TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
"Maal Mallisaa" ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመሞቱ በፊት ሰርቶ ያጠናቀቀው 3ኛ አልበሙ ሊወጣ እየተጠናቀቀ መሆኑ ተሰምቷል። የአዲሱ አልበም ማስታወቂያዎች በመዲናችን አዲስ አበባ እየተለጠፉ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአልበሙን መውጣት በሚጠባበቁት ዘንድ ልዩ ትኩረትን ስቧል። የአልበሙ ስያሜ "Maal Mallisaa" እንደሚሰኝም ታውቋል። የአዲሱ አልበም መውጫ ቀን መቼ ነው? የሚለው ለጊዜው…
#HachaluHundessa

የዝነኛው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሴ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ሰርቶ ያጠናቀቀው ሙሉ አልበም በሚቀጥለው ሳምንት ይለቀቃል ብለዋል።

ወ/ሮ ፋንቱ ደምሴ ፥ የፊታችን ሰኞ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ በ34 ዓመቱ ከተገደለ 1 ዓመት እንደሚሆነው አስታውሰዋል።

አክለውም ፥ "ህዝቡ ለእሱ ያለውን ስሜት አውቃለሁ፤ ድምፁን መስማት ያፅናናቸዋል ብዬ አስባለሁ" ብለዋል።

ወ/ሮ ፋንቱ የድምፃዊ ሃጫሉ አዲሱ (3ኛው) አልበም ከመሞቱ ብዙም ሳይቆይ በፊት የተቀዱ ስራዎች እንዳሉት ተናገረዋል።

አዲሱ አልበም "Maal Mallisaa" የሚሰኝ ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙ "መፍትሄው ምንድነው ?" የሚል ነው።

በነገራችን ላይ አልበሙ በቀጣይ ሳምንት ለገበያ የሚቀርብ ቢሆንም ዛሬ ማምሻውን ጀምሮ በ iTunes ላይ ቀርቧል ፤ እዛ ላይ በመግዛት ማዳመጥ ይቻላል።

ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ አልበሙ በCD አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ለገበያ ይቀርባል።

ውድ የቲክቫህ አባላት አልበሙን ህጋዊ በሆነ መንገድ ብቻ በመግዛት እንድታዳምጡ እናበረታታለን፤ በማህበራዊ ሚዳያዎች ላይ በህገወጥ መንገድ እንዳይሰራጭ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ አድርጉ።

ድምፃዊ ሃጫሉ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም ምሽት በሰው እጅ በጥይት ተመቶ መገደሉ ይታወሳል።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
#HachaluHundessa

አዲሱ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ “ማል መሊሳ (Maal Mallisaa) የሙዚቃ አልበም በዓለም አቀፉ የኢንተርኔት የሙዚቃ መሸጫ በiTunes ወርልድ ቻርት ሽያጭ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አልበሙ እስከ ትናንት ባለ መረጃ በተለቀቀ በሁለት ቀናት ውስጥ ነው 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለው።

“ማል መሊሳ” አለበም በ iTunes በሀገራት ባለው ሽያጭ ያለው ደረጃ ሲታይ በአውስትራሊያ፣ በካናዳ እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች 1ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በአሜሪካ በ2ኛ ደረጃ ላይ፣ በብሪታንያ 9ኛ ደረጃ ላይ እንዲሁም በበርካታ ሀገራት እስከ 10 ባሉ ደረጃዎች ላይ መቀመጥ ችሏል።

በአይቱንስ ወርልድ የሙዚቃ ሽያጭ ሰንጠረዥ በየሰዓቱ የሚለዋወጥ ሲሆን ፤ የሙዚቃው የሽያጭ ደረጃ ሊጨምር አሊያም ሊቀንስ ይችላል።

አልበሙ በሀገር ውስጥ የኢንተርኔት የሙዚቃ መሸጫ በሆነው በ “ አውታር ” ላይም በ1ኛ ደረጃ እየተሸጠ ይገኛል ሲል አል አይን በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

@tikvahethiopia