AMBO UNIVERSITY
በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስም የተቋቋመው የባህል ማዕከል ተከፈተ!
-የሎሬቱ ሀውልት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊቆምላቸው ነው
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ስም የተቋቋመው የባህል ማዕከል ተከፈተ። የሎሬቱ ሀውልት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊቆምላቸው ነው።
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን አምቦ ካበቀለቻቸው ባለ ምጡቅ አዕምሮ መካከል በስነፅሁፍና በትያትር ዘርፍ በፈርጥነት የሚጠቀሱ ምሁር ቢሆኑም፤ በሚገባቸው ልክ ክብር እንዳለተሰጣቸው በሎሬቱ ስም ዛሬ በአምቦዩኒቨርሲቲ የመታሰቢያ የባህል ማዕከል በተከፈተበት ወቅት ተገልጿል።
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ታደሰ ቀና እንዳሉት፤ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን የጥበብ ሰው ብቻ ሳይሆኑ የሰብአዊ መብትሟጋች ነበሩ። በስራዎቻቸው በሀገራቸው የተዘጉትን ታሪካዊና ማህበራዊ መስተጋብሮች ሲተቹና እንዲስተካከሉ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሲያደርጉ ነበር፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-21-8
Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግብጽ እና ኢትዮጵያን እያወዛገበ ያለው በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ቀጥሏል። በሚቀጥለው ዓመት ኃይል ማመንጨት ይጀምራሉ የተባሉት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ግንባታም በመከናወን ላይ ይገኛል። የግድቡ ሰሞነኛ መልክ ምን እንደሚመስል ከቪዲዮው ይመልከቱ።
#Video: DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Video: DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🔖እናስተዋዉቅዎ!
Addis - global fashion provides only orginal products. We offer quality service and commited to deliver comfort to our clients.
Free delivery is available.
Call us : 0923 29 52 32
Subscribe us on our telegram chanel : join https://t.iss.one/addisglobalfashion
@addisglobalfashion
upgrade your class!

#SNNPRS
በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የተመሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራር በኮንታ ልዩ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረሰተብ ክፍሎች በዛሬው እለት ጎብኝተዋል፡፡ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ22 ሰዎች ህይወት ማለፋ ይታወሳል፡፡ ከዚያም በኋላ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ በጥቅሉ የ25 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 481 አባወራዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የክልሉ መንግስት ከተጎጂ ቤተሰቦች ጎን እንደሚቆም ተናግዋል፡፡
Via EBC

ጥቅምት 2/2012 በኮንታ ልዩ ወረዳ በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ውድ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያን! ነብስ ይማር! #ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MinistryOfPeace
በአፋር ክልል እና በሶማሌ ክልል መካከል የተፈጠረ ችግር በውይይት ለመፍታት ከስምምነት መደረሱን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሰላም ሚኒስቴር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ዘላቂ መፍትሔ ዳይሬክተር ጄኔራል ምግባሩ አያሌው እንደገለፁት ሚኒስቴሩ ወደ ሁለቱ ክልሎች የላከው የልዑካን ቡድን የሁለቱን ክልሎች የሰላም ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የሰላም ኮንፈረንስ ለማካሄድ ከስምምነት ደርሰዋል።
ወደ አካባቢው የተንቀሳቀሰው ግብረ ኃይል ለችግሩ እልባት ለመሻት መጠነ ሰፊ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተር ጀኔራሉ ፣ የመፍትሄ ሃሳቦች ጎን ለጎን በመሰጠት እየሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ አክለዋል። በዋናነት ለችግሩ እልባት ተሰጥቷል፤ በቀጣይነት ዘላቂ የሆነ ሰላም በአካባቢው እንዲኖር የተለያዩ ስራዎች እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ከሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ፦
በቅድሚያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኖቤል ሰላም ሽልማት በማግኘታቸው የተሰማውን የላቀ ደስታ ሶዴፓ ይገልፃል። የሶማሌ ክልል ህዝብ ከሌሎች የሀገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን ለዘመናት ለነፃነት፣ እኩልነትና በመፈቃቀድና መከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት ጠንካራ ትግል ሲያደርግ የቆየ ከመሆኑም ባሻገር እንደ ሌሎች የአገራችን ህዝቦች ሁሉ በገዥ መደቦች ይደርስበት በነበረው በደልና ጭቆና ሳይንበረከክ ክብሩን ያላስደፈረና ለህልዉናው አደጋ የሆኑ ጉዳዮችን ሲመክት የቆየ ሀገር ወዳድ ህዝብ ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-21-10

የኤሌክትሮኒክስ የታክሲ ስምሪት አገልግሎት ለመስጠት 14 ድርጅቶች ፈቃድ ጠየቁ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአንድ ወር በፊት ይፋ ያደረገውን የኤሌክትሮኒክስ የታክሲ ስምሪት መመሪያ ተከትሎ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩ እንዲሁም አዳዲስ 14 ድርጅቶች ፈቃድ ለማግኘት አመለከቱ።
ካመለከቱት ድርጅቶች መካከል የተወሰኑት በድምፅ፣ በመተግበሪያዎች እና በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አማካኝነት አገልግሎቱን ለመስጠት ማመልከታቸውን በባለሥልጣኑ የፈቃድ አሰጣጥ የሥራ ኀላፊ የሆኑት አልአዛር ይርዳው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
እንደ ኀላፊው ገለጻ፤ አገልግሎቱን ለመስጠት ጥያቄውን ያቀረቡትን ድርጅቶች ከመመሪያው አንፃር እየመረመሩ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥም ፍቃዱን ለመስጠት የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-21-11
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከአንድ ወር በፊት ይፋ ያደረገውን የኤሌክትሮኒክስ የታክሲ ስምሪት መመሪያ ተከትሎ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩ እንዲሁም አዳዲስ 14 ድርጅቶች ፈቃድ ለማግኘት አመለከቱ።
ካመለከቱት ድርጅቶች መካከል የተወሰኑት በድምፅ፣ በመተግበሪያዎች እና በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አማካኝነት አገልግሎቱን ለመስጠት ማመልከታቸውን በባለሥልጣኑ የፈቃድ አሰጣጥ የሥራ ኀላፊ የሆኑት አልአዛር ይርዳው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።
እንደ ኀላፊው ገለጻ፤ አገልግሎቱን ለመስጠት ጥያቄውን ያቀረቡትን ድርጅቶች ከመመሪያው አንፃር እየመረመሩ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥም ፍቃዱን ለመስጠት የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-21-11
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#GONDAR | ሰሞኑን በአማራ ክልል በጎንደር ከተማ እና አካባቢው ተፈጥሮ ከነበረው ግጭት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው ሲጣራ ከነበሩ 119 ተጠርጣሪዎች መካከል ሃምሳ ስምንቱ መለቀቃቸውን የጎንደር ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። የከተማው የሰላም እና የህዝብ ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን ለጀርመን ራድዮ እንደገለፁት በግጭቱ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እና ሰዎች መፈናቀላቸውን ተናግረዋል። ስለ ሟቾቹ እና ተፈናቃዮቹ ብዛት የተጠየቁት ኃላፊው ቁጥሩን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። የጎንደር ከተማን ተዘዋውሮ የተመለከተው የጀርመን ራድዮ ጋዜጠኛ የከተማው ነዋሪው መደበኛ የዕለት ከዕለት ስራውን ሲያከናውን ታዝቧል። አቶ ተስፋም በጎንደር ብቻ ሳይሆን በአካባቢው ያለው ሰላም ወደ ቀድሞው ሁኔታ እየተመለሰ ነው ብለዋል።
ምንጭ፦ የጀርመን ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የጀርመን ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዛይራይድ
ዛይራይድ ለአርቲስት ሙሉአለም ታከለ በገባው ቃል መሰረት ለህክምናው ማገዣ በድርጅቱ መስራች አቶ ሀብታሙ በኩል 115,000 ለገሰ።

በምሥራቅ አፍሪካ ከባድ ዝናብ እንደሚወርድ ተተነበየ!
የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ትንበያ ባለሙያዎች በምሥራቅ አፍሪካ ክልሎች ከባድ ዝናብ መውረድ እንደሚቀጥል ተንብየዋል። ሀገሮቹ ከባድ ዝናብና የጎርፍ መጥለቅለቅ ሲፈራረቅባቸው ቆይቷል።
ክልሎቹ የኢትዮጵያና የሱዳን ደቡባዊ ክፍሎችን፣ ኡጋንዳን፣ የታንዛንያ ሰሜን ክፍል፣ እንዲሁም ኬንያ ሲሆኑ፣ ሌላ ጊዜ እነዚህ ሃገሮች ከመስከረም እስከ ታኅሳስ ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚያገኙት ዝናብ ውሱን መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የውቅያኖስና የህዋ አስተዳደር ገልጿል።
Via VOA

#KoyeFeche
ትላንት በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች ሊካሄዱ የነበሩ የነበሩ ስብሰባዎች በተደራጁ ወጣቶች ተስተጓጉለዋል። በከተማዋ ኮዬ ፈጬ በተባለው አካባቢ በተፈጠረው ሁከት ቢያንስ 2 ሰዎች መጎዳታቸውን የዓይን እማኞች ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል። በአቃቂ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ንብረት የሆነ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ንብረትም ወድሟል።
በኮዬ ፈጬ አካባቢ በተለያዩ ጊዜያት በተደራጁ ወጣቶች መንገድ ሲዘጋ እና የአካባቢውን ነዋሪዎች ለስጋት የሚዳርጉ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ቆይተዋል። ትናንት በዚሁ ስፍራ የተከሰተው ግን ከወትሮው ለየት ያለ እንደነበር እና በሁለት የተደራጁ የወጣቶች ቡድኖች መካከል የተፈጠረ እንደሆነ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ለጀርመን ሬድዮ ገልጸዋል። አቶ ደረጀ ቤጊ የተባሉ የዓይን እማኝ የትላንትናው ሁከት የተከሰተው ከሌሎች ስፍራዎች በተሽከርካሪ ተጓጉዘው በመጡ ሰዎች ነው ይላሉ።
“ትናንት የእኛ ልጆች በኮዬ ፈጬ ወረዳ 9 ስብሰባ ነበራቸው ፤ የወረዳው ሃላፊዎች እናንተ እዚህ መሰብሰብ አትችሉም ቅሊንጦ ሂዱ አሉዋቸው። ልጆቹን አታለዋቸው ነው ወደዚያ የላኳቸው። እነርሱን ከላኩ በኋላ ግን የአማራ ልጆች እኔ የነፍጠኛ ልጅ ነኝ የሚል ከነቴራ ለብሰው በመምጣት ለእነዚያ የከለከሉትን አዳራሽ ለእነዚህ ፈቀዱላቸው። ይሄ ነው ቁጣ የቀሰቀሰው” ሲሉ ሁከቱን መንስኤ ነው ያሉትን ለጀርመን ሬድዮ አስረድተዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-21-12
Via DW

TIKVAH-ETHIOPIA
የፀጥታ ችግሩ መነሻ ምን እንደሆነ እንደማያውቁ የተናገሩት በአካባቢው የሚኖሩ የቤተሰባችን አባላት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ እየሰሙ እንደሆነ፣ ወጣቶች ተደራጅተውና ዱላ ይዘው ሲንቀሳቀሱ እንደተመለከቱ፣ የፀጥታ ሃይሎች ሁኔታውን ለመቆጣጠር በአካባቢው እንደተሰማሩ፣ የአምቡላንስ ድምፅ በአካባቢው እንደሚሰማ ገልፀዋል። #video: Hils/የቲክቫህ ቤተሰብ ከቦሌ ቡልቡላ/ @tsegabwolde @tikvahethiopia
የካቲት 12 ሆስፒታል በህክምና ከሚያገለግሉ የቤተሰቦቻችን አባላት በመጣልን መልዕክት፦ ዛሬ ቦሌ ቡልቡላ በነበረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ከ25 የሚበልጡ ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ተከታትለዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ትብብርና ፉክክር ሚዛናዊ መሆን አለባቸው!›› አቶ ዮናስ ዘውዴ
ሀገራችን በብዙ ርዕዮተ ዓለም ሙከራ ውስጥ ብትቆይም እስካሁን ድረስ የምዕራቡን አስተሳሰብ ስንቃርም ቆይተናል፡፡ አሁን ላይ መደመር ሀገራዊ መፍትሔን ይዞ መጥቷል፡፡ መደመር የሰው ልጅ ምንድን ነው ብሎ ይጠይቃል እንዲሁም የሰውን ልጅ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የህልውና ፍላጎቶችን በመመለስ ያምናል፡፡
መደመር መጨፍለቅ ማለት አይደለም መደመር አሀዳዊነትም ማለት አይደለም መደመር የተበታተነ አቅምን ወደ አንድ ማምጣት ማለት ነው፡፡ የመደመር መነሻ ከነበረው ነገር ላይ ነው፡፡ የተሰሩ ሥራዎችን ንዶ እንደ አዲስ አይገነባም ነገር ግን ያሉትን ይዞ ክፍተታቸውን ይሞላል እንጂ፡፡
https://telegra.ph/ETH-10-21-13
#TIKVAH_ETHIOPIA
PHOTO: EPA

‹‹የኢኮኖሚው ስብራት ምልክቶች››
በዛሬው አዲስ ወግ የውይይት መድረክ ላይ የመደመር መጽሐፍን ከኢኮኖሚ አንጻር ማብራርያ የሰጡት አቶ ማሞ ምህረት ለኢኮኖሚ ስብራቱ ምልክቶች ብለው ያስቀመጧቸው ነገሮች ፡- በቂ የስራ ዕድል አለመኖሩ፣ ኢፍታዊ ሆነ የሀብት ክፍፍል፣ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባትንና ደካማ የሆነ የመንግስት ፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም ሀገራችን 15% የዋጋ ንረትን ስታስተናግድ ቆይታለች ብለዋል፡፡ ነገር ግን ከላይ የተነሱት የኢኮኖሚው ስብራት ምልክቶች እንጂ ዋናው ችግር ያለው ምርታማነትና ተወዳዳሪነት መቀነሱ ነው ያሉት አቶ ማሞ ለዚህም የስርዓት ጉድለቱን እንደምክንያትነት አስቀምጠዋል፡፡ ይህ የስርዓት ክፍተትም ምንጩ በየዘርፉ ያሉ ባለድርሻ አካላት መስራት የሚጠበቅባቸውን ሥራ አለመስራታቸው፣ መንግስታዊ ጣልቃ ገብነትና ዝርክርክ አሰራሮችን እንደ ምክንያትነት አስቀምጠዋቸዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-21-14

#UPDATE
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ተከስሰዉ ጥፋተኛ የተባሉ አራት ተከሳሾች ለፍርድ ቤት የቅጣት ማቅለያ አናቀርብም አሉ። ተከሳሾቹ ይህን ያሉት ጉዳያቸውን ሲመለከት ለቆየው እና ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ላስቻለዉ የከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ነው። አራቱ ተከሳሾች ይህን ውሳኔ ያሳለፉት “በሃሰት ተቀነባበረ ላሉት ክስ እዉቅና አንሰጥም” በሚል ነው። የዛሬው ችሎት የተሰየመበት የከፍተኛው ፍርድ ቤት በፌደራል፣ በአዲስ አበባ እና በማረሚያ ቤቶች ፓሊሶች ተከብቦ እንደነበር የጀርመን ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል። ጋዜጠኞችን ጨምሮ የችሎቱ ታዳሚያን የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ በከባድ ጥበቃ ስር ሆነው መከታተላቸውንም ገልጿል። ፖሊስ የተከሳሽ ቤተሰቦች መጀመሪያ ወደ ችሎት እንዳይገቡ ከልክሎ የነበረ ቢሆንም ተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ የችሎቱን ውሎ እንዲከታተሉ ተፈቅዶላቸዋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት ለጥቅምት 18 ቀን 2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

#Afar #Tigray
የትግራይና የአፋርን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የሰላም ኮንፈረንስ በአላማጣ ከተማ ተካሄደ። በራያ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት በተዘጋጀው ኮንፈረንስ ክልሎቹን በመሠረተ ልማት አውታሮች ለማስተሳሰር ትኩረት እንደተሰጠው ተመልክቷል።

126 ሺህ በላይ ወገኖች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል!
በዋግህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ድርቅ ባስከተለው ችግር ምክንያት ለጉዳት የተጋለጡ ወገኖችን ለመርዳት የምግብ እህል እየተጓጓዘ መሆኑን የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መልካሙ ደስታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በዞኑ ከክረምቱ ዝናብ መዛባት ጋር ተያይዞ ባጋጠመው ድርቅ 126 ሺህ በላይ ወገኖች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ድርቁም በሰሃላና በዝቋላ ወረዳዎች ቢጎላም በቀሩት አምስት ወረዳዎች በከፊል መከሰቱን ተናግረዋል።
ለችግር የተጋለጡት እነዚህ ወገኖችን ለመታደግ ከክልሉ መንግስት ጋር በመነጋገር ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ስንዴ፣ ዘይትና ክክ ማጓጓዝ መጀመሩን አስታውቀዋል። በቅርብ ቀናትም ማከፋፈሉ እንደሚቀጥል አስረድተዋል። በተጨማሪም ከ65 ሺህ በላይ የቤት እንስሳት መኖ ፍለጋ ከወረዳ ወደ ወረዳ መሰደዳቸውንም ጠቁመዋል።
https://telegra.ph/ETH-10-21-15
Via ኢዜአ

#Update የአፍሪካ ሴት መሪዎች ኔትወርክ ምዕራፍ በኢትዮጵያ ተመሰረተ። ኔትወርኩ ሌሎች ሴት መሪዎችን እየተደጋገፉ ለማፍራት እንደሚያስችል ተገለጸ። የኔትወርኩ ምዕራፍ በኢትዮጵያ መመስረት ትናንት በሸራተን አዲስ ይፋ በሆነበት ወቅት የተገኙት ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንደተናገሩት፤ የምዕራፉ መመስረት ለኢትዮጵያ ሴቶች ትልቅ ስኬት ነው።ኔትወርኩን በምሳሌነት መምራት ይገባል። ፕሬዚዳንቷ በኢትዮጵያ ጠንካራ የሴት መብት የሚያስከብር ድርጅት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወደ አመራርነት ሲመጡ ድርብ ኃላፊነት እንዳለባቸው አመልክተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HPR
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎችና የማሻሻያ ሞሽን ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ።