ከ3,500 በላይ ኢትዮጵያውያን ከሱዳን ተመለሱ።
ከ3500 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሱዳን ወደኢትዮጵያ መግባታቸውን የመተማ ዮሐንስ አካባቢ የመንግስት ኃላፊዎች እና የኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ማስታወቁን ናሁ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የመተማ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ባለሞያ የሆኑት አቶ ስጦታው ጫኔ ፥ ኢትዮጵያውያኑ ሱዳን ውስጥ በተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት መመለሳቸውን ገልፀዋል።
ሱዳን (ገዳሪፍ አካባቢ) በግብርና እና በቀን ስራ ይተዳደሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ብለዋል።
ከ80% በላይ የሚሆኑት ከካርቱም ነው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት።
ከሰሞኑ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ በነበረው ውጥረት እና በሱዳን ባለው የኢኮኖሚ ቀውስ ኢትዮጵያውያኑ መመለሳቸውን ገልፀል።
አሁንም ከሱዳን ወደኢትዮጵያ የሚመለሱ ዜጎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የኮሚኒኬሽን ባለሞያው ጠቁመዋል።
ከጥቅምት መጨረሻ ጀምሮ የሱዳን ጦር ምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች የፈፀመውን ትንኮሳ የከትሎ አካባቢው ውጥረት ስፍኖበት መቆየቱን ቴሌቪዥን ጣቢያው በዘገባው አስታውሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

👆ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ የሶስትዮሽ ስብሰባ የፕሬስ መግለጫ።
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በበይነ-መረብ ስብሰባ አካሂደዋል።
ሱዳን የባለሙያዎቹ የተጨማሪ ሃላፊነት ቢጋር ካልተዘጋጀ በቀር ውይይት መካሄድ አይችልም የሚል አቋም መያዟ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የሱዳንን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል በግድብ ደህንነት ፣ በመረጃ ልውውጥ እንዲሁም በሌሎች ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ መፍትሄ ለመስጠት ዝግጁነቷን ገልጣለች።
* ዝርዝር መረጃውን ከላይ ከተያያዘው መግለጫ ይመልከቱ።
Via Ministry of Water,Irrigation and Energy - Ethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#SriwijayaAirBoeing737 ጥቁር ሳጥኑ (የበረራ መረጃ መመዝገቢያው) ተገኘ። ከጃካርታ ከተማ በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እንደተከሰከሰ የሚታመነው የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን (Sriwijaya Air Boeing 737) ጥቁር ሳጥን መገኘቱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...በህይወት የሚገኝ ሰው ስለመኖሩ አጠራጣሪ ነው" - የኢንዶኔዥያ ጦር ጠ/አዛዥ
የኢንዶኔዥያ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ትላንት ከጃካርታ ከተነሳ በደቂቃዎች ውስጥ ባህር ላይ ከወደቀው የመንገደኞች አውሮፕላን በህይወት የሚገኝ ሰው ስለመኖሩ አጠራጣሪ መሆኑ አሳውቀዋል።
ባህር ላይም የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች መገኘታቸውን ገልጸዋል።
አሁንም በርካታ የሰውነት ክፍል አካላት በባህር ላይ እየተገኘ መሆኑ ተገልጿል።
የመንገደኞቹ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ይፋዊ መረጃ እየጠበቁ ነው።
ምንም እንኳን ከአደጋው የተረፈ ሊኖር እንደማይችል ቢነገርም አንዳንድ ቤተስቦች የሚወዷቸውን በህይወት ለማግኘት 'በተስፋ' ይፋዊ መረጃ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
አውሮፕላኑ በውስጡ 56 መንገደኞች (7 ህፃናትን ጨምሮ) ፥ 6 የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ነበር ይበር የነበረው።

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,381
• በበሽታው የተያዙ - 524
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 79
አጠቃላይ 128,316 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,994 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 113,374 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
202 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

ተጨማሪ የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያደረጉ ከመከላከያ የከዱ አመራሮችም እርምጃ እንደተወሰደባቸው መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።
በዚሁ መሰረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡-
1ኛ- ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል ፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበሩና አሁን የህወሓት ሎጂስቲክ ሃላፊ
2ኛ- ብርጋዴል ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም ፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ የነበሩና በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ ህወሓትን የተቀላቀሉ
3ኛ- አስር ከፍተኛ መኮንኖች
4ኛ - ሁለት መስመራዊ መኮንኖች
5ኛ- አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበሩና ከፖሊስ ከድተው ወደ ህወሓት የተቀላቀሉ ናቸው።
በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ የህወሓት አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሰራዊቱ ማምሻውን ገልጿል።
እነዚህም ፦
1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበሩ
2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩ
3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበሩ
4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበሩ
5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበሩ
6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበሩ
7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተጨማሪም ሁለት ከሀገር መከላከያ ከድተው ህወሓትን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ ናቸው። ~ ENA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#AxumUniversity
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂዎች የቲክቫህ አባላት እስካሁን አለመጠራታቸውን ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ውስጥ እንደከተታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።
ተማሪዎቹ በትግራይ ክልል ያለውን ከባድ ሁኔታ ቢረዱም ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰጠው አይነት መፍትሄ በፍጥነት ተግባራዊ ይደረጋል ብለው ቢጠብቁም እስካሁን ምንም እንደሌለ ገልፀዋል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ጉዳይ የሚከታተለው የሀገር አቀፍ ተማሪዎች ህብረት የአስክሱም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ጉዳይ ከዚህ በፊት ልክ እንደዓዲግራት መፍትሄ ያገኘ መሆኑን ገልጿል።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጨርሰው በመውጣታቸው የዓዲግራት እንዲሁም የአክሱም ተማሪዎች መቐለ ገብተው ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ በMoSHE አቅጣጫ ተቀምጧል።
በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረትም የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል።
ለአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገም።
ተማሪዎችን ለመጥራት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በማስተባበር ላይ በመዘግየቱ ነው እስካሁን የቆየው።
ተመራቂ ተማሪዎችን ለመጥራት ስራዎች እየተሰሩ ፣ ዝግጅቶችም እየተደረጉ መሆኑን ተገልጿል።
በMoSHE አቅጣጫ መሰረት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመረቁት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ነው።

ጋዜጠኛ ሀብቴ ያዕቆብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ (SMN) መስራች እና አመራር ጋዜጠኛ ሀብቴ ያዕቆብ በድንገተኛ ህመም በሚኖርበት ደቡብ አፍሪካ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ታህሳስ 29 በሞት ተለይቷል፡፡ ጋዜጠኛ ያዕቆብ ከSMN መስራችነት ባለፈም የረጅም ጊዜ የሲዳማ ሕዝብ የመብት ተሟጋች እንደሆነ ተገልጿል። እንዲሁም የሲዳማ ዳያስፖራ ኮሚውኒቲ መስራችና አመራር አባልም ነበር።…
#UPDATE
የጋዜጠኛና ሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሀብቴ ያዕቆብ አስክሬን ትላንት ምሽት #ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) ገብቷል።
ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሀብቴ ያእቆብ ባጋጠመው ህመም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ማረፉ ይታወቃል።
አስከሬኑ ይኖርበት ከነበረበት ደቡብ አፍርካ ትላንት ምሽት አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ደርሷል።
ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ደግሞ ሀዋሳ ኤርፖርት ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
የጋዜጠኛ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሀብቴ ያዕቆብ ስርዓተ ቀብር በሀዋሳ ምሺን መቃብር ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።
* አስክሬኑ ወደኢትዮጵያ ከመሸኘቱ በፊት በደቡብ አፍሪካ የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሂዶ ነበር። ፕሮግራሙ ላይ ቤተሰቦቹ ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ወዳጆቹ ፣ በደ/አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ተገኝተው ነበር። (ፎቶው ከላይ ተያይዟል)
Via Getahun D Darimo , UMH

" ...ፈተናዉ ተሰርቋል" - ፈተና የወሰዱ ሃኪሞች
ባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት ለትምህርት ዕድል የደረጃ እድገት መለያ ፈተና ከወሰዱ እና በመንግሥት ተቀጥረው ከሚሰሩ ጠቅላላ ሐኪሞች መካከል የተወሰኑ ሃኪሞች ፈተናው ቀድሞ ወጥቷል የሚል ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ።
በመጀመርያ ዲግሪ በህክምና ትምህርት ትምህርታቸውን ተከታትለው ተመርቀው በመንግሥት የህክምና ተቋማት ላይ በመላው ኢትዮጵያ እየሠሩ የሚገኙ ወደ 5 ሺህ የሚሆኑት ጠቅላላ ሐኪሞች በትምህርት ዕድል መልክ የሚሰጥ የደረጃ እድገት ለማግኘት በአቅራቢያቸው የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በመምረጥ በ20 ዩኒቨርሲቲዎች ለምዘና ተቀምጠው ነበር።
ሆኖም #በቴሌግራም ፈተናው ቀድሞ በመውጣቱ ቅሬታ አድሮብናል በማለት ሐኪሞቹ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
አንድ ቅሬታ አቅራቢ ፈተናው እሁድ ዕለት ቀድሞ ወጥቶ ተፈታኞች ይዘው ገብተው ነበር ብሏል።
ባለፈዉ ሳምንት ሰኞ ሙሉ ቀን ሁለት መቶ (200) ጥያቄዎች ለመመዘኛነት ቀርበው መፈተናቸውን የገለፀው ፈተናችንን ጨርሰን እንደወጣን ጥያቄዎቹ ቀድመው እንደወጡ ማወቅ ችለናል ሲል ለሬድዬ ጣቢያው ተናግሯል።
ሃኪሞቹ ጉዳዩ ዳግም እንዲታይ ሲሉ ጠይቀዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ሬድዮ ጣቢያው ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጤና ሚኒስቴር ምላሽ እንዲሰጥ ለማድረግ ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት አሳውቋል።

ተጨማሪ...
የድህረ ምረቃ ስፔሻሊቲ ትምህርት መግቢያ ፈተና ቀድሞ መውጣትን በተመለከት ፈተና የወሰዱ ሃኪሞች ለኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ቅሬታቸውን ዛሬ በደብዳቤ አቅርበዋል።
ሃኪሞቹ ከፈተናና ምዘና ተቋም እንዲሁም ከህክምና ሙያ ስነምግባር አንፃር ተፃራሪ በሆነ መልኩ የፈተናው ጥያቄዎች ከፈተናው መስጫ ጊዜ ቀደም ብሎ እንዲወጣ ተደርጓል ብለዋል።
ፈተናው ከመስጠቱ በፊት በተፈታኞች እጅ ፈተናው ተገቢ ባልሆነ መልኩ እንዲደርስ መደረጉንም አስረድተዋል።
የፈተናው ጥያቄዎች ቀድመው መውጣታቸውን የሚገልፁ የሃኪሞቹ መረጃዎች እና ማስረጃዎች መካከል ፦
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል የተፈተኑ ሃኪሞች ፈተናው ስለመውጣቱ ለፈታኝ አካላት አሳውቀዋል። እነሱም ለሚመለከተው አካል እንዲያሳውቁ መነገራቸው የአይን እማኞች ናቸው።
- የተወሰኑ ተፈታኞች ፈተናውን ቀድመው በቴሌግራም የተቀበሉበር ሰዓት እና ቀን ተጨባጭ ማስረጃ አለ (ይህን ማስረጃ ሃኪሞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልከዋል)
- በጣም ብዛት ያላቸው ጥያቄዎች በየቻናሉ እየዞሩ ሲሆን ፈተናው ላይ ያልመጡ ጥያቄዎች መኖር ከማዕከላዊ የጥያቄ ባንክ እንደወጡ የሚያመለክት ነው ብለዋል (ይህንም በማስረጃ አስደግፈው ለቲክቫህ ልከዋል)
* ዛሬ ለMoH እንዲገባ የተደረገው የቅሬታ ደብዳቤ (የመፍትሄ ሃሳቦችንም ያካተተ ነው) ከላይ ተያይዟል። በተጨማሪ ፈተናው ከመስጠቱ በፊት ተፈታኞች በ Xender ሲለዋወጡ የሚያሳይ መረጃም ከላይ ተያይዟል።
በፈተናው መሰረቅ ወይም ቀድሞ መውጣት ቅሬታ ያደረባቸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሃኪሞች መፍትሄ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ይገኛሉ።