TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በቃፍታ ሁመራ ወረዳ የአንበጣ መንጋ ተከሰተ!

በትግራይ ምዕራባዊ ዞን በቃፍታ ሁመራ ወረዳ ልዩ ስሙ ሕለጌን በተባለው ቀበሌ የአንበጣ መንጋ ከትናንት ጀምሮ መከሰቱን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ኤክሳይዝታክስ

ከላይ ባለው ምስል የምትመለከቱት የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፋባቸው ዕቃዎች ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ የተደረጉ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
excise_amharic_new_8.pdf
21.1 MB
#ኤክሳይዝታክስ

ይህ ከኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው የPDF ፋይል ስለ ኤክሳይዝ ታክስ የተሟላ መረጃ የሚሰጥ ነው። ውድ ቤተሰቦቻችን ፋይሉን ከፍታችሁ ብታነቡት ስለኤክሳይዝ ታክስ ለሚፈጠርባችሁ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣችኃል።

[21.1 MB WiFi ተጠቀሙ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በአወዳይ ምን ተፈጠረ?

ዛሬ በአወዳይ ከተማ በመንግሥት እና በተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች መካከል ግጭት መከሰቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ዛሬ ጠዋት የጠቅላይ ሚንስርት ዶክተር ዐብይ መንግሥት እና ፓርቲን ለመደገፍ የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ የወጡ ሲሆን፤ በተቃራኒው ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩን መንግሥት በመቃወም መፈክር እየሰሙ የወጡ ሰዎች እንደነበሩ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

አንድ ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ የፖሊስ ባልደረባ ለቢቢሲ እንደተናገረው "ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን ለመደገፍ ሰዎች ሰልፍ ወጡ። ከዛ ለምን ለድጋፍ ወጣችሁ የሚሉ ሌሎች ሰዎችም መውጣት ጀመሩ።

ተከትሎም ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚያወግዝ መፈክር በማሰማት ድንጋይ መወርወር ጀመሩ" በማለት የግጭቱን አጀማመር ያስረዳል። በደንጋይ ተመተው እና በዱላ ተደብድበው ጉዳት የደረሰባቸው ብዙ ሰዎች መኖራቸውን የፖሊስ አባሉ ተናግረዋል።

More https://telegra.ph/BBC-02-20

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቢራ ምርቶች ላይ የተደርገው የዋጋ ጭማሪ!

- የቢራ ሳጥን ዋጋ እስከ 140 ብር ሲጨምር በርሜል ድራፍት ከ300 ብር በላይ ጨምሯል።

- በአዲስ አበባ ገበያ አንድ ሳጥን ቢራ (24 ጠርሙስ) ከፋብሪካ እንደወጣ የሚያከፋፍልበትን ዋጋ ወደ 430 ብር ከፍ አድርጓል፡፡ ሐበሻ ቢራ በበኩሉ የፋብሪካ ዋጋውን ወደ 415 ብር ከፍ አድርጓል፡፡ ሐይኒከን ቢራ በዋልያ ምርቱ ላይ ከቢጂአይ እኩል የአንድ ሳጥን ቢራ መሸጫ ዋጋውን ወደ 430 ብር አሳድጓል፡፡

- የአንድ በርሜል ድራፍት የማከፋፈያ ዋጋ ላይ የ345 ብር ጭማሪ ተደርጓል፡፡ እስካሁን ሲከፋፈልበት በነበረው 815 ብር ላይ የ345 ብር ተጨምሮ ታክሎበት፣ በ1,165 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ዋሊያ ድራፍት በበርሜል 340 ብር ጨምሮ 1,600 ብር እንደሚያከፋፍል መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

- በ15 ብር ይሸጡ የነበሩ፣ 330 ሚሊ ሌትር መጠን ያላቸው ቢራዎች ከየካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ 20 ብር እና ከዚያ በላይ እየተሸጡ ነው፡፡ ከ15 እስከ 20 ብር ይሸጡ የነበሩ ግለሰብ ነጋዴዎችና ግሮሰሪዎችም ከ25 እስከ 30 ብር መሸጥ እንደጀመሩ እየታየ ነው፡፡

More https://telegra.ph/ሪፓርተር-02-20

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የምግብና መዋቢያ ምርቶች መያዛቸው ተገልጻል!

ግምታዊ ዋጋቸው ከ6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን መደሃኒትና የመዋቢያ ምርቶችን በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዙ በቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉን የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ቅቤ እና ማርን ከባእድ ነገሮች ጋር ቀላቅለው ሲሸጡ የተገኙ 13 ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱንና 72 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ጉዳያቸው በህግ እየታየ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሜዲን ወንዶሰን አልሞተም፤ ወሬው ሀሰት ነው!

"ከኮሜዲያን ወንዶሰን መሸሻ (ደኩሌ) ጋር በተያያዘ የሚነዛው ወሬ ውሸት መሆኑን ማረጋገጥ ችያለሁ። ኮሜድያን ደኩሌ በህይወት አለ።" - ጋዜጠኛ ተቦርነ በየነ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ እውቅና [የሶስት ወር] የሰጣቸው 11 ፓርቲዎች፦

- ኤጀቲማ ፌደራሊስ ፓርቲ /ኤፌፓ/
- ሱማሌ ፌደራሊስት ፓርቲ
- የካፋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ህብረት/ካህዴህ/
- የፊንፊኔ ህዝቦች ለፍትህ እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ /ፊህዴ/
- የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
- ኅብረት ለዲሞክራሲና ለነፃነት ፓርቲ/ኅዴነፓ/
- የሲዳማ አንድነት ፓርቲ /ሲአፓ/
- ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ፓርቲ
- የሶማሌ ብሄራዊ ፓርቲ /ሶብፓ/
- የኢትዮጵያ አንድነት አርበኞች ግንባር /ኢአአግ/
- የወለኔ አርሶአደር ህብረት

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የአቶ አሸብር ባልቻ ሹመት...

ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ በዓለምአቀፍ ቢዝነስ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ያገኙት አቶ አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ፡፡

አቶ አሸብር ከስዊዲን ሀገር ኬ. ቲ. ኤች ዩኒቨርሲቲ በዘላቂ ኢነርጂ ምህንድስና ዘርፍ ተጨማሪ ኮርሶችን ወስደዋል፡፡

አቶ አሸብር በበደሌ ቢራ ፋብሪካ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ በተከዜ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት፣ የገባ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ በመሆን ካገለገሉ በኋላ ከጥቅምት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ይህን ኃላፊነት እስከተቀበሉበት ቀን ድረስ የኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ስራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ አሸብር ባልቻ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን በተለያዩ የስራ መደቦች በባለሙያነትና በኃላፊነት ለ16 ዓመታት አገልግለው ከየካቲት 09 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙን በዋና ስራ አስፈፃሚነት እንዲመሩ በተቋሙ የሥራ አመራር ቦርድ መሾማቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬም የቀጠሉት የድጋፍ ሰልፎች...

ከሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች ሲካሄዱ የነበሩ የድጋፍ ሰልፎች ዛሬም ቀጥለዋል። በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አመራርን የሚደግፍ ሰልፍ በሀዋሳ፣ በቢሾፍቱ፣ እንዲሁም በፊቼ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልፆልናል።

የሰልፉ ተሳታፊ የሆኑ የተወሰኑ ሰዎችን ያነጋገርን ሲሆን "ሀገር በስድብ እና በጥላቻ አይገነባም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሰሩትን ስራ ከማንቋሸሽ እና የፌስቡክ ዘመቻ ከማካሄድ ለህዝቡ አማራጫ ሀሳብ ማቅረብ ይቻላል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ እስካሁን ላደረጉት አስተዋፆ ምስጋና እንጂ ስድብ አይገባቸውም" ብለዋል።

PHOTO : SOCIAL MEDIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HAWASSA

ዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ በሀዋሳ እየተደረገ ያለው ሰልፍ ላይ ከሲዳማ አስተዳደርና ከ36 ወረዳዎች የተውጣጡ የሲዳማ ብሄር ተወካዮች ፣ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞችን ያሳተፈ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስፈርት የማያሟሉት የግል ትምህርት ቤቶች...

- 1615 የግል ትምህርት ቤቶች ለመኖሪያ ቤት ታስበው የተሰሩ ናቸው

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች በተማሪ ብዛት 52 በመቶ ድርሻ ቢኖራቸውም አብዛኞቹ የትምህርት ሚኒስቴርን መስፈርት እንደማያሟሉ ተገለጸ።

አንድ ሺህ 615 የግል ትምህርት ቤቶች ለመኖሪያ ቤት ታስበው በተሰሩ ቤቶች ተማሪዎችን በተጨናነቀ ሁኔታ እያስተማሩ እንደሚገኙ መሆኑም ታውቋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የግል ትምህርት ቤቶች የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ...

የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ የግል ትምህርት ቤቶች የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ በሕብረተሰቡ ላይ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን በጥናት ማረጋገጡን ገለጸ።

የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር በበኩሉ ጥናቱ ሁሉን ያላሳተፈና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው ብሏል።

ባለስልጣኑ የገበያ ነጻነትን ያለአግባብ በመጠቀም ጸረ ውድድር ስምምነትና የተከለከሉ የንግድ አሰራሮች በተስተዋለባቸው የትምህርት ተቋምት ላይ ጥናት አድርጓል።

በተመረጡ 100 የግል ትምህርት ቤቶች በተካሄደው ጥናት ላይ የተገኘውን ውጤት አስመልክቶ ባለስልጣኑ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ውይይት አድርጓል።

በጥናቱ መሰረትም በትምህርት ቤቶቹ የትምህርት ተቋማቱ መጻህፍትን አሳትመው መሸጥና የደንብ ልብስ ከተወሰኑ ተቋማት ብቻ እንዲገዙ የማስገደድ ሁኔታ ተስተውሏል።

በተጨማሪም ”ፈተና የሚመጣው ከማጠናከሪያ ትምህርት ነው” በሚል አስገዳጅ በሆነ መልኩ ተማሪዎች ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ ማድረግ፣ ለተማሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ተወዳዳሪነት በሌለው መልኩ በከፍተኛ ዋጋ የማቅረብ ሁኔታ እንደሚስተዋል በጥናቱ ተመልክቷል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት...

መንግስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ የሚገድቡ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሳሰበ።

ምክር ቤቱ በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ላይ እንደተገለጸው መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ የፓርቲዎችን ነጻ እንቅስቃሴ የሚገድቡ የህግ የበላይነት ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ እንዲሰጣቸው አሳስቧል።

ኢዜማ ፣ ኦፌኮ ፣ አረና፣ ኦነግ እና ለሎች አገራዊና ክልላዊ ፓርቲዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸውን በፈለጉት ቦታ ለማካሄድ ሲሞክሩ በተለያዩ ቡድኖች እና ተቋማት የፖለቲካ እንቅስቃሴያችንን እንዳናካሂድ እክል ፈጥረውብናል ማለታቸው ይታወሳል።

የጀመርነው የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚሳካው የህግ የበላይነት ሲረጋገጥ ብቻ ነው ያለው የምክር ቤቱ መግለጫ ህብረተሰቡ እና ማህበራዊ ተቋማት ለህግ የበላይነት ቅድሚያ እንዲሰጡም ጠይቋል።

ምርጫ ቦርድም የጀመረውን ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ጤናማ ግንኙነት እንዲኖረው የሚያስችሉ ስራዎቹን አጠናክሮ እንዲቀጥል ምክር ቤቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ጠይቋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 2,120 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 75,730 በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,120 የደረሰ ሲሆን 75,730 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 16,155 መድረሳቸውን ተመልክተናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- የሟቾች ቁጥር 2,247 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 76,790

በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እንዲሁም በቫይረሱ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከባለፉት ቀናት ጋር ሲተያያ እየቀነሰ እንደሆነ እየተገለፀ ይገኛል።

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,247 የደረሰ ሲሆን 76,790 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 18,590 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ በመከላከያ ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ!

በኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

የልኡካን ቡድኑ በቆይታው ከሳዑዲ ዓረቢያ የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ፈያድ ቢን ሃመድ አል-ሩዋሊ እና የሳዑዲ ዓረቢያ የመከላከያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይቶችን አካሂዷል፡፡

በውይይቶቹ በኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል በመከላከያ ዘርፍ ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከር እና በሌሎች ቀጠናዊ የጋራ ስጋቶች ዙሪያ በትብብር መሥራት እና የልምድ ልውውጥ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክርና የሐሳብ ልውውጦች ተደርገዋል፡፡

#FDREDefenseForce
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia