#Update
የአሜሪካ መንግስት ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ፥ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ስምምነት ማወጁ ግጭት እና የሚፈፀሙ ጭካኔዎችን ለማስቆም፣ ያልተገደበ ሰብአዊ ርዳታን በማድረስ በኩል በመሬት ላይ ለውጥ ካመጣ አዎንታዊ እርምጃ ሊሆን ይችላል ብሏል።
ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተልን ነው ያለው የአሜሪካ መንግስት፤ ግጭቱን ለማስቆም፣ ትግራይ ክልልን ለማረጋጋት እንዲሁም የኢትዮጵያን መንግስት አንድነት፣ ሉዓላዊነቱን እና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት የሚጠብቅ ሁሉን አቀፍ ውይይት ለማድረግ አውድ እንዲፈጥር ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ፣ ላልተወሰነና በድርድር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያድረጉ ጥሪ እናቀርባለን ብሏል።
የአሜሪካ መንግስት፥ ሁሉም ወገኖች ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕግን በጥብቅ እንዲያከብሩ ፣ ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነት እንዲኖር እንዲያደርጉ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና በደሎችን የፈፀሙ አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበትን ገለልተኛ መንገድ እንዲያመቻቹ ጠይቋል።
የአሜሪካ መንግስት በመግለጫው ፥ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ አስከፊ የሆነውን የሰብዓዊ ሁኔታ መፍታት ነው ብሏል።
ከዚህ ቀደም የረሀብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል የተባሉ 900,000 ሰዎች ጨምሮ ለሌሎችም ሕይወት አድን የምግብ ዕርዳታ አቅርቦትን ለማፋጠን አሜሪካ ከኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከትግራይ ባለሥልጣናት፣ ከተባበሩት መንግስታት እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ለመስራት ዝግጁ ናት ብሏል የሀገሪቱ መንግስት በመግለጫው።
ከዚህ ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በትግራይ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን በፍጥነት እንዲመልሱ እና ሰብአዊ ድርጅት ሠራተኞች ደህንነታቸውን እንዲያረጋግጡ ያልተገደበ የመንቀሳቀስ ነፃነትን እንዲፈቅዱ እንጠይቃለን ብሏል።
@tikvahethiopia

ኢትዮጵያ ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ የማስወጣቱን ዘመቻ አጠናክራለች።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባገኘነው መረጃ በትናትናው ዕለት 1 ሺ 657 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

#ጭልጋ
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ከጭልጋ ከተማ እና አካባቢው ተፈጥሮ የነበረው የሰላም ችግር እየተሻሻለ መምጣቱን አስታውቋል።
ኮማንድ ፖስቱ ከጭልጋ እና አካባቢው አስር ቀበሌ ከሃይማኖት አባቶች ፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች፣ ከወረዳና ቀበሌ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጉ ሪፖርት ተደርጓል።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮማንድ ፖስት አመራር ሌ/ጀ ይመር መኮነን ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ዞንን የሽብርተኞች አደባባይ በማድረግ የሀገርን ሰላም ለማሳጣት የሚንቀሳቀሱ የፀረ-ሰላም ሃይሎች ላይ እርምጃ እተወሰደ ይገኛል ብለዋል።
አክለውም ፥ በኮማንድ ፖስቱ እንዲሁም በህብረተሰቡ የጠነከረ ቅንጅት በየጊዜው መሻሻሎች እየተመዘገቡ እንደመጡም ገልፀዋል።
የ33ኛ ክ/ጦር አዛዥ ኮ/ል ደስታ ተመስገን በበኩላቸው የተመዘገበውን ማህበራዊ እንቅስቃሴ እና ሰላም በቀጣይነት ለማረጋገጥ ህብረተሰብ እና የፀጥታ አካላት ይበልጥ ተባብረው መስራት አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል።
የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የሃገር ሽማግሌዎች ሰላምን ለበጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ መዘጋጀታቸውን እና በህዝብ ውስጥ ሰላማዊ ሰው በመምሰል ሃሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት ለግጭት የሚዳርጉ ወንጀለኞችን በመጠቆም ከኮማንድ ፖስቱ ጋር እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸው ተነግሯል።
ምንጭ፦ የሀገር መከላከያ ሰራዊት

“የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ሰኔ 21/2021 ዓ.ም. የወሰደው ‘በሰብዓዊ ምክንያት ተኩስ የማቆም አዋጅ’ ትግራይ ውስጥ ላለውን ግጭት መፍትኄ ለማግኘት ትክክለኛ እርምጃ በመሆኑ እንደግፈዋለን” ሲሉ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ትግራይ ውስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲገኝ መንገድ ለመጥረግ እንዲቻልም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት አጠቃላይና ሁሉን አቀፍ የሆነ ቋሚ ተኩስ ማቆም ላይ እንዲደረስ እንዲሠሩ የኅብረቱ ሊቀ መንበር ጠይቀዋል።
ለዚህም ሁሉም ዓይነት የግጭት ሁኔታዎች እንዲቆሙ ፤ በዓለም አቀፍ ህግ መሠረት ሲቪሎችን ከአደጋ ለመጠበቅ እና ክልሉ ውስጥ ለተጎዱት ሁሉ እጅግ አስፈላጊ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ የሰብዓዊ እርዳታ ተዋናዮች ደኅንነቱ የተረጋገጠ ተደራሽነት እንዲኖራቸው ለማስቻል ሁሉም ወገኖች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አድርገዋል።
ለትግራይ ክልል ግጭት የፖለቲካ መፍትኄ እንዲፈለግም ሊቀ መንበሩ በተጨማሪ መጠየቃቸውንና በሃገሪቱ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጥረቶች የአፍሪካ ኅብረት ድጋፉን ለመስጠት ያለውን ያልተቋረጠ ዝግጁነት ማሳወቃቸውን ከፅ/ ቤታቸው የወጣው መግለጫ ይጠቁማል። (VOA)

የኢትዮጵያ የፌዴራሉ መንግስት ካወጀው የተናጠል ሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ ተኩስ አቁም ጋር ተያይዞ የሚወጡት መግለጫዎች ቀጥለዋል።
በተለያዩ ወቅት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር እና ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው ያገለገሉት ፦
- ዴቪድ ሺና፣
- ቪኪ ሐድልስተን፣
- ፓትሪሺያ ሃስላች፣
- ኦውሪሊያ ብራለዚል
- ቲቦር ናዥ የተኩስ አቁም ውሳኔውን ተከትሎ መግለጫ አውጥተዋል።
በትግራይ ክልል የነበረውን ሁኔታ በቅርበት ሲከታተሉ መቆየታቸውን ገልጸው የፌደራሉ መንግሥት የሰላም አማራጭ ማቅረቡ "ትልቅ እፎይታን ፈጥሮልናል" ብለዋል።
አምባሳደሮቹ ይህ መልካም አጋጣሚ መታለፍ የለበትም ያሉ ሲሆን በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በሙሉ በመንግሥት የቀረበውን ጥሪ እንዲቀበሉ አሳስበዋል።
የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ስፍራዎች በበጎ አድራጊ ተቋማት ተደራሽ እንዲሆኑ፣ በትግራይ ያሉ የውጭ ኃይሎች ከግጭቱ ክልል ለቀው እንዲወጡ እና የግጭቱ ተሳታፊዎች ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም በትግራይ ቀጣይ ሁኔታ ላይ ከስምምነት ለመድረስ ውይይትና ድርድር እንዲያደርጉ ጥሪ ማቀረባቸውን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሀገር መከላከያ ሰራዊት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ በመከላከያ በኩል ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ናቸው መግለጫውን የሰጡት።
ምን አሉ ?
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፦
- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከመቐለ ለቆ በመውጣቱን ገልፀዋል። "እንደምንወጣ ከሳምንታት በፊት የነገርናቸው የውጭ ተቋማት ነበሩ ብለዋል።
- በሁሉም አቅጣጫ ማለትም በሱዳን ፣ ኤርትራ አፋር እና አማራ ወሰን ዝግ መሆኑን ገልፀዋል።
- የፌዴራል መንግስት ከዚህ በኋላ በትግራይ ክልል ዙሪያ ለሚኖር ችግር ተጠያቂ እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡
- ዓለም አቀፍ ተቋማት ፥ “ከዚህ በኋላ ዕርዳታ ደረሰ አልደረሰ ብለው የፌዴራል መንግስትን ሊጠይቁ” እንደማይገባ ገልፀዋል፤ የትግራይ ክልልን በተመለከተ ሙሉ ኃላፊነቱን አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው "ህወሃት" እንደሚወሰድ አሳውቀዋል።
- በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት ኢትዮጵያን ለከፍተኛ ኪሳራ እንደዳረጋት ገልጸዋል፤ በልማት ሂደቱ ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ተናግረዋል፡፡
- ሕወሃት የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ እንደጣለ ተናግረዋል፤ ሱዳን የኢትዮጵያን ሉኣላዊ ድንበር ጥሳ እንድትገባ አጋልጦ እንደነበርም ገልፀዋል።
- 8 ወራት ብቻ የጦር ወጪን ሳይጨምር የፌደራሉ መንግሥት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማደረጉን ገልጸዋል።
ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-Update-06-30

TIKVAH-ETHIOPIA
#Live የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተረጋገጡ የምርጫ ክልሎችን ውጤት እያሳወቀ ይገኛል። በአሁን ሰዓት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ። ከላይ በ Voice Chat አድምጡ። @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ምርጫ_ቦርድ_የ6ተኛዉ_አጠቃላይ_ሀገራዊ_ምርጫ_ዉጤት_.pdf
2.7 MB
#ምርጫ2013
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው ዕለት ይፋ ያደረጋቸው የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶች ከላይ በ PDF ፋይል (2.7 MB) ተያይዟል።
@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው ዕለት ይፋ ያደረጋቸው የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶች ከላይ በ PDF ፋይል (2.7 MB) ተያይዟል።
@tikvahethiopia
#Tigray
በትግራይ በሚገኙት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልጆቻቸውን ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች ሙሉ በሙሉ ኔትዎርክ በመቋጠረጡ ልጆቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ተማሪዎች ስላሉበት ሁኔታም በአስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ልጃቸውን ልከው የሚያስተምሩ የቲክቫህ አባል፥ ስላልጃቸው ደህንነት ማወቅ ባለመቻላቸው በከፍተኛ ሁኔታ እሳቸውን ጨምሮ መላ ቤተሰቡ ጭንቀት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ተቋማቱን አምነው ጥሪ ሲቀርብ ልጃቸውን እንደላኩ የገለፁት አባላችን ተቋማቱን የሚይመራው አካል እስካሁን ግንፅ ማብራሪያ አለመስጠቱ እጅግ እንዳሳዘናቸው አስረድትዋል።
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ልጃቸውን ልከው የሚያስተምሩ ሌላ እናት በላኩት መልዕክት ልጃቸውን ባለፉት ቀናት ሊያገኙት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው በፌዴራል እና መከላከያ ጥበቃ ስር ነበር እኛም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው በሚል ነው ልጆቻችን አምንነ የላክነው አሁን ግን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አናውቅም ብለዋል።
የፌዴራል ጠባቂዎች ቀድመው እንደሚወጡ ከታወቀ ለምን ልጆቻችን እንዲመለሱ አልተደረግም ሲሉም ጠይቀዋል ? ቤተሰብ በእጅጉ ተጨንቋል አስቸኳይ ማብራሪያ እንፈልጋለን ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወላጆች እያቀረቡት ላለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው፤እስካሁን ግን ምላሽ አላገኘም።
በሌላ በኩል የራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ ነው፥ በግቢው የቀሩ ተማሪዎች እንዳሉ የራያ ዩኒቨርሲቲ ቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል።
በትግራይ በኔትዎርክ መቋረጥ ምክንያት መሬት ላይ ስላለው አሁናዊ ሁኔታ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት አልተቻለም።

ይህ ገፅ የዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ) ገፅ ነው ?
ፌስቡክ ላይ ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ዓዴፓ Assimba Democratic party-ADP በሚል ስም የተከፈተ እና ከ20 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ገፅ #ሀሰተኛ ነው።
ከትላትን ጀምሮ ይህን ገፅ ዋቢ አድርገው የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲሁም አንድ ዓለም አቀፍ ሚዲያ (ዶቼ ቨለ) መረጃዎችን ሲያጋሩ ተመልክተናል።
የፓርቲው ሊቀመንበር ከመታሰራቸው ከወራት በፊት ገፁ ሀሰተኛ ስለመሆኑ አሳውቀው ነበር።
የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዶሪ አስገዶም "ገፁ ሀሰተኛ መሆኑን ፣ በዚሁ ሀሰተኛ ገፅ ላይ የሚወጡ መረጃዎች እና መግለጫዎች ዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ዓዴፓ)ን የማይወክሉ እንደሆነ" በተደጋጋሚ ገልፀው ነበር።
አቶ ዶሪ አስገዶም ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ በኢሮብ ወረዳ የኤርትራ ወታደሮች ወረራ እየፈጸሙ ነው በማለታቸው ሳቢያ ለእስር ስለመዳረጋቸው ነው ከፓርቲው የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው።
አቶ ዶሪ ታስረው የሚገኙት አዲስ አበባ ውስጥ ነው።

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በአፋርና በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና መሰጠት ተጀምሯል።
ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም በሶማሌ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና መሰጠት እንደጀመረ ይታወቃል።

#HachaluHundessa
አዲሱ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ “ማል መሊሳ (Maal Mallisaa) የሙዚቃ አልበም በዓለም አቀፉ የኢንተርኔት የሙዚቃ መሸጫ በiTunes ወርልድ ቻርት ሽያጭ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
አልበሙ እስከ ትናንት ባለ መረጃ በተለቀቀ በሁለት ቀናት ውስጥ ነው 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለው።
“ማል መሊሳ” አለበም በ iTunes በሀገራት ባለው ሽያጭ ያለው ደረጃ ሲታይ በአውስትራሊያ፣ በካናዳ እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች 1ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በአሜሪካ በ2ኛ ደረጃ ላይ፣ በብሪታንያ 9ኛ ደረጃ ላይ እንዲሁም በበርካታ ሀገራት እስከ 10 ባሉ ደረጃዎች ላይ መቀመጥ ችሏል።
በአይቱንስ ወርልድ የሙዚቃ ሽያጭ ሰንጠረዥ በየሰዓቱ የሚለዋወጥ ሲሆን ፤ የሙዚቃው የሽያጭ ደረጃ ሊጨምር አሊያም ሊቀንስ ይችላል።
አልበሙ በሀገር ውስጥ የኢንተርኔት የሙዚቃ መሸጫ በሆነው በ “ አውታር ” ላይም በ1ኛ ደረጃ እየተሸጠ ይገኛል ሲል አል አይን በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

#Tigray በትግራይ በሚገኙት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልጆቻቸውን ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች ሙሉ በሙሉ ኔትዎርክ በመቋጠረጡ ልጆቻቸው ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ተማሪዎች ስላሉበት ሁኔታም በአስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ልጃቸውን ልከው የሚያስተምሩ የቲክቫህ አባል፥ ስላልጃቸው ደህንነት ማወቅ ባለመቻላቸው በከፍተኛ ሁኔታ…
#MoSHE
የኢፌዴሪ ሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ማምሻው በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ላሉ ተማሪዎች ቤተሰቦች አጭር መልዕክት አሰራጭቷል።
ሚኒስቴሩ በመልዕክቱ በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት እና የተቋማት አመራሮች ጋር እየመከረ እንደሚገኝ ገልጿል።
የተማሪዎች ቤተሰቦችም በትዕግሥት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

#Ethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ሞት አልተመዘገበም።
እንደ ኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ዕለታዊ ሪፖርት በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሞት አልተመዘገበም።
ከረጅም ወራቶች በኃላ ነው በ24 ሰዓት ውስጥ ምንም ሞት አለመመዝገቡ ሪፖርት የተደረገው።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 4,974 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 137 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ፦
- በመላው የትግራይ ከተሞች ኔትዎርክ ባለመኖሩ መሬት ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለ ለማወቅ አሁንም አዳጋች እንደሆነ ቀጥሏል።
- በተባበሩት መንግስታ ድርጅት (UN) የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ትግራይ ውስጥ ሁሉም የታጠቁ ወካላ ስለተኩስ አቁሙን እንዲያከብሩ ማለታቸው።
- ተመድ-UN መቐለ እና ሽረ የተረጋጋ ሁኔታ አለ ያለ ሲሆን በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ግን ግጭት እንዳለ ጠቁሟል። ቴሌኮሚኒኬሽን እና ኤሌክትሪክ በመላው ትግራይ እንደተቋረጠ መሆኑን ገልጿል።
- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ወደ ኤርትራ እና ሱዳን የሚወስደው ድንበር ዝግ መሆኑን፣ ወደ አፋር እና አማራ በኩል ያለው ወሰንም ዝግ መሆኑን ገልፀዋል፤ የእርዳታ እና ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሄደው ከመሃል ሀገር ነው እሱ ይገባል ከዛ ውጭ ግን (ከእርዳታ ውጭ) ሌሎች እንቅስቃሴዎች እንዳይኖር ጥብቅ ፍተሻ ይደረጋል ብለዋል።
- በትግራይ ክልል የታወጀው የተኩስ አቁም አዋጅ #ጊዜያዊ ሊሆን ይችላል በሚል የአሜሪካ ም/ቤት አንጋፋ አባላት እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ዴሞክራቱ ሪግሪ ሜክስ TPLF ኤርትራ ለመግባት መዛቱ ግልፅ እና አደገኛ ግጭቱን የማባባስ ተግባር ይሆናል ብለዋል።
- አቶ ጌታቸው ረዳ፥ "የተኩስ አቁም" ከመደረጉ በፊት የኤርትራ ጦር ይውጣ ብለዋል፤ የኤሌክትሪክ ኃይል እና ቴሌኮሚኒኬሽን እንዲመለስም አሳስበዋል፤ ኤሌክትሪክ እና ሌሎች አገልግሎቶችን አቋርጦ ሰላም ለማውረድ መጠበቅ አይቻልም ሲሉ ገልፀዋል።
- UNICEF በትግራይ ክልል ህፃናት ላይ ስለተጋረጠው አደጋ አሳውቋል።
- ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ከጋዜጠኞች ጋር የነበራቸው ቆይታ ፤ ባለፉት 8 ወራት ከወታደራዊ ጉዳዮች ወጪ ለመንገድ ለመብራት፣ ለሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ትግራይ ውስጥ ከአንድ መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ገልፀዋል።
ሁሉንም በዝርዝር ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tigray-Update-06-30-2
(ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የተዘጋጀ የተሰባሰበ ሪፖርት)

Telegraph
Tigray Update
#Tigray በትግራይ ያለው ሁኔታ በግልፅ ለማወቅ አዳጋች ሆኖ ቀጥሏል። በመላው የክልሉ ከተሞች ኔትዎርክ ባለመኖሩ መሬት ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም። አንዳንድ ዓለም አቀፍ ተቋማት በሳተላይት ስልክ ያለውን ሁኔታ ለማሳወቅ እየጣሩ ይገኛሉ፤ ሁኔታዎች አሁንም እንዳልተሻሻሉ እና ለሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ፈታኝ መሆኑን እየገለፁ ነው። በክልሉ ኔትዎርክ ከመቋረጡ በተጨማሪ በክልሉ የኤሌክትሪክ…
#Update
ኢትዮጵያ በትናትናው ዕለት 2 ሺ 386 ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ በማስወጣት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጋለች።
ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደሀገር የመመለሱ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል።