TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ትላንት የሀገር መከላከያ ሰራዊት አቶ ስብሓት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የህወሓት አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ማስታወቁ ይታወሳል። በመንግስት ስር ያለው ኢዜአ አመራሮቹ እንደተያዙ የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃ በማህበራዊ ሚዲያ አሰራጭቷል። ማምሻውን በመገናኛ ብዙሃን በተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚቀርብም ገልጿል። @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

ቀደም ሲል እንደተገለፀው አቶ ስብሃትን ጨምሮ ዘጠኝ የህወሓት አመራሮች በመከላከያ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃ ምሽቱን በኢዜአ በኩል ተሰራጭቷል።

የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር የዋሉት በማዕከላይ ትግራይ ውስጥ ኤዴር አዴት በሚባል አከባቢ ልዩ ስሙ "ጅራ" በሚባል ቦታ ሲሆን ዛሬ በጦር አውሮፕላን ተጭነው አዲስ አበባ ገብተዋል። [50 MB]

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#SriwijayaAirBoeing737 ከጃካርታ ከተነሳ በደቂቃዎች ውስጥ ደብዛው የጠፈው እና በፍላጋ ላይ የሚገኘው የኢንዶኔዥያ የመንገደች አውሮፕላን (Sriwijaya Air Boeing 737) በውስጡ 56 መንገደኞች (7 ህፃናትን ጨምሮ) ፥ 6 የበረራ ሰራተኞችን ይዟል። አውሮፕላኑ የጠፋው ከጃካርታ ወደ ፖንታይናክ እየበረረ በነበረበት ወቅት ነው። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ከጃካርታ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ግንኙነቱ የተቋረጠው የመንገደኞች አውሮፕላን ባሕር ላይ ሳይከሰከስ እንዳልቀረ ተነገረ።

በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ቢያንስ አንድ ፍንዳታ ማየታቸውን እና መስማታቸውን ለBBC ተናግረዋል።

አንድ ዓሳ አስጋሪ ለቢቢሲ የኢንዶኔዢያ አገልግሎት ፥ የአውሮፕላኑን መውደቅ መመልከቱንና አብሮት ከነበረው መርከበኛ ጋር ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመመለስ መወሰናቸውን ተናግሯል።

"አውሮፕላኑ አንደ መብረቅ ባሕሩ ላይ ወድቆ ውሃው ላይ ነው ፈነዳው" ሲልም ተናግሯል።

"ለእኛ በጣም ቅርብ ነበረ፤ ስብርባሪው የነበርንበትን መርከብ ለጥቂት ሊመታው ነበር።" ሲልም አክሏል።

የኢንዶኔዢያ ትራንስፖርት ሚኒስቴር አውሮፕላኑን የመፈለግና ነፍስ ማዳን ጥረት እተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የኢንዶኔዢያ ባሕር ኃይል አውሮፕላኑን ለመፈለግ ተሰማርቷል። ~ BBC

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,952
• በበሽታው የተያዙ - 220
• ህይወታቸው ያለፈ - 11
• ከበሽታው ያገገሙ - 113

አጠቃላይ 127,792 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,985 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 113,295 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

200 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነገ በአ/አ የሚዘጉ መንገዶች !

የታላቁ የሩጫ ውድድር ምክንያት የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ኮቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ህንፃ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል የሚወስደው መንገድ የቀድሞ አራተኛ ክፍልጦር

- ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው ኬኬ ህንፃ ወይም ጨርቆስ ማዞሪያ

- ከሳር ቤት ወደሜክሲኮ ለሚመጡ አፍሪካ ህብረት አደባባይ

- ከካርል አደባባይ ወደከፍተኛ ፍ/ቤትየሚወስደውመንገድ ልደታ ፀበል

- ከጦርኃይሎች ወደ ሚክሲኮ ለሚመጡ ኮካ መገንጠያ ሜክሲኮ ለሚመጡ ጆስሐንሰን

– ከመርካቶ በጎማ ተራ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚመጡ በርበሬበረንዳ

- ከተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በጎማ ቁጠባ የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር (ሼልድሬንስ)

- ከቸርቸር ወደ አምባሳደር ፣ ሜክሲኮ እና ለገሃር ለሚመጡ ቴድሮስአደባባይ

- ከአዋሬ ወደ ካዛንቺስ ለሚመጡ ሴቶች አደቤይ

- ከመገናኛ ወደ 22 ለሚመጡ ዘሪሁን ህንፃ

- ከቦሌ መድኃኒያለም የሚመጡ አትላስ ሆቴል አካባቢ

ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ በተጨማሪም ከውስጥ ለውስጥ መንገዶች ተወዳዳሪዎቹ ወደሚያልፉባቸው መንገዶች መውጣት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንድትጠቀሙ መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪም ወድድሩ በሚካሄድባቸው መንገዶች ከማለዳው 11 ሰዓት ከ 30 ጀምሮ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ ነው።

ማንኛውም አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥም ሆነ ለፖሊስ መረጃ ለመስጠት 011-1-11-01 11 እና በ991 ነፃ የስልክ ቁጥሮች መጠቀም ይቻላል።

(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የነገው የታላቁ ሩጫ መነሻ እና መድረሻ ፦

ወድድሩ መነሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ ይጀምራል ፥ በአዲስ አበባ ስታዲዮም - ሜክሲኮ አደባባይ - በልደታ ቤተክርስቲያን በማድረግ በዛጉዌ ህንፃ በኩል በመታጠፍ - በጌጃ ሰፈር - ጎማ ቁጠባ በፍልውሃ በመድረግ በካዛንቺስ - በኡራኤል ቤተክርስቲያን የአትላስ መንገድን ይዞ አክሱም ህንፃ አጠገብ መድረሻውን ያደርጋል።

PHOTO : FILE
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ከጃካርታ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ግንኙነቱ የተቋረጠው የመንገደኞች አውሮፕላን ባሕር ላይ ሳይከሰከስ እንዳልቀረ ተነገረ። በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ቢያንስ አንድ ፍንዳታ ማየታቸውን እና መስማታቸውን ለBBC ተናግረዋል። አንድ ዓሳ አስጋሪ ለቢቢሲ የኢንዶኔዢያ አገልግሎት ፥ የአውሮፕላኑን መውደቅ መመልከቱንና አብሮት ከነበረው መርከበኛ ጋር ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመመለስ መወሰናቸውን…
#update

የኢንዶኔዢያ ባለስልጣናት የመንገደኞች አውሮፕላኑ ወድቆበታል ብለው ያመኑትን ቦታ ባሕር ላይ መለየታቸውን አስታውቀዋል።

ዛሬ ከባሕር ውስጥ የአውሮፕላኑ የበረራ መመዝገቢያ ሳጥን ሳይሆን አይቀርም የተባለ ምልክት በፍለጋ ላይ በተሰማሩ ሠራተኞች ተገኝቷል።

አውሮፕላኑ ወድቆበታል ወደተባለው የባሕሩ ክፍል ከ10 በላይ መርከቦች ከባሕር ኃይል ጠላቂ ባለሙያዎች ጋር ተሰማርተዋል።

"በሁለት ቦታዎች ላይ ከአውሮፕላኑ ጥቁር ሳጥን ውስጥ የተላለፉ ሳይሆኑ የማይቀሩ ምልክቶችን ለይተናል" ሲሉ የኢንዶኔዢያ የአደጋ ጊዜ ፍለጋና ነፍስ የማዳን ተቋም ኃላፊ ባጉስ ፑቱሂቶ ተናግረዋል።

መርማሪዎች የአውሮፕላኑ ናቸው በተባሉ ጎማ እና ሌሎች ስብርባሪዎች ላይ ምርመራ እያደረጉ ነው።

የጃካርታ ፖሊስ ቃል አቀባይ ዩስሪ ዩኑስ እንደተናገሩት በፍለጋና ነፍስ የማዳን ሥራ ላይ ከተሰማሩ ሠራተኞች ሁለት ሻንጣዎችን መቀበላቸውን አሳውቀዋል።

"አንደኛው ሻንጣ የተሳፋሪዎችን ንብረት የያዘ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ የሰው አካል ያለበት ነው" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። አክለው "አስካሁን የመለየት ሥራ እያከናወንን ነው" ብለዋል።

የፍለጋና ነፍስ የማዳን ሥራው ቅዳሜ ምሽት ላይ እንዲቋረጥ ተደርጎ ዛሬ ዕሁድ ጠዋት ተጀምሯል።

በፍለጋው ላይ እንዲያግዙ አራት (4) አውሮፕላኖች ተሰማርተዋል።

የጠፋው አውሮፕላን #ኢትዮጵያ ውስጥ ተከስክሶ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውና ከበረራ ውጪ እንዲሆን የተደረገው የቦይንግ ማክስ 737 አይነት እንዳልሆነ አየር መንገዱ አሳውቋል። ~ BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GreatEthiopianRun

የ20ኛው የ2013 ዓ.ም የታላቁ ሩጫ የወንዶች አሸናፊዎች ፦

1ኛ. አቤ ጋሻሁን - ከአማራ ማረሚያ

2ኛ. ታደሰ ወርቁ - ደቡብ ፓሊስ

3ኛ. ሚልኬሳ መንገሻ - ከሰበታ ክለብ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#GreatEthiopianRun

የ20ኛው የ2013 ዓ.ም የታላቁ ሩጫ የሴቶች አሸናፊዎች ፦

1ኛ. ፅጌ ገ/ሰላማ - ከኢትዮ አትሌትክስ

2ኛ. መድን ገ/ስላሴ - ከንግድ ባንክ

3ኛ. ገበያነሽ አያሌው - ከመከላከያ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
20ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር።

ፎቶ : Great Ethiopian Run
@tikvahethsport @tikvahethiopia
#AddisAbabaPoliceCommission

የ2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የ2013 ታላቁ ሩጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ነው የተጠናቀቀው።

ለውድድሩ በሰላም መጠናቀቅ የአ/አ ከተማ ነዋሪዎች፣ የፌዴራል ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት፤ የፕሮግራሙ አዘጋጆች እና የተሳታፊዎች ላደረጉት ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EuropeanUnion

የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከተወያዩ በኋላ በሁሉም የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲመቻች ጠየቁ።

የእርዳታ ድርጅቶች ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የክልሉን አንዳንድ አካባቢዎች አንዲጎበኙ የተፈቀደላቸው ቢሆንም ይህ ከህወሓት ጋር ውጊያዎች የተካሄዱባቸውን ሁሉንም የክልሉን አካባቢዎች የሚያካትት አይደለም ተብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በምግብ አቅርቦት እጥረትና በዘረፋ ሳቢያ አሳሳቢ ነው ሲል ገልጾታል።

የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊው ጆሴፍ ቦሬል በትግራይ ክልል ውስጥ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር መመቻቸት አለበት ብለዋል።

ኃላፊው ጨምረውም ይህ ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበ ጥያቄ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት መፈጸም ያለበት አስፈላጊ እርምጃ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

More : https://telegra.ph/BBC-01-10

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የማሌ ብሔረሰብ “የዶኦማ” ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ትላንት ተከበረ።

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የማሌ ብሔረሰብ ለ7ኛ ጊዜ “የዶኦማ” ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ትላንት ተከብሯል።

በዓሉ ጥር መባቻ በየዓመቱ የሚከበር ነው።

በአንድ ንጉስ ስር 13 ባላባቶች በሚከውኑት ባህላዊ ስነ ሰርዓት ዓመቱ የሰላም፣ የጥጋብ፣ የአንድነት፣ የፍቅርና የብልጽግና እንዲሆን “ዖፃ” ወይም ፀሎት በማድረግ ዓመቱን የሚያስጀምሩት ልዩ ስፍራ ያለው ክብረ በዓል ነው።

የማሌ ብሔረሰብ ንጉስ አቶ እርባኖ ድልቦ ይህንን ስነ ስርዓት በበላይነት እንደመሩት ተገልጿል።

በበዓሉ ከዞኑ ከሁሉም ወረዳዎች፣ ከአጎራባች ዞኖች እና ወረዳዎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተው አጋርነታቸውን ለማሌ ልማት ማህበር በገንዘብ እና በተለያየ መንገድ ገልፀዋል። ~ SRTA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT