TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ሙስጠፋ ማን ናቸው?⬆️

አቶ ሙስጠፋ ሙሐሙድ ዑመር በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሶማሌ ክልል #ጊዜያዊ መሪ ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ሙስጠፋ በክልሉ በስልጣን ላይ ያለዉ የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አባል ባይሆኑም በጊዜያዊነት ላለፉት ሁለት ሳምንታት በሥልጣን የቆዩትን አሕመድ አብዲ መሐመድን ተክተው ለመጪዎቹ ሁለት አመታት ክልሉን ይመራሉ።

በርዕሰ-መሥተዳድርነት እንዲያገለግሉ መመረጣቸው እስከተሰማ ድረስ ከነ ቤተሰቦቻቸው ኬንያ ይኖሩ የነበሩት አቶ ሙስጠፋ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሶማሊያ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በመስራት ላይ ነበሩ።

ኢትዮጵያ ከወጡ በኋላ የሕጻናት አድን ድርጅትን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ አገልግለዋል።

አቶ ሙስጠፋ የተወለዱት ከጅጅጋ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ በምትርቀው አዋሬ የተባለች አነስተኛ ከተማ በ1964 ዓ.ም. ነው። ትምህርታቸውን በደገሐቡር እና በሐረር የመድሐኒዓለም ትምህርት ቤቶች ተከታትለዋል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪቸውን በኤኮኖሚክስ አግኝተዋል። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በዚያው በኤኮኖሚክስ ከለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ በተልዕኮ ትምህርት አግኝተዋል።

ከዚህ ቀደም የሶማሌ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የዶክተር አብዱል መጂድ ሑሴን መምህራን ማሰልጠኛ ማዕከል ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

ከኢትዮጵያ ለምን ወጡ⬇️

አቶ ሙስጠፋ በቅርቡ ከሥልጣናቸው የተነሱት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር የክልሉን የርዕሰ-መሥተዳድርነት ሥልጣን ሲቆጣጠሩ ነው የሶማሌ ክልልን የለቀቁት።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኤኮኖሚክስ ተማሪ ሳሉ የአቶ ሙስጠፋ ጓደኛ የነበሩት አቶ ዚያድ አሕመድ የቀድሞው ርዕሰ መሥተዳድር አብዲ መሐመድ ዑመር "ያደርሱባቸው የነበረውን ችግር #ሸሽተው" ከነ ቤተሰቦቻቸው #ኬንያ ለመግባት መገደዳቸውን ያስታውሳሉ።

ከሁለት አመታት በፊት አቶ ሙስጠፋ በክልሉ መንግሥት ላይ የሚሰነዝሩትን ተቃውሞ እንዲያቆሙ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ አሻፈረኝ በማለታቸው የምኅንድስና ባለሙያ #ወንድማቸው ፋይሰል ኦማር በልዩ ፖሊስ ከደገሐቡር ከተማ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ #መገደላቸው ይነገራል። አቶ ዚያድም "ውጪ ያሉት አራማጆች በአብዲ ኢሌ ላይ ወይም በነበረው አገዛዝ ላይ ተቃውሞ ካሰሙ ወይም አንድ ነገር ካደረጉ ቤተሰቦቻቸው ይታሰራሉ ወይም ይገረፋሉ። አቶ ሙስጠፋም ወንድማቸውን ያጡት በዚህ አጋጣሚ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ዚያድ የድሮ ጓደኛቸው የሶማሌ ክልልን ለመምራት ይመረጣሉ የሚል ቅድሚያ ግምት አልነበራቸውም። "አልጠበቅኩም። እሱ የውጪ ሰው ነው። የፓርቲ አባልም አልነበረም" ይላሉ። አቶ ሙስጠፋ ከዚህ ቀደም ክልሉን ይመሩ የነበሩት አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር የሚታወቁ የለውጥ አቀንቃኝ ነበሩ። በክልሉ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚያጋልጡ የቀድሞውን አስተዳደር
የሚሞግቱ ጽሁፎች በሶማሊኛ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ሲፅፉ ቆይተዋል። በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይም የጎላ ተሳትፎ ነበራቸው።

የሶማሌ ክልል ፖለቲካን በቅርብ የሚከታተሉት አቶ ዚያድ ተመራጩ ፕሬዝዳንት በርካታ እና ውስብስብ የቤት ሥራ እንደሚጠብቃቸው አልዘነጉም። "የሕግ የበላይነት፣ ሰላም እና መረጋጋት መምጣት አለበት። ሥራ አስፈፃሚው፣ ሕግ አውጪው እና ሕግ ተርጓሚው ሪፎርም ይፈልጋል" ይላሉ አቶ ዚያድ።

ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ (DW Amharic)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ፦

- በመላው የትግራይ ከተሞች ኔትዎርክ ባለመኖሩ መሬት ላይ ምን እየተካሄደ እንዳለ ለማወቅ አሁንም አዳጋች እንደሆነ ቀጥሏል።

- በተባበሩት መንግስታ ድርጅት (UN) የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ትግራይ ውስጥ ሁሉም የታጠቁ ወካላ ስለተኩስ አቁሙን እንዲያከብሩ ማለታቸው።

- ተመድ-UN መቐለ እና ሽረ የተረጋጋ ሁኔታ አለ ያለ ሲሆን በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ግን ግጭት እንዳለ ጠቁሟል። ቴሌኮሚኒኬሽን እና ኤሌክትሪክ በመላው ትግራይ እንደተቋረጠ መሆኑን ገልጿል።

- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ወደ ኤርትራ እና ሱዳን የሚወስደው ድንበር ዝግ መሆኑን፣ ወደ አፋር እና አማራ በኩል ያለው ወሰንም ዝግ መሆኑን ገልፀዋል፤ የእርዳታ እና ሰብዓዊ ድጋፍ የሚሄደው ከመሃል ሀገር ነው እሱ ይገባል ከዛ ውጭ ግን (ከእርዳታ ውጭ) ሌሎች እንቅስቃሴዎች እንዳይኖር ጥብቅ ፍተሻ ይደረጋል ብለዋል።

- በትግራይ ክልል የታወጀው የተኩስ አቁም አዋጅ #ጊዜያዊ ሊሆን ይችላል በሚል የአሜሪካ ም/ቤት አንጋፋ አባላት እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ዴሞክራቱ ሪግሪ ሜክስ TPLF ኤርትራ ለመግባት መዛቱ ግልፅ እና አደገኛ ግጭቱን የማባባስ ተግባር ይሆናል ብለዋል።

- አቶ ጌታቸው ረዳ፥ "የተኩስ አቁም" ከመደረጉ በፊት የኤርትራ ጦር ይውጣ ብለዋል፤ የኤሌክትሪክ ኃይል እና ቴሌኮሚኒኬሽን እንዲመለስም አሳስበዋል፤ ኤሌክትሪክ እና ሌሎች አገልግሎቶችን አቋርጦ ሰላም ለማውረድ መጠበቅ አይቻልም ሲሉ ገልፀዋል።

- UNICEF በትግራይ ክልል ህፃናት ላይ ስለተጋረጠው አደጋ አሳውቋል።

- ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ከጋዜጠኞች ጋር የነበራቸው ቆይታ ፤ ባለፉት 8 ወራት ከወታደራዊ ጉዳዮች ወጪ ለመንገድ ለመብራት፣ ለሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ትግራይ ውስጥ ከአንድ መቶ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ገልፀዋል።

ሁሉንም በዝርዝር ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tigray-Update-06-30-2

(ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የተዘጋጀ የተሰባሰበ ሪፖርት)

@tikvahethiopia
#ጊዜያዊ_መታወቂያ !

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ መመሪያ ፥ የጊዜያዊ መታወቂያ አሰጣጥ ስርዓት መመሪያ አውጥቷል፡፡

* መመሪያው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Confirmed በደቡብ አፍሪካ በነበረው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ድርድር ላይ ከብዙ ክርክሮች በኃላ በሁለቱም ወገኖች የተፈረመው የስምምነት ዝርዝር ሰነድ ከላይ የተያያዘው ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ የተለያዩ ስምምነቱን የሚገልፁ " Draft " ወረቀቶች ሲሰራጭ የነበር ቢሆንም ከሰላም ንግግሩ አመቻቾች (አፍሪካ ህብረት)፣ ከሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎች…
#Update

ዛሬ " የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ " አባላት ፤ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አጠቃላይ ሂደት እና ቀጣይ ስራዎችን በሚመለከት ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ለሁለቱ ም/ቤቶች አፈ-ጉባኤዎች ፣ ለክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮች ፣ ለከፍተኛ ባለስልጣናት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሀሴን የተናገሩት ፦

- ስምምነቱ በዋናነት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላም፣ ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነትን ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝቦችን የጋራ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ተጠናቋል።

- በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችልና ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ማክበር እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

- ከህገ-መንግስት ውጪ ያሉ እንቅስቃሴዎች ቆመው በትግራይ ክልል በህገ-መንግስቱ መሰረት ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ #ጊዜያዊ_አስተዳደር ይቋቋማል።

- ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ቀደመው ማህበራዊ ትስስር እንዲመለሱ በጋራ ይሰራል።

- የወደሙ ተቋማትን ጨምሮ የመልሶ ግንባታ ስራዎች በጋራ ርብርብ ሊከናወኑ ይገባል። የትስስርና የተግባቦት ስራዎች የህዝቦችን መጻኢ የጋራ ጉዞ ታሳቢ ያደረጉ ሊሆኑ ይገባል።

- በግጭቱ ምክንያት በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲ እንዲሁም በሌሎች መስኮች የደረሰውን ጫና በማስተካካል ረገድ በትብብር መስራት ይጠበቃል።

- የመገናኛ ብዙሃን #ቁርሾዎችን ማባባስ ሳይሆን ዜጎች ከችግሩ ተምረው በቀጣይ አብሮነታቸውን አጠናክረው የሚሄዱበትን ሁኔታ መፍጠር ላይ ሊሰሩ ይገባል።

- #በማወቅም ሆነ #ባለማወቅ የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚሰሩ ኣካላትን በጋራ ማስቆም ይገባል።

- ሁሉም ዜጋ ለሰላም ስምምነቱ #ተግባራዊነት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሊወጣ  ይገባል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ዕግዱ ተነሳ።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በማህበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ጥሎት የነበረውን #ጊዜያዊ ዕግድ ዛሬ አርብ ማንሳቱን አሳውቋል።

@tikvahethiopia