TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WolaitaSodo

በወላይታ ሶዶ ከተማ የወላይታ ህዝብ የክልል ጥያቄ ዛሬ ታህሣስ 10/4/2012 ዓም ዓመት መሙላቱን ምክንያት በማድረግ ሁሉም የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች የሀገር ሸማግሌዎች፣ ወጣቶችና ሴቶች ነጋዴዎች መንግስት ሰራተኞች በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚገኘው ጉተራ አዳራሽ ወይይት አድርገዋል። የዕለቱ ተሳታፊዎች የህዝብ ጥያቄ በሠላማዊ መንገድ ብቻ መቀጠል አለበት ብለዋል።

(ወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር)
@tikvahethioia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
በወላይታ ሶዶ ከተማ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ! በወላይታ ዞን - ወ/ሶዶ ከተማ በደቡብ ክልል ጥያቄ በተቋቋመው የኮማንድ ፖስት ከትናንት ታኅሳስ 9 ማምሻውን ጀምሮ እስከ ዛሬ ታህሳስ 10 ድረስ ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የዞኑን የክልልነት ጥያቄ ተሟጋቾች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካለከል አሸናፊ ከበደ፣ ወርቅነህ ገበየሁ እና ቡዛየሁ ቡቼ የተባሉ በማኅበራዊ ትስስር…
#UPDATE

በወላይታ ሶዶ ከተማ ከትናንት ማታ ጀምሮ በኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩ ግለሰቦች መካከል ከዎብን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱአለም ታደሰ ውጪ ሁሉም መለቀቃቸው ተሰምቷል።

ከነዚህም መካከል፦

•አቶ አሸናፊ ከበደ
•አቶ ወርቅነህ ገበየሁ
•አቶ አማኑኤል ሞጊሶ
•አቶ ቡዛየሁ ቡቼ
•አቶ ጥጋቡ ደጀኔ
•ብርቱካን እንደሚገኙትበት ለማወቅ ተችሏል። ግለሰቦቹ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የወላይታ ህዝብ የክልልነት ጥያቄ እንዲመልስ የሚታገሉ እንደሆኑ ነው የሰማነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#YouthConnect

በወጣቶች የክህሎት ልማት እና የስራ ፈጠራ እንዲሁም ፋይናንስን ለወጣቶች ተደራሽ ማድረግ ትኩረቱ የሆነው ዮዝ ኮኔክት ኢትዮጵያ መርሀ-ግብር ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡ 'ትስስር በምክንያት' በሚል መሪ ቃል ነው መርሀ-ግብሩ ይፋ የተደረገው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የትግራይና የፌደራል መንግስቱ ግንኙነት በጣም አሳሳቢ ነው!" - ዶ/ር አብርሃም ተከስተ

የትግራይ ክልል በተደጋጋሚ እያጋጠመኝ ነው ባለው ችግር ሳቢያ ከፌደራል መንግሥት ጋር ያለው ግንኙነት "በጣም አሳሳቢ" አሳሳቢ ወደ ሆነ ደረጃ እደረሰ መምጣቱን የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ዶ/ር አብረሃም ተከስተ ለቢቢሲ ተናገሩ።

ዶ/ር አብረሃምይህንን ያሉት ከትናንት በስቲያ ለሥራ ጉብኝት ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ ሊያደርጉ የነበሩ የቻይና የሻንሺ ግዛት ልዑካን 'በፌደራል መንግሥት ትዕዛዝ' ወደ ትግራይ ክልል እንዳይጓዙ ተደርጓል ሲል የትግራይ ክልል መንግሥት ቅሬታውን ካሰማ በኋላ ነው።

More👇
https://telegra.ph/BBC-12-20

(ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ለሁላችንም የምትመች ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ" በሚል የተካሄደው የሰላም ኮንፈረንስ የማጠቃለያ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው!

"ለሁላችንም የምትመች ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ" በሚል ርዕስ በተዘጋጀውና በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘው የሰላም ኮንፈረንስ የማጠቃለያ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከሰዓት በሰላም ኮንፈረንሱ ላይ ተገኝተዋል።

ኮንፈረንሱ ባለፉት ሳምንታት በአማራና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥታት የንግድ ማኅበረሰብ፣ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን አንቂዎች፣ ወጣቶች፣ የሃይማኖትና የማኅበረሰብ አመራሮች መካከል ሲካሄዱ የቆዩት ጉባኤያት ማጠናከሪያ ነው።

ጉባኤያቱ ልዩነቶችን አስታርቆና አቻችሎ የሁለቱን ክልላዊ መንግሥታት ሕዝቦች ለማቀራረብ ታስበው የተዘጋጁ መሆናቸውን የጠቅላይ ሚንስቴር ፅ/ቤት አስታውቋል።

(Office of the Prime Minister-Ethiopia)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREAttorneyGeneral

በሀገሪቱ በሚጉኙ የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርስቲዎች) ብሔርን መሰረት ባደረገ መልኩ በተከሰተው ሁከትንና ብጥብጥ በሰው ህይወት፣ እንዲሁም በአካል እና በንብረት ላይ በተፈፀመው ወንጀል ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በነዚህ አካባቢዎች ከ16 በላይ የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች ተለይተው ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወላይታ ሶዶ ወደመደበኛ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች ነው!

በከተማይቱ መግቢያ ና መውጫ አሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል። በከተማይቱ የባጃጅ፣ እምዲጉም አገልግሎት ሰጪ ሆቴሎች እና ሌሎችም በከፊል አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወላይታ ዞን አስተዳደር ህዝቡ ላሳየው ጨዋነት ምስጋናውን አቀረበ!

የወላይታ ህዝብ ዛሬ የኢፌዴሪ ህገ-መንግሥትን በማክበር ረገድ ላሳየው ጨዋነት የዞኑ አስተዳደር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለተለያዩ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ እንዳገለጹት የወላይታ ህዝብ ከአንድ ዓመት በፊት ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ያቀረበውን ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግሥታዊ ጥያቄ የክልሉ መንግሥት ምላሽ አለመስጠቱን ለማውገዝ ዛሬ ታህሳስ 10/2012 ዓ.ም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲጠይቅ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ የደቡብ ክልል ኮማንድ ፖስት ትናንትና ከሰዓት በኋላ በሰጠው መግለጫ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሌለ የቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ ህገ-መንግሥታዊ ስርዓትን በማክበር ላሳየው ጨዋነት ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

More👇
https://telegra.ph/WRS-12-20

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ትግራይን በኢኮኖሚ የማዳከም አንድ አካል ነው!" - የትግራይ ክልል መንግስት

ያልታወቀ 'የፌደራል መንግስት' አካል የቻይና ሻንዢ ግዛት ባለስልጣናት እና ኢንቨስተሮች ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ መከልከሉ የትግራይ ክልላዊ መንግስት አሳውቆ የጉዞ ክልከላው "ትግራይን በኢኮኖሚ የማዳከም አንድ አካል ነው" ሲል ገልፆታል፡፡

(DW)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

በደቡብ ወሎ ዞን ከመካነ ሠላም ወደ ደሴ ሲጓዘ የነበረ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በ5 ሰዎች ላይ የሞትና በሌሎች ቁጥራቸው ባልተገለጸ ተሳፋሪዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

(AMMA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ESAT...

"ESAT የተባለው ሚዲያ የህዝብን ህገ - መንግስታዊ መብት ጥያቄን በማጠልሸት እንዲሁም በዎላይታ ብሄር ላይ ግልጽ የህዝብን ሞራል የሚነካ ጥላቻ ንግግር ማታ ዕለታዊ በተባለው ፕርግራም ላይ ማድረጋቸውን በዎላይታ ህዝብ ስም በግልፅ አወግዛለሁ። በተጨማሪም ጣቢያው እንዲታረምና ሰፊውን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ ጉዳዩን ለብሮድካስት ባለስልጣን ድረስ እንወስዳለን" - አቶ ዳጋቶ ኩምቤ (የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrAbiyAhemedAli

"ዩኒቨርሲቲ የሚኬደው ለመገዳደል ሳይሆን ለመማር ነው። እነዚህን ወጣቶች ለግጭት የሚጠቀሙ አካላት አይጠፉም፤ በአሁኑ ወቅት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጠንካራ ጥበቃ የማደራጀት ስራ ተከናውኗል በተጨማሪም በጥፋተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ሞጣ ከተማ አስተዳደር ዛሬ አመሻሽ ላይ (ከምሽቱ 1:30) ጀምሮ በከተማዋ በሚገኘው የታላቁ ጀሚዑል ኸይራት መስጂድና ሌሎች ሁለት መስጅዶች ላይ የማቃጠል ተግባር መፈፀሙ ተሰምቷል።

ይህ አስደንጋጭ ድርጊት ከመፈፀሙ ቀደም ብሎ ፈፃሚዎቹ እና ምክንያቱ በግልፅ ባይታወቅም በጥንታዊው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ሙከራም ነበር ተብሏል።

በአሁን ሰዓት በከተማይቱ ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማም ነው ከአካባቢው እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች የሚጠቁሙት። የሱቆች ዝርፊያ እየተካሄደ እንደሆነና በሰዎች ላይም አደጋ መድረሱ እየተገለፀ ነው። የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ሁኔታው ከዚህ የከፋ አደጋ ከማድረሱ በፊት ሊያስቆሙና አጥፊዎችንም በመለየት ለህግ ሊያቀርቡ ይገባል።

ሞጣ ከተማ፦

ማህበረሰቡ ለእልፍ አመታት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ፣ በሃይማኖት መቻቻል፣ በመከባበር፣ በመዋደድ የሚኖርባት ከተማ እንደሆነች ነው የሚነገርላት። መንግስት አጥፊዎች በአፋጣኝ ለፍርድ ማቅረብ እና ለህዝብ ማሳወቅ አለበት። አፋጣኝ የእርቅ መርሃ ግብርም ሊዘጋጅ፣ የተጎዱም ሊካሱ፣ የተቃጠሉ መስጊዶችም በአስቸኳይ ሊገነቡ ይገባል። ነዋሪዎችን የማያባራ ግጭት ውስጥ ለመክተት እየተደረጉ ያሉ አደገኛ እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል።

ከኡስታዝ አቡበክር አህመድ👇
https://telegra.ph/TIKVAH-12-21

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WALTA

ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽ ኮርፖሬት ከትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካዔል ጋር በተያያዘ በተለቀቀው ሀሰተኛ መረጃ ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ብሎ የጠረጠራቸው አራት የተቋሙ ሰራተኞችን ከስራ አግዷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

የፌደራሉ እንዲሁም የክልሉ መንግስት በሞጣ አካባቢ ለተፈጠረው ችግር እጅግ አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ ሊፈልጉ ይገባል። ህዝቡንም የማረጋጋት ስራ በአፋጣኝ ሁኔታ ሊሰራ ይገባል። ችግሮች አሁን ካሉበት ሳይባባሱ እንዲሁም ሳይዛመቱ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ እናሳስባለን። ልዩ ትኩሩት በሞጣ ከተማ ለተፈጠረው ችግር!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሞባይል ስልክ ስክሪን ማጠንከሪያነት አገልግሎት ላይ የሚውለው ቴክኖሎጂ በተጠቃሚዎች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እንደሌለ ተገለጸ!

ሰሞኑን በሃገራችን በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው በብዛት ከቻይና ወደ ሃገር ውስጥ የሚገባ የናኖ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው (Nano coating machine) ለሞባይል ስልክ ማጠንከሪያነት አገልግሎት ላይ በመዋል ላይ ይገኛል፡፡

ይህንን ተከትሎ ከተገልጋዮች እና የተለያዩ ሚዲያ አካላት በደረሰ መረጃና በቀረበው ጥያቄ መሰረት ወደ ሃገር እየገባ ባለው የዚህ ቴክኖሎጂ መሳሪያ ከጨረራ አንጻር ጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጠንቅ መኖሩና አለመኖሩን ለማጣራት የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ በመገኘት በመጋዘን ውስጥ ከሚገኙ (Nano coating machine) መሳሪያዎች ውስጥ ናሙና በመውሰድ ባደረገው የቁጥጥር እና ምርመራ ሥራ መሳሪያው የኢትዮጵያ ጨረራ መካላከያ ካስቀመጠው ጉዳት ከሚያስከትሉ የጨረራ መጠን ልኬት በታች የሆነ እና በህዝብ እና በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት አለመኖሩን አረጋግጧል፡፡

አዮን ፈጣሪ ስላልሆኑ የጨረራ አይነቶች አዮን ፈጣሪ ያልሆኑ የጨረራ አይነቶች በርካታ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ልዕለ ሀምራዊ ሞገድ (UV Radiation) ይገኝበታል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-20

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የዕምነት ተቋማት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች የክሽፈታችን መገለጫዎች ናቸው። ሌላው ሰው የሚያከብረውን፣ የሚያመልከውን፣ ተደፍቶ የሚጸልይበትን እና ከፈጣሪው ጋር የሚገኛኝበት ሥፍራ ማቃጠልና ማውደም እርስ በርሳችን አለመከባበራችንን ነው የሚያሳየው። እጅግ የኋላቀርነትም ምልክት ነው። በእምነት ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በጋራ ልናወግዝ ይገባል። [ትናንት] በምስራቅ ጎጃም፣ ሞጣ አካባቢ በመስጊዶች ላይ የተፈጸመው ጥቃት እጅግ አስነዋሪ የወንጀል አድራጎት ነው። መንግስት ድርጊቱን የመጸሙትን ሰዎች ወደ ፍርድ በማቅረብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ አለበት። ለእምነት ተቋማትም በቂ ጥበቃ ሊደረግ ይገባል።" - ያሬድ ሀይለማርያም (የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው AHRE ዋና ዳይሬክተር)
.
.
.
"የእምነት ተቋማት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማውገዝ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው። ሃይማኖትንና ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች ወደማያባሩ ቀውስ ውስጥ ሊከቱ እንደሚችሉ ይታወቃል። በመሆኑም በቤተክርስቲያን፣ በመስጅድ እና በተለያዩ የእምነት ተቋማት ላይ የሚደርሰውን የተቀነባበረ ሴራ በመገንዘብ ችግሩን በሰከነ መንፈስ ማክሸፍ ይገባል። አረመኔያዊ ድርጊት በመፈጸም የሚሳተፉ አካላትን ለይቶ ለህግ ማቅረብ ለነገ የማይተው ጉዳይ ነው።" - ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ (የትራንስፖርት ሚኒስትር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሞጣ ከተማ በሀይማኖት ተቋማት ላይ የደረሰውን ጥቃት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በጽኑ ያወግዛል!

በምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ ትላንት አርብ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ በጥንታዊና ታሪካዊው ሞጣ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የእሳት ቃጠሎ የተነሳ ሲሆን፣ በቤተ ክርስቲያኑ ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በከተማው ነዋሪ ርብርብ እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ይህንን ተከትሎ የተወሰኑ ወጣቶች በመስጊዶችና አንድ የንግድ ቤት ላይ የእሳት ቃጠሎ እንዲደርስ አድርገዋል። ሱቆችን የመዝረፍ ሙከራም ተካሂዷል። አብን በሞጣ ከተማ በሁለቱም የእምነት ተቋማትና በንብረት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በጥብቅ ያወግዛል።

ድርጊቱም በምንም አይነት መንገድ ጠንካራ ትስስር ያለውን የሞጣና አካባቢው ህዝበ ክርስቲያንና ህዝበ ሙስሊም የሚገልጽ ሳይሆን ጥቂት በስሜት የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ድርጊት እንደሚሆን ይረዳል።

የአማራ ሕዝብ ለሺህ ዓመታት የተለያዩ ሀይማኖቶች ተከባብረው፣ሙስሊሙ አብያተ ክርስቲያን፣ ክርስቲያኑ መስጊዶች ሲገነቡ አብሮ እየገነባ፣በሰላም የሚኖሩበት ህዝብ ሲሆን፣ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአማራ "ክልል" በተለይ በእስልምና እምነት ተቋማት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች መጨመራቸው አሳሳቢ ነው። የእምነት ተቋማት ላይ የሚደረግ ጥቃት የአማራን ሕዝብ እሴት የማይወክል፣ ፍፁም ህገወጥና በአስቸኳይ ሊታረም የሚገባ ተግባር ነው ብሎ ንቅናቄያችን ያምናል።

የክልሉ መንግስት በህዝባችን የእምነት፣የትምህርትና የንግድ ተቋማት ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶችንም ሆነ የህዝባችን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሰርጎ ገቦችን መቆጣጠር አለመቻሉ በጣም አሳዛኝና አስቸኳይ መፍትሄ የሚያሻው ነው።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-21

@tikvahethiopia
#IMF

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ( አይ ኤም ኤፍ) ለኢትዮጵያ የ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ፡፡ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ያጸደቀው ይህ ድጋፍ የኢትዮጵያን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ለመደገፍ  የሚውል  መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትዝብት...

እውነት እናተ የቲክቫህ ቤተሰብ ናችሁ?

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ በሚያስፈራ መልኩ መጥፎ ድርጊቶችን እንደማውገዝ የሚያፎካክሩ፣ የኔ ብቻ ይነገርልኝ ስለ ሰው ምን አገባኝ የሚሉ፣ ያለፈውን ነገር እያነሱ የሚያስተያዩ የሚያወዳድሩ፣ ባለፈው እንዲህ ሲሆን መች ቀረበ የሚሉ፣ የሰው ልጆችን ሞትና ስቃይ ሳይቀር የሚያወዳድሩ፣ አንዱን ጥፋት በሌላ ጥፋት ለመሸፈን የሚፈልጉ እየበዙ ነው። መጥፎ ድርጊትን እኩል ካላወገዝን ሀገራችን ለማጥፋት ቀዳሚዎቹ እኛ እንሆናለን።

አንዳንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የሚመስሉ ነገር ግን ስለቤተሰባችን ዓላማ ምኑንም የማያውቁ ሰዎች የራሳቸው ጉዳይ ብቻ እስካልተነገር ድረስ በተለያዩ አቅጣጫዎች ሲፈልጉ ዘረኛ፣ ተላላኪ፣ አሽቃባጭ፣ እያሉ ስድባቸውን ጥላቻቸውን ያዘንቡብናል። እኛም በትዕግስት ወገኖቻችን ናቸውና ይህ ጥላቻ መጥፎ ነው የሚጎዳውም ራስን ነውና ይቅርባችሁ እያልን ክፉ ሳንናገር እያስረዳን ነው። ሚዛናዊ ነገር አታቀርቡም የሚሉ የቤተሰባችን አባላት ደግሞ ማስረጃችሁን አቅርቡ ሲባሉ ስድብ፣ የጥላቻ ንግግር ይልካሉ ወይም ችግሮችን ፈልገው ሊነግሩን ይጥራሉ። ሁሉም ነገር ገፁ ላይ ስላለህ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል።

እውነተኛ ትችት እና ቅሬታ ካላችሁ በማስረጃ ብቻ አቅርቡ፤ ያንን ማድረግ ካቃታችሁ የጥላቻ ንግግሮቻችሁን የምናስተናግድበት አቅም የለንም! የጥላቻ ንግግር የምትናገሩና ምንም ማስረጃ ሳይኖራችሁ የምትሳደቡ እንዲሁም የቤተሰቡን ስም የምታንቋሽሹ ሰዎችን ከቤተሰባችን ለመቀነስ እንገደዳለን፤ ማንም ሰው የተሰማውን መናገር ይችላል፣ ቅር ያለውን መግለፅ ይችላል ግን መረጃ፣ ማስረጃ ማቅረብ አለበት ያንን ሳያደርግ የሚሳደብ ግን ሆን ብሎ በህዝቦች መካከል እልቂት እንዲፈጠር የሚፈልግ ነውና እሱ የቤተሰባችን አባል መሆን አይችልም።

@tikvahethiopiaBot