TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EkaKotebeHospital

"ግዴታዬን እና ሞያዬን አክብሬ ህዝቤንና ሀገሬን በማገልገል ላይ እገኛለሁ። እኔ ልጅ፣ ንብረቴን ሳልል ቅድሚያ ሰጥቼ እንደማገለግላችሁ እናንተም በቤት ቆዩ ፤ ይህን ካደረጉ ለሞያዬ ክብር እንደሰጡልኝ እቆጥረዋለሁ። ይሄን ጊዜ አልፈን ከቤተሰቦቻችን ጋር እንድንቀላቀል ፈጣሪ ይርዳን!"

#DoctorsinAction
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EkaKotebeHospital

የኮሮና ቫይረስን በማከም ስራ ላይ ለተሰማሩ ሃኪሞችና ባለሙያዎች ከከፋ ዞን የአገር ሽማግሌዎች የማርና በግ ስጦታ ተበረከተላቸው።

የከፋ ዞን አስተዳደርና የአገር ሽማግሌዎች በአዲስ አበባ ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገኝተው የኮሮናቫይረስን በማከም ስራ ለተጠመዱ ባለሙያዎች ግምቱ ከ100 ሺህ ብር በላይ የሆነ የማርና በግ ስጦታ ዛሬ አበርክተዋል።

የከፋ ዞን የአገር ሽማግሌዎች ተወካይ አቶ አድማሱ አቱሞ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ሀኪሞችና ባለሙያዎች እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን ሳይሳሱ ለኅብረሰተባቸው እያዋሉ ነው።

''በዚህ አበርክቷቸውም ፈጣሪ ከጎናቸው እንዲሆን እንመኛለን፣ ለሞራል እንዲሆናቸው የበረከት ምሳሌ የሆኑትን የማርና በግ ስጦታ አበርክተናል'' ብለዋል።

ሀኪሞችና ባለሙያዎች ጥረታቸው ለፍሬ በቅቶ ታማሚዎች አገግመው ለቤታቸው እንዲበቁ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia