሮ ተከሳሾች እነ ዶ/ር ወርቅነህ መከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡላቸው በጠየቁት ጥያቄ መሰረት ፍ/ ቤቱ መርምሮ ለተከሳሾች በመከላከያ ምስክርነት የሚቀርቡ አካላት መጥሪያ እንዲደርሳቸው ትዛዝ ሰቶበታል።
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ ሜ/ጀነራል አብዱል ሰላምን እና ኮነሬል ሸጋውን በፌደራል ፖሊስ በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸው ያዘዘ ሲሆን ኮ/ል አስመረት ኪዳኔ እና ሻለቃ ሰመረ ሀይሌን ደግሞ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በኩል መጥሪያ እንዲደርሳቸው አዟል።
ውጤቱን ለመጠባበቅ ለመጋቢት 8 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷል።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ