TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በኮቪድ-19 የህይወታቸው ያለፈው ግለሰብ! በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ካለፈ 11 ሰዎች መካከል አንደኛው ከካፋ ዞን እንደሆነ ይታወቃል። ግለሰቡ የ55 ዓመት ዕድሜ ያላቸው በዴቻ ወረዳ በሃ ቀበሌ ውስጥ ሞተው የተገኙ ሲሆን በኃላም በተደረገው የአስክሬን ምርመራ ነው በቫይረሱ መጠቃታቸው የተረጋገጠው። እስካሁን ከሟቹ ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ 34 ሰዎች ተለይተው ወደ ቦንጋ…
ካፋ ዞን!

የካፋ ዞን ጤና መምሪያ ከቦንጋ ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን ሁለተኛ ዙር የቤት ለቤት የኮሮና ምልክት ልየታ ስራ ተጀምረ ሲሆን ናሙናዎችን በስፋት እንደሚወሰድ በዛሬው ዕለት ገልጿል።

መምሪያው ከዴቻው ሞት ጋር ቀጥታ ግንኑኝነት ያላቸውንና በቦንጋ ዩኒቨርስቲ በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሰዎች የመጀመሪያ ዙር ናሙና የሚወሰድ መሆኑን የገለፀ ሲሆን እስከአሁን 61 ሰዎች መለየታቸውን አሳውቋል፡፡

በዛሬው እለትም ትላንት ዴቻ ወረዳ 'ባጃጅ ውስጥ ሞቶ' የተገኘና ከጊምቦ ወረዳ የተጠረጠረ በድምሩ ሁለት (2) ናሙና የላከ ሲሆን የተላኩ የ12 ናሙናዎች ውጤት እንዳልደረሰውና ሲደርሰው ለህዝብ በይፋ ይገለፃል ብሏል።

የካፋ ዞን ጤና መምሪያ ባለሀብቶች ለጤና ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ "የመከላከያ ቁሳቁሶች" በመግዛት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ያስተላለፈ ሲሆን ህብረተሰቡ የሀሰተኛና የአሉባልታ ወሬዎችን ሳያዳምጥ ትክክለኛ መረጃዎችን ከጤና ባለሙያና ከመንግሥት አካላት በውሰድ ሳይደናገጥ ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከአ/አ ወደ ደቡብ ክልል የገባችው የኮቪድ-19 ታማሚ! ምንም እንኳን በክልሉ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 174 የላብራቶሪ ምርመራ አዲስ በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ ሰው ባይኖርም በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 12 ደርሰዋል። የክልሉ ጤና ቢሮ ባወጣው መግለጫ አንዲት የ28 ዓመት ሴት አዲስ አበባ በተደረገ ምርመራ ፖዘቲቭ ሆና ወደ ክልሉ (ጉራጌ ዞን፣ ቸሃ ወረዳ) ከገባች በኃላ…
#DrAbdulsemedWorku

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብዱልሰመድ ወርቁ ከሁለት ቀን በፊት የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ባወጣው መግለጫ አንዲት የኮሮና ቫይረስ ታማሚ በሆስፒታሉ የህክምና ማዕከል እንድትቆይ ተደርጋለች ብሎ ያወጣው መረጃ ትክክል አይደለም ብለውናል።

ይህች የ28 ዓመት ወጣት በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ እናትየ ቀበሌ ነዋሪ ስትሆን አዲስ አበባ ለቅሶ ደርሳ በመመለስ ላይ ሳለች በኮሮና ቫይረስ መያዟ በመረጋገጡ ወደ አገና ህክምና ማዕከል እንድትገባ ተደርጋለች።

ከእሷ ጋር የቀጥታ ግንኙነት የነበራቸው አስራ ሶስት (13) ግለሰቦች ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርገዋል። በተመሳሳይ ቸሃ ወረዳ ላይ አዲስ አበባ ለቅሶ ደርሰው የተመልሱና ከነኚህ ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ 34 ግለሰቦች ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርገዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አማራ ክልል! ዛሬ በ26/9/2012 ዓ/ም በአማራ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ስድስት (6) ሰዎች ሁሉም ወንድ ሲሆኑ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ናቸው፤ የእድሜ ክልላቸው ከ23 እስከ 62 ዓመት ውስጥ ይገኛል። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው። አጠቃላይ በአማራ ክልል ያለው የቫይረሱ ስርጭት ፦ • ምዕ/ጎንደር - 68 ሰዎች • ማ/ጎንደር…
ትኩረት ለምዕራብ ጎንደር ዞን!

በምዕራብ ጎንደር ዞን ላለው ሁኔታ ልዩ ትኩረት መስጠት ካልተቻለ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል።

በትላትናው ዕለት በአማራ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ስድስት (6) ሰዎች ከምዕራብ ጎንደር ዞን እንደሆኑ ይታወሳል።

እኚህ የሀገራችን ዜጎች ሱዳን ውስጥ የነበሩ በቀን ሰራተኝነት ሲሰሩ የቆዩና በመተማ ዮሃንስ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ሲሉ በመተማ ዮሃንስ ኬላ በተደረገ ምርመራ የተያዙ ናቸው። ሁሉም ከህብረተሰቡ ሳይቀላቀሉ ወደ ኮቲትና ገንዳ ውሃ ለይቶ ማቆያ የገቡ ናቸው።

ሱዳን ውስጥ ያለው የቫይረሱ ስርጭት እጅግ እየጨመረ ነው። በምዕራብ ጎንደር ዞን ያለው ሁኔታም አሳሳቢ ሆኗል። በአካባቢው ጠንካራ የክትትል ስራ ሊሰራ ካልተቻለ በሀገር ደረጃ የሚከፈለው ዋጋ ከባድ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 5,499 ደረሱ!

የሱዳን ጤና ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው ሪፖርት (የማክሰኞ) በሀገሪቱ ተጨማሪ 189 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው አሳውቋል።

በተጨማሪ የሰባት (7) ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ ሰማንያ ስድስት (86) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 5,499 የደረሰ ሲሆን ከነዚ መካከል 314 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 1,711 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 150 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 150 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,141 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃምሳ (150) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,636 ደርሷል፡፡

ቫይረሱ የተገኘባቸው 94 ወንድ እና 56 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ3 እስከ 72 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 147 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ሶስቱ (3) የውጭ ዜጎች ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 123 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 1 ሰው ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 3 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 13 ሰዎች ከአማራ ክልል እና 6 ሰዎች ከሶማሌ ክልል ናቸው።

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው አራት (4) ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 250 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 18 ደረሰ!

የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ህክምና ሲደረግለት የነበረ ፣ ከዚህ ቀደም ተጓዳኝ ህመም ያለበትና በፅኑ ህክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላትናው ዕለት ህይወቱ አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ስምንት (18) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ዕለታዊ መግለጫ (ግንቦት 27/2012 ዓ/ም በCARD እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተዘጋጀ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 150 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 5,141 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሃምሳ (150) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1,636 ደርሷል፡፡ ቫይረሱ የተገኘባቸው 94 ወንድ እና 56 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ3 እስከ 72 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 147…
#Oromiyaa

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 417 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 92 ደርሰዋል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ40 ዓመት ኢትዮጵያዊት የሰበታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

ታማሚ 2 - የ18 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም ፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ እስካሁን 8,757 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል ፤ ዘጠና ሁለት (92) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ሃያ (20) ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ የሁለት (2) ሰዎች ህይወት በኮቪድ-19 ምክንያት አልፏል።

Via @tikvahethAFAANOROMOO (Biiroo Fayyaa Oromiyaa)

@tikvhhethiopiaBot @tikvahethiopia
#SNNPR

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግሥት 170 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሶስት (3) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 16 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ38 ዓመት ወንድ ከሀዋሳ ፤ የረጅም ርቀት አሽከርካሪ።

ታማሚ 2 - የ66 ዓመት ወንድ ከሀዋሳ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት #የሌላቸው

ታማሚ 3 - የ28 ዓመት ወንድ ከሀዋሳ ፤ የረጅም ርቀት አሽከርካሪ።

ሶስቱም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ግለሰቦች ሀዋሳ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,205 ደርሰዋል! 

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ግንቦት 27/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 1,205 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 123 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 8 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 12 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው የተቀሩት 103 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ ሃያ ሶስት (123) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦

• አዲስ ከተማ - 50 ሰዎች
• ልደታ - 4 ሰዎች
• ጉለሌ - 16 ሰዎች
• ቦሌ - 21 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 6 ሰዎች
• አራዳ - 3 ሰዎች
• ቂርቆስ - 10 ሰዎች
• የካ - 3 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 2 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 0
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 8 ሰዎች

አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,205 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦

• አዲስ ከተማ - 355 ሰዎች
• ልደታ - 180 ሰዎች
• ጉለሌ - 157 ሰዎች
• ቦሌ - 120 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 116 ሰዎች
• አራዳ - 51 ሰዎች
• ቂርቆስ - 51 ሰዎች
• የካ - 49 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 43 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 29
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 54 ሰዎች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጣልያን ከዛ ሁሉ መከራ እየወጣች ነው...

በጣልያን የአገር ውስጥ በረረራዎችና ጉዞዎች ተፈቅደዋል ፤ አገሪቱ ዓለም አቀፍ ድንበሮቿንም እየከፈተች ትገኛለች።

አገሪቱ እቀባዎችን በማቃለሉ ሂደት የመጨረሻውን ምዕራፍ በገባደደችበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ተስፋ የተሞላው ንግግር ማሰማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

"አሁን ፈገግ ልንል፣ ልንደሰት ይገባናል፤ ከዚያ ሁሉ መከራ እየወጣን ስለሆነ…" ቀጥለውም "አሁን አገራችንን በኢኮኖሚ የመጠገን ሥራን እናፋፍማለን" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ይህ ወረርሽኝ (ኮቪድ-19) በአገራችን ሥር ነቀል መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እንድንነሳ እድል ሰጥቶናል፤ አገራችንን በድጋሚ ነድፈን #ልንገነባት ይገባል" ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠ/ሚ ጁሴፔ በዚህ ተስፋን በሰነቀው ንግግራቸው ማብቂያ ሕዝባቸው በፍጹም #እንዳይዘናጋ መክረዋል። በተለይም ማኅበራዊ ርቀትን መጠበቅና ጭምብል ማጥለቅ መዘንጋት የለበትም ብለዋል። እነዚህን ቸል ማለት ዋጋ ያስከፍላል ሲሉ አስምረውበታል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SNNPR ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግሥት 170 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሶስት (3) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 16 ደርሷል። የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦ ታማሚ 1 - የ38 ዓመት ወንድ ከሀዋሳ ፤ የረጅም ርቀት አሽከርካሪ። ታማሚ 2 - የ66 ዓመት ወንድ ከሀዋሳ ፤ የውጭ ሀገር…
#HAWASSA

በሀዋሳ ከተማ ከተለያየ አከባቢ የመጡና ከኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ጋር ንኪኪ ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የተለዩ ሰዎች ቁጥር 418 መድረሱን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ቡሪሶ ቡላሾ ተናግረዋል።

አቶ ቡሪሶ ቡላሾ እንደገለፁት በዛሬው ዕለት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሁለቱ (2) ግለሰቦች ሀገር አቋራጭ የተሽከርካሪ ሹፌሮች መሆናቸውን ገልፀዋል።

ሶስተኛው ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ 'ከክብረመንግስት' ለሌላ ህክምና የመጣ እና በኮሮና ተጠርጥሮ በለይቶ ማቆያ የነበረ ምርመራ ተደርጎለት ፖዘቲቭ መሆኑ እንደታወቀ አቶ ቡሪሶ ተናግረዋል።

አቶ ቡሪሶ ህብረተሰቡ የሚያደርገውን ጥንቃቄ እንዲጨምር አሳስበው ማንኛውንም ውጤት ከተማ አስተዳደሩ እየተከታተለ ለህዝብ ይፋ ማድረጉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- በጅቡቲ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ4,054 ደርሷል። የጅቡቲ ጤና ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ 119 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን አሳውቋል። በሌላ በኩል 49 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

- በኬንያ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 2,340 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት 124 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በተጨማሪ የሟቾች ቁጥር 78 ደርሷል። ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 592 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AMHARA

ዛሬ በ27/9/2012 ዓ/ም በአማራ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ አስራ ሶስት (13) ሰዎች ሁሉም ወንድ ሲሆኑ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ናቸው፤ የእድሜ ክልላቸው ከ20 እስከ 63 ዓመት ውስጥ ይገኛል። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ናቸው።

አጠቃላይ በአማራ ክልል ያለው የቫይረሱ ስርጭት ፦

• ምዕ/ጎንደር - 81 ሰዎች
• ማ/ጎንደር - 1 ሰው
• ጎንደር ከተማ - 3 ሰዎች
• ደሴ ከተማ - 2 ሰዎች
• ባህር ዳር ከተማ - 4 ሰዎች
• አዊ ብሄረሰብ- 3 ሰዎች
• ሰ/ሸዋ - 2 ሰዎች
• ሰ/ወሎ - 3 ሰዎች
• ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን - 1 ሰው
• ደ/ጎንደር - 1 ሰው
• ምስ/ጎጃም (ድንበር ተሻጋሪ) - 1 ሰው

እስካሁን ድረስ በአማራ ክልል 2,495 የላንራቶሪ ምርመራ ተደርጓል ፤ አንድ መቶ ሁለት (102) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሀዋሳው የምርመራ ማዕከል ብልሽት ገጥሞታል ?

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግሥት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ የሀዋሳው ምርመራ ማዕከል ብልሽት ገጥሞታል እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን ለSRTA ተናግረዋል።

የቢሮው ኃላፊ ክልሉ ያለውን የምርመራ አቅም ለማሳደግ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ አሳውቀዋል። በአሁን ሰዓት የሀዋሳው እና የሶዶው የምርመራ ማዕከላት አግልግሎት እየሰጡ መሆኑንም ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአርባ ምንጭ ላብራቶሪ ማለቁንና የምርመራ ማዕከሉ በሳምንቱ መጨረሻ (እሁድ) በይፋ ተመርቆ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ አስረድተዋል።

ክልሉ የምርመራ አቅሙን ይበልጥ ለማሳደግም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምርመራ ማዕከልን ስራ ለማስጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ አቅናው ካውዛ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት...

#መታጠብ - ሁሌም ቢሆን ከንክኪ በኃላ እጅዎን በሳሙና በሚገባ መታጠብ አይዘንጉ።

#መቆየት - አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ለእርሶ ፣ ለቤተሰብዎና ለማህበረሰቡ ጤና ሲሉ 'በቤትዎ ውስጥ መቆየትን' ይምረጡ።

#መራራቅ - ከቤት የሚወጡ ከሆነ በሁሉም ቦታ ሲገኙ አካላዊ ርቀትዎን ይጠብቁ።

#መሸፈን - ከቤትዎ ወጥተው ሲንቀሳቀሱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግዎን እንዳይዘነጉ።

በተጨማሪ ችግሩ በሀገር ላይ የመጣ ነውና አቅም የሌላቸው ወገኖችን #በመርዳት ይህንን ፈተና በጋራ ማለፍ እንችላለን!

እናመሰግናለን ~ ቲክቫህ ኢትዮጵያ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሜክሲኮ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው!

በሜክሲኮ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ12,000 በልጧል።

ረቡዕ ዕለት በሀገሪቱ የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር በአሜሪካ በተመሳሳይ ቀን ከተመዘገበው በልጧል፤ የ1,092 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በሌላ በኩል በብራዚል የሟቾች ቁጥር ከጣልያን በልጧል። በአጠቃላይ በብራዚል በኮሮና ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 34,039 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia