TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 16 ሰዎች ተያዙ...

በአሶሳ ከተማ በምሽት የዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 16 ባጃጆች ከእነ አሽከርካሪዎቻቸው በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ ፅሀፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በፅሀፈት ቤቱ የወንጀል መከላከል ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ኢንስፔክተር ደረጃ ኢታና እንደገለፁት በከተማው የሚፈፀም የዘረፋና ስርቆት ወንጀል እየተበራከተ መጥቷል፡፡ ችግሩን ለማስቆም ፖሊስና ህብረተሰቡን ያቀፈ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ከየካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

ግብረ ኃይሉ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ መሠረት በማድረግ እስከ አሁን ድረስ 16 ባጀጆችን ከእነ አሽከርካሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስረድተዋል፡፡

አሽከርካሪዎቹ በእኩለ ለሊት እየተዘዋወሩ ዘረፋ ለሚፈፅሙ ግለሰቦች የትራንስፖርት አገልግሎቱን በመስጠት ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው ብለዋል። ካናቢስ የተባለ አደንዛዝ እፅ በማዘዋወር የተጠረጠሩ ሌሎች ስምንት ግለሰቦችንም ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ሥራ እንዲውሉ አድርጓል።

#ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JawarMohammed

ወደወለጋ፣ወደኢሉባቦር ኦፌኮ ድጋፍ የለውም፤መሪዎቹም [ጃዋርን ጨምሮ] ወደዛ ላይሄዱ ይችላሉ የሚሉ ስጋቶች አሉ ተብለው 'ኬላ' በተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ የተጠየቁት አቶ ጃዋር መሃመድ የሰጡት ምላሽ፦

ምንሄደው ድጋፍ ያለን ቦታ ብቻ አይደለም። ምንሄደው ድጋፍ ለማጠናከር ነው። እኛ በሁሉም ወረዳ ላይ ህዝባችንን ማነጋገር እንፈልጋለን። ግን ሰዉ ይረሳል እንጂ በጣም ነገሮች በተጧጧፉበት እና መንግስት በጣም በተዳከመበት፣ በሌለበት ወቅት እኔና በቀለ እስከ አሶሳ ድረስ ሰው ማንም በማይሄድበት፣ የመንግስት ባለስልጣን ሀገር ጥሎ በጠፋበት ወቅትም ስንሄድ ነበር። አሁንም ወደምዕራብ እንሄዳለን።

ምዕራብና ደቡብ እንደሚታወቀው ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ ህጋዊ ያልሆነ ኮማንድ ፖስት አለ። ያ ኮማንድ ፖስት እንዲነሳ በህጉ challenge እናደርጋለን። እኛ ብቻ አይደለንም ጥምረት ፈጥረን እየሰራን ነው ያለነው ከኦነግ ጋር፣ ከኦብፓ ጋር አብረን ወደፊት የምናደርገው እንቅስቃሴ ይኖራል።

የማንሄድበት ዞን አይኖርም። ኦሮሚያ ውስጥ ብቻ አይደለም ወደ ተለያዩ ክልሎች የመሄድ እቅድ አለን። ደፍሮ ለሚለውም የተያያዝነው ትግል እንጂ ዳንስ አይደለም። ስለዚህ ሁሉም ቦታ እንሄዳለን። ስንሄድ ደግሞ በተጨባጭ ይታያል።

#TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለታሰሩ ኮድ 2 VAN መኪናዎች ጉዳይ፦

አቶ ደበሌ ቀበታ [ከጉሙሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር] ለፋና የተናገሩት፦

አስመጪዎቹ አድርገው የነበረው ፤ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ለግል መገልገያ የሚውሉ አይደሉም ይሉና ዲክላር ያደርጉ ነበር። በዚህ ልክ ዲክላር ካደራረጉ በኃላ ኤክሳዝ ታክስ ሳይከፍሉ ለግል መገልገያ እቃ ነው ወይም ለህዝብ ማመላለሻ ነው ብለው በግልፅም ለጉሙሩክ ሳይገልፁ በተጭበረበረ መልክ ይጠቀሙበት እንደነበረ ጥናቱ አሳየ።
.
.
ስለዚህ በዚህ ምክንያት መንግስት መሰብሰብ ይገባ የነበረው ኤክሳይዝ ታክስ ከነዚህ ተሽከርካሪዎች ያጣል። አገልግሎቱን ህብረተሰቡ ያግኝ በሚል ውሳኔ ነው መንግስት ከነዚህ ተሽከርካሪዎች ኤክሳይዝ ታክስ አልሰበስብም ያለው።
.
.
ኦፊሻል የሆነ ውሳኔ መወሰን ቢሆንም፤ አንዱ የንግድ ፍቃድ አውጥተው እነዚህን ተሽከርካሪዎች ወይም ኮድ 1 ወይም ወደ ኮድ 3 መቀየር ይገባቸዋል። ውሳኔዎቹ ጉዳት የማያደርሱ ሆኖ በምርጫው ላይ የተመሰረተ አይ እና ለታክሲ አገልግሎት እናውለው ወይም ለህዝብ ማመላለሻነት እናውለው ፤ ኮድ ሁለት የሚለው ይመክናል፤ ትራንስፖርት ባለስልጣን ሄደው ያመክኑትና ተሸከርካሪው ኤክሳይዝ ታክስ ለተተወላቸው አላማ ማዋል አለባቸው።

📹5 MB
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአብን ህዝባዊ ውይይት...

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የአዲስ አበባ ማስተበባበሪያ ፅ/ቤት በመጪው እሁድ የካቲት 15 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር አልማዝዬ ሜዳ አጠገብ በሚገኘው በቄራ ወረዳ 5 ሸማቾች ማኅበር አዳራሽ በንቅናቄው የማታግያ አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ዙሪያ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ሕዝባዊ ውይይት እንደሚያካሂድ አሳውቋል።

ምንጭ፦ አብን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሌላ መረጃ፦

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ የምስራቅ ጎጃም ዞን የአዋበል ወረዳ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት በስኩት እነጋትራ ቀበሌ ከሚገኙ አባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር በእነጋትራ ፍልቅልቅ ከተማ እሁድ የካቲት 15 ከጠዋቱ 4:30 ጀምሮ ውይይት እንደሚያደርግ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HAWASSA

የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ ዛሬ ሀዋሳ ከተማ በነበረ የድጋፍ ሰልፍ ላይ "የሲዳማ ህዝብ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ባደረገው ትግል ለዘመናት ሲገደል እና ሲታሰር ቆይቶ ፤ የህዝቡ የረጅም ጊዜ ጥያቄ «ተገቢ» መልስ ያገኘዉ በለውጡ ነዉ ተደምጠዋል።

አስተዳዳሪው "አካባቢያችንን የትርምስ እና የግጭት ቀጠና በማድረግ ለውጡን ለማደናቀፍ የቋመጣችሁ ከእንግዲህ ጊዜ እና ገንዘባችሁን በማጥፋት ባትደክሙ ይሻላችኋል" ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና...

በአዲሱ ፍኖተ ካርታ መሰረት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባለሙያዎች ሲዘጋጅ የነበረው ፈተና የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በኩል እንዲዘጋጅ በመወሰኑ ኤጀንሲው ፈተናውን በማዘጋጀት ላይ ይገኛል።

ፈተናው አለም አቀፍ ደረጃው የጠበቀ ለማድረግም በተቋሙ ያሉ ባለሙያዎች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ጋር በቅንጅት እየተሰሩ ሲሆን የፈተናው ዝግጅት ወደ መጠናቀቅ እየተቃረበ ነው።

የፈተናውን የህትመት ስራ ለመጀመርም የተለያዩ ማተሚያ ቤቶችን ባሳተፈ መልኩ ጨረታ ወጥቷል። ባለፈው አመት የተከሰተው ችግር ማህበረሰቡ በተቋሙ ላይ የነበረውን እምነት የሸረሸረ እና መጥፎ ትዝታን አስቀምጦ ያለፈ ነበር።

በዘንድሮ ዓመት የሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና ባለፉት አመታት ያጋጠሙ ችግሮች ዳግም እንዳይከሰቱ በተሻለ ጥንቃቄ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተሰምቷል።

ፈተናው ያለምንም ችግር በስኬት እንዲጠናቀቅ የተማሪ ፣ ወላጅ እና ማህበረሰብ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ ትምህርት የፖለቲካ ማስፈፀምያ እንዳይሆን እያንዳንዱ ህብረተሰብ አስተዋጽኦውን እንዲያበረክት ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በቡራዩ ከተማ ከደቂቃዎች በፊት አለመረጋጋት መፈጠሩን፤ ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ሲሰማም እንደነበር ከቡራዩ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ተገልፆልናል።

በከተማይቱ የሰው ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረም ተረድተናል። ዝርዝር የተጣሩ ጉዳዮችን እንድታነቡ እናደርጋለን፤ የሚመለከታችሁ አካላት ግን ትኩረት እንድትሰጡ ለማሳወቅ እንወዳለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ከሊቢያ ዳርቻዎች ወደ አውሮፓ ለመድረስ ተስፋ ያደረጉ 91 የአፍሪካ ስደተኞችን የጫነች ጀልባ ሜዲትራኒያን ባሕር ላይ መጥፋቷን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ እና ክራይስስ ሆትላይን አስታወቁ።

ጀልባዋ ከሊቢያ ዋና ከተማ #ትሪፖሊ በስተምሥራቅ ባሕር ዳርቻ በኩል ወጥታ መሠወሯ ነው የተጠቀሰው። ስለጠፉት ስደተኞች ምንም ዓይነት መረጃ አለማግኘታቸውን የስደተኞቹ ዘመዶች እና ቤተሰቦች ተናግረዋል።

[አሶሼትድ ፕሬስ,ኢቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዐብይ ፆም ወቅትን በተመለከተ መግለጫ ተሰጠ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበር ተክለሃይማኖት አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የዐብይ ጾም ወቅትን አስመልከቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ብጹእነታው በመግለጫቸው እንዳሉት ምዕመናን የዘንድሮውን ጾም ሲከውኑ ከጥላቻ እና ቂም ራሳቸውን በማራቅ እና በጾም ወቅት ከጥላቻና ዛቻ፣ ከበቀልና ተንኮል ርቀው መሆን አንዳለበት አሳስበዋል፡፡

‹‹እጃችንም፣ እግራችንም፣ አፋችንም ዓይናችንም፣ ጆሯችንም፣ ውስጣችንም በመንፈሳዊ ሕይወት አሸብርቀን መጾም ይገባናል፡፡ በዚህ ወቅት መስማትና ማዳመጥ ያለብን እግዚአብሔርን ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ድምጽ ፍቅርና ሠላም በመሆኑ አንድነትና ስምምነት፣ ዕርቅና ይቅርታ ፍትሕና እውነት፣ እኩልነትና ኅብረት በማድረግ ለሀገር ሠላም በመጸለይ ሊሆን ይገባል›› ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ሁኔታ እንድትወጣ ምዕመኑ በጾምና ጸሎት በአንድ ልቦና ለሀገሩ ሠላም እና ዕድገት፣ ፍትሕ እና እውነት በመቆም ጾሙን መከወን እንደሚገባቸውም ብጹእነታቸው አሳስበዋል፡፡

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION በቡራዩ ከተማ ከደቂቃዎች በፊት አለመረጋጋት መፈጠሩን፤ ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ሲሰማም እንደነበር ከቡራዩ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ተገልፆልናል። በከተማይቱ የሰው ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረም ተረድተናል። ዝርዝር የተጣሩ ጉዳዮችን እንድታነቡ እናደርጋለን፤ የሚመለከታችሁ አካላት ግን ትኩረት እንድትሰጡ ለማሳወቅ እንወዳለን። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የበራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሰለሞን ባልታወቁ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል ሲሉ የቲክቫህ ቡራዩ ቤተሰቦች አሳውቀውናል። ከደቂቃዎች በፊት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰሙ እንደነበር የቤተሰባችን አባላት ሲገልፁ ነበር።

በከተማው ከተፈጠረው አለመራጋጋት ጋር ተያይዞ ቁጥሩ በርከት ያለ የፀጥታ ኃይል ወደ ከተማይቱ [ቡራዩ] እየገባ እንደሆነ የቲክቫህ አባላት እየገለፁ ይገኛሉ።

በድንገተኛው ክስተት ስጋት ያደረባቸው የንግድ ተቋማት ባለቤቶች የንግድ ቤቶቻቸውን ሲዘጉ እንደተመለከቱ የቡራዩ ቤተሰቦቻችን አሳውቀውናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደቡብ ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው!

በደቡብ ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ [#COVID19] ስርጭት በሀገሪቱ እየጨመረ በመሆኑ ቫይረሱን ለመከላከል የምታደርገውን እርምጃ አጠናክራለች።

ትናንት ብቻ 53 አዲስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን ሪፖርት ያደረገችው ሀገሪቱ ዛሬ ደግሞ 52 ተጠቂዎች መለየታቸውን አስታውቃለች። በርካታ ወታደሮች የቫይረሱ ምልክት ታይቶባቸው፣ የወታደሮች መኖሪያ ካምፕንም በዝግ መከታተል ጀምራለች።

አሁን በአጠቃላይ 156 ተጠቂዎች ያሉባት ሀገሪቱ በብዛት ምልክት ታይቶባቸዋል የተባሉ 9,000 የአንድ ቤተ እምነት ተከታዮች በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲሆኑ አድርጋለች።

[ቢቢሲ፣ አል-ዓይን]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሮና ቫይረስ የመኪና ሽያጭን አቃውሷል...

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በየካቲት ወር የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ ቻይና ውስጥ የመኪኖች ሽያጭ በ92 በመቶ መቀነሱን የዘርፉን ንግድ የሚከታተለው አካል አሳወቀ።

የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ለመቆጣጠር ሲባል የሰዎች እንቅስቃሴ በመገደቡ ገዢዎች ወደ መኪና ነጋዴዎች መሄድ በማቆማቸው ሽያጩ በከፍተኛ ደረጃ እንዲያሽቆለቁል ምክንያት ሆኗል።

በመላው ቻይና በየካቲት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ላይ በቀን በአማካይ 811 መኪኖች ብቻ በመሸጣቸው ግብይቱ በ96 በመቶ መቀነሱን ተገልጿል።

የቻይና መኪና አምራቾች ማህበር የመኪና ሽያጭ ተቋማት በሮቻቸውን ሲከፍቱ ሽያጩ እየጨመረ እንደሚሄድ ተስፋውን ገልጿል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እስካሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ያለበት ሰው እንደሌለ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። ውድ ቤተሰቦቻችን ዝርዝር ጉዳዮችን ከላይ በምስሉ ላይ እንድታነቡ ለመጠቆም እንወዳለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የበራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሰለሞን ባልታወቁ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል ሲሉ የቲክቫህ ቡራዩ ቤተሰቦች አሳውቀውናል። ከደቂቃዎች በፊት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰሙ እንደነበር የቤተሰባችን አባላት ሲገልፁ ነበር። በከተማው ከተፈጠረው አለመራጋጋት ጋር ተያይዞ ቁጥሩ በርከት ያለ የፀጥታ ኃይል ወደ ከተማይቱ [ቡራዩ] እየገባ እንደሆነ የቲክቫህ አባላት እየገለፁ…
ተጨማሪ መረጃ፦

ቀደም ብለው የቡራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሰለሞን ታደሰ ዛሬ በቡራዩ ከተማ በጥይት ተመተው መገደላቸውን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቡራዩ ቤተሰቦች አሳውቀው ነበር።

ከ30 ደቂቃ በፊት ቢቢሲ ይዞት በወጣው ዘገባ ከኮማንደር ሰለሞን ታደሰ ጋር አብሮ የነበሩት የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የልዩ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተስፋዬ ድንቁም በጥይት ተመተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ዘግቧል።

ሁለቱ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ላይ ጥቃቱን የሰነዘረው አካል ማንነት እስካሁን ግልጽ አለመሆኑን እና እስካሁን በወንጀሉ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው አለመኖሩንም የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ኦቶ ጌታቸው እንዳሉት ከሆነ በሁለቱ ባለስልጣናት ላይ ጥቃቱ የተሰነዘረው የቡራዩ ከተማ አስተዳደር አቅራቢያ ምሳ እየተመገቡ ሳሉ ነበር። በጥይት ተመተው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙት ኮማንደር ተስፋዬ የሚገኙበትን ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም።

ምንጭ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ስካይ ላይት ሆቴል በተለያዩ ከተሞች ሊገነባ ነው...

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስካይላይት ሆቴል ቅርንጫፎችን በአገሪቷ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ለማስገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑን አሰታውቋል።

ሆቴሎቹ በዳሎል ፣ በኤርታሌ ፣ በባሌ ተራሮች፣ በራስ ዳሽን፣ በአርባ ምንጭና በሌሎች የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች እንደሚገነቡ ነው የተሰማው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#NewsAlert

የኮሮና ቫይረስ ሊባኖስ መግባቱ ተረጋገጠ!

የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ [COVID19] ተጠቂ መገኘቱን አረጋግጧል። ከኢራን ወደ ቤሩት ገብታለች የተባለች የ45 ዓመት የሊባኖስ ዜግነት ያላት ሴት ቫይረሱ እንደሚገኝባት ተረጋግጧል። ሌሎች ሁለት በቫይረሱ ሳይጠቁ አይቀሩም የተባሉ ሰዎች ላይ ደግሞ ምርመራ እየተደረገባቸው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"በእኔ ደረጃ በአደባባይ የሚሰደብ ጠ/ሚ የለም" - ዶ/ር አብይ

ከሰሞኑን በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ከህዝብ ጋር ውይይት ያደርጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተከታዩን ሲናገሩ ተደምጠዋል፦

አሁን ወጥቶ ሚሳደበውን ወጥቶ ሚራገመውን ሁሉ ሰድበን፣ ሁሉ አስረን እንችለዋለን? በኢትዮጵያ ውስጥ እንደምታውቁት በኔ ደረጃ በአደባባይ ሚሰደብ ጠቅላይ ሚኒስትር የለም።

ድሮ ተሳድባችሁ ሳይሆን፤ ልትሳደቡ አስባችኃል ተብላችሁ ትታሰሩ ነበር። አስባችኃል ያልኩት ቀልድ አይደለም፤ 'ድምፃችን ይሰማ' እኮ እንዲህ አስባችኃል ተብለው የታሰሩ ናቸው።

ህገ መንግስት ይከበር፣ የሃይማኖት እኩልነት ይከበር፣ ድምፃችን ይሰማ ሲሉ፤ አይ ይሄን አይደለም ያላችሁት ያሰባችሁት ሌላ ነገር አለ ተብለው ነው የታሰሩት። እንጂማ ህገ መንግስት ይከብር እንዴት ሰው ያሳስራል።

አሁን ደግሞ ህገ መንግስት ይከበር፣ ሙስሊም እውቅና ያግኝ፣ እስላሚክ ባንክ ይኑር፣ መጅሊሱ ተቋም ይሁን፤ ተቋም ይሁን ማለት ምን እንደሆነ አይገባችሁም፤ ለምሳሌ ሳዑዲ በህግ እውቅና ካልሰጠን በስተቀር እስላሚክ ሴንተር መፈራረም አይችልም ከመጅሊስ ጋር፤ አሁን እውቅና አግኝተን ወር ሳይሞላ 80 እና 90 ሚሊዮን ዶላር እያመጣን ነው እኮ።

ይሄን የሚየውቁ ሰዎች እኛን መልሰው የሙስሊም ጠላይ ይላሉ። ሚናገር ሰው ሚያጥላላ ሰው ካለ ትክክል አይደለም። እንኳን መስጅድ የአንድ ሰው ደሳሳ ጎጆ መቃጠል የለበትም።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ባዘጋጀው እና የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ተወካይ ወ/ሮ ሄተር ፈላይን በተገኙበት በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ባለው የለውጥ እንቅስቃሴ እና ምርጫ 2012 አስመልክቶ ውይይት ተካሂዷል፡፡

አዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በተካሄደው እና ዓላማው በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የፖለቲካ እና የምርጫ ዝግጅት ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መረጃ ለመሰብሰብ እንደሆነ በተገለጸው በዚሁ የውይይት መድረክ፣ የምርጫውን የግዜ ሰሌዳ፣ በተፎካካሪ ፓርቲዎች እና በገዥው ፓርቲ መካከል ያለው ግንኙነት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያጋጥሟቸው ችግሮች፣ የምርጫ ቦርድ ዝግጅት እና አቅም፣ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የሀሳብ ልውውጥ ተደርጓል፡፡

በውይይቱ የተገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች አጠቃላይ የለውጥ ሂደቱን እና ምርጫ 2012 አስመልክቶ ያጋጠሟቸውን ችግሮች እንዲሁም ገዥው ፓርቲ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ላይ በማድረስ ላይ ነው ያሏቸውን ልዩ ልዩ ጫናዎች ለኤምባሲው ተወካዮች ገልጸዋል፡፡ የመንግስት ሀብትን እና ሚዲያን በብቸኝነት መጠቀም ፓርቲዎቹ በገዠው ፓርቲ ላይ ካነሷቸው ችግሮች መካከል ይገኙበታል፡፡

የፓርቲዎቹ ተወካዮች የአሜሪካ መንግስት ከሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በእኩል ርቀት ላይ ሊቆም እና በተለይ ለገዢው ፓርቲ የተለየ ድጋፍ ማድረግ የፖለቲካ ሜዳውን እና በዚህ አመት በሚካሄደው ምርጫ ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

More https://telegra.ph/ETH-02-21-2

#FreedomandEqualityParty

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

በዛሬው የሂልተን ሆቴል የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፉ ፓርቲዎች፦

1. ኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ)
2. አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)
3. ኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
4. አረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉአላዊነት (አረና)
5. ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)
6. የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)
7. ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)

ምንጭ፦ ነፃነትና እኩልነት ፓርቲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot