TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrMercyMwangangi

በኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 435 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,195 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ተጨማሪ ሃያ አራት (24) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በኬንያ አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 435 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት የአንድ (1) ሰው ህይወት አልፏል፤ ይህም አጠቃላይ የሟቾችን ቁጥር ወደ ሃያ ሁለት (22) ከፍ አድርጎታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንደ ሀገር የተከሰተውን የደም እጥረት ለመፍታት እንዲረዳ በኦሮሚያ ክልል የደም ልገሳ ንቅናቄ ተጀመረ!

(የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን)

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ደም በመለገስ ንቅናቄውን አስጀምረዋል።

በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ የለጋሽ መጠን በመቀነሱ በሀገር ደረጃ የደም ክምችት እጥረት መኖሩን የደም ባንክ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ምሳሌ በመሆን ንቅናቄውን በይፋ ማስጀመራቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል፡፡ በሁሉም የክልሉ ዞኖች ልገሳው ተጠናክሮ አንደሚቀጥልም ተናግረዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱማሊያ በአንድ ቀን 70 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ!

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሊያ ተጨማሪ 70 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 671 ደርሷል።

በሌላ በኩል ሶስት (3) ተጨማሪ ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 34 ደርሷል።

በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት የሶስት (3) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ሰላሳ አንድ (31) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- ዋይት ሐውስ፤ የአሜሪካ መንግሥት ጤና አማካሪ የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ፋውቺ ምክር ቤት ቀርበው እንዳይመሰክሩ አግዷል። ዶክተር ፋውቺ፤ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን የመከቱበት መንገድ ትክክል ነው ወይስ አይደለም በሚለው ላይ ነበር እንዲመሰክሩ የታሰበው - #BBC

- በትናንትናው ዕለት የሩሲያ የግንባታ ሚኒስትር ብላድሚር ያኩሼቭ በኮሮና ተይዘው በሆስፒታል ሕክምና መከታተል መጀመራቸውን አረጋግጠዋል። ምክትላቸው ዲሚትሪ ፎልኮቭም በኮሮና መያዛቸውን መስሪያ ቤታቸው አረጋግጧል - #DW

- በደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 6 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ስድስቱም (6) ከውጭ የገቡ ናቸው።

- በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት 802 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ዛሬ ሪፖርት የተደረገው ኬዝ ከየካቲት 30 በኃላ የተመዘገበ ዝቅተኛው ቁጥር ነው።

- በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት የ276 ሰዎች ሞት ሲመዘገበ 2,588 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በቻይና ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙን ሪፖርት አድርጋለች። ዛሬ በሀገሪቱ ሞት ሳይመዘገብ አምስተኛ ቀኑን ይዟል።

- FDA ለኢቦላ በሽታ የሚውለውን ሬምዴሲቬር የተባለውን መድኃኒት ለአስቸኳይ ጊዜ የኮቪድ-19 ህክምና እንዲውል ፈቅዷል። ይህ ጸረ ቫይረስ የሆነው መድኃኒት በኮቪድ-19 በጽኑ ታመው ሆስፒታል የሚገኙ ሰዎችን ለማከም ይውላል። የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር ኮሚሽነር የሆኑት ስቴፈን ሃን 'ይህ የኮቪድ-19ን ለማከም ዕውቅና የተሰጠው የመጀመሪያው መድኃኒት ነው' ብለዋል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProfessorHirutWoldemariam

በአሁኑ ወቅት አገሪቱ 27 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የለይቶ ማቆያ ማዕከል ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ሲሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም ገልጸዋል፡፡ በእነዚህም ከ9ሺህ በላይ ዜጎችን በማቆያው ውስጥ መሆናቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

በቀጣይ ሁኔታዎች እየታዩ ዩኒቨርሲቲዎቹ 90 ሺህ ሰዎችን በለይቶ ማቆያነት እንዲይዙ ለማስቻል የማዘጋጀት ሥራ መሰራቱንና ከማቆያነት ባሻገርም ጊዜያዊ የመመርመሪያ ጣቢያ ሆነው እንዲያገለግሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል - #ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrYakobSeman

በጤና ሚኒስቴር የጤና ነክ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር ያዕቆብ ሰማን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ከተናገሩት ፦

- በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዋች ቁጥር እና የከፋ ጉዳት ሊደርስ የሚችለው ሰኔ መጨረሻና ሐምሌ መጀመርያ ቀናት ነው።

- በሀገር አቀፍ ደረጃ አሁን የምናደርገውን ጥንቃቄ ባናደርግ ከ27 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ኮሮና ያጠቃብን ነበር፤ በደንብ ከተጠነቀቅን ደግሞ የዚህን ቁጥር 60 በመቶ ወይንም 16 ሚሊዮን መቀነስ ይቻላል።

- ወረርሽኙ (ኮቪድ-19) ሊያደርስ የሚችለው የከፋ ውጤት ገና አላለፍነውም፤ ኮሮና ወረርሽኝ አንድ ሀገር ገብቶ የሚብስበት ጊዜ ገና የሚመጣ ነውና መዘናጋት አደገኛ ነው።

ተጨማሪ : https://telegra.ph/ኢትዮኤፍኤም-05-02

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrBowaleAbimbola

በናይጄሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መቆጣጠር ዋነኛ ሥራው የሆነው ተቋም ኃላፊ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው በምርመራ መረጋገጡን ቢቢሲ ዘግቧል።

ኃላፊው ዶክተር ቦዋሌ አቢምቦላ የካቲት ወር መጨረሻ ላይ በንግድ ከተማዋ ሌጎስ ውስጥ በሚገኘው ያባ የተላላፊ በሽታዎች ሆስፒታል ውስጥ በአገሪቱ የመጀመሪያዎቹ የቫይረሱ ታማሚዎች ተቀብለው አገልግሎት ከሰጡት ሐኪሞች መካከል አንዱ መሆናቸውን ቢቢሲ አስታውሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ሳቢያ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ጠባቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ መናገራቸው DW ዘግቧል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት በዚህ ሳቢያ በአገሪቱ ዕርዳታ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በአጠቃላይ ወደ 30 ሚሊዮን ያሻቅባል።

መንግስት የኮሮና ወረሽኝን ለመከላከል ያቋቋመው የምኒስትሮች ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት ባደረገው እና ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በመሩት ውይይት ለዚህ ብቻ ኢትዮጵያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል።

የኮሮና ወረርሽኝን ለመቋቋም ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት፣ ከአውሮፓ ኅብረት፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታኒያ እና ቻይና 2.1 ቢሊዮን ዶላር ዕገዛ መጠየቋን አቶ አሕመድ ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር በቅርቡ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በትናንትናው ዕለት የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ጫና ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የ411 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ አጽድቋል። የዓለም ባንክ በበኩሉ 750 ሚሊዮን ዶላር የበጀት ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚችል የፋይናንስ ሚኒስትሩ አስረድተዋል - #DW

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በዩናይትድ ኪንግደም የሟቾች ቁጥር 28,131 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ621 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል በአንድ ቀን 4,806 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- ባለፉት 24 ሰዓት በኳታር 776 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 14,872 ደርሰዋል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 474 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። በሌላ በኩል 1,900 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በቱርክ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 124,375 ደርሰዋል፤ በአንድ ቀን 1,983 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የሟቾች ቁጥር በ78 ጨምሮ በአጠቃላይ 3,336 ሆኖ ተመዝግቧል።

- ግብፅ በዛሬው ዕለት 298 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 6,193 ደርሷል።

- በጋና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,169 ደርሰዋል፤ ባለፉት 24 ሰዓት 95 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። #GHS 88% በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ግልፅ የሆነ የጉዞ ታሪክ የላቸውም ብሏል።

- በAfricaCDC መረጃ መሰረት በአፍሪካ 1,701 ሰዎች ሞተዋል፤ 41,330 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ 13,621 አገግመዋል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር ከ243,024 ደርሷል፤ 1,102,551 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 3,456,207 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

#COVID19 ወረርሽኝ ዝግጁነት እና ምላሽ ለመስጠት የህክምና እና ለይቶ ማቆያ ማዕከላትን በመዘጋጀት ረገድ እጅግ በጣም ጥሩ ስራ የተሰራ መሆኑን በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሺያላይዝድ ሆስፒታል፣ በቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሜድካል ኮሌጅ እና በሚሊኒየም አዳራሽ ባደረግነው ጉብኝት ለማየት ችለናል።

የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል የሚሰጠውን መድሀኒቱን ለተላመድ የቲቢ በሽታ ህክምና አገልግሎት ጨምሮ ሁለቱም ሆስፒታሎች በመደበኛነት ይሰጡአቸው የነበሩትን አጠቃላይ የጤና አጠባበቅ አገልግሎቶች መስጠታቸውን ቀጥለዋል። እንዲሁም በጊዜያዊ ለይቶ ማቆያነት እያገለገለ የሚገኘውን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲንም ጎብኝተናል።

(የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኢትዮጵያና የአጎራባች ሀገራት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወቅታዊ መረጃ ፦

- ጅቡቲ በቫይረሱ የተያዙ 1,112፣ ሞት 2፣ ያገገሙ 686

- ኬንያ በቫይረሱ የተያዙ 435፣ ሞት 22፣ ያገገሙ 152

- ሶማሊያ በቫይረሱ የተያዙ 671፣ ሞት 31፣ ያገገሙ 34

- ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 533፣ ሞት 36፣ ያገገሙ 46

- ኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ 133፣ ሞት 3፣ ያገገሙ 69

- ደቡብ ሱዳን በቫይረሱ የተያዙ 45፣ ሞት 0፣ ያገገሙ 0

- ኤርትራ በቫይረሱ የተያዙ 39 ፣ ሞት 0 ፣ ያገገሙ 26

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,560 ላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 135 ደርሷል።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ49 ዓመት ኢትዮጵያዊ የባቱ /ዝዋይ/ ነዋሪ አዲስ አበባ ህክምና በመከታተል ላይ ያለ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የለውም (በጤና ተቋም ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ)

ታማሚ 2 - የ45 ዓመት ኢትዮጵያዊት የስልጢ ወረዳ፣ ስልጤ ዞን ነዋሪ (ደቡብ ክልል) ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የላትም (በቤት ለቤት ቅኝት እና አሰሳ የተለየች)

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ስድስት (6) ሰዎች ከድሬዳዋ ከተማ ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሰባ አምስት (75) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል ስልጤ ዞን በተደረገ ቤት ለቤት አሰሳ አንዲት ሴት የኮረና ቫይረስ የተገኘባት መሆኑ ተረጋገጠ!

(በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ)

በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ አንዲት የ45 አመት ዕድሜ ያላት ጾታዋ ሴት የሆነች የኮረና ቫይረስ ምልክቶች በቤት ለቤት ቅኝት ታይቶባት ናሙና ተወስዶ በደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም ላብራቶሪ በተደረገ የናሙና ምርመራ መሠረት በኮረና ቫይረስ መያዟ የተረጋገጠ በመሆኑ በዛሬው ዕለት በጤና ሚኒስተር የ24 ሰዓታት ሪፖርት እንደተገለጸው በአሁኑ ሰዓት በወራቤ ለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል እንድትገባ የተደረገ ሲሆን በመልካም ጤንነት ላይ ትገኛለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethmagazine

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መግባቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ ድርጅቶች ባለሃብቶች ፣ የመንግስት ተቋማት ፣ የውጭ ሀገር ኤምባሲዎች የተለያዩ ድጋፎች እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል በዚህ ሳምንትም ባለሃብቶች፣ የመንግስት ተቋማት፣ ድርጅቶች የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸውን አሳውቀውናል።

ለሌሎች መነሳሳት ይሆን ዘንድ ሁሉንም መልዕክቶች ከ8:00 ጀምሮ በ ( @TIKVAHETHMAGAZINE ) ቻናላችን ላይ እናስቀምጣቸዋለን።

ትክክለኛው የTIKVAH-MAGAZINE ገፅ ከ 185,000 በላይ አባላት የሚገኙበት ብቻ ነው፤ ይህ ሊንክ ወደ ገፁ ይወስዳችኃል https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrLiaTadesse በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,560 ላቦራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 135 ደርሷል። የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦ ታማሚ 1 - የ49 ዓመት ኢትዮጵያዊ የባቱ /ዝዋይ/ ነዋሪ አዲስ አበባ ህክምና በመከታተል ላይ ያለ፤ የውጭ ሀገር…
የዛሬው ሪፖርት ማንቂያ ደውል ይሁነን!

በዛሬው ዕለት የሰማናቸው 2 የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ኬዞች ሁላችንንም ሊያነቁ ፣ ካለንበትም የመዘናጋት እና የቸልተኝነት እንቅስቃሴ ሊያወጡን ይገባል።

ሁለቱም በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ግለሰቦች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ሁላችንንም በእጅጉ ሊያሳስበን ይገባል ፤ አካሄዳችንንም ቆም ብለን እንድንገመግም ያስገድደናል።

የታማሚዎች ማገገም እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝና ተስፋ የሚሰጥ ቢሆንም ሰዎች እያገገሙ ነው ማለት ቫይረሱ አይሰራጭም ወይም ቫይረሱ እየጠፋነው ማለት አይደለምና ትልቅ ዋጋ ከመክፈላችን በፊት መዘንጋቱ፣ ትዕግስት ማጣቱ፣ ቸልተኝነቱ ሊያበቃ ይገባል ለማለት እንወዳለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል ስልጤ ዞን በተደረገ ቤት ለቤት አሰሳ አንዲት ሴት የኮረና ቫይረስ የተገኘባት መሆኑ ተረጋገጠ! (በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ) በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ አንዲት የ45 አመት ዕድሜ ያላት ጾታዋ ሴት የሆነች የኮረና ቫይረስ ምልክቶች በቤት ለቤት ቅኝት ታይቶባት ናሙና ተወስዶ በደቡብ ክልል ህብረተሰብ ጤና ተቋም ላብራቶሪ በተደረገ የናሙና ምርመራ መሠረት በኮረና ቫይረስ መያዟ የተረጋገጠ…
ተጨማሪ መረጃ ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አቅናው ካውዛ ፦

(በደሬቴድ)

- ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው የ45 ዓመት ሴት በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ጡጦ ዞጋሬ ቀበሌ አካባቢ ነዋሪ ናቸው። ግለሰቧ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ቤት ለቤት በተደረገ አሰሳ ነው።

- ግለሰቧ በተለምዶ የጉልት ስራ ተብሎ በሚጠራው ግብይት የሚተዳደሩ ሲሆን የጉዞ ታሪክ የላቸውም።

- ግለሰቧ በአሁኑ ሰዓት በወራቤ ለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል እንድትገባ ተደርጓል።

- ሰባት የቤተሰቡ አባላትና ጎረቤቶቻቸው ጭምሮ ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ ተደርጓል።

- በቫይረሱ የተያዙት ሴት ባለቤት በተደረገለት ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ ተረጋግጧል።

- በደቡብ ክልል በድምሩ ሁለት (2) በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አሉ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#SPAIN

(በቢቢሲ እና ሲጂቲኤን)

በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ164 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል ፤ ይህ የሟቾች ቁጥር ከመጋቢት 9/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው ቁጥር ነው።

በአሁን ሰዓት በአጠቃላይ 217,446 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 25,264 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

በሌላ በኩል በስፔን ከነገ ጀምሮ በሕዝብ ትራንስፖርት ውስጥ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ ግድ መሆኑን አስታውቃለች። አገሪቷ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የጣለቻቸውን ጥብቅ ገደቦች ቀስ በቀስ እያላላች ነው፡፡

በስፔን የሚገኙ አዋቂዎች ከሰባት ሳምንታት በኋላ እሁድ ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከቤት በመውጣት አካላዊ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ ከ14 ዓመት በታች ላሉ ህጻናት በቤት ውስጥ የመቀመጥ ገደቡ የላላው ከሳምንት በፊት ነበር፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በደቡብ ክልል ሀላባ ዞን በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዙ ስለተረጋገጠው የ25 ዓመት ወጣት ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ አጥናው ካውዛ ፦ - በደቡብ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው ወጣት በዛሬው ዕለት በጤና ሚኒስቴር መገለጫ የተገለፀው ሁለተኛው ታማሚ ነው። - ወደ ሱማሌ ክልል ናሙና ተልኮ ምርመራ ተደርጎ የናሙናው ውጤት ሳይጠናቀቅ ሰዎቹ ከሞያሌ ወደ ደቡብ…
#UPDATE

(ሀላባ ዞን አስተዳደር)

በሃላባ ቁሊቶ ከተማ በኮሮና ቫይረስ ከተያዘው ግለሰብ ጋር የቅርብ ንኪኪ የነበራቸው ግለሰቦችን በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ተብሏል፡፡

በዛሬው ዕለት (ሚያዚያ 25/2012 ዓ/ም) በኮቪድ-19 ከተያዘው ግለሰብ ጋር ንኪኪ እንደነበራቸው የተጠረጠሩ እስካሁን 40 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲሆኑ መደረጉም ታውቋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia