TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት...

#መታጠብ - ሁሌም ቢሆን ከንክኪ በኃላ እጅዎን በሳሙና በሚገባ መታጠብ አይዘንጉ።

#መቆየት - አስገዳጅ ካልሆነ በቀር ለእርሶ ፣ ለቤተሰብዎና ለማህበረሰቡ ጤና ሲሉ 'በቤትዎ ውስጥ መቆየትን' ይምረጡ።

#መራራቅ - ከቤት የሚወጡ ከሆነ በሁሉም ቦታ ሲገኙ አካላዊ ርቀትዎን ይጠብቁ።

#መሸፈን - ከቤትዎ ወጥተው ሲንቀሳቀሱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግዎን እንዳይዘነጉ።

በተጨማሪ ችግሩ በሀገር ላይ የመጣ ነውና አቅም የሌላቸው ወገኖችን #በመርዳት ይህንን ፈተና በጋራ ማለፍ እንችላለን!

እናመሰግናለን ~ ቲክቫህ ኢትዮጵያ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 35,245 ደርሷል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦
• ቦሌ - 5,708
• ኮልፌ ቀራንዮ - 4,061
• ጉለሌ - 3,552
• የካ - 3,545
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 3,456
• አዲስ ከተማ - 3,318
• አራዳ - 2,992
• ቂርቆስ -2,634
• ልደታ - 2,623
• አቃቂ ቃሊቲ - 2,517
• ከለይቶ ማቆያ - 514
• አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 325

#መራራቅ #መቆየት #መታጠብ #መሸፈን😷

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 አጫጭር መረጃዎች ፦

- ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በህንድ የ1,144 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፤ 85,919 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በብራዚል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 818 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ሲያልፍ 32,129 ሰዎች በቫይረሱ መያቸው ተረጋግጧል።

- ሜክሲኮ ውስጥ በ24 ሰዓት 601 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።

- በአሜሪካ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር 207,538 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓታ 942 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አልፏል።

- በአፍሪካ በኮሮና የተያዙ ሰዎች 1,444,619 ደርሰዋል። በቫይረሱ በተያዙ ሰዎች ብዛት ደ/አፍሪካ ፣ ሞሮኮ ፣ ግብፅ፣ #ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።

- በመላው ዓለም በኮሮና መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 32,420,147 ደርሷል ፤ 987,815 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 23,934,098 ሰዎች አገግመዋል።

#መታጠብ #መቆየት #መራራቅ #መሸፈን😷
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia